ይህች ጦማር ለሙሽሪት አክሊለ ብርሃን እና ለሙሽራው ድንቁ መንግሥቱ ጋብቻ በተዘጋጀው እራት ግብዣ፤ በከንሳስ ደብረሣኅል መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ቀርባ የነበረችውን ትምህርት የያዘች ናት። ወደ ጦማር ለመለወጥ ስዘጋጅ፤ ዓረቦች በወገኖቻችን ላይ የሚፈጽሙትን ግፍና በደል ሰማሁ፤ በአንድ ወቅት ባንድ ቤተሰብ ላይ ሞትና ሠርግ ባንድ ቀን ተፈጸሞ የደረሰባቸው ሁኔታ ተሰማኝ፤ ይህንንም በ፪ኛው አንቀጽ በ፭ኛው ገጽ ላይ ገልጨዋለሁ። ጦማሯ ሁሉንም ስለምትዳስስ ለሁሉም ቀርባ ሁሉም ቢያነባት ስለምትጠቅም ላንባቢ ትቅረብ የሚለው ሀሳብ ስለበዛ የቀረበች ናት። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply