በዓለም ዙሪያ የተበተናችሁ ወገኖቻችን በኛ ሎንደን በምንኖረው የኦርቶዶክስ ሀማኖት ተከታይ በሆንን ኢትዮጵያውያን ላይ በአንድ መነኵሴ ነኝ ባይ የቀበሮ ባሕታዊ ግለሰብ አማካኝነትና በወያኔ ቀጠረኞች የደረሰብንን ይቅር የማይባል በደል ዕለት በዕለት እንደምትከታተሉና መጨረሻችንን ለማየት በጉጉት እንደምትጠባበቁ እዚህ ያሉት ወንድሞችና እህቶች በሚገባ ያውቁታል። ያመሰግናሉም። ታዲያ ከዚያች ቀውጢ የሁዳዴ ጾም መያዢያ ማግስት፣ ጀምሮ የተዘጋብን ቤተክርስትያን ጉድይ እስካሁን እልባት ሳያገኝ፣ ቀርቶ ሕጻናቱም፣ አይቆርቡም፣ አዛውንቱም፣ ወይዛዝርቱም እግዚአብሔርን ማምለኪያ ቦታ አላገኙም። ይኸ በደል ባንድ ካኽን ንኝ ባይ ሲፈጸም በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪአው መሆን አለበት። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ከድጡ ወደ ማጡ!
“አፍሪኮም ወደ አገርህ ተመለስ”
የአፍሪካ አንድነትን 50ኛ ዐመት የመመስረቻ በዓል ቀን ምክንያት በማድረግ የወጣ መግለጫ! "እኛ እዚህ በአዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ ዋና ከተማ የተሰበሰብነው የአፍሪካ መሪዎችና መንግስታት፣ ማንኛውም አገርና ህዝብ የራሱን ዕድል ወሳኝ መሆኑን እናምናለን፤ በዚህም ምክንያት ነፃነት፣ እኩልነት፣ ትክክለኛ ፍርድና ክብር የአፍሪካ ህዝብ መሰረታዊ የመብት ጥያቄዎችና የሚገባውም መሆኑን ጠንቅቀን እናውቃለን፤ በመሆኑም የተፈጥሮ ሀብታችን የመጠበቅና፣ ህዝቦቻችንም የተፈጥሮ ሀብታቸውን የመጠቀምና፣ ለሚገባቸው የህብረተሰብና የኢኮኖሚ ዕድገት የማዋል መብታቸው እንደሆነ እናምናለን፤ ለዚህም እንታገላለን።" እ.አ.አ. በግንቦት 25 1963 ዓ.ም በሞዲቦ ኪዬታና ሲልቫኖስ ኦሊምፒዮ የረቀቀውና፣ በጊዜው ነፃነታቸውን የተቀዳጁት 33 የእፍሪካ መንግስታት ያፀደቁት ስምምነት መልዕክቱና ዋናው መሰረተ-ሃሳቡ … [Read more...] about “አፍሪኮም ወደ አገርህ ተመለስ”
የአደባባይ የብልግና ቧልት በሕጉ እንዴት ይታያል?
የዛሬው ጽሑፍ የሚያጠነጥነው በወንጀል ሕግ ዙሪያ ነው፡፡ የወንጀል ሕግና የኅብረተሰቡ የሞራል አስተሳሰብ የጠበቀ ቁርኝት አላቸው፡፡ በአብዛኛው በኅብረተሰቡ እንደ ኃጢአት ወይም ነውር የሚቆጠሩ ድርጊቶች በወንጀል ሕግም የሚያስጠይቁ ናቸው፡፡ አመንዝራነት፣ ስርቆት፣ ስድብ፣ ግብረ ሰዶም ወዘተ. ኃጢአት ወይም ነውር ብቻ ሳይሆኑ ወንጀልም ተደርገው በወንጀል ሕጉ እንደሚያስቀጡ ተመልክቶ እናገኛለን፡፡ ይሁን እንጂ ኃጢአት ወይም ነውር የሆነ ድርጊት ሁሉ ግን ወንጀል ላይሆን ይችላል፡፡ ዝሙት አዳሪነትን ለዓብነት ብንመለከት ድርጊቱ ኃጢአት ወይም ነውር መሆኑ ባያጠያይቅም፣ በወንጀል ሕጋችን በመርህ ደረጃ የወንጀል ኃላፊነት የማያስከትል ድርጊት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ የወንጀልና የኃጢአት ግንኙነት ስፋት እንደ ኅብረተሰቡ የሞራል አስተሳሰብ የሚለያይ ስለሚሆን በሁሉም ዘንድ ተመሳሳይ መግባባት ላይኖር … [Read more...] about የአደባባይ የብልግና ቧልት በሕጉ እንዴት ይታያል?
ከእሁድ እስከ እሁድ
አልሸባብ በሶማሊያ ተሽመደመደ፤ ሼኽ ዳሒር ሃዌስ ተይዘዋል፤ አሸባሪነትን በመዋጋት ሲሞዳሞዱ የቆዩት ኢትዮጵያና አሜሪካ ወዴት ያመሩ ይሆን? የአልሸባብ መሪዎች በራሳቸው ተዋጊዎች መገደላቸው ተሰማ። ከተገደሉት መካከል አንደኛው ያሉበትን ለጠቆመና ላጋለጠ አምስት ሚሊዮን ዶላር ጉርሻ እንደሚሰጥ የታወጀባቸው ነበር። የቪኦኤ የአማርኛው ክፍል በዘገበው ዜና መሰረት አልሸባብ በሶማሊያ እየተንኮታኮተ የመክሰም ደረጃ ላይ መድረሱን አመላካች ይመስላል። አብዱልአዚዝ አቡ ሙስ አብ ባሠራጨው የድምፅ መልዕክት የሙጃሕዲኑ ታጣቂዎች በመካከላቸው መከፋፈልን ለመፍጠር ይጥሩ በነበሩ አባሎቻቸው ላይ ዘመቻ ካካሄዱ በኋላ የተወሰኑትን በቁጥጥር ሲያውል፣ እጅ ለመስጠት አሻፈረኝ ያሉ ነበሩ ብሏል። “ሁለቱ እጃቸውን እንዲሰጡ ሲጠየቁ አሻፈረን ብለው አንገራገሩ፣ በተኩስ መካከል ተገደሉ፤ አምላክ ነፍሳቸውን … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
ኦባማ – “ዴሞክራሲ ከራባችሁ ኬክ ብሉ”
በድጋሚ ከተመረጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አፍሪካን እየጎበኙ ያሉት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በሴኔጋል ጉብኝት ባደረጉት ወቅት የግብረሰዶማውያን መብት ሊከበር እንደሚገባው አስታወቁ፡፡ የአገራቸው ጠቅላይ ፍርድቤት ሰዶማውያንን የሚደግፍ ውሳኔ ሰሞኑን በማሳለፉ ደስታቸውን ገለጹ፡፡ የሴኔጋሉ አቻቸው ግብረሰዶማውያን እንዳይወነጀሉ ለማድረግ አገራቸው ዝግጁ አለመሆኗን ተናገሩ፡፡ ሰሞኑን በአፍሪካ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ፕሬዚዳንት ኦባማ ጉብኝታቸውን በጀመሩባት ሴኔጋል የግብረሰዶማውያንን መብት በተመለከተ ለአፍሪካውያንና ለመሪዎቻቸው ማብራሪያና “ትምህርት” ሰጥተዋል፡፡ “መንግሥታት ዜጎቻቸውን እንዴት ሊያስተናገዷቸው ይገባል፤ ሕጉስ እንዴት ሊያያቸው ይገባል ለሚለው ጥያቄ መልሱ ሁሉም ሰው በእኩልነት ሊስተናገድ ይገባዋል” በማለት “ግብረሰዶማዊነት ወደፊት” የሚያስብል ንግግር … [Read more...] about ኦባማ – “ዴሞክራሲ ከራባችሁ ኬክ ብሉ”
አንተ ማነህ?
“... እንዲያውም ይህ በሽታ አልበቃ ብሎን ከዚህ በባሰ መልኩ መቀሌ ከተማ ላይ አደዋና መቀሌዎች፣ ባሕርዳር ከተማ ላይ ጎንደሬ፣ ጎጃሜ፣ ወሎዬና ሸዌ፣ናዝሬት ከተማ ላይ የወለጋ፣ የባሌ፣ የአሩሲና የሸዋ ኦሮሞዎች፣ አዋሳ ከተማ ላይ ሀዲያ፣ ከንባታ፣ ወላይታ ሶዶ ወዘተ በማለት የሚታየው የሹመትና የጥቅም ሽኩቻ ዘመነ መሳፍንትን ምስጋና ይግባው የሚያሰኝ ሆኗል (ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል እንዲሉ)፡፡ … “በተቃዋሚው ጎራ የተሰለፉት ፖለቲከኞቻችንም ቢሆኑ የስልጣን እድሉ ቢገጥማቸው ምን ሁኔታ እንደሚፈጠር ለመገመት ነቢይ መሆን አያስፈልግም፡፡ (አብዛኛዎቻችን ከቂም በቀል አዙሪት ገና ያልወጣን በመሆኑ) ይህን ያልኩትም ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ ያሳዩት አሳፋሪ ንትርክና የትዕቢት ባሕሪ በቂ የማንነት መገለጫ ስለሆነ ነው፡፡ … “… (ስለዚህ) ሰው ሆኖ ሰው ያለመሆን ማንነት” አለ ማለት … [Read more...] about አንተ ማነህ?
“ምስጢር ካወጣህ ቤተሰቦችህን እንፈጃቸዋለን”
“የደረሰብኝን ስቃይ ለማንም ብናገር ቤተሰቦቼን በሙሉ እንደሚፈጁ አስጠንቅቀውኛል” ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ በዝዋይ እስር ቤት ለወራት ስቃይ የተፈፀመበት ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ይባላል፤ አርሲ አርባ ጉጉ ተወልዶ አዳማ/ናዝሬት አድጎ፣ በ1998 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሲዮሎጂ ተመርቋል፡፡ በ2000 ዓ.ም በባህልና ቱሪዝም ሚ/ር በሲኒየር ካልቸራል ኤክስፐርትነት የስራ መደብ እስከ ሚያዝያ 2003 ሰርቷል፡፡ ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በግልፅ ባልተረዳው ምክንያት የመንግስት ደህንነት ሀይሎች ተያዞ ለ23 ወር በዝዋይ እስር ቤት ከፍተኛ ስቃይ እየተፈፀመበት መቆየቱን ይናገራል፡፡ መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም ከእስራት ሲለቀቅም አንድ ጊዜም እንኳን ፍርድ ቤት እንዳልቀረበ ለፍኖተ ነፃነት አስረድቷል፡፡ ከወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ጋር ያደረግነውን ቆይታ … [Read more...] about “ምስጢር ካወጣህ ቤተሰቦችህን እንፈጃቸዋለን”
አንዲት የኮንትራት ሰራተኛ በጅዳ ቆንስል በር ታንቃ ሞተች
በጅዳ መጠለያ አንዲት የኮንትራት ሰራተኛ በጅዳ ቆንስል በር ታንቃ ሞተች በሪያድ "ኢትዮጵያዊቷ አሰሪዎቿን ለመበቀል የ6 አመት ህጻን ገደለች" የሳውዲ ጋዜጣ ዘገባ ኮንትራት ስራ መጥተው ተፈናቅለው በጅዳ ቆንስል መጠለያ ከሚገኙት ቁጥራቸው ወደ 80 ከሚጠጉት እህቶች መካከል አንዷ እህት ከሁለት ቀናት በፊት እሁድ ጁን 23 ቀን 2013 በጅዳ ቆንስል ግቢ በር ራሷን አንቃ መግደሏ ታውቋል። ጉዳዩን ለማጣራት የዚህችው እህት ሬሳ ከቦታው ሲነሳ በቦታው ነበሩ ወደ ተባሉት በጅዳ ቆንስል የዲያስፖራና ተፈናቃይ ዜጎች ሃላፊ ወደ ሆኑት ቆንሰል ሙንትሃን በስልክ ለማግኘት ያደረግኩት ሙከራ አልተሳካም። ስለተፈጠረው አሳዛኝ ክስተት አካባቢው ከነበሩ የአይን እማኞች ለማጣራት ባደረግኩት ሙከራ ሟች በኮንትራት ስራ ከወሎ ወደ ሳውዲ አረቢያ መጥታ ከአመት በላይ ከሳውዲ አሰሪዎች ቤት ስትሰራ … [Read more...] about አንዲት የኮንትራት ሰራተኛ በጅዳ ቆንስል በር ታንቃ ሞተች
ምነዋ ! ማንዴላችን ? !
ምነዋ ! ማንዴላችን ? ! ድምጽህ ቁርጥ ቁርጥ አለ አመመህ ምነው ደከመህ በማረፊያህ ? አፍሪካን ከአንባገንን ልጆቿ ጸድታ ሳታይ ምነዋ መድከም ማሸለብህ ? የኢትዮጵያን ስርየት ሳይበሰር ምነዋ የመለየት ጉዞን መጀመርህ ኢትዮጵያ ከደዌ ተላቃ ሳትጎበኛት ምነዋ አትቀስቅሱኝ አልክ አንቀላፋህ ? ምነዋ መልአከ ሞት ከበበህ የስንብት መርዶ ጽልማሞት ግርማውን አለበሰህ ምነዋ ጠንካራውን ጉልበትክን ፈተነብህ የእማማን አፍሪካን ድህነት ማየቱ ታከተህ ! ምነዋ ማንዴላ?. . . (ይህ ከግጥሙ ተቀንጭቦ የተወሰደ ሲሆን ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) ነቢዩ ሲራክ … [Read more...] about ምነዋ ! ማንዴላችን ? !
ኦባንግ ከቴላቪቭ ባለስልጣናት ጋር ይመክራሉ
እስራኤል ኢትዮጵያ ውስጥ በህዝብ ፍላጎት የሚመረጥ የተረጋጋ መንግስት እንዲቆም ከመቼውም ጊዜ በላይ የምትንቀሳቀስበት ወቅት ላይ መሆኗን ለማሳሰብ በነገው እለት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እንደሚመክሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ አስታወቁ። የሒብሩ ዩኒቨርስቲ ምሁራንና ማህበረሰብ ለአቶ ኦባንግ መልክት ድጋፍ እንዲያደርጉ የሚጠይቅ ንግግር ያደርጋሉ። በእስራኤል የሚኖሩ ስደተኛ ወገኖችን አስመልክቶ ቃል እንደተገባላቸውም አመልክተዋል። አቶ ሳሙኤል አለባቸው “መኖርና መሞት ስላለ ወደ ህሊናችን ልንመለስ ይገባል" አሉ። የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር የአሜሪካ እንደራሴ (ኮንግረንስማን) ክሪስ ስሚዝ በመሩት የምክክር ሸንጎ ላይ ንግግርና ማብራሪያ ካሰሙ በኋላ ወዲያውኑ በቀጥታ ወደ እስራኤል አምርተው ነበር። ለሁለት ጉዳዮች ወደ እስራኤል ያመሩት አቶ ኦባንግ የኢትዮጵያን … [Read more...] about ኦባንግ ከቴላቪቭ ባለስልጣናት ጋር ይመክራሉ