ባለፈው ሳምንት የዘንድሮውን የደመራ በዓል አከባበር በዜና ማሰራጫዎች የተመለከቱ ግሪካዊ ቄስ ባነሱት ጥያቄ የተቀሰቀሰብኝን ስሜት፤ ለዚህች ክታብ መግቢያ ላደርገው ፈለኩ። “ባገርህ የተደረገውን የመስቀሉን በዓል በመገናኛ ዘዴወች አይቼው በጣም ደስ ይላል። ሄደህ ነበር? ብለው ጠየቁኝ። “አልሄድኩም” አልኳቸው። “ለምን አልሄድክም? ብለው መልሰው ጠየቁኝ። ያሰለቼኝ ጥያቄ ስለሆነ የጥያቄቸውን መስመር በመቀየር “እርስዎን ምኑ ነው ያስደሰተዎ? ብየ ጠየኴቸው። “አከባበሩ ደስ ይላል” አሉኝ። “የእርሰዎ መንፈስ የተማረከው ባከባበሩ መብልጭልጭ ነው። የኔን መንፈስ የሚማርከው ደግሞ በበዓሉ የሚወሱት እነ ቆስጠንጢኖስ፤ ዲዮቅልጥያኖስ፤ እነ ቅድስት እሌኒና የአባ አጋግዮስ አስከፊ ባህርይ ነው። ከዚህም ጋር ደመራ የሚለው የበዓሉ መጠሪያ እንደሚያመለክተው፤ ከልጅነት ጀምሮ ለበዓሉ የክብር መርገፎች በቤተ ክርስቲያናችን እና በየመንደሩ የሚዘመሩት፤ በየቤቱ የሚከናወኑት ድርብርብ ውበት ሰጭ ባህሎች ናቸው። ይህ የተከበረው ቅዱስ በዓል እርሰዎን ለመሰሉ ለውጭ ሰዎችና ታሪኩን ሳይገነዘቡ በብልጭልጭታው ብቻ የሚነዱትን ወገኖች ለማምታት መሳሪያ በመሆኑ እጅግ አያዘንኩ ነው” አልኳቸው። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply