የብዙ ሺህ ዘመናት የመንግሥትነት ታሪክ የነበራት አገራችን ኢትዮጵያ ዛሬ መንግሥት አልባ አገር ናት ብሎ ደፍሮ መናገር የሚቻልበት ወቅት ላይ ደርሰናል።
ኢትዮጵያ የፀረ ቅኝ አገዛዝ ትግል ፋና ወጊና የበርካታ ጥቁር ሕዝብ የነፃነት ትግል ማነቃቂያ ምሳሌ ሆና ቆይታለች፤ ህዝቧም ክብር ያለው ነበር። አሁን ባለንበት ዘመን ግን ኢትዮጵያዊነት የሚያሳፍር የኢትዮጵያውያንም ዋጋ ከእንስሳት ይልቅ የወረደበት ወቅት ላይ እንገኛለን።
በየተሰደድንበት ሁሉ እንገረፋለን፣ እንታሰራለን፣ እንገደላለን፣ ሴቶች እህቶቻችን ይደፈራሉ። ይህ የኢትዮጵያዊያን የቀን ከቀን ሕይወት ነው! ዓይኖቻችን በርካታ ግፎችን ተመልክተዋል! ጆሮዎቻችን ስፍር ቁጥር የሌለውን የወገኖቻችንን የሰቆቃ ድምፅና የድረሱልኝ ጥሪ አድምጠዋል! በጥቅሉ ኢትዮጵያውያን ረክሰናል! ኢትዮጵያዊ መሆን አሳፋሪ ሆኖአል።
ይህችን ጽሁፍ እንድከትብ ያነሳሳኝ ሰሞኑን በሳዑዲ አረቢያ በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና ኢሰብዓዊ የሆነ ድርጊት ሲሆን ሴቶች እህቶቻችን ከባሎቻቸው ተነጥለው ተወስደው አንዳንዶቹም በሚወዷቸው ቤተሰቦቻቸው ፊት በብዙ የአረብ ጎረምሶች ተደፍረዋል። በዚሁ የተነሳ ህይወታቸው አልፏል፣ ብዙዎች በአደባባይ ደማቸው ፈስሷል፣ በግፍ ተገድለዋል፤ የተረፉትም በአሰቃቂ ሁኔታ ምግብና ውሃ በሌለባቸው ማጎሪያዎች ተወርውረዋል።
የእነዚህ ወገኖቻችን የድረሱልኝ የጣር ጥሪ አዕምሮን ይረብሻል።
ለነገሩ እንዲህ አይነት ነገር ሲከሰት ዜጎቹ ላይ ይህ ጥቃት የደረሰበት አገር መንግስት በደሉን በፈፀመው መንግስት ላይ ጦርነት እስከ ማወጅ የሚያደርስ እርምጃ ሊያስወስድ እንደሚያስችል ግልፅ ነው። አነሰ ቢባል ግን ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ርምጃ ሊወሰድ የግድ ነው። ይህ ሁሉ ወግ ግን መንግስት ካለው አገር እንጂ ካልታደለችው ኢትዮጵያችን እንዴት ሊገኝ ይችላል?
ዋነኛዉ የመንግሥት ሃላፊነት የዜጎችን ደህንነት መጠበቅና የአገርን ሉዐላዊነት ማስከበር መሆኑ ቢሆንም ኢትዮጵያን የሚገዛው ህወሃት መራሹ ቡድን ግን በሁለቱም አይታማም፤ድንበራችንን ለባዕዳን ደግሞ ደጋግሞ በመስጠት የአገር ክህደት ፈፅሞአል። በርካታ ዜጎቻችን ከመኖሪያ ቀያቸው አፈናቅሎ ለሰቆቃና ለስደት ዳርጎ ከእነርሱ የተቀማውን መሬት አንድ ፓኮ ሲጋራ ሊገዛ በማይችል ዋጋ ለባዕዳን ቸብችቦታል።
የዚህ ዕድል ተጠቃሚ ከሆኑት ውስጥ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የሆኑት፤ በኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ በተካሄደው ጦርነት መሳሪያና ገንዘብ ሲያቀብሉና ሲያቀባብሉ የነበሩት ዛሬም የዜጎቻቸውን ከርስ ለመሙላት ከአላሙዲን ጋር በተደረገ ስምምነት (መሞዳሞድ) በብዙ ሺህ ሄክታር የሚገመት መሬት የወሰዱብን እነዚሁ ዛሬ በወገኖቻችን ላይ አሰቃቂ በደልን የሚፈፅሙት የሳዑዲ አረቦች ናቸው። የህወሃት አገዛዝም ከዜጋው ይልቅ ለእነርሱ እየሰገደ ክብራችንን በሙሉ ጠቅልሎ ሸጦታል።
ከዚህ የተነሳ ቢንቁን ቢገድሉን ማን ጠያቂ አለባቸው?
የዚህ ሁሉ ግፍ ተጠቂ የሆነው ህዝብ ስደትን መምረጡ አንድ ነገር ሆኖ፤ የሚሰደደው ደግሞ ወደ እነዚሁ መሬታቸውን ወደወሰዱባቸው አረቦች መሆኑ የእንቆቅልሹ ሌላው ገፅታ ነው።
እነዚህ ወገኖች ሲሰደዱ ስርዓቱ ከስደተኞች ሊያገኝ የሚችለውን ጥቅም ያሰላል እንጂ ስለሚሰደዱ ዜጎች ግድ የሚሰጠው አይደለም። አሁን በሳዑዲ አረቢያም ሆነ በሌሎች የአረብ አገራት የሚሰደዱትን ዜጎች በኤጀንሲ ስም የሚልኩትና የወገኖቻችንን የሽያጭ ዋጋ ለራሳቸው የተቀማጠለ ኑሮ መደጎሚያ የሚያውሉት የህወሃት ባለስልጣን ዘመዶችና የስርዓቱ ታማኞች መሆናቸው የአደባባይ ምስጢር ነው። በሳውዲ የኢትዮጵያ አምባሳደርና ቤተሰቦቻቸው ሳይቀሩ የዚሁ የሰው ሺያጭ ኢንቨስትመንት ዋነኛ ተዋናዮች መሆናቸው ይነገራል።
ታድያ በሳዑዲ አረቢያ ባሉ ወገኖቻችን ጣርና መከራ በተመለከተ የህወሃት አገዛዝ ጠንካራ አቋም ከመውሰድ ይልቅ የድርጊቱ ሰለባ በሆኑት ወገኖቻችን ቁስል ላይ እንጨት የመስደድ ያህል ችግር እየደረሰባቸው ያሉት ህጋዊ ፈቃድ የሌላቸው ናቸው በማለት ሲሳለቅ ተደምጧል።
ለመሆኑ ህጋዊ ፈቃድ የሌላቸው ቢሆንስ ዜጎች አይደሉምን? ጥፋት ቢኖርስ በህጋዊ መንገድ ሊጠየቁ ይገባል እንጂ እንዲህ አይነት ሰቆቃ እንዲደርስባቸው እንዴት ይፈቀዳል? ህገወጥ የተባሉትንስ ከአገር ቤት እስከ ውጭ ያለውን የሰው ሽያጭ ሰንሰለት የሚያካሂዱት የራሱ የህወሃት ባለሟሎች አይደሉምን? ይህንስ በማለት ከተጠያቂነት ማምለጥ የሚችሉ ይመስላቸዋልን?
አይደለም! ይልቅስ አገሬ ኢትዮጵያ መንግስት አልባ አገር እንደሆነች ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፥ መንግስት በሌለበት ደግሞ የዜጎችን ደህንነት መጠበቅና የአገርን ሉዓላዊነት ማስከበር በህዝቡ ጫንቃ ላይ ብቻ ይወድቃል።
በመሆኑም በሳዑዲ አረቢያ ያሉ ወገኖቻችንን ሰቆቃ ለማስቆም ኢትዮጵያውያን በተለይ በውጭ የምንኖር ሁሉ በምንገኝበት አገር በሳዑዲ አረቢያ ኢምባሲዎች ፊት የተዘጋጁ ሰላማዊ ሰልፎች ላይ በመገኘት በኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው ግፍና ግድያ ባስቸኳይ እንዲቆምና ይህ ካልሆነ ግን ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስከፍላቸው እናስገንዝባቸው።
ህወሃት ገና ከጅምሩ በነጻ አውጪ ስም አገር መምራት ሲጀምር ኢትዮጵያን እንደ አገር በመቁጠር ሳይሆን ሕገወጥነትን እና የመሣሪያ የበላይነትን በገሃድ በማሳየት ለመሆኑ የዛሬ 22ዓመት በየአደባባዩ የተረሸኑ ኢትዮጵያውያን ደም ህያው ምስክር ነው፡፡
ስለሆነም ሁለተኛውና ዋነኛው ጉዳይ ለዚህ ሁሉ ስደትና ውርደት ግድያና ሰቆቃ የዳረገንን የህወሃት አገዛዝ እና አስተሳሰቡን ጭምር ነቅለን መንግስት አልባ የሆነችውን አገራችንን የህዝብ መንግስት ባለቤት ለማድረግ የሚካሄደውን ዕልህ አስጨራሽ ትግል በመቀላቀል የድርሻችንን እንወጣ።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!
ዳንኤል ከኖርዌይ በተለይ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የተላከ
anteneh says
Amen . TPLF eko agern limera sayhon sijemer Tigrayn ligenetil asbo sayasbew zufan lay yeweta yewenbedewoch tirikim (ye mafia ) budin new mechereshaw gin tekarbual aykerm
በለው! says
እኛ ፈቅድን ህወአት አዋረደን! በለው!
“ኢትዮጵያ የምትመራው ከትጥቅ ትግል ጀምሮ እስካሁን ድረስ በኤርትራውያንና በትውልደ ኤርትራውያን ነው እኔም ኤርትራዊ ነኝ” ስብሃት ነጋ ከሀገር ፍቅር ሬዲዮ ጋዜጠኛ ንጉሴ ወልወደማርያም በዋሽንግተን ዲሲ ከተናገሩት የተወሰደ”።
*ለመሆኑ መንግስት ምንድነው? ገድሎ ሬሳህን አሞራ እንዳይበላው የሚጠብቅ ወታደር ያለው ማለት ይሆን?
*ኢትዮጵያ እንደ ታላቅ አንድ ሀገር ሳትሆን በወሮ በላ ተከፋፍላ በክልል ታጥራ እንድትኖር በህወአት ማኒፌስቶ(ሕገመንግስት) ፅሑፍ ተረቆላት፣ ህዝቦቹ በፊት ያልነበሩ፣ እንዳአዲስ ተፈጥረው ለመሬት፣ ለወደብ፣ ለዳርድንበር፣ ለቋንቋ፣ ለባሕልና ለታሪክ፣ ለአንድነትና አብሮ መኖር እሴት ላይናገሩ እንኳንም በቁማቸው ስለሚኖሩበት መሬትና መብት ፣ሞተውም ኪራይ የሚከፍሉባት የመጤዎች መስፈሪያ ስትባል ህዝቡ ፣ባርኔጣውን ደፍቶ፣ናገቱን በሻርብ አስሮ፣ በቀን በቀን ዘፈን እየነገደ እንደከብት ሲፈነጥዝ ፳፪ ኣመት አለፈ።የሚበላው ሌላ የሚያገሳው ሌላ እንዴት ይጨፍራል ይህ ህዝብ ሳይበላ? አያት.. ቅድም አያት ደማቸውን አፍሰው አጥንታቸውን ከስክሰው በክብር ያቆዩለትን በሀገሩ በወንዙ በቀዬው ለመብታችን አንናገርም እነቢኝ አንልም! እንገረፋለን፣ እንታሰራለን፣ እንገደላለን፣ ሴቶች እህቶቻችን ይደፈራሉ።ለመሆኑ በሰው ሀገር ሄዶ ክብር ስጡኝ ማለት አግባብ ነውን? ባለቤቱ እራሱ የጣለውን ….!?
*የአፍሪካን ፳፭ከመቶ ድራጎት የሚቀማ መንግስት፣ መሬት፣ ወደብ፣ ግድብ፣ ለውጭ ዜጋ የሰጠ መንግስት፣ ፲፩ከመቶ ለ፰ዓመት ያላቋረጠ ዕድገት፣ የዳቦ ዕጥረት፣ ውሃና መብራት ዕጦት፣ ያጎናፀፈ ራእይ ደረት ሲደቃለት፣ ንፍሮ ሲወቃለት፣ ባነር ሲወጠረወለት፣ ሆድአደር አድርባይ ሲወጠርበት፣ዲያስፖራ ለሀጭና ንፍጡን ያዝረከረከለት ፤ሻማና ጧፍ የባከነበት፣ የብሄር ብሄረሰብ ለቅሶ ትዕይንት፣(የፍትወት) የሴክስ ቱሪዝም የተከፈተበት፣ ዜጋ(ግብረሰዶም) የተስፋፋበት፣ሃይማኖት እንደአሸን የፈላበት፣የህጻናትና ሴቶች ልጆች ንግድ የተከፈተበት፤፵፻በሚበልጡ መንግስታዊ ባለሀብት የሰው ልጆች የመሸጫና መለወጫ የንግድ ድርጅቶች በወታደራዊ ባለሀብቶች ሲቋቋም፣ይህ የኢትዮጵያዊያን የቀን ከቀን ሕይወት ነው! ዓይኖቻችን በርካታ ግፎችን ተመልክተዋል!
**በሳዑዲ አረቢያ በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ በሱዳን፣ በኬንያ፣ታንዛኒያ፣ጋና፣ በግብፅ፣በደቡብ አፍሪካ፣ ኢሰብዓዊ የሆነ ድርጊት ተፈፅማል። ሴቶች እህቶቻችን ከባሎቻቸው ተነጥለው ተወስደው አንዳንዶቹም በሚወዷቸው ቤተሰቦቻቸው ፊት በብዙ የአረብ ጎረምሶች ተደፍረዋል። በዚሁ የተነሳ ህይወታቸው አልፏል፣ ብዙዎች በአደባባይ ደማቸው ፈስሷል፣ በግፍ ተገድለዋል፤ የተረፉትም በአሰቃቂ ሁኔታ ምግብና ውሃ በሌለባቸው ማጎሪያዎች ተወርውረዋል።በኢትዮጵያም ከዋና ከተማው አዲስኣበባ እና በአራቱም ማዕዘን ላለፊት ፳፪ዓመታት ግፉ ነበር አለ ይቀጥላል።እንዲያውም በውጭ ኢንቨስተሮች የሚደርሰው የሰብዓዊ መብት እረገጣ ፣በገዛ ሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ እጅጉን የከፋና የከረፋ ነው።ከዚህ የተነሳ ሌሎች በሀገራቸው ቢንቁን ቢገድሉን ማን ጠያቂ አለባቸው?
እኛ የሞቱ ጠ/ሚኒ “ሀገር ማለት ወንዙ፣ ተራራው፣ ሽንተረሩ፣ አደለም ‘ሕዝቡ’ ነው” አሉ፡ ለመሆኑ ይህ ብሔር ብሄረሰብ ሕዝብ አደለም እንቨስተር ብቻ ነው ህዝብ ማለታቸው ይሆን?ለመሆኑ እነኝህ ብሄር ብሔረሰቦች ታስረው ተደብድበው ተሰደው ተገለው እንደሚያልቁ ተጠንቶበታል ማለት ነው?አለበለዚያ ሀገር አልባ ናቸው፡ መሬቱ በኮንትራት የሚሰፍሩበት ስለሆነ እንደሀገራቸው አይቆጠርም ማለታቸው ነው?ለዚህም ይሆን መንግስት(ህወአት) ለመሬት ከፍተኛ ፍቅር ያደረበት? ከሚናገሩት ይልቅ የሚሰሩትን ማየት ተገቢ ነው።አሁን በውጭ ሀገር ኤምባሲዎች ላይ የሚደረግ ጩኸት ዋጋ ያስከፍላል፡በህወአት መንገስት ላይ መነሳት ግን ዘላቂ ትቅም አለው በለው! “አህያውን ፈርቶ ዳውላውን”ለዚያውም ሕግን ባልተከተለ የጉልበት ፉከራና ዛቻ መዘዙ ከባድ ነው። ምን አልባት ሌሎች አረብ ሀገሮችም ተመሳሳይ አጻፋና ከሀገራችን ውጡልን አመፅና የጉልበት እርምጃ ወስደው የከፋ ችግር በስደተኛ ወገኖቻችን ላይ እንዳይደረስ መጠንቀቅ ነው። ግዜውን ጠብቆ ግን በሀገር ውስጥ ማንነትን ማሳየት ተገቢና ሕጋዊ የዜግነት በመብት ነው።!!ይህንን ከ፳፪ኣመት በፊት ብለነው ቢሆን ከ፵ዓመት በፊት ስለሰው ልጅ ክበር ተሟግተው ቢሆን ዛሬ እንኳን አረብ ሀገር አደለም አውሮፓና አሜሪካ አንሰደድም ነበር።*ደብረጺዮን ገብረሚካዔል፣ቴዎድሮስ አድሃኖም፣በረከት ስምኦን፣…እና ሌሎችም “ከሥልጣን ይውረዱ ።ህወአት/ሻቢያ ሆድአደር፣ አድርባይ ደደብ ብሄር ብሔረሰብን ከፊት አስቀምጠው የሚጋልቧቸው ሽመልስ ከማል፣ሬድዋን ሁሴን፣ ዲና ሙፍቲ ኀይለማርያምመ ደስአለኝ፣ ሸፈራው ሽጉጤ፣ ሸፈራሁ ተ/ማርያምን በመተካካት ከኋላ ቂጣቸውን እየገረፉ በገዛ ብሔረተኞቻቸው እያስቀጠቀጡ ኢትዮጵያውያኑን ተበቀሏቸው።ሀገራቸውን፣ ወደባቸውን፣ መሬታቸውን፣ ሕጻናት ልጆቻቸውን፣ ወጣት ሴቶቻቸውን፣ባህልና አብሮ መኖርን ገፈው በማኅበር ተደራጅተው ሸጧቸው፡፡ ተው ብለናል!አላህዋክበር ቀልድ ሆኗል አሁንም ጃዋር መሀመድና ተስፋዬ ግብረእባብ ከህወአት ጋር በመተባባር ይህንኑ መተላላቅ ሀገርህ ድረስ ያመጡልሃል አፍክን ከፍተህ ጠብቅ!!ቂጥህን ገልበህ ከመጨፈርና በራዕይ ከማረር ተነስ እንቢኝ በለው!!
*በዚሁ አጋጣሚ “ነብዩ ሲራክ…ግሩም ተክለሃይማኖት የተባሉ ግለሰቦች ለዘመናት ሲጮሁ፤ሲያለቅሱ፣ሲጣሩ፣ያዳመጠ፣የረዳቸው የለም..አሁን የሚታየው ግርግር የውሸትና ለትንሽ ቀን ነው። እያንዳንዱ መዝሙርና ዘፈን በማውጣት የችሎታ መለማማጃ ባያደርጋቸው የተሻለ ነው። ኢህአዴግ ሻቢያን ከሥልጣን ያባር ኀይለመለስ ደስአለኝ ይውረድ! መንግስት እንደዕቃ የሸጠውን ወጣት በራሱ ወጪ ይሰበስባል ማለት ውሸት ነው!። ይህ ወጣት በሰው ሀገር በነፃነት መኖር አለብኝ ሀገሬን ለህወአት ቤተሰቦች ሰጥቻለሁ ማለት የለበትም። አሁን ይህ ትውልድ መጠየቅ ያለበት ህወአት/ወያኔ/ኢህአዴግ ልጆችና ቤተሰቦች የት ናቸው?።ቻይና፣ ሕንድ፣ አውሮፓ፣ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ በወር ፭ሺህ ዶላር ይላክላቸዋል፣ ቤት ተገዝቶላቸዋል፣ይነግዳሉ፣ ወደፊት በመተካካት የሚቀጥለውንም ትውልድና መሬት ለመሸጥ ተዘጋጅተዋል።
ለመሆኑ ኢትዮጵያ የማናት? ይህ የተበሳቆሉትን የተገረፉትን የተበደሉትን ለኢህአዴግ ቤተሰቦች በተግባር ማሳየት አለባቸው። ያለቀሱለት የመልስ ራዕይ እዚህ ላይ ለመድረስ ነበርን? ሁለት ወር ሙሉ ደረት መድቃት፣ረግዶ ሻማና ጧፍ ማቃጠል ትርፉ ይህ ነው ልመናቸውና ራእዩ ተፈፅሟል።ቤተክርስቲያን ማቃጠል ሰው በሜንጫ መግድልና ከእነነፍሱ ገደል ጨምረው አላህዋክበር!የሚሉ ሁሉ ልብ ይግዙ! ዋነኛው ጉዳይ ለዚህ ሁሉ ስደትና ውርደት ግድያና ሰቆቃ የዳረገንን የህወሃት አገዛዝ እና አስተሳሰቡን ጭምር ነቅለን መንግስት አልባ የሆነችውን አገራችንን የህዝብ መንግስት ባለቤት ለማድረግ የሚካሄደውን ዕልህ አስጨራሽ ትግል በመቀላቀል የድርሻችንን እንወጣ። “ኢትዮጵያ እጆቻን ዘርግታ የተበታተኑ ቅን አሳቢ ልጆቻን ትሰበስባለች! ሀሴትም ታደርጋለች! በለው! በቸር ይግጠመን ከሀገረ ከናዳ
bek says
Dear brother Belew
You describe every thing clear. Thank you for your comment.
KINDEYA says
when did you take this photo EPRDF dose not have such a solder during this or now i will not be sure but i think the picture is not from Ethiopia or it is taken from Addis Abeba’s marteir museum