• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የኢትዮጵያን መንግስት ለፍርድ ለማቅረብ ከተነሱት ስዊድናዊ ጠበቃ ጋር ውይይት ተደረገ

November 15, 2013 06:27 pm by Editor Leave a Comment

ቅዳሜ ኖቬምበር 2 ቀን 2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ መድረክ በስዊድን የወያኔን መንግስት በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ለማቅረብ የተጀመረውን ክስ መነሻ በማድረግ የክሱን ሂደት ከሚመሩት ከስዊድናዊው ጠበቃ ከስቴላ ያርዴና ከሌሎች እንግዶች ጋር በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ወይይት አደረገ።

million
ም/ኢኒስፔክተር ሚሊዮን ብሩ

ውይይቱ ከቀኑ 14፡00 ሰዓት የተጀመረ ሲሆን ውይይቱን የከፈቱት የመድረኩ ሊቀ መንበር ም/ኢኒስፔክተር ሚሊዮን ብሩ ናቸው። ኢኒስፔክተር ሚሊዮን በንግግራቸው መክፈቻ ጥሪ የተደረገላቸውን እንግዶችና ተሰብሳቢውን ህዝብ አመስግነው መድረኩ የተቋቋመበት ዓላማ በሀገር ውስጥና በውጪ የሚደረገውን የነጻነት ትግል የተደራጀ መልክ ይዞ የሚጓዝበት መንገድ ለማመቻቸትና በየጊዜውም ይህንን መሰል ውይይት በማድረግ ትግሉን ለመርዳት መሆኑን ገልጸው የዛሬውንም ስብሰባ የዚህ መነሻ እንደሆነ አስታውቀዋል።

ዶ/ር ሙሉዓለም አዳም
ዶ/ር ሙሉዓለም አዳም

ከሳቸው በመቀጠል መድረኩን እንዲመሩ የተጋበዙት ጋዜጠኛ ወንድማገኝ ጋሹ፤ ዶ/ር ሙሉዓለም አዳምን የመጀመሪያው ተናጋሪ አድርገው ጋብዘዋል። ዶ/ር ሙሉዓለም የመድረኩን አዘጋጆች አመስግነው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በአስከፊ ሁኔታ ላይ መውደቁን ሙስናውም እያደረ መባባሱን የመንግስት ባለስልጣኖች ወደ ውጪ የሚያሸሹት ገንዘብ እየናረ መሄዱን ገልጸዋል።

እንዲሁም የዘር ፖለቲካ እየተስፋፋ መሄዱን፣ የስለላ መዋቅሩም መጠናከሩንና ህዝቡን መግቢያ መውጫ ማሳጣቱን ከዚያም አልፎ በውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ድረስ መዝለቁን አስረድተዋል። የወቅቱን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርንም ንግግር በመጥቀስ በሰላማዊ ሁኔታ የሚደረገው ትግል አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ እንደወደቀ አመላክተዋል።

ሁለተኛው ተናጋሪ የመድረክ መሪው ጋዜጠኛ ወንድማገኝ ጋሹ ሲሆኑ እርሳቸውም  በሀገራችን ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ የሰው ልጅን የሰውነት ደረጃ ያቃለለ፣ ሙሉ ለሙሉ ያዋረደና መብት የገፈፈ መሆኑን ጠቅሰው፣ ለሃያ ደቂቃ የቆየ ይህንኑ የሚያመላክት ፊልም አሳይተዋል።

wendmagegne
ጋዜጠኛ ወንድማገኝ ጋሹ

ቀጥሎም የተነሱበትን አላማ እንዲያስረዱ በጉጉት ይጠበቁ የነበሩት ስዊድናዊው ጠበቃ ስቴላ ያርዴ ንግግር እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል። ጠበቃ ስቴላ ያርዴ የስዊድን ቴሌቪዥን ባሳየው ዘጋቢ ፍልም ስሚታቸው እንደተነካ ገልጸው ይሄንን አሰቃቂ ወንጀል የፈጸመውን የወያኔን መንግስት ለፍርድ ለማቅረብ እንደተነሱ አስረድተዋል።

በፊልሙ ላይ የታዩት የወንጀል ድርጊቶች ለተነሳንበት ክስ አሳማኝ መረጃ ከመሆኑም በላይ በተለይ በእስር ላይ ያሉ ስዎችን የመድፈርና የማስወለድ ድርጊት ወንጀሉን የሚያከብደው ሲሆን በቅርባችን ባሉት ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ላይም የተፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰትና በደል ክሱን እንደሚያጠናክርው ገልጸዋል።

ሁኔታውን ሲያብራሩም አሁን ያሉንን መረጃዎች ይዘን ለሚመለከተው አካል አመልክተናል። ወደ ቀጣዩ እርምጃ ለማለፍ የነሱን ውሳኔ መጠበቅ ይኖርብናል። የስዊድን ፖሊስም ለዚህ ጉዳይ ትብብሩን አልነፈገንም ብለዋል።

stellan-yarde
ጠበቃ ስቴላ ያርዴ

ከተሰብሳቢው ህዝብም ክሳችሁ ትኩረት ይዞ የተነሳው በኦጋዴን በታየው በደል ብቻ ነው ወይስ በሌሎችም ክልሎች የተፈጸመውን አጠቃሎ ይይዛል? ለተባሉት ሲመልሱ በሌሎች ክልሎች የተፈጸመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ድርጊቱን በሚያስረዳ መልክ ማስረጃ አሰባስበን መያዝ የመጀመሪያ ስራችን ይሆናል ብለዋል።

ማስረጃ ልንሰጣችሁ ብንፈልግ በምን መልኩ ማቅረብ እንችላለን ለተባለው ጥያቄ ደግሞ ሲመልሱ ማስረጃ ለመስጠት በተናጠል እኔን ማግኘት አያስፈልጋችሁም ከተለያየ ሰውና ቦታ የምታገኙትን መረጃ ይህንን የሚያሰባስብ የመረጃ ቡድን አቋቁማችሁ ቡድኑ መረጃዎችን አጣርቶና አሰባስቦ ቢሰጠን የተሻለ ይሆናል ብለዋል።

ye afar tenagare
የአፋር ሰብዓዊ መብት ተወካይ

በስብሰባው ላይ የተገኙት የአፋር ህዝብ ብሄራዊ ክልል የሰብዓዊ መብት ተወካይ በበኩላቸው በአፋር ህዝብ ላይ እየተደረገ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ከሌላው ክልል የማይተናነስ መሆኑን ገልጸው በእጃቸው የሚገኘውን መረጃ ለጠበቃ ስቴላ ያርዴ ሰጥተዋል።

መቶ አለቃ አበረ አዳሙ
መቶ አለቃ አበረ አዳሙ
tesebsabe hezb
ተሰብሳቢው ህዝብ በከፊል

የመጨረሻው ተናጋሪ መቶ አለቃ አበረ አዳሙ ሲሆኑ እርሳቸውም ‹‹ድርጅታዊ ዘረኝነት›› በሚል ርዕስ የተሰብሳቢውን ህዝብ ስሜት የሳበ ንግግር አድርገዋል። በዚሁ ንግግራቸው እንዳብራሩት የኢትዮጵያ መንግስት የድርጅታዊ ዘረኛነትን አገዛዝ አጥብቆ ለመያዝ የክልልና የፌዴራል ፖሊስን፣ የደህንንነት መምሪያውን፣ የመከላከያ ሰራዊቱን፣ የስራ ፈጻሚ ክፍሎች እንዲሁም የገንዘብ ገቢ የሚያስገኙ ተቋማትን በአንድ ዘር በማደራጀት ሃላፊዎች መድቦ ምንም አይነት ቀዳዳ ሳይከፍት ሁሉን ነገር ከቁጥጥሩ ስር በማድረግ ድርጅታዊ ዘረኝነቱን ለማጠናከር ችሏል ብለዋል።

በመሆኑም ተቃዋሚ የሆንን ሁሉ ይህንን ድርጅታዊ ዘረኝነት አውቀን ትግላችንን ማጠናከር ይገባናል ለዚህም የሚያገለግለን መተባበርና እርስ በርሳችን መተሳሰር ሲሆን ይህን የአፈና መዋቅርም ማፍረስ የምንችለው በተጠናከረ የአንድነት ትግል ብቻ ነው በማለት ሰፊ ማብራርያ ሰጥተዋል። የመቶ አለቃ አበረ ንግግር በብዙዎች ታዳሚዎች ዘንድ ለለውጥ የሚያነሳሳ ስሜት ፈጥሮ ነበር። በመጨረሻም የውይይት መድረኩ ለወደፊትም ከልዩ ልዩ እንግዶች ጋር በዚህ መልክ ወይይቶች እንደሚደረግ ገልጾ ውይይቱ 18፤00 ስዓት ላይ ተጠናቋል። (ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የተጠናቀረው ዘገባ ወለላዬ ከስዊድን)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Politics

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule