• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

Editor

ኢህአዴግ ከሳዑዲ ጋር መቆሙን አረጋገጠ!

November 16, 2013 12:00 am by Editor 4 Comments

ኢህአዴግ ከሳዑዲ ጋር መቆሙን አረጋገጠ!

አዲስ አበባ ላይ በሳዑድ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ ሊካሄድ የነበረ የተቃዉሞ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ። አሶሺየትድ ፕረስ እንደዘገበዉ ፖሊስ በመቶዎች የሚቆጠሩን ሰልፈኞች ለመበታተን ኃይል ተጠቅሟል። መንግስት ፈቃድ እንዳልተሰጠዉ በማመልከት ቁጥራቸዉን ባይጠቅስም የታሰሩ መኖራቸዉን ገልጿል። ሰልፉን ያስተባበረዉ የተቃዉሞ ወገን ሰማያዊ ፓርቲ በበኩሉ ሁለት ሊቃነመናብርቱን ጨምሮ አንድ መቶ ሰዎች ገደማ መያዛቸዉን አመልክቷል። የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል ፀረ አረብ ስሜት ሊፈጥር የሞከረ ያሉት ተቃዉሞ ሰልፍ አዘጋጆች ከሚመለከተዉ አካል ፈቃድ ባለማግኘታቸዉ እንደሚከሰሱ ለአዣንስ ፍራንስ ፕረስ ገልጸዋል። በፖሊስ ከተደበደቡት አንዱ እንደሆነ የገለጸዉ አስፋዉ ሚካኤል፤ መንግስት የሳዉዲ አረቢያን ድርጊት ላይ የቀረበዉን ተቃዉሞ ለምን ማገድ እንደፈለገ እንዳልገባዉ ለዜና ወኪሉ … [Read more...] about ኢህአዴግ ከሳዑዲ ጋር መቆሙን አረጋገጠ!

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

ጭንቁን ቀን እንዴት እንለፍ!?

November 15, 2013 08:52 pm by Editor Leave a Comment

ጭንቁን ቀን እንዴት እንለፍ!?

ጥላቻው እያደገ ሔዷል፣ ሳውዲ አሰሪዎች ኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኞቻቸውን ድሮ ድሮ በአረቦች ዘንድ የተከበርን፣ የታፈርን የእኛን የሃበሻ ልጆች "ጨካኞች ፣ የማይታመኑ!" እያሉ ጥላቻቸውን መገልጽ ጀምረዋል። November 14,2013 የወጣው አረብ ኑውስ Recent clashes make Saudis wary of Ethiopian maids በሚል ርዕስ ስር ሳውዲ አሰሪዎች ኢትዮጵያን ሰራተኞችን ለማባረር እየዛቱ ነው! ይህ የአረብ ኒውስ ዘገባ በሹክሹክታ የምንሰማው ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የሪያድ መንፉሃን ግጭት ተከትሎ ደም እድገብሮም ለኢትዮጵያን ተሰጠው ወደ ሃገር ቤት የመግባትን እድል ለመጠቀም ከሃያ ሽህ በላይ ኢትዮጵያውያን የሪያድ መጠለያዎችን አጨናንቀዋል። እንዲውም በሪያድ የኢትዮጵያ አምሳደር ቁጥሩን ወደ ሃያ ሶስት ሽህ እንደሆነ ረቡዕ November 14,2013 ለወጣው አረብ … [Read more...] about ጭንቁን ቀን እንዴት እንለፍ!?

Filed Under: Politics Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

ሰባተኛው የለውጥ መዘውር ነጥብ እየቀረበ ይሆን?

November 15, 2013 07:32 pm by Editor 5 Comments

ሰባተኛው የለውጥ መዘውር ነጥብ እየቀረበ ይሆን?

ኢትዮጵያ የዘውድ ስርዓት ከወረደ በኋላ ባልተረጋጋ የለውጥ ማዕበል ውስጥ መናጥ ከጀመረች 40 ዓመታት እየደፈነ ነው። የየካቲት 1966 ዓም አብዮት ዘንድሮ 40 ዓመት ይሞላዋል። ከ 1966 ዓም በፊት በነበሩት ስልሳ አመታት ውስጥ ሀገራችን ከሁለት መቶ አመታት በላይ በዘመነ መሳፍንት የእርስ በርስ ግጭት ከቀረው ዓለም ጋር የነበራት ግንኙነት በብዙ መልኩ የተለያየ እና ጠንካራ የማይባል ነበር። ከ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመርያ እስከ አጋማሹ ማለትም 1966 ዓም በነበሩት ዓመታት ውስጥ ሀገራችን ፍፁም ከሆነው የፊውዳል ስርዓት ወደ ዘመናዊነት ለመግባት ብዙ ነገሮች በየዘርፉ የጀመረችባቸው አመታት ነበሩ። ዘመናዊ መንግስት ስርዓት- እንደ ፓርላማ፣ ዩኒቨርስቲዎች፣ የአየር መንገድ አገልግሎት፣ የመብራት ኃይል ማስፋፋት፣ በዓለም አቀፍ ግንኙነትም ሆነ በአህጉራዊ እና አካባቢያዊ ፖለቲካ ውስጥ … [Read more...] about ሰባተኛው የለውጥ መዘውር ነጥብ እየቀረበ ይሆን?

Filed Under: Politics Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

የኢትዮጵያን መንግስት ለፍርድ ለማቅረብ ከተነሱት ስዊድናዊ ጠበቃ ጋር ውይይት ተደረገ

November 15, 2013 06:27 pm by Editor Leave a Comment

የኢትዮጵያን መንግስት ለፍርድ ለማቅረብ ከተነሱት ስዊድናዊ ጠበቃ ጋር ውይይት ተደረገ

ቅዳሜ ኖቬምበር 2 ቀን 2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ መድረክ በስዊድን የወያኔን መንግስት በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ለማቅረብ የተጀመረውን ክስ መነሻ በማድረግ የክሱን ሂደት ከሚመሩት ከስዊድናዊው ጠበቃ ከስቴላ ያርዴና ከሌሎች እንግዶች ጋር በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ወይይት አደረገ። ውይይቱ ከቀኑ 14፡00 ሰዓት የተጀመረ ሲሆን ውይይቱን የከፈቱት የመድረኩ ሊቀ መንበር ም/ኢኒስፔክተር ሚሊዮን ብሩ ናቸው። ኢኒስፔክተር ሚሊዮን በንግግራቸው መክፈቻ ጥሪ የተደረገላቸውን እንግዶችና ተሰብሳቢውን ህዝብ አመስግነው መድረኩ የተቋቋመበት ዓላማ በሀገር ውስጥና በውጪ የሚደረገውን የነጻነት ትግል የተደራጀ መልክ ይዞ የሚጓዝበት መንገድ ለማመቻቸትና በየጊዜውም ይህንን መሰል ውይይት በማድረግ ትግሉን ለመርዳት መሆኑን ገልጸው የዛሬውንም ስብሰባ የዚህ መነሻ እንደሆነ … [Read more...] about የኢትዮጵያን መንግስት ለፍርድ ለማቅረብ ከተነሱት ስዊድናዊ ጠበቃ ጋር ውይይት ተደረገ

Filed Under: Politics

ሰላማዊ ሰልፍ በባዕድ ሀገራት እና “አስራ አንደኛው ቀን” በሳውዲ አረቢያ

November 15, 2013 10:58 am by Editor Leave a Comment

ሰላማዊ ሰልፍ በባዕድ ሀገራት እና “አስራ አንደኛው ቀን” በሳውዲ አረቢያ

በሳውዲ አረቢያ በወንድምና እህቶቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለውን አሰቃቂ ግፍና መከራ ለመቃወም በትላንትናው እለት ህዳር 5 ቀን 2006 ዓ.ም በጀርመን ፈራንክፈርት ሳውዲ አረቢያ ቆንስላ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተገኝቼ ነበረ። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ሰላማዊ ሰልፍ በባዕድ ሀገራት እና “አስራ አንደኛው ቀን” በሳውዲ አረቢያ

Filed Under: Politics Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

ሠርግ በጥንታዊት ኢትዮጵያ እምነትና ባህል የሠርግ ሥነ ስርዓት

November 15, 2013 10:53 am by Editor Leave a Comment

ሠርግ በጥንታዊት ኢትዮጵያ እምነትና ባህል የሠርግ ሥነ ስርዓት

ይህች ጦማር ለሙሽሪት አክሊለ ብርሃን እና ለሙሽራው ድንቁ መንግሥቱ ጋብቻ በተዘጋጀው እራት ግብዣ፤ በከንሳስ ደብረሣኅል መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ቀርባ የነበረችውን ትምህርት የያዘች ናት። ወደ ጦማር ለመለወጥ ስዘጋጅ፤ ዓረቦች በወገኖቻችን ላይ የሚፈጽሙትን ግፍና በደል ሰማሁ፤ በአንድ ወቅት ባንድ ቤተሰብ ላይ ሞትና ሠርግ ባንድ ቀን ተፈጸሞ የደረሰባቸው ሁኔታ ተሰማኝ፤ ይህንንም በ፪ኛው አንቀጽ በ፭ኛው ገጽ ላይ ገልጨዋለሁ። ጦማሯ ሁሉንም ስለምትዳስስ ለሁሉም ቀርባ ሁሉም ቢያነባት ስለምትጠቅም ላንባቢ ትቅረብ የሚለው ሀሳብ ስለበዛ የቀረበች ናት። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ሠርግ በጥንታዊት ኢትዮጵያ እምነትና ባህል የሠርግ ሥነ ስርዓት

Filed Under: Opinions

የወያኔ ሴራና ግፍ ለማን አቤት እንበል??

November 15, 2013 10:33 am by Editor 1 Comment

የወያኔ ሴራና ግፍ ለማን አቤት እንበል??

ኢትዮጵያውያን ብዙ ጮኽን ያዳመጠን ግን የለም፡ ፡ ለሰው ጩኽን፤ ለፈጣሪ ጩኽን፤ ለመሬትም ጮህን፤ አንዳች ምላሽ በመሻት፤ ጩኽታችን ግን ለሠማይና ለምድርም ጮህን፤ ጩኸታችን ግን የቁራ ጩኽት ሆኖ ቀረ፡፡ የተፈረደብን የመከራ ዘመን ከማለቅ ወይ ከመገባደድ ይልቅ እየጨመረ ሄደ፡፡ በግልፅ የሚታየውን ችግራችንን፣ ከፊታችን ሳይቀር የሚነበበው ጉስቁልናችን፣ ሚሊዮኖችን ምርኮኝ ያደረገ ርሃባችን፣ ፀሐይ የሞቀው የርስበርስ ፍጅታችንን ደመናን ቀርቶ የጎጇችንን ጣሪያ ማለፍ የተሳነው ምህላና ፀሎታችን ብዙዎች በየቀኑ ሽቅብ የምንረጨው እንባችን፤ ሁሉም በማንም ዘንድ ተሰሚነት አላገኘም፡፡ አሁንም ለቅሶና ዋይታችን ተባብሶ እንደቀጠለ ነው ሲባል።አሁንማ ማን የማይጮህ አለ? ሁሉንም የሚያስጮኸው ግን አንድ ነገር ነው፣የወያኔ … [Read more...] about የወያኔ ሴራና ግፍ ለማን አቤት እንበል??

Filed Under: Opinions

መንግሥት አልባ አገር!

November 14, 2013 09:31 pm by Editor 4 Comments

መንግሥት አልባ አገር!

የብዙ ሺህ ዘመናት የመንግሥትነት ታሪክ የነበራት አገራችን ኢትዮጵያ ዛሬ መንግሥት አልባ አገር ናት ብሎ ደፍሮ መናገር የሚቻልበት ወቅት ላይ ደርሰናል። ኢትዮጵያ የፀረ ቅኝ አገዛዝ ትግል ፋና ወጊና የበርካታ ጥቁር ሕዝብ የነፃነት ትግል ማነቃቂያ ምሳሌ ሆና ቆይታለች፤ ህዝቧም ክብር ያለው ነበር። አሁን ባለንበት ዘመን ግን  ኢትዮጵያዊነት የሚያሳፍር የኢትዮጵያውያንም ዋጋ ከእንስሳት ይልቅ የወረደበት ወቅት ላይ እንገኛለን። በየተሰደድንበት ሁሉ እንገረፋለን፣ እንታሰራለን፣ እንገደላለን፣ ሴቶች እህቶቻችን ይደፈራሉ። ይህ የኢትዮጵያዊያን የቀን ከቀን ሕይወት ነው! ዓይኖቻችን በርካታ ግፎችን ተመልክተዋል! ጆሮዎቻችን ስፍር ቁጥር የሌለውን የወገኖቻችንን የሰቆቃ ድምፅና የድረሱልኝ ጥሪ አድምጠዋል! በጥቅሉ ኢትዮጵያውያን ረክሰናል! ኢትዮጵያዊ መሆን አሳፋሪ ሆኖአል። ይህችን ጽሁፍ … [Read more...] about መንግሥት አልባ አገር!

Filed Under: Opinions Tagged With: Full Width Top, Middle Column

The Kingdom from hell and Ethiopians

November 14, 2013 10:28 am by Editor Leave a Comment

The Kingdom from hell and Ethiopians

Today it is said that there are over a quarter of a million Ethiopians in the Kingdom of Saudi Arabia. The vast majority are young economic refugees working as maids, chauffeurs, and house servants. Women outnumber men and judging by the conditions in Ethiopian it is safe to say most have less than eight grade education. Most arrive with an employment contract for a  specified period of time while a few are undocumented refugees working menial jobs. Saudi Arabia with a population of about 27 … [Read more...] about The Kingdom from hell and Ethiopians

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

ከካሌብነት ወደ ከልብነት

November 14, 2013 08:25 am by Editor 1 Comment

ከካሌብነት ወደ ከልብነት

ኢትዮጵያ እመ-መከራ የግዜር መመራመሪያው የስቃይ ቤተ-ሙከራ መውደቅማ ነበር ያባት እንደ ያሬድ እስከ ሰባት እንደ በላ ብላቴና፣ የእንክርዳድ ሙልሙል እንጎቻ የትውልዴ እጣ ፋንታ ፣ መውድቅ መውድቅ መውድቅ ብቻ… አጤ ካሌብ የተባለ የኢትዮጵያ ንጉሥ ባንድ ወቅት በቅድመ-እስልምና የመን የሚኖሩ ክርስቲያኖች ባንድ ያይሁድ ገዥ መዳፍ ስር መማቀቃቸው አስቆጥቶት ቀይ ባሕርን ተሻግሮ ተበቅሎላቸዋል። የዛሬውን አያድርገውና፣ እንኳን ለቤት ለጎረቤት ጥቃት የሚቆረቆር ንጉሥ ማፍራት ችለን ነበር፤ አንኳን ለቤት ለጎረቤት እርዳታ የሚበቃ ጉልበት ማካበት ችለን ነበር። ዛሬ ግን ጊዜ ከካሌብነት ወደ ከልብነት ደረጃ አውርዶናል። (“ከልብ” በግዕዝ ውሻ ማለት ሲሆን በአማርኛ ዘይቤ አንድ ሰው ያለ ካሳ ያለ ጉማ ደሙ ፈሶ ሲቀር ደመ ከልብ ሆነ ይባላል)። አቅመ-ቢስ ሕዝቦች በጉልቤ ሕዝቦች መዳፍ … [Read more...] about ከካሌብነት ወደ ከልብነት

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

  • « Previous Page
  • Page 1
  • …
  • Page 323
  • Page 324
  • Page 325
  • Page 326
  • Page 327
  • …
  • Page 392
  • Next Page »

Primary Sidebar

Recent Posts

  • Defected Fano Spokesperson Alleges Orthodox Fano Is Pursuing Ties with Radical Islamist Groups Houthis and Al Shabaab November 24, 2026 06:38 am
  • “ፋኖ እንደ ሁቲ እና አልሸባብ ካሉ ዓለም አቀፍ የሽብር ቡድኖች ጋር ለመሥራት ጥረት እያደረገ ነው” November 23, 2026 10:52 pm
  • በፋኖ ስም ከአማራ ገበሬና ከዳያስፖራ የሚሰበሰበው በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የጥቂት አመራሮች መበልጸጊያ ሆኗል November 20, 2026 08:54 am
  • የቴሌኮም ጌትዌይ፣ የዳታ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ደህንነት – የዌብስፕሪክስ ጉዳይ ከባለቤትነት ክርክር በላይ ነው! November 17, 2026 11:54 pm
  • “የጫካ ቱጃሮች!”— የፋኖ አመራሮች ስለተሰማሩበት የገንዘብ ዝርፊያ አስደንጋጭ መረጃ November 17, 2026 05:43 pm
  • በየወሩ 4 ሚሊዮን ብር እየተከፈለው ሀገር ሲያፈርስ የነበረው ሪፖርተር November 16, 2026 01:17 am
  • ሻርኮቹ ከውጭ እስከ ሀገር ውስጥ ያደሩት ድር፣ ዌብስፕሪክስን (WebSprix) የመጠቅለሉ ድራማና ብሔራዊ ስጋት November 14, 2026 12:42 am
  • የመለስ ዜናዊን ጭንብል የገፈፈው የትህነግ ሚዲያ (EMF) ምስክርነት November 13, 2026 03:32 pm
  • ትህነግ በወታደራዊና በፖለቲካዊ መስክ እንደሞተ ሁሉ በሪፖርተር በኩል የሚዲያ ግብዓተ መሬቱ ተፈጽሟል November 13, 2026 01:13 am
  • በከባድ ታክስ ማጭበርበር የሚፈለጉት አቶ አበባው ደስታ፣ አማራጭ የቴሌኮም ጌትዌይ ፕሮጀክትን ሊጠቀልሉ ነው November 12, 2026 03:50 am
  • “ፋኖ ወደ ኦሮሚያ ገብቶ ሕዝብ እየገደለ ነው” የኦነግ ሸኔ (OLF/OLA) ተወካይ ጃል ጅረኛ November 10, 2026 05:12 pm
  • ከትህነግ የተማረኩና ከውጭ ሀገራት የገቡ ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች በቃሊቲ ለእይታ ቀረቡ November 6, 2026 03:36 pm
  • የመንግሥት ኃላፊዎች ወደ ሁርሶ የተወሰዱበት ምሥጢር November 5, 2026 12:43 pm
  • መንግሥት ሰማ፤ ሪፖርተር ተዘጋ፤ ግን ለምን? ምሥጢሩ ምንድነው? November 3, 2026 12:09 am
  • ኢትዮጵያ በሰማይ ላይ ነዳጅ የሚሞሉ የኢሉሺን (Il-78) አውሮፕላኖችን ከሩሲያ ልትገዛ ነው October 30, 2026 08:57 am
  • ካይሮ ያጣችውን የሩሲያ ጄቶች አዲስ አበባ የታጠቀችበት ምሥጢር October 29, 2026 10:26 am
  • ኢትዮጵያ ሱ-35 ተዋጊ ጄቶች እና የኤስ-400 ዘመናዊ የአየር መከላከያ ስርአት በመታጠቅ ከሰሃራ በታች ብቸኛዋ ሀገር ሆናለች October 28, 2026 11:00 am
  • ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በ“ካሚካዜ” ድሮኖች ለመምታትና በዘር ግጭት ለማፍረስ ሰፊ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተሰማ October 27, 2026 11:14 pm
  • ጆን መዲድ “ቀዝኖ እና ልብሱ ተበላሽቶ” ነው መከላከያ የማረከው October 27, 2026 08:41 pm
  • በጆን መዲድ መማረክ አደረጃጀቱ እየተፈረካከሰ በመሆኑ እነ ወዲ እምበይተይ፣ ምግበይ፣ ቀጣዮች ሊሆኑ ይችላሉ October 27, 2026 09:17 am
  • ከታክስ ስወራ እስከ ሐሰተኛ ጋብቻ፦ በኢትዮጵያ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊ ዳያስፖራዎችን ለማደን የተዘረጋው አዲሱ የአሜሪካ መረብ October 21, 2026 09:26 am
  • ኔታንያሁ የሶማሊላንድን ሉዓላዊነት ያረጋገጠ አዲስ ቀጣናዊ ካርታ ይፋ አደረጉ October 20, 2026 03:20 pm
  • ትውልደ ሶማሊያዊቷ ናፊሳ በተዘቀዘቀ የአሜሪካ ሠንደቅ ፊት በሶማሊኛ ምርጫ ቅስቀሳ ማድረጓ ቁጣ ቀሰቀሰ October 20, 2026 09:21 am
  • በአሜሪካ የሚገኙ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊዎች ላይ የተደቀነው አዲስ ስጋት October 19, 2026 08:58 pm
Copyright © 2026 · Goolgule