• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በትግራይ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ካምፕ ዓመጽ ተካሯል

October 8, 2013 08:04 pm by Editor 5 Comments

አመጹ ከካምፕ ወደ ካምፕ እየተዛመተ ነው

በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ተመዝግበው በትግራይ-ኤርትራ ድንበር ዳርቻ በስደት ማቆያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ የኤርትራ ተወላጅ ስደተኞችና በኢህአዴግ መካከል የተፈተረው አለመግባባት ተካሯል። የሰው ህይወት ማለፉና ነጻ እንቅስቃሴ መከልከሉ ተሰምቷል፤ እስካሁን ስድስት ሞተዋል፤ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ በርካታዎች ቆስለዋል።

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውና በአውሮፓ ተቀምጠው ጉዳዩን የሚከታተሉ የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት ኦክቶበር 5 ቀን 2013 ምሽት ላይ በትግራይ ማይ ዓይኒ ወረዳ በሚገኝ የስደተኞች ካምፕ የተቀሰቀሰው ረብሻና ተቃውሞ ወደ ሌሎች ካምፖችም ተዛምቷል። በተለይም በትላንትናው እለት ሽሬ አካባቢ በሚገኘው አድ ሃሪሽ ካምፕ የተነሳው ተቃውሞ ጋብ ሊል የቻለው ኢህአዴግ ሃይል በመጠቀሙ እንደሆነ ተመልክቷል። በዚህም የሃይል ርምጃ የቆሰሉ በርካታዎች እንዳሉ ተመልክቷል።

በአካባቢው ነዋሪዎችና ገለልተኛ ታዛቢዎች ባለመኖራቸው ጉዳዩ ይፋ ባይወጣም የተፈጠረው አለመግባባት በሁሉም የስደተኛ ካምፖች እንዳይቀጣጠል ከፍተኛ ስጋት አለ። የዜናው ምንጮች እንደሚሉት ኢህአዴግ ልዩ ክትትል በማድረግ በአካባቢው የነበረውን ነጻ እንቅስቃሴ ዘግቷል። ቁጥጥሩንም አጥብቋል። አሁን የተጀመረው ተቃውሞና ረብሻ ስደተኛ መስለው ካምፕ በተቀላቀሉ የሻዕቢያ ሰላዮች የሚቀነባበር እንጂ ሻዕቢያ ያማረራቸው የሚፈጽሙት እንዳልሆነ ኢህአዴግ በስፍራው ባሉ አመራሮቹ እየተናገረ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሱዳን የስደተኞች ካምፕ የሚኖሩ 30 ሺህ የሚጠጉ የኤርትራ ስደተኞች የስራ ፈቃድ እንዲሰጣቸው ከውሳኔ መደረሱ ተሰምቷል። በዓለም ዓቀፉ የስደተኞች ተቋምና በሱዳን መንግሰት መካካል በተደረገ ሰፊ ድርድር ስደተኞቹ ፈቃድ ለማግኘት የሚችሉበት አግባብ ላይ ተደርሷል። በቅርቡ በውሃ ላይ በደረሰ አደጋ ህይወታቸውን በሚያሳዝን መልኩ ያጡትን ዜጎች ተከትሎ በስደት ጣቢያዎች ለረዥም ጊዜያት የተቀመጡ የኤርትራ ስደተኞች ስራ የሚሰሩበትና ጉዳያቸው ባጭር ጊዜ የሚታይበት አግባብ ሊኖር እንደሚገባ እየተጠቆመ ነው። ከስደተኞቹ ወገንም ይህ ጥያቄ በተደጋጋሚ እየቀረበ ነው።

የሻዕቢያን አገዛዝ በመሸሽ ኤርትራን የሚለቁ ዜጎች በየጊዜው መበራከታቸው ያሳሰበው የኤርትራ መንግስት ለዜጎቹ መሰደድ የሲአይኤና የኢህአዴግ እጅ አለበት በማለት በተደጋጋሚ ክስ ማቅረቡ አይዘነጋም። ከኤርትራ በኩል እንዲህ ቢባልም ኢህአዴግ በቀጥታ ጉዳዩን አያስተባብልም። ይልቁኑም ኢህአዴግ ራሱን ከሻዕቢያ የሚሻል የዲሞክራሲ አባት አድርጎ ስለ ኤርትራ ተወላጆች መብትና ጥቅም ተካራካሪ አድርጎ ነው የሚስለው። ቀደም ሲል የረብሻውን መቀስቀስ አስመልክተን በፌስቡክ ገጻችን ባሰፈርነው ዘገባ የቆሰሉት አራት ስደተኞች ሲሆኑ ህክምና ቢደረግላቸውንም ሊተርፉ አለመቻላቸው ተጠቁሟል። ዜናውን ያቀበሉን ክፍሎች እንዳሉት ስደተኞቹ በወያኔ ደህንነቶችና ሰላዮች አንተዳደርም በማለት ያነሱት ጥያቄ መልኩ ሳይቀይር የዓለምአቀፉ የስደተኞች ኮሚሽን ጣልቃ መግባት እንዳለበት ያሳስባሉ:።

ቀደም ሲል የተነሳውን ረብሻ አስመልክቶ የሚከተለውን ዜና ጽፈን ነበር። እስካሁን ድረስ ከሻዕቢያም ሆነ ከኢህአዴግ ስለደረሰው ችግር የተሰጠ አንዳችም ፍንጭ የለም። (Photo: JRS)

የኤርትራ ስደተኞች በትግራይ ተቃውሞ አነሱ
“በኢትዮጵያ ደህንነቶች አንተዳደርም”

የሻዕቢያን አገዛዝ በመሸሽ ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱ የኤርትራ ተወላጆች “በኢትዮጵያ ደህንነቶች ስር አንተዳደርም” በሚል የተቃውሞ ድምጻቸውን በማሰማታቸው ግጭት መነሳቱ ተሰማ። የስደተኛ ካምፑ አስተዳደሮች “ሻዕቢያ ያሰረጋቸው ሰላዮች እንጂ እውነተኛ ስደተኞች ይህንን ጥያቄ አያነሱም” ማለታቸውን ከስፍራው ከነበሩ ለመረዳት ተችሏል።

ኦክቶበር 5 ቀን 2013 ማምሻውን በትግራይ ማይኒ ወረዳ “ማይ ዓይኒ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የተቀሰቀሰው ረብሻ ሲነሳ ስደተኞቹ ያሰሙት ቅሬታ “በወታደሮች አንተዳደርም፣ የካምፑ ሰራተኞች በሙሉ ኢትዮጵያዊ ናቸው፣ የደህንነት ሰራተኞች ሊያስተዳድሩን አይገባም …” የሚሉ ሲሆኑ የጥያቄያቸው መደምደሚያ “በስደተኞች ድርጅት (UNHCR) ሰራተኞች እንተዳደር” የሚል ነው።

በተጠቀሰው ቀን ምሽት በጣሊያን ውሃ ላይ ሰጥመው ለሞቱ የኤርትራ ተወላጆች የሃዘን ስሜት ለማንጸባረቅ በተዘጋጀ የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት ላይ ረብሻው እንደተነሳ የገለጹት የስፍራው የጎልጉል ምንጭ፣ ረብሻውን ተከትሎ ድንጋይና የተለያዩ ቁስቁሶች መወርወራቸውን አመልክተዋል።

ረብሻውን ለማስቆም ታጣቂ የወታደሮች ተኩስ መክፈታቸውን የገለጹት ክፍሎች አራት ስደተኞች መቁሰላቸውን ተናግረዋል። ረብሻው እስኪነጋ ድረስ መቀጠሉንም ጠቁመዋል። ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ ረብሻው ስለመቆሙ የተባለ ነገር የለም።

የዜናው ምንጮች በካምፑ አስተዳደሮች በኩል ስለሚሰጠው ምላሽ ተጠይቀው “ሻዕቢያን አምልጠው ስደት ካምፕ በሰላም የደረሱ ስደተኞች በምንም መልኩ ተቃውሞ ሊያነሱ አይችሉም። ስደተኛ መስለው የተቀላቀሉ የሻዕቢያ የደህንነት ሰራቶች ናቸው ይህንን የሚያደርጉት” ሲሉ መስማታቸውን ተናግረዋል።

ከተባበሩት የስደተኞች ኮሚሽን በስደተኞች ስም የሚገባው ከፍተኛ ገንዘብ ይዘረፋል በሚል ውስጥ ውስጡን ቅሬታ እንደሚደመጥ የጠቆሙት እነዚህ ክፍሎች፣ ገንዘብን አስመልክቶ ስደተኞች ከሚያሰሙት ቅሬታ በላይ በሙስና ለተጨማለቀው ኢህአዴግ ለስደተኞች የሚላከው ገንዘብ መጠን እንዳሳሰበው ያስረዳሉ።

ስደተኞቹ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ በመሆናቸው ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚረዱዋቸው ወገኖቻቸው በባንክ የሚልኩላቸው ገንዘብ መብዛቱ ኢህአዴግን እንዳስጨነቀው ስለ አሰራሩ የሚያውቁ ክፍሎች አስረድተዋል። ከፍተኛ መጠን ያለው ብር ወደ ስደት ካምፖች የሚላከው “በትክክል ከዘመድ አዝማድ ወይስ ከሌላ?” የሚለውን ኢህአዴግ ማጥናት ከጀመረ መቆየቱን አመልክተዋል።

በማይ ዓይኒ ካምፕ ብቻ ከ4000 በላይ ስደተኞች እንደሚገኙ የሚገልጹት ምንጮች አብዛኞቹ የአስተዳደር ሰራተኞች የኤርትራ ዜግነት ያላቸው የኢህአዴግ ወዳጆች እንደሆኑ ቢገለጽም ስደተኞቹ ሊቀበሉት አልቻሉም። ተነሳ የተባለው ረብሻ በኢህአዴግና በሻዕቢያ መካከል ያለው ውጥረት በተካረረበት ወቅት መሆኑ ጉዳዩን እንዳያወሳስበው ስጋት አለ። አስተያየት ሰጪዎች አንደሚሉት ስደተኞቹ ኢትዮጵያ ምድር ቢገኙም የሚተዳደሩት በዓለም የስደተኞች ድርጅት ስር በመሆኑ ያለመሰለል መብታቸው የተጠበቀ ነው። እንደተባለው እየተሰለሉ ከሆነ አግባብ አይደለም ድርጊቱን ድርጅቱ ራሱ ያወግዘዋል ብለዋል።

በሌላ በኩል ግን የስደት ከለላ የሰጠችውን አገር ደህንነት በሚፈታተን መልኩ መንቀሳቀስ ሌላው ትልቁ የህግ ጥሰትይሆናል ሲሉ ተናግረዋል። ዜናውን አስመልክቶ ከኢህአዴግ ወገን እስካሁን የተባለ ነገር የለም። በኢትዮጵያ በተለያዩ የስደተኞች ካምፕና በአዲስ አበባ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የኤርትራ ተወላጆች መኖራቸው ይታወቃል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. በለው! says

    October 8, 2013 09:57 pm at 9:57 pm

    “ትናንት ያስገነጠሏቸው ባህር ጨመሯቸው! አትገንጠሉ ብለን የተዋጋናቸው ዛሬም መጠለያ ከለላ ሆንናቸው!”በለው!
    **ኤርትራ ኢትዮጵያዊነት በግድ ተጭኖብኛል፣ በአማራ ቅኝ ግዛት ሥር ሆኛለሁ፣ ጣሊያን ፓስታ በሹካ መብላትእና እንግሊዝ አፍራሽ ታሪክ አስታጥቆናል ነጭ በመፈራራቅ የገዙን ይበቃናል ብለው፣ አማራው አትገንጠሉ ሲል ህወአት፣ ኦነግ፣ አብንግ፣ የውጭ አሽቃባጭ አረብና ባርያ አሳዳሪዎቻቸው እየጎተጎቱ መና ከሰማይ ይወርዳል! ቀይ ባሕር ወርቅ ይታፈሳል! አሰብ ላይ ስንዴ ይመረታል! አስመራ ትንሿ ኒው ዮርክ ትሆናለች! ዳህላክ ..ላስቬጋስ ይሆናል! ሱማሊያ አምሽታችሁ… ጅቡቲ ታድራላችሁ… የመን የእናንተ ነው። ተገንጠሉ ሲሉ አቀዣበሯቸው። ያ. ሁሉ ጅግና የድሃ ልጅ እንደቅጠል እረገፈ..ፖለቲከኖችና ሆድአደር ምሁራን ገንዘብ ሰሩ፣ ልጆቻቸውን አሸሹ፣ገንዘብ ጭነው ጠፉ።

    *ዓለም በትዝብት ተሳለቀ…ታዋቂው ምሁሩ ሊቁ አቶ መልስ ዜናዊ ዕውቅናን አተረፉበት።የአክስታቸውን ልጅ ሥልጣንን ጠቅልሎ እንዳያበራቸው ሲሉ ቶሎ የመገንጠል እውቅና ሰጡ፣ ገንዘብ ለውጠው አስጊዎቻቸውን ሻቢያ በሌሊት ልብሳቸው እያስለቀሱ በአውቶቡስ እየጫኑ በረሃ ላይ ጣሏቸው። የፈረደበት አማራም ሳይቸግረው አትገንጠሉ ብሎ ሰንደቅ ዳርድንበር አንድነት ሲል ለራሱ ህዝብ አንዲትም ነገር ሳይሰራ ሞቶ ለትውልዱ ሁሉ ጠላት ሆነ! **ህወአት የሻቢያን ውለታ እረሳው ጭራሽም አሸባሪ የቀጠናው አተራማሽ አለው፤ባህሉንና ቋንቋን ሰበረና መብቱን ነፍጎ ጭረሽ ለሰላምና ለመገንጠልህ የሞተልህ የሚሞትልህ ህወአት/ወያኔ ነው በማለት የሁለቱም ዘር ያላቸው ባሕሪና ሥማቸውን የሚቀያይሩት ድንበር ተሻጋሪ ‘የሻቢያ ህወአት’ ልጆች መሳለቅ ጀመሩ “ሌባ አብሮ ሲሰርቅ እንጂ ሲካፈል አደጋ አለው” አንዱ አንዱን ለመጣል ለማጥፋት ፸ሺህ ወጣት በስምምነት ወስደው ባድሜ ላይ ፈጁ ሁለቱም አሸባሪ ኀይላት ተቀናቃኝ ትውልድን አጥፍተው ሥልጣናቸውን የዕድሜ ልክ ከትውልድ ትውልድ የሚተካካ በማለት በነጮች እየተወደሱ መሬትና ህዝብ በመሸጥ ከበሩ። ሆኖም በግራና ቀኝ የጥፋት ኀይሎችን እያሰለጠኑ አካባቢው ጭር እንዳይል ረብሻ እየፈጠሩ እራሳቸው ሰላም አስከባሪ እየሆኑ በድሃ ልጅ ነፍስ ቁማርን ተያያዙት” እና ሞቱ ጠ/ሚኒ የኤርትራ ልጆች በወር ቢያንስ ፪፻ ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ ይሉ ነበር። ለመሆኑ እንዴት ኤርትራውያን ኢትዮጵያ ገብተው አላለቁም? ? ችግሩ በኤርትራውያን ሥም ትግራውያን በስደተኝነት ፎርም ሀገር ጥለው እንዲጠፉ እየተደረገ ነው። ህወአትና ሻቢያ ሀገር ተቆጣጥሮ ሠላም ሰፍኖ፣ ነፃነት ተጎናፅፈው፣ እንዴት? ለምን?ሀገሩን ጥሎ በበረሃ ይሞታል? በባሕር የአዞ እራት ይሆናል? ሰውንት አካሉን ወንበዴ እያወጣ ይሸጠዋል?ምን አልባት ግፍ ያመጣው ቅጣት ይሆን? ለምን ይዋሻል? ለምን?
    ***ኤርትራውያን ከኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ነፃ ከወጡ በኋላ ትግራይ ከኤርትራ ነፃ ከወጣች በኋላ ብዙዎች የተቃዋሚ ፓርቲ በወያኔ አስተማሪነት ተመርቀዋል፣ ብዙዎች ያላገኙትን የዪኒቨርስቲ የነፃ ትምህርት ይሰጣቸዋል ትግራይና ኤርትራውያን አልተለዩም፣ ባለሀብትና ባለንብረት ሆነዋል፣ንግዱን ያጧጡፋሉ፣ ሙሉውን የሀገሪቱን ደህንነትና ኢኮኖሚም ተፈቅዶላቸዋል። “ከሞኝ ወፈር ሞፈር ይቆረጣል ነው ነገሩ” ሁሉም አሸባሪ ወንበዴ ናቸው።
    **ኦሮሞው ኮ/ል መንግስቱ ኀይለማርያም ” ኤርትራውያን ከአማራው በበለጠ ጭነት ማመላለሻ መኪና፣የነዳጅ መሸጫ፣ምግብ ቤቱንና ንግዱን ይዘዋል ችግራቸው ምንድነው? ” ብለው ነበር ።ልክ እንደ አሁኑ ‘ኦነግ’ ክርስቲያንና ሙስሊም ሆኖ በመተወን የሚያደርገው “የቁራ ጩኸት”እና ” የአዞ ዕንባ” መሆኑ ነው። ይህ ሀገር የማጥፋት ሕዝብ የመገንጠል አባዜ የባዕዳን ተላላኪነት የነበረ አለ የሚቀጥል ነው። ለመሆኑ ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል በደህንነት ኀላፊና ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሆኑ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የውጭ ጉዳይና የኢኮኖሚ ሚ/ር ሆነው ህወአት (ኢፈርትን ይዘውሩ የለምን) በረከት ስምኦን የሀገር ውስጥ ደህንነት የጠ/ሚኒስትሩ የፖለቲካ አመራር ፣ስብሃት ነጋ የህወአት ቃል አቀባይና የኤርትራ ጉዳይ ኀላፊ አደሉምን? ?

    ***ታዲያ ኤርትራ ወዴት ነው የተገነጠለችው ?በማይኒ ካምፕ ብቻ ከ፵፻ በላይ ስደተኞች ;በአዲስ አበባ ፻ሺህ የሚቆጠሩ የኤርትራ ተወላጆች መኖራቸው ይታወቃል።ሥማቸውን በአማራና በኦሮሞ ሥም ከቀየሩ እንደ ተስፋዬ ገብረ እባብ በሚስጥር በፖለቲካ ሥራ ከተሠማሩት፣ ከኦሮሞ በላይ ኦሮሞነትን የሚያንቆለጳጵሱ ጆሌ ብሸፍቱ !ዶ/ር መራራ ጉዲናን፣አቶ ቡልቻ ደመቅሳን፣ ዶ/ር ነጋሱ ጊዳዳን ኦሮሞነት የሚያንቃሽሹ የሚያጥላሉ ፣የአቶ ገብረመድሕን አርዓያን ትግሬነት የሚያሳንሱ ፣ በዝምድና በአበልጅ ጆሮ ጠቢ ሆነው በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ወሬ የሚለቅሙ አውቆ አበዶች፣ አንዳንዴም ኦሮሞ ተመሳሳይ የቁም ሞት እንዲሞት ኤርትራውያን በገቡበት ገደል ለመጨመር ተራራ ጫፍ ውጣ! ግፋ ጨፍጭፈው !የሚሉ የፖለቲካ በታኝ “የሙስሊም ኦሮሞ የሜንጫ አብዮተኖችም” ህዝብና ሀገር የሚጀውሩ የተፈጠሩትና የሚበረታቱት አንድ የነጭ የሚሽነሪ መፅሃፍ አያነበቡ፣ አፈ ታሪክንና ልብወለድን እንደእውነተኛታሪክ እየሰበኩ፣ በፉርኖ ዱቄት የተታለሉ፣ ደረቅ የወተት ዱቄት የቃሙ፣ አሁን ኢትዮጵያን ከሚመሩት ኤርትራውያንም ውጭ እልፍ አዕላፍ ናቸው ።ድሃው ኤርትራዊና ኢትዮጵያዊ ወጣት አዞ በላው !ዕድሜ ልክ መለመኛ መሳቀያ ሆነ!ተላገጡበት፣ ሰለቡት፣ አመከኑት!!

    ****ኦክቶበር ፭ቀን ፳፲፫ ማምሻውን በትግራይ ማይኒ ቀበሌ «ማይኒ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የተቀሰቀሰው ረብሻ ሲነሳ ስደተኞቹ ያሰሙት ቅሬታ» በወታደሮች አንተዳደርም፣ «የካምፑ ሰራተኞች በሙሉ ኢትዮጵያዊ ናቸው፣ የደህንነት ሰራተኞች ሊያስተዳድሩን አይገባም… »የሚሉ ሲሆኑ የጥያቄያቸው መደምደሚያ «በስደተኞች ድርጅት ዩ.ኤን.ኤስ.አር ሰራተኞች እንተዳደር» የሚል ነው።”
    – አዎን፣ ጌታ በባሪያው አይተዳዳርም ማለታቸው ይሆናል። ይህ የሻቢያና የህወአት መናናቅ “ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው ተዋቸው ይዋጣላቸው በለው!!
    *****”ስደተኞቹ ኢትዮጵያ ምድር ቢገኙም የሚተዳደሩት በዓለም የስደተኞች ድርጅት ስር በመሆኑ ያለመሰለል መብታቸው የተጠበቀ ነው”። ለመሆኑ ለሌላው ፹፭ ሚሊየን ኢትዮጵያዊ የቁም እስረኛ የሀገሩ ባዕድ ዜጋ ማን ይቁምለት?
    **ኢትዮጵያውያን በገዛ በሀገራቸው መናገር ፣መፃፍ፣ መሰብሰብ፣ ሠላማዊ ሠልፍ ለማድረግ፣ ፓርቲ ለማቃቋም፣ ለመንቀሳቀስ፣ንብረት ለማፍራትና በሀገሪቱ ተዘዋውረው ለመኖር፤ ሕዝብ ለመቀስቀስ ገዢው ፓርቲ መርጦ በሰጣቸው የተወሰነ ቦታና ክልል ብቻ እንደሆነ ኤርትራዊው ጠ/ሚር ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል ቃል አቀባይ አቶ ኀይለመለስ ደስአለኝ ዜናው በከባድ ማስጠንቀቂያ በዚሁ ሳምንት ‘ድምፃችን ይሰማ!’ ሲሉ ደንፍተዋል። ታዲያ በሀገራችን ከሚኖሩ ኤርትራውያን ስደተኞች መብት ያነሰ መብት ኢትዮጵያውያን ካለን በእርግጥም አቶ መልስ ምሁር ኤርትራዊ ነበሩ። ለዚህ አደለም አህታቸው ጠላ ሻጭ ወንድማቸው ጢቢኛ ሻጥ ሆነው ሟቹ መለስ ሀገር የሚሸጡት በአንድ ወቅት ሲያብራሩ ” ሀገር ማለት፦” ለእኔ ወንዙ ተራራው ሸንተረሩ አደለም ሕዝብ ነው”ብለው ነበር። ሕገመንግስቱ የሚለው “እኛ የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች” ይላል ግን እነዚህ ሕዝቦች እንደዓሳ በባህር እንደአዕዋፍ በዛፍ ላይ ይኖራሉ ማለት ነውን? ሀገር ባሕር ፣ወንዝ ፣ሸንተረር ፣ተራራ የለውም ማለት ነው? ሕዝቦች ሲሉ የአካባቢው ሰዎች የእኛ ናቸው በማለት ንብረታችን ንብረታቸው የሚል ጋብቻ ማለት ነው? ሕገመንግስቱ ሀገር ሉዓላዊነት አያወራም! ሰንደቁ የሚያስተዳድረውን ሕዝብና ሀገር ዳርድንበር አይገልፅም! የፓርቲ አርማ የታጋይ ምልክት አለው። ሕገመንግስቱም”የፓርቲ ማኒፌስቶ” እንጂ የሕዝብ አደለም! አይሆንም! ስለዚህ የተገነጠለ ሀገር የለም። በፈለገው ግዜ ሊጨፍርብህ ይችላል ለዚህም አላማጣ ወልቃይትና ሁመራ የትግራይ ሆኖ ትግራይ ከሱዳን ተዋሳኝ ሀገር ሆና በደረቅ ወደብ እንዲገናኝና መብራት ሰጥቶ ነዳጅ በመቅዳት እንዱስትሪ መር ታላቋ ትግራይ ትመሠረታለች የሚል ትራንስፎርሜሽን በመለስ እንደተቀየሰ ታጋይ አዜብ ከራዕይ የውርስ ደብዳቤአቸው ላይ ገልፀዋል ። ብሔር ብሔረሰብ በጭፋሮ ኦሮሞም በአማራና በአማርኛ ላይ ብቻ በጽንፈኝነት በቁሙ ሲቃዥ በ፻ዓት የተረሳ ፖለቲካ በእየአዳራሹና ቡና ቤቱ ሲፎልል፣ ሰያጨበጭብ፣ ቀለጠ በለው!።
    ግን ዕድሜ ለህወአት የፕሬዘዳንት ሥልጣንና ኅይል ደግሞ ተጎናፅፏል…መሬት ከአማራው ነጥቆ ለቻይና፣ለ ሕንድ፣ለቱርክና ለዓረብ በመሸጡ ፈንድቋል። ፅንፈኛና አሸባሪያንን በማሰልጠንና በማንቃት በዓለም ዙሪያ ሲሰብክ ይታያል። በሰላምና በፍቅር በስደት በትግራይ ክልል የሚኖሩ ኤርትራውያን ቤታቸው ነው ወገኖቻቸው ሞተውበታል፤ እንደተባለው እየተሰለሉ ከሆነ አግባብ አይደለም ድርጊቱን የስደተኞች ማሰባሰቢያው ያወግዘዋል ብለዋል።
    ** በሌላ በኩል ግን “የስደት ከለላ የሰጠችውን አገር ደህንነት በሚፈታተን መልኩ መንቀሳቀስ ሌላው ትልቁ የህግ ጥሰት ይሆናል: የሚለው ማ? ማንን ያዛል? ኤርትራውያን ስደተኞች በኢትዮጵያ ያላቸው ነፃነትና መብት ዜግነት አለን ብለው ተከልለው ከሚጨፍሩት ብሄር ብሔረሰቦች የበለጠ ነው ሊኮሩበት ይገባል።ኢትዮጵያዊነትና የኢትዮጵያውያን እንግዳ አቀባበልና ክብር ከማናቸውም ዓረብና ነጭ አማላይ፣ ሰባኪ ቅን ገዢዎቻቸው በበለጠ የሚያኮራ መሆኑን ይወቁት ሻቢያ ፈልፍሎ ለላከብን ባንዳዎች ለህወአት፣ኦነግ ፣ኦብነግ እና ሌሎችም ከዚህ ውድቀት ተምረው የተሻለውን መንግድ ቢይዙ በህዝባቸው በብሔራቸው በትውልድ ባያላግጡና ባያመክኑት ይሻላል። አድርባይነትና የምሁር ድንቁርናን ባያስፋፉ ይሻላል በለው !!
    “ታፍራና ተከብራ የኖረች ኢትዮጵያ ለዘለዓላም ትኑር! በቸር ይግጠመን ከሀገረ ካናዳ!>>

    Reply
    • selam says

      October 11, 2013 01:29 am at 1:29 am

      b%^&* tutti governi

      Reply
  2. ምነው ጃል says

    October 9, 2013 01:04 pm at 1:04 pm

    አረ… በናተህ ቀስ በል ይህ ሁሉ ለምንድነው ማን ምን አደረገህ ለተከሰቱት ሁሉም እነዲሁም ለሚከሰቱትም ጭምር መንግስት ብቻ ሳይሆን ህዝቡም እኮ ተጠያቂ ነው። ምነው ለመጣው… ከመጣው ሁሉ እያጨበጨብን…

    Reply
  3. Demessew says

    October 10, 2013 06:50 pm at 6:50 pm

    ከሁሉ በፊት በዚህ ዘግናኝ በሆነ አደጋ (የግፍ አገዛዝን እንሸሻለን ብለው) ለተሰዉ ኤርትራውያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እግዚአብሄር ነፍሳቸውን እንዲምራቸው እጸልያለሁ።
    በጣም አሳዛኝ አደጋ ነው የደረሰው።
    ሌላው የሚያሳዝነኝ ደግሞ ፤ መላው አለም የተሰማውን ከፍተኛ ድንጋጤና ሀዘን በስፋት እየገለጸ ባለበት ወቅት፡ እኛ ኢትዮጵያውያን፡ የቀድሞ ዜጎቻችን (ወይም እንደ አንዳንዶቻችን እምነት ከሆነ አሁን ኢትዮጵያዊ የምንላቸው ሰዎች) መጎሳት ብዙ ማለትና መቖጨት ሲገባን፡ ሀዘን መቀመጥ ሲገባን፡ ቤተሰቦቻቸውንና ዘመዶቻቸውን ማጽናናት፡ ለቅሶ መድረስ ወ መቀመጥ ሲገባን፡ ዝም ማለታችን ነው።
    ማንም ምንም ሲል አልሰማሁም አላየሁም። በምትኩ የሚጻፈው ወቅታዊ ያልሆነ ከላይ የተጻፈውን የሚመስሉ አስተያየቶችን ነው።
    እግዜር ይጠብቅን!

    Reply
  4. ዳዊት says

    October 20, 2013 12:27 pm at 12:27 pm

    እኔ የሚገርመኝ ኤርትራን በሚመለከት የሚቀርቡ ኣስተያየቶች የሚያሳዘን ነዉ እዚህ ላይ መታወቅ የሚገባዉ ኤርትራን ነጻ የወጣችዉ በልጆችዋ ነዉ ደርግን የመሰለ ፋሽሽት መንግስትን ከዚህ ምድር ያጠፋ ህዝበ የኤርትራ ህዝብ ነዉ ከ 300,000 በላይ የደርግ ሰራዊት ያለቀበት ነጻነታችንን አትንኩ፥አጋኖ ማዉራት,የሌለ ነገር ማዉራት,ትንሽ ጫፍ ይዞ መናገር የአብዛኛዉ ኢትዬጵያዊ ባህሪ በመሆኑ አይደንቀንም
    እባካችሁ ስለ አገራችሁ አስቡ እኛ ከደሮም ቢሆን ኢትዬጵያዉያን አይደለንም አንፈለግምም

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule