• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

መንገድ ወድቆ አየሁት

October 8, 2013 08:25 am by Editor Leave a Comment

ርሃብ፣ ድካም እና ሰቆቃው ለላፉት 12 ወራት ተፈራርቀውበታል። አንዴ በሰሃራ በረሃ ሌላ ግዜ ደግሞ በሜዲትራንያን ባህር የሰው አእምሮ ሊቀበለው የማይችል ስቃይ አልፎ እግሩ አውሮፓን ምድር ከረገጠ እነሆ አንድ ሌሊት አለፈ። ሰነድ ገብረጻድቅ ይባላል። ፊቱ እጅግ ተጎሳቅሏል። ከሰውነቱ ላይ አጥንቶቹ ይቆጠራሉ።

ወጣቱ  ተስፋ ወዳደረገባት የአውሮፓ ምድር ለመግባት የተነሳው ከአመት በፊት ነው። እንብርቱ የተቀበረችበትን ሃገር ተሰናብቶ ከወጣ ጀምሮ የደረሰበት መከራ ይህ ነው አይባልም። ሰነድን እመንገድ ወድቆ ነበር ያገኘሁት። ለጥቂት ደቂቃ አነጋገርኩት። ንግግሩ የሚረብሽ ነው። አጭር የቪዲዮ ቆይታችንን ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ።

ከ 300 በላይ የኢትዮጵያውያ እና የኤርትራ ተወላጆች የፈጀው የላምፔዱሳ እልቂት በአለም አቀፍ ዜና እየታወጀ ባለበት ሰዓት፤ ሌላ መርከብ ከሊቢያ ተነስታ በጣሊያንዋ የጠረፍ ከተማ በሲሲሊያ ደረሰች። ይህች መርከብ 250 ዜጎችን ጭና ነበር። በዚህች መርከብ ላይ የሞተ ባይኖርም የአራት ቀን ጉዞው የአራት አመት ሰቆቃ ነበር የሆነባቸው። ይህች በርካሽ የተገዛች መርከብ የመጫን አቅሟ 120 ሰዎችን ብቻ ነው። ተጓዦቹ ርሃብና ጥማትን መቋቋም ነበረባቸው። እጅ እግራቸውም ለአራት ቀናት መተጣጠፉ የግድ ነው።  እዚያው ይጸዳዳሉ።

የሊቢያን ጠረፍ እንዳቋረጡ፤ ትልቅ ማእበል ተነስቶ መርከቧን አናወጣት።  እናም መሃል መንገድ ላይ ቀጥ ብላ ቆመች። በሶርያ ሹፌሮች ወደሊቢያ ደውለው የህጻናትን ድምጽ ሲያሰሙ ካጣልያን እርዳታ ሊያገኙ እንደቻሉ ሰነድ አጫወተኝ።

የፖለቲካውና የኑሮ ሁኔታ አስገድዶት ስደትን የመረጠው ይህ ወጣት ጋር ባደረግኩት ቆይታ፤ በህይወት እዚህ መድረስ መቻሉ እንደትንግርት ነው የሆነብኝ።

ከሱዳን ተነስቶ ሊቢያ ለመግባት ሰሃራ በረሃን ማቋረጥ ነበረበት። የሰሃራ በረሃን ገሃነመ እሳት ተቋቁሞ ለ 21 ቀናት ተጓዘ። “እዚያ ህይወት ከንቱ ናት።”  አለኝ ሰነድ። አብረው ከነበሩት ውስጥ ገሚሱ እዚያው በረሃ ላይ ቀርቷል። በሙቀቱ ብቻ ሰውነታቸው እየፈራረሰ የሞቱ ወገኖች አሉ። ከረጅም የእግር ጉዞ በኋላ ዳግሞ፣ በሁለት ላንድ ክሩዘሮች ተጭነው ተጓዙ። እሱ የነበረበት ላንድ ክሩዘር 125 ሰዎችን ጭኗል። መጫን ከሚገባው አራት እጥፍ መሆኑ ነው።

“እንደዶሮ ከላይ እና ከታች፤ አንዱ በሌላው ላይ እየተደራረብን ተጫንን” አለኝ። ወጣቱ ሲናገር የሃዘን ስሜት አላየሁበትም። ሃዘኑን ጨርሶ የደነዘዘ በድን አይነት ነው የሆነብኝ። በሰሃራ በረሃ የሞተ ሰው መቅበር ጨርሶ አይታሰብም። እያንዳንዱ ይህ ተራ ስለሚጠብቀው የሚወድቀው ወገኑን እያየ የራሱን ነፍስ ለማትረፍ ነው የሚጓዘው። በዚህ የነብስ አውጭኝ ስቃይ መሃል ሴት እህቶቻችን እንዴት እንደሚደፈሩ ነገረኝ። ይህንን ለመስማት እንኳን ይዘገንናል።

ከነሱ ቀድሞ የተጓዘው ላንድ ክሩዘር ሰዎችን እንደዋዛ እያንጠባጠበ በረሃውን እየሰነጠቀ ይነጉዳል። እነ ሰነድ የተጫኑበት ፒክ አፕ ደግሞ አስከሬኖቹን እየረገጠ ይከተላል።

ከበሽታው፣ ከረሃብና ጥማቱ፣ ከበረሃው ንዳድ እና ከመኪና አደጋው በተአምር አምልጠው ሊቢያ ሲደርሱ፤ ጠረፍ ላይ እስር ነበር የጠበቃቸው። ሰነድ ቤንጋዚ በምትባል የሊቢያ ከተማ ገንፉጣ ከተሰኘ እስር ቤት ውስጥ ተከረቸመ። ለአራት ወራት እዚያ እንደቆየ በደላሎች በኩል 1000 የሊቢያ ዲናር ጉቦ ከፍሎ ከእስር ሊወጣ እንደቻለ ነገረኝ።

በሊቢያ በግምት ከዘጠኝ ሺህ በላይ ስደተኛ እስረኞች አሉ። አብዛኞቹ ኤርትራውያን እና ኢትዮጵያውያን ናቸው። የሱዳን፣የግብጸና የማሊ ስደተኞች አይታሰሩም። በድንገት ከታሰሩም ዜግነታቸውን አረጋግጠው በነጻ ይለቀቃሉ።

ሰነድ ከእስር እንደወጣ በደላሎች አማካኝነት ወደመርከብ ጉዞ ተላከ። ይህንን እየሰሩ ያሉ፤ ሊቢያ ያሉ የአራት ደላሎችን ስም ጠራልኝ። መድህኔ፣ ራፉ፣ ኤርምያስ እና ያሲን። እነዚህ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ደላሎች ናቸው።  ከዋናዎቹ የሊቢያ ደላሎች ጋር የሚያገንኙ ናቸው።

እነዚህ ደላሎች ዋስትና የሌለው (Use and throw) መርከብ በርካሽ ይገዙና ሰዎችን ከአቅም በላይ ይጭኑበታል።”እንደ እቃ ደራርበው ያስቀምጡናል።” አለ ሰነድ።

መርከቡ ጉዞውን ካጠናቀቀ ጣልያን – ሲሲሊ ላይ ያራግፍና እዚያው ይጣላል። የነ ሰነድ መርከብ የገባው ከላምፔዱሳው እልቂት በኋላ ነበር። ሲሲሊ እንደደረሰ እነሱን ያመጣው መርከብ እዚያው ተሰባብሮ ተጣለ።  120 ሰው መጫን የሚገባው የካምፐዱሳ መርከብ 500 ሰዎችን በመጫኑ ምክንያት ባህር ውስጥ ሰምጦ ቀረ። ሰነድ እዚህ ሊያገኛቸው ተስፋ ያደረገባቸው ጓደኞቹን ሁሉ እንዳጣ አጫወተኝ።

በለፉት 6 ወራት ብቻ ከስምንት ሺህ በላይ ስደተኞች ከሊቢያ ተነስተው ማልታ ገብተዋል። ጉዞ ከጀመሩት ገሚሶቹ መሆኑ ነው።  አሁንም 3000 የሚሆኑ ከሊቢያ እስር ቤት የወጡ ስደተኞች መርከብ እየጠበቁ ናቸው። እድለኞች ከሆኑ መርከቡ ወይ ጣልያን ያደርሳቸዋል፣ አልያም የሻርክ ምግብ ሆነው ታሪካቸው በሜዲትራንያን ላይ ይፈጸማል።

አቅራቢያዬ ከሚገኝ ስደተኞች የተጠለሉበት አንድ ህንጻ አምርቼ ነበር። እዚያም ከሶስጥ ቀናት በፊት የገቡ የኤርትራ ስደተኞችን አገኘሁ። አንደኛዋ ስደተኛ እዚህ በገባችበት ማእግስት መርዶ መጣ። አብሯት የተነሳው ወንድሟ በረሃ ላይ እንደወደቀ ተነገራት። ከሟቹ ጋር አብረው የነበሩ ሲናገሩ። “አሸዋ ውስጥ ቀብረነዋል። መቀብሩም ላይ ምልክት አድርገናል።” አሉ።

እንዴት ይረብሻል?

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule