እንደሚታወቀው፤ ኢጣልያኖች ኢትዮጵያን ለሁለተኛ ጊዜ በወረሩበት ዘመን፤ በዓለም-አቀፍ ሕግ በተከለከለ፤ በብዙ አውሮፕላኖች በተነሰነሰ የመርዝ ጋዝ በመጠቀም ጭምር፤ ለጊዜውም ቢሆን ወደ አዲስ አበባ ሲገሰግሱ፤ አጼ ኃይለ ሥላሴ ወደ እንግሊዝ ሐገር ተሰደው ለጥቂት ጊዜ እዚያ በመጠለል ትግላቸውን ቀጥለው ነበር።
በዚያን ጊዜ፤ ሥልጣናቸውን ለኢጣልያን መንግሥት እንዲያስረክቡና በሚቸራቸው ገንዘብ የተንደላቀቀ ኑሯቸውን እንዲቀጥሉ ብዙ ጉትጎታ አጋጥሟቸው ነበር። በዚህ ጽሑፍ የሚተኮርበት ልዩ የነበረ ጉትጎታ፤ የቫቲካን፤ በተለይ በጊዜው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መሪ በነበሩት፤ የፖፕ ፓየስ 11ኛ ሙከራ ነው። ለዚህም ዋናው ማስረጃ፤ “Ethiopia Under Mussolini (Fascism and The Colonial Experience), 1985; በተሰኘው መጽሐፉ፤ አልቤርቶ ስባኪ (Alberto Sbacchi) ከእንግሊዝ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መዝገብ በመጥቀስ እንደሚከተለው ያተተው ነው፤
“……Father Cyril C. Martindale, the Jesuit scholar representing the Pope, confirmed that the secretary of state at the Vatican, Eugenio Cardinal Pacelli (later Pope Pius XII), offered Haile Selassie 1 million (Sterling Pounds) on behalf of Italy in return for his abdication.” P 123
ትርጉም፤ የፖፑ ወኪል የነበሩት ጀስዊቱ ምሑር፤ አባ ሲሪል ሲ. ማርቲንዴል፤ ባረጋገጡት መሠረት የቫቲካን መንግሥት ዋና ጸሐፊ፤ ዩጂኒዮ ካርዲናል ፓቼሊ (በኋላ ፖፕ ፓየስ 12ኛ) ኃይለ ሥላሴ ሥልጣናቸውን እንዲለቁ በኢጣልያን መንግሥት ስም አንድ ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ አቅርበውላቸው ነበር።
ከላይ ለተጠቀሰው ሐተታ፤ ጸሐፊው (ስባኪ) ያቀረበው ማስረጃ ምንጭ፤ “FO 401/1937/XXIX/No.45” ነው።
በተጨማሪ፤ ሌላው አስደናቂ ጉዳይ ይኸው ጸሐፊ (ስባኪ) ተመራምሮ ያገኘው ማስረጃ፤ የተፈሪ መኮንን (በኋላ አጼ ኃይለ ሥላሴ) አሠልጣኝ የነበሩት የካቶሊክ ጳጳስ አንድሬ ማሪ ኤሊ ጃሮሶ የፈጸሙት ተግባር ነው። ጸሐፊው እንዳተተው፤
“Bishop Andre Marie Elie Jarosseau, Haile Selassie’s former tutor and a man who had influence over him, also invited the exiled ruler to recognize Italian sovereignty over Ethiopia. By submitting to Italy he could rule with Italian consent.” P. 124
ትርጉም፤ የኃይለ ሥላሴ የቀድሞ አሠልጣኝና ተሰሚነት የነበራቸው ጳጳስ፤ አቡነ አንድሬ ማሪ ኤሊ ጃሮሶ፤ ስደተኛው መሪ ኢጣልያ በኢትዮጵያ ላይ ያላትን ገዢነት እንዲቀበሉ ጋብዘው ነበር። ለኢጣልያ ተገዢ ከሆኑ በኢጣልያ ፈቃድ ሊገዙ ይችላሉ።
ለዚህም ሐተታ፤ ስባኪ ማስረጃው የሚገኝበትን ምንጭ እንደሚከተለው አቅርቧል፤
“Times (London), 29 April 1938; Le Petit Parisien, 22 August 1939; La Garonne, 22 August 1939; Bernoville, Monseigneur Jarosseau et la Mission des Gallas, p. 360” p. 127
በነገራችን ላይ፤ በአቶ ዘውዴ ረታ “የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መንግሥት” መጽሐፍ፤ ጃሮሶ፤ ምንም ማስረጃ ሳያቀርቡ ፖፕ ፓየስ 11ኛ ፋሺሽቶችን አውግዘዋል ማለታቸው ተገልጿል።
እውነቱ ግን፤ ፖፕ ፓየስ 11ኛ ፋሺሽቶችን የባረኩ መሆናቸውን ያረጋገጠው ማስረጃ፤ እ.ኤ.አ የካቲት 13፤ 1937 ዓ/ም (February 13, 1937) በታዋቂው በኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ (New York Times) ላይ እንደሚከተለው ተዘግቦ ይገኛል፤
“Earlier today the Pontiff (Pope Pius XI) had given his recognition of Italian sovereignty over Ethiopia by bestowing his apostolic benediction upon Victor Emmanuel as “King of Italia and Emperor of Ethiopia.”
ትርጉም፤ ቀደም ብሎ፤ ዛሬ፤ አቡኑ (ፖፕ ፓየስ 11ኛ) ቪክቶር ኢማኑኤልን “የኢጣልያ ንጉሥና የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት” በማለት ባርከው ኢጣልያ በኢትዮጵያ ላይ ያላትን ሥልጣን አረጋግጠዋል።
እርምት የሚያስፈልገው ሐተታ፤
ከዚህ በላይ በተጠቀሱትና እንዲሁም ከዚህ ቀጥሎ በሚቀርቡት ልዩ ልዩ ማስረጃዎች መሠረት፤ ፖፕ ፓየስ 11ኛና ቫቲካን ከሙሶሊኒና ከፋሺሽቱ መንግሥት ጋር እጅና ጓንት በመሆን በኢትዮጵያ ላይ ለተፈጸመው የጦር ወንጀል ተጠያቂ ስለ መሆናቸው ምንም ጥርጥር የለውም። ነገር ግን “የኃይለሥላሴ መንግሥት” በተሰኘ መጽሐፋቸው፤ የቀድሞ አምባሳደር ዘውዴ ረታ ፖፕ ፓየስ 11ኛ ተጠያቂ አለመሆናቸውን (ገጽ 295-315) በመጻፋቸው አንዳንድ ሰዎች እየተወናበዱ ነው። ለምሳሌ፤ ማያሚ፤ ሚኒያፖሊስ፤ ጀኒቫና አዲስ አበባ ከሚኖሩ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን የመጽሐፉን አባባል ዋጋ በመስጠት ለዚህ ጸሐፊ እስከ መደወል የደረሱ አሉ። ማስረጃ ከቀረበላቸው፤ አቶዘውዴ ራሳቸውን ማረም ፈቃደኛ መሆናቸውን ቢገልጹም፤ ከአስተማማኝ ምሑራንና ከታሪክ ድርሰቶች የቀረቡላቸውን ማስረጃዎች ባለመቀበል ተገቢውን እርምጃ አልወሰዱም። ሐሳባቸውን መግለጹ መብታቸው መሆኑ ቢታወቅም፤ መጽሐፉን የሚያነቡ አንዳንድ ሰዎች ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ደራሲው የእርምት መግለጫ እንዲያወጡ በተስፋ እየተጠበቁ ነው። ሌሎችም ቢጽፉ ይጠቅማል። የኢጣልያው ተወላጅ፤ አልቤርቶ ስባኪ፤ ቫቲካንን ሲያጋልጥ ከኢትዮጵያውያን የበለጠ አይጠበቅም?
የፖፕ ፓየስ 11ኛና የሙሶሊኒ/የፋሺሽቶች ሕብረት፤
የነዚህ ሁለት መሪዎች ሕብረት በኢትዮጵያ ላይ እጅግ አሰቃቂ የሆነ መከራና እልቂት አስከትሏል፤
1ኛ/ በመርዝ ጋዝ፣ በቦምብ፤ በጥይት፤ በስቅላት፤ ወዘተ፤ አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ተጨፍጭፈዋል። ከነዚሁ ውስጥ፤
በሶስት ቀኖች፤ አዲስ አበባ ብቻ 30 000 ሰዎች ተገድለዋል፤ እነአቡነ ጴጥሮስና ሌሎች ብዙ ጀግኖች ተሰውተዋል፤
2ኛ/ 2000 ቤተ ክርስቲያኖችና 525 000 ቤቶች እንዲሁም 14 ሚሊዮን እንስሶች ወድመዋል፤
3ኛ/ እጅግ ብዙ የኢትዮጵያ ንብረቶች ተዘርፈዋል፤ ለምሳሌ፤ ከ500 በላይ የሆኑ ሰነዶች በቫቲካን እጅ ይገኛሉ፤ “ፀሀይ”
የተሰኘች የኢትዮጵያ አውሮፕላን በኢጣልያ አየር ኃይል ቤተ መዘክር ትገኛለች።
ከላይ የተዘረዘረው የጦር ወንጀል አልበቃ ብሎ፤ በቅርቡ ደግሞ፤ ባለፈው ነሐሴ 2004 ዓ/ም፤ አፌሌ በምትሰኝ የኢጣልያ ከተማ፤ “የኢትዮጵያ ጨፍጫፊ” በመባል ለሚታወቀው ለሮዶልፎ ግራዚያኒ፤ የቫቲካን ካሕን በተገኙበት፤ የመታሰቢያ ኃውልት ተቋቁሞለታል።
ስለ ፖፕ ፓየስ 11ኛና ፋሺሽቶች ሕብረት ብዙ ተጽፏል። ከዚህ ቀደም ከተጻፉት ውስጥ የሚከተለውን በመጠቆም መመልከት ይቻላል፤
http://www.ethiolion.com/Pdf/10212012Evidence_of_pope_Pius_X.pdf
አንዳንድ ነጥቦችን ለማስታወስ፤
አቭሮ ማንሐታን፤ “The Vatican in World Politics” በተሰኘ መጽሐፉ (ምእራፍ 9፤ ለማንበብ፤ www.globalallianceforethiopia.org ይመልከቱ)፤
(ሀ) እ.ኤ.አ ከ1922 በፊት፤ ቫቲካንና ፋሺሽቶች ተጻራሪዎች ነበሩ። ከዚያ ዓመት ጀምሮ ግን፤ ቫቲካንና ፋሺሽቶች (ፖፕ ፓየስ 11ኛና ሙሶሊኒ) መቀራረብና መወዳጀት ጀመሩ። በዚሁ መሠረት፤ ፖፕ ፓየስ 11ኛ፤ “የካቶሊክ ፓርቲ” የተሰኘውን የፖለቲካ ድርጅታቸውን ደመሰሱ።
(ለ) እ.ኤ.አ. በ1926 “Mussolini is the man sent by Providence”
(ትርጉም፤ ሙሶሊኒ በፀጋ የተላከ ሰው ነው።) በማለት ፖፕ ፓየስ 11ኛ ሙሉ ድጋፋቸውን በይፋ በመግለጽ የኢጣልያን ሕዝብ የፋሺሽቱን ፓርቲ እንዲደግፍ አመቻቹ።
(ሐ) እ.ኤ.አ. በ1928፤ ፖፐ ፓየስ 11ኛና ሙሶሊኒ Lateran “ላተራን” የተሰኘውን ውል ተዋዋሉ። ውሉ ሲፈረም የሚያሳየውን ፎቶግራፍ ከዚህ በታች መመልከት ይቻላል። ስለዚህ ውል በManchester Guardian (February 12, 1929) የሚከተለው ተነቦ ነበር፤
“Pope Pius XI is credited with much admiration for Mussolini. That the Italian clergy as a whole are pro-Fascist is easy to understand, seeing that Fascism is a nationalist, authoritarian, anti-liberal, and anti-Socialist force.”
(ትርጉም፤ ፖፕ ፓየስ 11ኛ ለሙሶሊኒ ስላላቸው ክፍተኛ አድናቆት ይነገርላቸዋል። የፋሺሽት ሥርዓት አምባገነናዊ፤ ብሔርተኛ፤ ፀረ-ዲሞክራሲና ፀረ-ሕዝባዊ ኃይል ስለ ሆነ የኢጣልያ ካሕናት በአጠቃላይ የፋሺሽት ደጋፊ መሆናቸውን በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል።
(መ) ቫቲካን ከላይ የተጠቀሰውን ውል በመፈረሟ፤ ከፋሺሽቶቹ መጠነ-ሰፊ ገንዘብ ያገኘች ሲሆን በተጨማሪም፤ ሕጋዊ ሉዓላዊነት ተፈቀደላት። አቭሮ ማንሓታን እንደ ጻፈው፤
“It was the alliance of these two men, Pius XI and Mussolini, that influenced so greatly the social and political pattern, not only of Italy, but also of the rest of Europe in the years between the two world wars.”
(ትርጉም፤ የነዚህ የሁለት ሰዎች፤ የፖፕ ፓየስ 11ኛና የሙሶሊኒ ሕብረት ነበር በኢጣልያ ብቻ ሳይሆን በቀረው የአውሮፓ ክፍል ላይ በሁለቱ የዓለም ጦርነቶች መሀል በነበሩት ዓመቶች የማሕበራዊና የፖለቲካ ይዘት ከፍተኛ አጽንኦት ያሳደረው።)
በዚህ መሠረት፤ በሙሶሊኒ የተመራው የፋሺሽት ፓርቲ፤ በፖፕ ፓየስ 11ኛ ያልተቆጠበ ድጋፍ፤ ኢጣልያ በኢትዮጵያ ላይ ለፈጸመችው የወረራና የጦር ወንጀል ምን ያህል እንደ ጠቀማት መገንዘብ አያዳግትም። አቭሮ ማንሓታን በተጨማሪ እንደ ገለጸው፤
“Thus the Church became the religious weapon of the Fascist State; while the Fascist State became the secular arm of the Church.”
(ትርጉም፤ ስለዚህ፤ ቤተ ክርስቲያኗ (የካቶሊክ) የፋሺሽቱ መንግሥት ሃይማኖታዊ መሣሪያ ስትሆን፤ የፋሺሽቱ መንግሥት ደግሞ የቤተ ክርስቲያኗ ዓለማዊ ክንድ ሆነ።)
(ሠ) ቫቲካን የፋሺሽቱን ጦር መባረኳ የማይጠረጠር ሐቅ ነው። ካቶሊኩ ካሕን ጦሩን ሲባርኩ የሚያሳየውን ፎቶ ከዚህ በታች መመልከት ነው፤
(ረ) ፋሺሽቶች በኢትዮጵያ ላይ ያከናወኑትን ወረራ፤ የመከላከል ጦርነት መሆኑን ፖፕ ፓየስ 11ኛ ገልጸው ነበር። የፋሺሽቱ ጦር አዲስ አበባ ሲደርስ፤ ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የደስታ መግለጫቸውን እ.ኤ.አ. በግንቦት 12 ቀን 1936 በማወጅ፤ ፖፕ ፓየስ 11ኛ በዚህ ረገድ ከዓለም መሪዎች ከመጀመሪያዎቹ አንዱ እንደ ነበሩ ተረጋግጧል፤
“The triumphant joy of an entire, great and good people over a place which, it is hoped and intended, will be an effective contribution and prelude to the true place in Europe and the World.” (15)
(ትርጉም፤ ለአውሮፓና ለዓለም፤ መልካም ጅማሮና ሁነኛ ደረጃ ተገቢ አስተዋጽኦ እንዲሆን ለታቀደና ተስፋ ለተጣለበት ቦታ (ኢትዮጵያን ማለት ነው) የታላቅና ግሩም ሕዝብ (ኢጣልያኖችን ማለት ነው) ከፍ ያለ ደስታ።)
የፖፕ ፓየስ 11ኛን መግለጫ የበለጠ ያጠናከሩት ደግሞ የቱራኖ የካቶሊክ ጳጳስ ነበሩ። የሳቸው መግለጫ እንደሚከተለው ነበር፤
“The war against Ethiopia should be considered as a holy war, a crusade” (as Italian victory would) “open Ethiopia, a country of infidels and schismatics, to the expansion of the Catholic Faith.”
(ትርጉም፤ በከሐዲዎቹ ሐገር፤ በኢትዮጵያ፤ የካቶሊክን ሃይማኖት ለማስፋፋት ስለሚጠቅም፤ በኢትዮጵያ ላይ የተፈጸመው ጦርነት እንደ ቅዱስ ጦርነት፤ መንፈሳዊ ዘመቻ መቆጠር አለበት።)
ሌሎች ምሑራን ምን አሉ?
1ኛ/ ታዋቂቅ ደራሲ፤ አቶ ተክለ ጻድቅ መኩሪያ፤ “የኢትዮጵያ ታሪክ ከአፄ ቴዎድሮስ እስክ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ” በተሰኘው መጽሐፋቸው፤ገጽ 225-227፤ እንዳስቀመጡት፤
“ሙሶሊኒ በውስጣዊ አገሩ የንጉሡና (ቪክቶር ኢማኑኤል) የጳጳሱ (ፖፕ ፓየስ 11ኛ) አሳብ ከርሱ ጋር እንደ ተባበረለት ባወቀ ጊዜ በሮም እ.አ.አ. ጥቅምት 2 ቀን 1935 ዓ.ም. እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር መስከረም 21 ቀን 1928 ዓ.ም. ጦርነቱን ባስታወቀ በማግስቱ ወሰኑን አልፎ ጦርነት እንዲዠምር ለጄኔራል ደቦኖ ቴሌግራም አስተላለፈ።” (ገጽ 227)
“… ሁለቱን ጠበኞች በማስታረቅ ወይም ሙሶሊኒን በመንፈሳዊ አባትነታቸው በመገሰጽ ፋንታ በመንበረ ጴጥሮስ ሐዋርያ ተቀምጠው ለዓለም ሁሉ ክርስቲያን አባትነታቸውን የሚያጽድቁት የሮማ ሊቀ ጳጳስ ለሙሶሊኒ ቀኝ ክንድ ሆነው ይህ ዘመቻ የተቀደሰ ዘመቻ ነውና በርታ እያሉ ያጥናኑት ነበር ይባላል። የሳቸውን (ማለትም የፖፑን) አሳብ በመከተል ብዙ የባታቾቻቸው ጳጳሳት ለዘመቻ ርዳታ የሚሆን ብዙ ወርቅና ገንዘባቸውን ሰጡ። በዚህ በፖፑ ተግባር የተደነቁት ኤሊክ ሲንድረም የተባሉት የስዊድን ጋዜጣ ጸሐፊ…ልብን እንደ ጦር በሚወጋ ንግግር ወቅሰዋቸዋል። ሲሞን ረስቲን ተረጎሙልን፤ ቃሉም ከዚህ ቀጥሎ የተጻፈው ነው፤
“ቅዱስ ሆይ፤ እኔ በሰሜን አገር የተወለድሁ አንድ ፕሮቴስታንት ነኝ። ባገራችንም በስዊድን በግንባራችን የምንደፋው በእልፍኛችን ሆነን ከእግዚአብሔር ካምላካችን ጋራ ስንናገር ነው እንጂ ከሰው ጋራ ብንናገር ቁመን እንናገራለንና በእግርዎ ላይ ወድቄ ጫማዎን ስለማልስምዎ አይቆጡብኝ። ቅዱስ ሆይ እኔ አንድ ምስኪን ኃጢአተኛ ነኝ እርስዎ ግን የመድሐኒታችን ምትክ ነዎት። የማይሳሳቱም ነዎት፤ ይሁን እንጂ እኔ እነቅፍዎታለሁ። እርስዎ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ዋና ነዎት። ካቶሊካዊት ማለትም የሁሉ ማለት ነው። ዛሬ እንግዲህ የርስዎ ቤተ ክርስቲያን በውነቱ የሁሉ ቤተ ክርስቲያን ናት(?) እርስዎ ከሙሶሊኒ ጋራ ሆነው ከሌላው ዓለም ጋራ በጠብ አሉ። ርስዎና ከርስዎ በታች ያሉት ሌሎችም ጳጳሳት ኢትዮጵያ ለጣሊያን ቅኝ አገር እንድትሆን የሚገባ ነው ብለው ተናገሩ። ርስዎ መቼም የሐዋርያው የጴጥሮስ ተከታይ ነዎትና አይሳሳቱም።”
“… ቅዱስ ሆይ፤ ኢጣሊያ የፍርድ ሥራ ትሠራለች ብለው ሰብከዋል። የመሲና የቢረዲቤም ጳጳሳት ውርቃቸውን ሁሉ ለጦርነቱ ከሳራ እንደ ሰጡ ሰማን።እናንተ ጳጳሳት ይህንን ስታደርጉ እግዚአብሔር ከጣሊያን ጋራ ነው የማለት ያኽል ይመስለኛል። እንግዲህ ሌላው ዓለም ሁሉ የጣሊያንን ሥራ ቢቃወም የእግዚአብሔርን ፍርድ ይቃወም ይሆን? ኢትዮጵያውያንስ አገራቸው ሲጠብቁ በእግዚአብሔር ላይ ተነስተው ይኸንን ርስዎ እንዳሉ ኢጣሊይ የጽድቅ ውጊያ ከሆነ ሌላውም ዓለም ይህንን የጽድቅ ጦርነት ቢቃወሙ መቼም ከናንተ በቀር ሌላው ዓለም ሁሉ እግዚአብሔርን የካደ ይመስላል።
“… የኢትዮጵያ ሰዎች አገራቸውን ለመጠበቅ ቢሰበስቡ የኢጣሊያን አውሮፕላን ጥርግ አድርጎ ቢያጠፋቸው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ነው። ሲቶችንና ሕጻናትን በቦምብ ሲያጠፉ እግዚአብሔርን ያገለግላሉ።
“… በድሮ ዘመን ግን ቤተ ክርስቲያን ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር መታዘዝ ይገባል ብላ ታስተምር ነበር።”
“… ቅዱስ ሆይ፤ ርስዎ መናገር በተገባዎት ጊዜ ዝም አሉ፤ ዝም ማለትም በተገባዎ ጊዜ ተናገሩ። … የዓለምን ሰላም የሚያውከውን ወንበዴውን ቢያወግዙት ኖሮ ለቤተ ክርስቲያንም እንዴት ያለ ጥቅም በሆነ ነበር። ምናልባትም እርስዎ በታሰሩም ነበር። ምናልባትም እንደ ድሮ ዘመን ከርስቲያኖች ወደ ሰማእትነት ሞት በደረሱ ነበር። ዓለምም ሁሉ ከርስዎ ጋር በሆነ ነበር።….(ዓለምም) የእግዚአብሔር አገልጋይ እንደሆኑ በተረዳ ነበር።” (ገጽ 225-227)
2ኛ/ ስለ ቫቲካንና ፋሺሽቶች ሕብረት ያቀረብኩላቸውን ማስረጃዎች ከተመለከቱ በኋላ ሌሎች ምሑራን የገለጹት፤
ሀ) ታዋቂው የኢትዮጵያ ታሪክ ምሑር፤ በቅርቡ፤ ስለ አጼ ኃይለ ሥላሴ፤ “The Lion of Judah in the New World”, 2011 የተሰኘ መጽሐፍ የደረሱት፤ ፕሮፌሰር ቲዮዶር ቬስታል፤ ከዚህ በታች የተጠቀሰውን መልእክት ላኩልኝ፤
“Your work is most convincing for those with ears to hear and eyes to see.” (ትርጉም፤ ሥራህ መስማት የሚፈልጉ ጆሮዎችና ማየት የሚፈልጉ ዓይኖች ላሏቸው ሰዎች እጅግ በጣም አስተማማኝ ነው።)
(ለ) ሌላው ታዋቂ ምሑር፤ እርሳቸውም፤ በቅርቡ፤ “The Symphony of My Life” በተሰኘአርእስት ስለ ሕይወታቸው ታሪክና ስለ ኢጣልያን ወረራ መጽሐፍ የደረሱት፤ ዶር. ሥዩም ገብረ እግዚአብሔር፤ ከላይ የተጠቀስወን በፖፕ ፓየስ የተገለጸውን የደስታ መልእክት ካረጋገጡ በኋላ፤ ከዚህ በታች የቀረበውን መልእክት ላኩልኝ፤
“From my book you can note, how one of the Catholic priests took the personal responsibility to entice me to be a priest! How we the seminarians marched outside Harar in a heavily Moslem country protected by Fashist military to attend church every week! Picture P 63 . This was a clear policy of the Catholic church in support of Fascism. The establishment of “Collegio Ethiopico” within the vatican compound was to train and indoctrinate Ethiopian seminarians. We were then told that if we become good potential priests, we will be eligible to go to Rome for further education(indoctrination”! There was a definite crusade to propagate Catholicism in Ethiopia with the help of fascism based on Aparthaid policy I had faced on my way to priesthood!
(ትርጉም፤ ከመጽሐፌ ማየት እንደምትችለው፤ አንድ የካቶሊክ ካሕን እኔን ወደ ቅስና ለመሳብ የግል ኃላፊነት ይዞ ነበር። ገጽ 63 ላይ ባለው ፎቶግራፍ እንደሚታየው፤ ከሐረር ወጣ ባለ፤ እስላሞች በሚበዙበት (ክፍለ) ሐገር፤ ተማሪዎቹ፤ በፋሺሽት ወታደሮች እየታጀቡ፤ በየሳምንቱ ይሰለፉ ነበር። ይህም፤ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን፤ ለፋሺሽዝም ያላትን ድጋፍ በግልጽ የሚያሳይ ፖሊሲ (መርሆ) ነበር። በቫቲካን ግቢ የተቋቋመው “ኮሌጂዮ ኢትዮፒኮ” ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን ለማሠልጠንና ለማሳመን ነበር። በዚያን ጊዜ ተነግሮን የነበረው፤ ጥሩ የቅስና አዝማሚያ ካሳየን፤ ወደ ሮም ተልከን፤ ለቀጣይ ትምሕርት (ማሳመን) እጩ እንድንሆን ነበር። ወደ ቅስና በምጓዝበት፤ ባጋጠመኝ፤ በዚያ በዘረኛ (በ”አፓርቴይድ”) መርሆ፤ በፋሺዝም እርዳታ፤ በኢትዮጵያ፤ የካቶሊክ እምነትን ለመስበክ ዘመቻ መካሔዱ የተረጋገጠ ነበር።)
ስለ “የዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ – የኢትዮጵያ ጉዳይ” ዓላማ፤
በእንግሊዝኛ Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause የተሰኘው ድርጅታችን ዓላማዎች፤
1ኛ/ ቫቲካን የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንድትጠይቅ፤
2ኛ/ የኢጣልያ መንግሥት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተገቢ ካሣ እንዲከፍል፤
3ኛ/ የኢጣልያ መንግሥትና ቫቲካን የተዘረፉትን የኢትዮጵያ ንብረቶች እንዲመልሱ፤
4ኛ/ ለጦር ወንጀለኛው ለግራዚያኒ የተቋቋመው መታሰቢያ እንዲወገድና፤
5ኛ/ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኢትዮጵያ ላይ የተፈጸመውን የፋሺሽቶች የጦር ወንጀል በመዝገቡ እንዲያውል ነው።
ጉዳዩ የሐገር መብትንና ክብርን የሚመለከት ስለ ሆነ ዓለም-አቀፋዊ ድጋፍ እያገኘ ነው። ለምሳሌ፤ ድረ-ገጻችን፤ www.globalallianceforethiopia.org ላይ ያለው አቤቱታ እስካሁን ድረስ ከ30 ሐገሮች በላይ በሚኖሩ 4818 ሰዎች ተፈርሟል። ይህንን ጽሑፍ የሚያነቡ፤ ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች ቢፈርሙት መልካም ነው።
ቸሩ የኢትዮጵያ አምላክ፤ የውድ ሐገራችንን መብትና ክብር ለመጠበቅ ያብቃን።
———————————————————————————————————————————————–
የዚህን ጽሑፍ ረቂቅ ተመልክተው እጅግ ጠቃሚ የሆኑ አስተያየቶቻቸውን ላበረከቱልኝ ለልዑል ኤርምያስ ሣህለ ሥላሴ፤ ለአምባሳደር ዓለማየሁ አበበና ለዶር. ሚካኤል ወሰን ጥልቅ ምሥጋናዬን እገልጻለሁ።
(ማሳሰቢያ) አቶ ኪዳኔ ዓለማየሁ በቅርቡ ለተመረጡት ጳጳስ ፍራንሲስ ቀዳማዊ ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ የላኩትን ደብዳቤ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።
እሽከመቼ says
ውድ አቶ ኪዳኔ ዓለማየሁ፤
ላቀረቡልን ትንተና ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ሁላችንም በያለንበት የምናደርገው ጥረት የነገዋን ኢትዮጵያን ዕጣ ይወስናል።
ቁም ነገሩ ደግሞ፤ አሁን ላለንበት የፖለቲካ ሀቅ፤ ይህ ክስተት የሚሠጠው እንደምታ ነው። ባሁኑ ሰዓት በሀገራችን ውስጥ የሃይማኖት ተቋማትን ለፖለቲካ መሣሪያነት በመጠቀም፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት የኢትዮጵያን ሕዝብ መብት ገፎ ሀገራችንን ወደኋላ እየጎተታት ነው። ፋሽስቱ ጣሊያን ቫቲካንን መሣሪያው እንዳደረገው ሁሉ፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ደግሞ የኢትዮጵያ ተዋሒዶ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያንን በትውልድ ሀረግ ተመስርቶ እየጎተተ፤ የእስልምና ተከታይ ወገኖቻችንንም እያረደና እያባረረ እንደፋሽስቱ እየገዛን ነው።
ይህ ሕገወጥ ቡድን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክም ሆነ ባህል ተቆርቋሪ ሆኖ ጣቱን እንደማያነሳ እናውቃለን። ምንም እንኳ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት አያደርገውምና እኛም አርፈን እንቀመጥ ባይባልም፤ ግቡን ሊመታ የሚችለው የትግሬዎችን ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ማስወገድ ቅድሚያ ሊሠጠው አለሚገባ፤ ጉዳዩን ከኢትዮጵያ ሕልውና ጋር ማዛመዱ ግዴታ ይሆናል። ስለጥረትዎ ምስጋናዬ የተጠበቀ ነው።