ኢትዮጵያውያን ብዙ ጮኽን ያዳመጠን ግን የለም፡ ፡ ለሰው ጩኽን፤ ለፈጣሪ ጩኽን፤ ለመሬትም ጮህን፤ አንዳች ምላሽ በመሻት፤ ጩኽታችን ግን ለሠማይና ለምድርም ጮህን፤ ጩኸታችን ግን የቁራ ጩኽት ሆኖ ቀረ፡፡ የተፈረደብን የመከራ ዘመን ከማለቅ ወይ ከመገባደድ ይልቅ እየጨመረ ሄደ፡፡
በግልፅ የሚታየውን ችግራችንን፣ ከፊታችን ሳይቀር የሚነበበው ጉስቁልናችን፣ ሚሊዮኖችን ምርኮኝ ያደረገ ርሃባችን፣ ፀሐይ የሞቀው የርስበርስ ፍጅታችንን ደመናን ቀርቶ የጎጇችንን ጣሪያ ማለፍ የተሳነው ምህላና ፀሎታችን ብዙዎች በየቀኑ ሽቅብ የምንረጨው እንባችን፤ ሁሉም በማንም ዘንድ ተሰሚነት አላገኘም፡፡ አሁንም ለቅሶና ዋይታችን ተባብሶ እንደቀጠለ ነው ሲባል።አሁንማ ማን የማይጮህ አለ? ሁሉንም የሚያስጮኸው ግን አንድ ነገር ነው፣የወያኔ ግፍ።
ክርስትያኑ | ይጮሃል |
ሙስሊሙም | ይጮሃል |
የመንግስትሰራተኛ | ይጮሃል |
የግልተቀጣሪ | ይጮሃል |
ቀጣሪው | ይጮሃል |
ስራ እጡ | ይጮሃል |
ነጋዴው | ይጮሃል |
ሸማቹ | ይጮሃል |
ሰራዊቱ | ይጮሃል |
ጋዜጠኛው | ይጮሃል |
እምነት የሌለው | ይጮሃል |
የጠገበው | ይጮሃል |
የራበው | ይጮሃል |
ይጮሃል | ይጮሃል |
ፖለቲከኛው | ይጮሃል |
ፍትህ ያጣው | ይጮሃል |
እስረኛው | ይጮሃል |
ታሪክ | ይጮሃል |
ሰሚአልባ | ይጮሃል |
እራሱ ጩኸት | ይጮሃል |
እሪ | በከንቱ |
ተንኮለኞች ያጠመዱትን ወጥመድ የደገሱልን መከራና የሰቆቃ ድግስ ከዘመናት በፊት በሴራ መክረው ያወጁብን የጥፋት ዘመን በብሄርና በጎሳ ከፋፍለው የኢትዮጵያን አንድነት ለመነጣጠል በመካከላችን የከተቱብን የተኩላ መንጋ ሁሉም እንዳሰቡት ሆኖ ትንቢታቸው ሲይዝላቸውና ምኞታቸው ሲሳካላቸው በስቃያችን ይደሰታሉ፡፡ በቁስላችን የጋለ ብረት እየሰደዱ ለቅሷችንን እንደ ጥጋብ፣ ጭንቀት ጥበታችንን እንደ ደስታ፣ ጦርነታችንን እንደ መዝናኛ፣ መባዘናችንን እንደ በረከት፣ የርስ በርስ እልቂታችንን እንደሰላም በመቁጠር ያላግጡብናል፡፡ እውነቱን የማያውቁ ይመስል የላኳቸውን እንደራሴዎች የሚሰሩትን የማይረዱ ይመስል፡፡ የእኛን መከራና ችግር እንደማያውቁ ሆነው በመቆለል በጣት የሚቆጠሩ የተሻለ ኑሮ የሚኖሩ በገጠር በግብርና የሚተዳደሩትን ከተማ ያሉ ሃብታችን በመመልከት ብቻ ጥሩ ኑሮ ላይ ነን ይላሉ፡፡ እነዚያም ተቀብለው “ይኽ መቸ አነሳችሁ፤ ጥሩ ኑሮ እየኖራችሁ ነው” በማለት ይሳለቁብናል፡፡
ጥቂት የምትባል የመናገር፣ የመፃፍ ግድብ (ዴሞክራሲ) መብት በማየት ብቻ ዴሞክራሲያችን እዚህ ደርሷል በማለት አዎንታዊ አብነት ወስደው ከእኛ አልፈው ለሌሎች አገሮች ማስተማሪያ ሊሆን እንደሚገባ ይሰብካሉ፡ ፡ ይህ ድርጊታቸው በዴሞክራሲ ላይ ብቻ ሳይሆን በሰው ልጆችም ላይ እንደማፌዝ የሚቆጠር ከመሆኑም በተጨማሪ ለይስሙላ ያህል በውሸት በሚያመልኩት በእግዚአብሄርም ዘንድ በእጅጉ አስነዋሪና ሃጢያት መሆኑን ሊገነዘቡት ይገባቸው ነበር፡፡ ፈጣሪ የሰውን ልጅ በቀለምና በዘር በስልጣኔና በመልካም ምድር ልዩነት እየፈጠራችሁ ተፋጁ (አፋጁ) አላለም፡፡ ከዚህ ነጥብ አኳያ ተምረዋል የተባሉት አማረዋል፡፡ እነዚህ ወገኖች እየሰሩት ያለው ግፍና በደል ሲጤን መሰልጠናቸው ሳይሆን መስይጤናቸውንና ፀረ ሰውም፣ ፀረ ፈጣሪም መሆናቸውን የሚያሳይ ነው፡፡
ሀገራዊም ሆነ አለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የሚመቹ ባለመሆናቸው ተናግረን የምንደመጥበት፣ አኩርፈን የምንጠጋበት፣ ፍትህን የምናገኝበት አንድም አለኝታ የለንም፡፡ ሁሉም ነገር ያዘነበለው ወደ ገዢዎቻችን በመሆኑ የችግራችን መጠን ስፋትና ጥልቀት ተነግሮ አያልቅም፡፡ ፈጣሪ ጭምር አስጨናቂ ዘመን እንድንገፋ የፈረደብን ይመስላል፡፡ ከታሰርንበት የኑሮ ሰንሰለት ከገባንበት ምድራዊ ሲኦል ነበልባላዊ እቶን የሚታደገን ከቶ ማነው? ዳዊት በመዝሙሩ አቤቱ ጌታ ሆይ እስከመቼ ነው የምትተወኝ ያለው ወዶ አይደለም፡፡ እንደኛ ክፉኛ ቢጨንቀው እንጂ፡፡ በርግጥ መከራ ሲበዛ ያነሆልላል፤ ስቃይ ሲበዛ መፈጠርን ያስረግማል፤ ግፍና በደል ከአንድ ሰው የመሸከም አቅም ሲያልፍ ራስን ብቻ ሳይሆን ፍጣሪን ድረስ ሊያስክድ ይደርሳል፡፡
ምንም እንኳን “እረኛ ቢያኮርፍ ምሳው እራት ይሆነዋል” እንዲሉ አኩራፊ ቢያኮርፍ ከራሱ በላይ የሚጎዳው ባይኖርም የችግሩ ክረት ፈጣሪን እስከ መውቀስ ቢያደርሰው ቢያንስ ሊያስነውረው የሚገባ አይመስለኝም፡፡ በክርስቲያኑ ህይወት እንግልትና የቁም ስቅልን የሚያሳይ አሳር ሲገጥም በመፅናናት የሚጠቀስ አንድ መፅሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌ ነው፡ ፡ የኢዮብ ስቃይ ከእኛ ከኢትዮጵያውያን ስቃይ ማወዳደር የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ለዘመንም ሆነ ከሌሎች መሰል ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ችግሮች አንፃር የኢዮብን ከእኛ አስቸጋሪ ህይወት ላነፃፅር አልችልም፡፡
የመከራ ዶፍ የወረደበት ኢዮብ በደረሰበት ስቃይ ሰማይ ምድሩ ተደፍቶበት ጭንቅ ውስጥ በነበረበት ወቅት ከተናገረው ጥቂት እናስታውስና እኛ ከተዘፈቅንበት የችግር ማጥ አኳያ ብሶት ምን ያህል እንደሚያናግር እንመልከት፡፡ ከችግርና ከረሃብ ብዛት የተነሳ በለሊት ተነስተው ወደ በረሃ እየሄዱ ስራ ስሮችን ያኝኩ ነበር፡፡ ጨው ጨው የሚል የበርሃ ቅጠላ ቅጠሎን ይለቅሙ ነበር፡፡ ሰዎች ሌቦችን እየጮሁ እንደሚያባርሩ እነርሱም ከህብረተሰቡ መካከል ያባርሯቸው ነበር፡፡ መኖሪያቸውም በየዋሻውና በየገደሉ ስር በተቆፈረ ጉድጓድ ውስጥ ነበር፡፡
በየጫካው እየዞሩ እንደዱር አውሬ ይጮሁ ነበር:: በየቁጥቋጦው ስር ተጠግተው ይኖሩ ነበር፡፡ አሁን ግን ልጆቻቸው እየሰደቡኝ ይዘባበቱብኛል:: ተፀይፈውኝ ከእኔ ይርቃሉ ያለ አንዳች ፍርሃት እፊቴ ምራቃቸውን ይተፋሉ እግዚአብሄር ሃይሌን አድክሞ ስላዋረደኝ እነርሱም ልጓሙ እንደወለቀለት ፈረስ በላዬ ይፈነጩብኛል፡፡ የኛ ሲቃይም ከላይ ከተጠቀሰው ከኢዮብ ሲቃይና መከራ ቢበልጥ እንጂ አያንስም ችግራችን በዝቷል፤ ሸክማችን ከብዷል፤ እንዲቀልልን ለማን አቤት እንበል?
የኢትዮጵያዊያን መከራ በወያኔ ገዢዎቻቸው-ወያኔዎችም የኢትዮጵያን ልጆች በመከራ ገዙአቸው። በጽኑ ዘረኝነት፥ በስደት፥ ከስፍራ በማፈናቀል ሁሉ፥ በእስር ቤት ሁሉ ያሉ ይጮሃል፥የእስራኤላዊያንን ነፃነት የሰጠ እግዚአብሄር ለኢትዮጵያዊያንም ነፃነታችንን እንድንጎናፀፍ ይረዳናል። እኔ ለኢትዮጵያ የጉብኝት ዘመን እንደደረሰ አምናለሁ፥እስከዛው በአንድነታችን ፀንተን ጬኸታችንን ወደ ነፃነት እንቀይረዋለን።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ዳዊት ገሰሰ ከኖርዌይ
Revolution4ethiopia@gmail.com
Elias kebede says
በአሁን ሰአት እንደግብፅ የአለቀው አልቆ ወያኔን ከነስሩ መንቀል ነው።