• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የምርትና የሕዝብ እድገት እሽቅድድም

October 6, 2013 11:38 am by Editor 1 Comment

እአአ በ1798 (ከሁለት መቶ አሥራ አምስት ዓመታት በፊት) መምሬ ቶማስ ሮበርት ማልቱስ የሚባል የ32 ዓመት የብሪታንያ ቄስ የዘመኑን የነገረ ንዋይ አስተሳሰብ የለወጠ አዲስ ሀሳብን የያዘ መጽሐፍ አሳተመ፤  ሀሳቡ በጣም ግልጽ ነበረ፤ የሰው ልጆች ቁጥር እድገት መጠኑ እያጠፈ የሚሄድ ነው፤  የሕዝብ ቁጥር 1፣ 2፣ 4፣ 8፣ 16፣ 32፣ 64፣ 128፣  እያለ የሚጨምር ነው፤ ከእርሻ የሚገኘው ምርት ደግሞ የእድገቱ መጠን አያጥፍም፤ 1፣ 2፣ 3፣ 4፣ 5፣ 6፣ 7፣ 8፣ 9፣ 10፣ እያለ የሚሄድ ነው፤  የመምሬ ማልቱስን ሀሳብ በሌላ መንገድ ካየነው የበላተኞች ቁጥር እያጠፈ ሲያድግ የምግቡ አቅርቦት የሚያድገው ግን በጣም በዝግተኛ ፍጥነት ነው፤ የሚል ነው፤  እንግዲህ የሕዝብ ቁጥርና የምርት አቅርቦት እኩል መጓዝ ሲገባቸው የሕዝቡ ቁጥር እየቀደመ ስለሚገኝ፣ መምሬ ማልቱስ የደረሰበት መደምደሚያ የሕዝቡን ቁጥር ለመቀነስ በሰው ልጆች መሀከል በሽታ፣ ችጋርና ጦርነት የማይቀሩ ይሆናሉ፤ ችጋር፣ ጦርነትና ሌሎችም አደጋዎች በሕዝቦች ላይ እየደረሱ የሕዝብ ቁጥርና የምርት እድገት በሚያደርጉት መሽቀዳደም መሀከል ሚዛንን ይጠብቃሉ።

መምሬ ማልቱስ በነበረበት ዘመን ላይ ሆኖ ከሃምሳና መቶ ዓመታት በኋላ እውቀትና (ሳይንስ) የእውቀት ጥበብ የሚያስከትሉትን መሠረታዊ የአስተሳሰብ፣ የአሠራርና የኑሮ ለውጥ ለመገንዘብ አልቻለም፤ እንዴት ብሎ? በመምሬ ማልቱስ ዘመን በአንድ ሄክታር መሬት ላይ የሚገኘው ምርት አምስት ኩንታል ብቻ ቢሆን በኋላ ግን በአንድ ሄክታር ላይ በእውቀትና በእውቀት ጥበብ ኃይል ምርቱን ከእጥፍም በላይ ማምረት የሚቻልበት ዘመን መጣ፤ ምርጥ ዘር፣ ማዳበሪያ፣ የተለያዩ የእርሻ ዘዴዎች የእርሻውን ሥራ ቀልጣፋና ምርታማ አደረጉት፤ በዚህም ምክንያት የመምሬ ማልቱስን ሀሳብ ብዙ ሰዎች ይነቅፉት ጀመር፤ ሆኖም የመምሬ ማልቱስን ሀሳብ ዛሬም ቢሆን ሙሉ በሙሉ ጊዜ አልሻረውም፡፡

ከመሠረት ለመጀመር — አንድ አገር መሬት አለው፤ ሕዝብ አለው፤ መሬትም ሆነ ሕዝብ በጥሬአቸው ከቆሙ የመምሬ ማልቱስ ትንተና መደምደሚያ መሬቱ ከሚችለው በላይ የሆነውን ሕዝብ ችጋር፣ በሽታና ጦርነት ያነሣዋል፤ መሬትና ሕዝብ ብቻ አገርን አያቆሙም፤ በሕዝብ መሀከል ያለውን ግንኙነት፣ እያንዳንዱ ሰው ከሌሎች ጋር ያለውን አብሮ የመኖር ትስስር ሕግና ሥርዓት እንዲኖረው ያስፈልጋል፤ የመሬትም ሀብት አጠቃቀም በእኩልነትና በፍትሐዊነት ዘዴ ለመደልደል ሕግና ሥርዓት ያስፈልጋል፤ እንግዲህ ሕዝቡ ኑሮውን በሕግና በሥርዓት ለመምራት አንድ መንግሥት የሚባል እንደእድር ያለ ድርጅትን ይፈጥራል፤ እያንዳንዱ ሰው በግሉ የኑሮ ጣጣ ተወጥሮ በሚራወጥበት ጊዜ መንግሥት የሚባለው ድርጅት ለጠቅላላው ማኅበረሰብ የሚበጀውን ይሠራል።

በእያንዳንዱ ሰው የኑሮ ግዴታ መሬቱ ያለማቋረጥ በጥቅም ላይ እየዋለ በግጦሽና በእርሻ፣ በሌሎችም ምክንያቶች እየተጎዳ ይሄዳል፤ በዚህም የተነሣ መሬቱ የሚሰጠው ጥቅም በያመቱ ይቀንሳል፤ የመሬቱ መደህየት ከሕዝብ መደህየት ቀድሞ ይመጣል ማለት ነው፤ እንግዲህ መንግሥቶች የሚቋቋሙት እንዲህ ያለ ሁኔታ እንዳይፈጠር፣ ከተፈጠረም ብዙ ጉዳት እንዳያደርስ አስፈላጊ እርምጃዎችን ለመውሰድ ነው፤ በኢትዮጵያ ስለኢትዮጵያ የሚፈበረከው የአሐዝ መረጃ ወይም ስታቲስቲክስ አስተማማኝ ነው ባይባልም አማራጭ ባለመኖሩ ልንጠቀምበት እንገደዳለን፤ ለምሳሌ በ2004 ዓ.ም. የስታቲስቲክስ ጽ/ቤት ባወጣው መረጃ መሠረት የታረሰው መሬት 13 690 119 ሄክታር ነበር ይባላል፤ የስታቲስቲክስ መሥሪያ ቤት ገበሬዎች ሳይሆን ባለይዞታ የሚላቸው 14 747 439 ይሆናሉ፤ ይህንን ቁጥር በአምስት ስናባዛው (በአንድ የገጠር ቤተሰብ በአማካይ አባሎች) 73 737 195 ይሆናል፤ ይህንን ቁጥር ከ2007 የሕዝብ ቆጠራ ውጤት ጋር ማስተያየቱ ያስተምራል፤ ከዚያም በላይ አንዳንዶቹ ቁጥሮች በሌላ ቦታ አይደገሙም፤ ወይም መልካቸውን ለውጠው ይቀርባሉ።

ለጊዜው ግን ለያዝነው ርእስ የሚከተሉትን አሐዞች እንመልከት፤ በመጀመሪያው ሰንጠረጅ ባለይዞታ የተባሉት ገበሬዎችና የታረሰው መሬት (በሄክታር) በሦስት ዓመት ውስጥ ያሳዩትን ለውጥ ለማሳየት ይሞክራል፤ ሠንጠረጅ ሁለት ደግሞ የእርሻ ምርት (እህል፣ ጥራጥሬና የቅባት ዘር) ከገበሬው ቁጥር ጋር ለማነጻጸር ይሞክራል፤ ኢትዮጵያ የተአምር አገር መሆንዋን ተንተርሶ የስታቲስቲክስ ጽ/ቤት የእርሻ መሬቱንም በ2004 ዓ.ም. ትንሽ አሳድጎታል፤ አይቻልም ማለት አይደለም፤ በመስኖና በእርከን የእርሻውን መሬት መጨመር ይቻላል።

ሠንጠረጅ አንድ

የታረሰ መሬትና (በሄክታር) የገበሬዎች ቁጥር 2002-2004 ዓ.ም

ዓ.ም.

ባለይዞታ

እድገት ከመቶ

መሬት (ሄክታር)

ካለፈው ዓመት እድገት ከመቶ

አማካይ ድርሻ

መሬት ለባለይዞታ(ሄክ)

2002

13439174

100.0

12953636

100.0

0.96

2003

14789071

110.0

13358883

103.13

0.90

2004

14747439

109.7

13690119

105.69

0.93

ምንጭ የስታቲስቲክስ ጽ/ቤት ድረ-ገጽ

ዋናው ነጥብ ግን የስታቲስቲክስ ጽ/ቤት የፈለገውን ያሀል ቢጠማዘዝም እውነቱን እምብዛም ሊለውጠው አልቻለም፤ የቁጥር ነገር ወዲያ ቢሉት አራት፣ ወዲህ ቢሉት አራት ሆነና በአማካይ የአንድ ገበሬ እርሻ አንድ ሄክታር እንደማይሞላ መሸሸግ አልተቻለም፤ በእርሻ መሬቱ ላይ ያለው ጭነት በጣም ከፍተኛ ነው፤ እውነተኛውን የሕዝብ ቁጥር ብናውቅ ደግሞ ጭነቱ ምን ያህል የበለጠ እንደሆነ እንረዳ ነበር፤ የዓለም ባንክና የአሜሪካው ዓለም-አቀፍ የስለላ ድርጅት (ሲአይኤ) የኢትዮጵያን ሕዝብ ቀጥር በአሁኑ ጊዜ ከዘጠና ሚልዮን በላይ ያደርሱታል፤ በአገር ውስጥ የሚነገረው ቁጥር ግን በሰባና በሰማንያ መሀከል ነው፤ የዛሬ ሠላሳ አምስትና አርባ ዓመት ግድም በደቡብ (በተለይ በከምባታና ሀድያ፣ በወላይታና በሲዳሞ፣ በደራሳ) የሕዝብ ቁጥር የሚፈነዳ እንደሆነ ተናግሬ ነበር፤ በትግራይና በወሎም፣ በሰሜን ሸዋም በመሬቱ ላይ ያለው ጭነት ከባድ ነው።

ሠንጠረጅ ሁለት

የእርሻ ምርትና (አህል፣ጥራጥሬና የቅባት) የገበሬዎች ድርሻ

ዓ.ም. ምርት ኩንታል  ካለፈው ዓመት እድገት ከመቶ የባለይዞታ ቁጥር የባለይዞታ/የዓመት ድርሻ ኩንታል የአንድ ሰው የወር ድርሻ ኪሎ

2002

180758897

100.0

13439174

13.45

22.25

2003

203485288

112.57

14789071

13.76

22.92

2004

218569429

120.92

14747439

14.82

24.67

ባለይዞታ ምናልባት በአማካይ አምስት ሰዎችን ያካትታል፤ ነፍስወከፍ እያንዳንዱን ሰው ይመለከታል።

በእነዚህ ሁለት ሠንጠረጆች ላይ በግርድፍ (መረጃው ነው ግርድፍ!) የሚታየውን እውነት መሸሽግ አይቻልም፤ በወር 25 ኪሎ እህል ከችጋር  አለመውጣትን ያሳያል፤ መሬት ተትረፍርፎ ሠራተኛ ሕዝብ የጠፋበት አገር አንዳልሆነም ይታያል፤ ታዲያ ለህንድና ለቻይና፣ ለሌሎችም መሬት በችሮታም ሆነ በሽያጭ የምንሸጥበት ምክንያት ዕብሪት ከወለደው እብደት ሌላ ምን ሊኖር ይችላል?

ምንጭ: Mesfin Woldemariam Blog

መሬት የማን ነው? ክፍል አንድ – ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. koster says

    October 6, 2013 09:51 pm at 9:51 pm

    Population growth is not the Problem, as Long as there is injustice, greedy like woyane ethnic fascists even there will be 5 Million Ethiopians, the first one Million woyane ethnic fascists will have everything and the rest will suffer as usual.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule