መለስ “ከዋሸኸን ትሞታለህ” መለስ ሀዋሳን ክልል ለማድረግ ቃል ገብተው ነበር የሲዳማ አገር ሽማግሌዎች አቶ መለስ እድሜያቸው አጭር እንደሚሆንና እንደሚቀሰፉ ነግረዋቸው እንደነበር ተሰማ። በክልሉ የአገር ሽማግሌ ከሚባሉት መካከል አንዱን በማነጋገር በተለይ ለጎልጉል የተላከው መረጃ እንደጠቀሰው መለስ እድሜያቸው ሊያጥርና በድንገት ሊቀሰፉ የሚችሉት የሲዳማን ባህላዊ ልብስ ለብሰው ከዋሹ ነበር። እንደመረጃው መለስ በ1997 ዓ ም ምርጫ ውጥረት ውስጥ በነበሩበት ወቅት አራት ተከታታይ ቀናት ሃዋሳ የብሄር ብሄረሰቦች አዳራሽ ውስጥ የብሄረሰቡን ተወላጆች ሰብስበው አነጋግረው ነበር። “አዲስ አበባ ያለው ድንኳናችን ፈርሷል። እዚህም ከፈረሰ በቃን ማለት ነው” በማለት የአገር ሽማግሌዎችን በተማጸኑበት ንግግራቸው መለስ አስቀድሞ ተቃውሞ ገጥሟቸው ነበር። ስብሰባው አዳራሽ ውስጥ ሙሉ ልብስ … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
“አማራንና አማርኛን ማጥፋት የህወሃት ፕሮግራም ነው”
አማርኛ ተናጋሪዎችን የማመናመን፣ የማደህየት፣ የማራቆትና ክልላቸውን እያሳነሱ የማጥፋት እቅድ በህወሃት መርሃግብር ውስጥ የተካተተ ዋና ተግባር እንደሆነ ተገለጸ። አማርኛ ቋንቋንም ማሽመድመድ የዚሁ እቅድ አካል መሆኑ ተዘግቧል። አቶ ገ/መድህን አርአያ ከኢሳት ሬዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በህወሃት ፕሮግራም ገጽ 18 አካባቢ "አማራ የትግራይና የኤርትራ ህዝብ ጠላት እንደሆነ ተመልክቷል" ብለዋል፡፡ አያይዘውም አማራ ማጥፋት የቅስቀሳው ዋና መሳሪያ ቢሆንም የትግራይ ህዝብ አልተቀበለም ብለዋል። ቅስቀሳውን አንቀበልም ያሉ "የትግራይ ሸዋ" ተብለው መገደላቸውን ይፋ አድርገዋል። በተለይ የድርጊቱ ዋና አስተባባሪ በማለት የጠቀሷቸው አቶ መለስ ዜናዊ፣ አቶ ስብሃት፣ አቶ ስዩም መስፍን፣ አቶ አባይ ጸሐዬን የጠቀሱት አቶ ገ/መድህን፣ በ1972 በሰሜን ጎንደር የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸሙን … [Read more...] about “አማራንና አማርኛን ማጥፋት የህወሃት ፕሮግራም ነው”
የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ
በአሁኑ ሰዓት በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን መፈናቀል በመቃውም በኦስሎ ከተማ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠርቷል፡፡ በአካባቢው የምትገኙ ሁሉ በሰልፉ ላይ እንድትገኙ አዘጋጆቹ ጥሪያቸውን ያቀርባሉ፡፡ መረጃውን ከምስሉ ላይ ይመልከቱ፡፡ … [Read more...] about የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ
World Bank Must End its Support for Human Rights Abuses in Ethiopia
ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ጎልጉል “ኢህአዴግ አንገቱን ታንቋል” ዓለም ባንክ ርምጃ ለመውሰድ ጫፍ ደርሷል በሚል እና ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ!! ብያኔው ከጸና ኪሣራው በቢሊዮን ዶላር ሊደርስም ይችላል! በሚል ርዕስ ሰፋ ያለ ዘገባ ማቅረባችን ይታወቃል፡፡ የዓለም ባንክ እስካሁን ውሳኔውን ይፋ በማድረግ ለኢትዮጵያ የሚሠጠውን ዕርዳታና ብድር ምርመራ እንዲደረግበት አለማስጀመሩ የብዙዎች ጥያቄ ከሆነ ሰንብቷል፡፡ ኢህአዴግ ከዓለም ባንክ የሚሠጠውን ዕርዳታ ለፖለቲካ ተግባር ማዋሉ የመርማሪው ቡድን ቦታው ድረስ በመሄድ ምርመራ አድርጎ ያረጋገጠ ቢሆንም ከየአቅጣጫው እየተሰነዘሩ ያሉት ተጸዕኖዎችም በከፍተኛ ሁኔታ እየተጠናከሩ መጥተዋል፡፡ የዚህ ጦማር ዋንኛ ዓላማም በዚሁ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ A multi-billion dollar aid program … [Read more...] about World Bank Must End its Support for Human Rights Abuses in Ethiopia
መሬት ነጠቃ ለአሜሪካ ም/ቤት ሊቀርብ ነው
በመጪው ሰኞ ሚያዚያ7፤2005ዓም (April 15፣ 2013) በአፍሪካ ስለሚደረገው የመሬት ነጠቃ አስመልክቶ የአሜሪካ ም/ቤት የፖሊሲ አውጪዎችና በጉዳዩ ላይ የሚሟገቱ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎችን እንዲሁም ባለሙያዎችን ሃሳብ ለማዳመጥ ስብሰባ መጥራቱ ታወቀ፡፡ በአሜሪካ የተወካዮች ምክርቤት በአፍሪካ፣ በዓለምአቀፍ ጤና፣ በዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብቶችና ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ንዑስኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑት ክሪስ ስሚዝ ከፍተኛ አማካሪና የአፍሪካ ኤክስፐርት የሆኑት ግሬጎሪ ሲምፐኪንስ ስብሰባውን እንደሚመሩትም ከወጣው መረጃ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በአፍሪካ የሚካሄደውን የመሬት ነጠቃ አስመልክቶ በተጠራው ስብሰባ ላይ መግለጫ ከሚሰጡት አፍሪካውያን መካከል ጋናዊው ምሁር ዶ/ር ጆርጅ አዪቴ የሚገኙበት ሲሆን ከኢትዮጵያ ብቸኛው ተጠቃሽ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር … [Read more...] about መሬት ነጠቃ ለአሜሪካ ም/ቤት ሊቀርብ ነው
ከእሁድ እስከ እሁድ
ሼኽ መሐመድ “ለቀቅ አድርጉን” አሉ ከኢትዮጵያ “አንድም ሳንቲም” እንዳልወሰዱ ተናገሩ ባለፈው ሳምንት ከፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ የገዟቸውን የላይኛው አዋሽ አግሮ ኢንዱስትሪ፣ የጐጀብ እርሻ ልማትና የቡና ማደራጃና ማከማቻ ድርጅት የርክክብ ፊርማ በሆቴላቸው ሸራተን አዲስ መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም. ውለታ በፈጸሙበት ወቀት “አንዳንድ የመገናኛ ብዙኅን እባካችሁ ለቀቅ አድርጉን እንሥራበት፡፡ አሁን ጊዜው የሥራ ነው እንጂ የአሉባልታ አይደለም፡፡ የመንግሥት ባለሥልጣናትንም አትጨቅጭቋቸው፡፡ ውጤቱን የሚያውቁት እነሱ ናቸው፡፡ ለእናንተ በሬ እንኳ ዝግ ነው፡፡ እባካችሁ በአገር ልማት ላይ እወቁበት፡፡ ነገር ፍለጋ፣ ቁስቆሳና አሉባልታ አያዋጣም፤ አገራችንን እንገንባ፤” በማለት ማሳሰቢያ አዘል መልዕክት ማስተላለፋቸውን ሪፖርተር ዘገበ። የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት በስነ ስርዓቱ … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
ሰላማዊ ትግል እና የመለስ ራዕይ ዘር-የማጥራት ወንጀል ስለመሆኑ
ከጉራፈርዳ እና ከቤንሻንጉል-ጉምዝ የተሰሙት ድምጾች ዘር የማጥራት (Ethnic Cleansing) ወንጀል በኢትዮጵያ ህጋዊ መሆን መጀመራቸውን አስታወቁ። እነዚህ ድምጾች የኢትዮጵያ ፌዲራል መንግስት እና የክልል መንግስቶች ኢትዮጵያን ለመበተን ውስጥ ውስጡን የነበራቸውን የአሳብ እና የተግባር ስምምነት ገሃድ በማውጣት የኢትዮጵያ አንድነት አደገኛ ምዕራፍ ላይ መድረሱን ግልጽ አደረጉ። የኢትዮጵያ አንድነት ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ለሚመኙ አገር ወዳዶች በሙሉ እንቅልፍ የሚነሳ መልዕክት አስተላልፈዋል ከጉራፈርዳ እና ከቤንሻንጉል-ጉምዝ የተሰሙት ድምጾች ። የኢትዮጵያችን ጉዳይ ያገባናል ለሚሉ አገር ወዳድ ዜጎች በሙሉ የኢትዮጵያ ህዝብ የመንግስት ስልጣን ባለቤት እስከሚሆን ድረስ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመከላከል ያልተቋረጠ በድስፕሊን የታነጸ ሰላማዊ ትግል ማድረግ … [Read more...] about ሰላማዊ ትግል እና የመለስ ራዕይ ዘር-የማጥራት ወንጀል ስለመሆኑ
SMNE’s Press release
Oromo Democratic Front (ODF) Declares Commitment to Work with Others towards a Democratic, Multi-national Ethiopia: Is this the Same “New Ethiopia” We in the SMNE Envision? On March 30, 2013, I had the privilege of watching history in progress while attending the first meeting of the newly formed Oromo Democratic Front (ODF) as an observer. Those involved included most of the founding leaders of the Oromo Liberation Front (OLF). As they announced their new vision, direction and organization … [Read more...] about SMNE’s Press release
የ እስክንድር ወንጀሉ መምከሩና ኣቅጣጫ ማሳየቱ ብቻ ነው
ኣንድ ጊዜ ኣባባ ተስፋየ ከዚያ ከሚያምርባቸው የ ልጆች ክፍለ ጊዜ ዝግጅታቸው ጠፉብኝና ኸረ የት ገቡ? ብየ ኣንዱን ጠየኩ። “ኣልሰማህም እንዴ ?” በፍጹም ምን ሆኑ? ደንገጥ ብየ እንደገና ጠየኩ። ያ ሰው እየሳቀ “ባለፈው ጊዜ ኣዲሱ ኣመት የሰላምና የእርቅ ያድርግልን ብለው በመናገራቸው የመንግስት ሰዎች ማን ሲጣላ ኣዩ? ብለው ኣባረሩዋቸው እኮ!” ሲለኝ ለደቂቃዎች እንደዚያ የሳቅኩበት ጊዜ ትዝ ኣይለኝም። የሁለታችንም ሳቅ ካለቀ በሁዋላ እውነተኛው ስሜት ሲመጣ ደሞ ያስለቅሳችሁዋል። ነገሩ እውነት መሆን ኣለመሆኑን ኣጥብቄ ኣልጠየኩም፣ ለነገሩ ከዚያ ቀን በሁዋላም ከብዙ ሰው ይህንኑ ሰማሁ። ነገሩ በትክክል ሆነም ኣልሆነም ያ ሁሉ ሰው መንግስት እንደዚያ ሊያደርግ ይችላል ብሎ ማሰቡ ራሱ ነገሩ መሆኑን ኣለያም ሊሆን መቻሉን ያሳያል። በዚያች ኣገር ምን የማይሆን ኣለና። በዚህ ስደነቅ … [Read more...] about የ እስክንድር ወንጀሉ መምከሩና ኣቅጣጫ ማሳየቱ ብቻ ነው
ዕድገትና ለውጥ በኢትዮጵያ ወይስ በፍጥነት ወደ ማዕከለኛው ዘመን ጉዞ!
ሰሞኑን ለአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሸን የገንዘብና የዕድገት ሚኒስትሩ አቶ ሱፊያን አህመድ የሁለት ዐመት ተኩሉን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ውጤት ሲያብራሩ፣ ከአንዳንድ ሁኔታዎች በስተቀር በአጠቃላይ ሲታይ የኢኮኖሚው ዕድገት አመርቂና ጥሩ ውጤት በማሳየት ላይ እንደሆነ በመዝናናት አብራርተዋል። በሳቸውም አገላለጽ፣ የተተለመው የኢኮኖሚ ዕድገት 11 በመቶ ሲሆን፣ ኢኮኖሚው ያስመዘገበው ዕድገት ግን 8.5 በመቶ ብቻ ነው። ወደ ዝርዝር የመስኮች ዕድገት ሲመጣ በሚኒስትሩ አገላለጽ፣ የኢንዱስትሪው ዘርፍ 17.9 በመቶ ያድጋል ተብሎ ሲጠበቅ፣ ያደገው ግን 13.6 በመቶ 2 ብቻ ነው። በእርሻውም መስክ እንደዚሁ የተጠበቀውን ግብ መምታት እንዳልቻለና፣ 8.5 በመቶ ያድጋል ተብሎ የተጠበቀው 4.5 በመቶ ብቻ እንዳደገ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ ለማብራራት እንደሞከሩት፣ የኢኮኖሚው ዕድገት እንደተጠበቀው ግቡን … [Read more...] about ዕድገትና ለውጥ በኢትዮጵያ ወይስ በፍጥነት ወደ ማዕከለኛው ዘመን ጉዞ!