አሜሪካና ሌሎች ለሰብአዊ መብት መከበር ዋጋ የሚሰጡ አገሮች በሙሉ በ”አዲስ አበባው” አገዛዝ ላይ ጠንካራ አቋም መያዛቸውን ያለ አንዳች ማወላወል ማሳየት እንደሚገባቸው አሳስበው የነበሩት ኮንግረንስ ማን ክሪስ ስሚዝና ባልደረባቸው እንደራሴ ኬረን ባስ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ተጠቆመ። በሰኔ (ጁን) ወር "… የአሜሪካ መንግስትም ሆነ ሌሎች የምዕራብ አገራት፣ ኢህአዴግ ኢትዮጵያዊያን ላይ እየፈጸመ ያለውን ተግባር በመረዳት አቋማቸውን በግልጽ ማስቀመጥ ይገባቸዋል” የሚል ጥሪ ያስተላለፉት ክሪስ ስሚዝ አዲስ አበባ መምጣት ኢህአዴግን እንዳሳሰበው ለማወቅ ተችሏል። "ኢትዮጵያ ከመለስ በኋላ" በሚል አጀንዳ ተዘጋጅቶ የነበረውን የምክክር ስብሰባ የመሩት የአሜሪካን ምክር ቤት እንደራሴ /ኮንግረንስማን/ ክሪስ ስሚዝና ሌላዋ ባልደረባቸው እንደራሴ ኬረን ባስ ኢህአዴግ እስር ቤቶችን እንዲያሳይ፣ … [Read more...] about እንደራሴ ስሚዝ አዲስ አበባ ሊሄዱ ነው
ኬኒያዊው ጠበቃ ስለየሱስ የሞት ፍርድ ሔግ ክስ ከፈተ!
የየሱስ ክርስቶስ ክስ፣ ፍርድና ሞት ተገቢው የሕግ አሠራር የተከተለ አይደለም፤ ጉዳዩም እንደገና መታየት አለበት በማለት ኬኒያዊው ጠበቃ ዶላ ኢንዲዲስ ሔግ ለሚገኘው ዓለምአቀፉ ፍርድቤት ክስ ማሰማቱን ጀሩሳሌም ፖስት ኬኒያ የሚታተመውን ናይሮቢያን ጋዜጣን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ የቀድሞ የኬኒያ ፍርድቤት አፈቀላጤ የነበረው ይኸው ጠበቃ በወቅቱ የሮም ቄሣር የነበረውን ጢባሪዮስ ቄሣር፣ ጲላጦስን፣ የአይሁድ መሪዎችን፣ ንጉሥ ሔሮድስን፣ የአሁኑን የጣልያንና የእስራኤል መንግሥታትን ከስሷል፡፡ “ማስረጃው በመጽሐፍቅዱስ ላይ ይገኛል፤ ይህንን ደግሞ ማንም ሊክድ አይችልም” የሚለው ጠበቃ የሱስ በወቅቱ ተገቢውን ፍርድ እንዳላገኘ ጉዳዩም በትክክል በፍርድ ሒደት ውስጥ እንዳላላፈ ጠቁሟል፡፡ ጉዳዩ ሁለት ሺህ ዓመታት ያስቆጠረ ቢሆንም አሁን ያሉት የጣሊያንና የእስራኤል መንግሥታት በዚያን ጊዜ (በስቅለት) … [Read more...] about ኬኒያዊው ጠበቃ ስለየሱስ የሞት ፍርድ ሔግ ክስ ከፈተ!
Revolution is a Must! What must be considered? Next is …
Before 22 years: I grow up in small town with my “colorful” friends whose his father and mother are from Eritrea, Mendefera, another friend his father from Eritrea Kessela , mother from Ethiopia Wollega Horo Guduru, other 2 friends father from Tigray Axum and Mother from Wollga Mendi. As young friends we were happy and free from any evil thinking about each other. We have been living in love and joy; I don’t remember a single hostile day among us, except childish quarreler immediately dropped. … [Read more...] about Revolution is a Must! What must be considered? Next is …
የሃይማኖት እኩልነት በዲሞክራሲ ሥርዓት እንዴትነት የፈጠረው ተቃርኖ በዚህ “መንግሥት”
የዚህ ጽፉፍ መቸት ከጥቂት ወራት በፊት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር አሁን ሥራ ላይ ያዋለውን መመሪያ ባወጣበት ወቅት ጋዜጣ ላይ የጻፍኩት ጽፉፍ ነው እነሆ፡- መሰንበቻውን የፌዴራል ጉዳዮች ሚንስቴር የእምነት ተቋማትን ለመመዝገብ (ለመቆጣጠር) አንድ መመሪያ ማውጣቱና እያነጋገረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህ መመሪያ የተረቀቀውና ተግባራዊ ሊደረግ ታስቦ የነበረው በተመሳሳይ ዓላማና አንቀጾች በተለያዩ ሰብአዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ተሰማርተው ይሠሩ የነበሩትን መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን (NGOs) ያሽመደመደው፣መፈናፈኛ ያሳጣውና ከአገልግሎት ውጪ ያደረገው ደንብ ወይም መመሪያ ወጥቶና ተግባራዊ ሆኖ ለዓላማቸው አመርቂ ውጤት እንዳስመዘገበላቸው ባወቁ ጊዜ ነበር፡፡ ይህንን ውጤት በማየትም በተመሳሳይ መልኩ ደንቡን ወይም መመሪያውን በሃይማኖት ተቋማትም እንዲፈጸም ቢያደርጉ የልባቸው ሊደርስ … [Read more...] about የሃይማኖት እኩልነት በዲሞክራሲ ሥርዓት እንዴትነት የፈጠረው ተቃርኖ በዚህ “መንግሥት”
የሳውዲዋ ልዕልት የመብት ገፈፋ ክስና የኢትዮጵያዊቷ ጉብል አበሳ . . .
የሳውዲ ንጉሳውያን ቤተሰብ አባል የሆኑት የ42 አመት እመቤት በምድረ አሜሪካ በቤት ሰራተኛቸው መብት ገፈፋ ተከሰው ለፍርድ ቀርበዋል። ልዕልቷ ኬንያዊዋን የቤት ሰራተኛቸውን በአነስተኛ ክፍያ ከ16 ላላነሱ ሰአታት በመክፈል እና የኬንያዊቷን ሰራተኛ ፖስፖርት ለባለቤቷ ባለመስጠታቸው ተከሰው በምድረ አሜሪካ ለወህኒ ከተዳረጉበት በ5 ሚሊዮን ዶላር ዋስ ቢፈቱም ዛሬም ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ሰምተናን። ይህንን ዜና ሳነብ ያን ሰሞን " ጋዜጠኛ ነህ አሉ እርዳኝ? " ብላ ከወደ ደማም በተንቀሳቃሽ ስልኬ እየደወለች የምታነባዋ ኢትዮጵያዊት እህት ፍዳ አስታወስኩ ! ዛሬ ረፋዱ ላይ ያነጋገርኳት ይህች እህት የሚደርስባት ግፍ ሳያንስ የተሰደደች የምትገፋበትን የወር ደመወዟን ላለፉት በርካታ ወራት እንዳልተሰጣት ገልጻልኛለች ። ዛሬ በጣሙን ከፍቷት እያለቀሰች ከገባችበት ስቃይ እታደጋት ዘንድ … [Read more...] about የሳውዲዋ ልዕልት የመብት ገፈፋ ክስና የኢትዮጵያዊቷ ጉብል አበሳ . . .
“ጴጥሮስ ያቺን” ቃል!
“ፋሺስቶች ያገራችንን አርበኞች ሽፍታ ቢሏቸው እውነት እንዳይመስላችሁ፡፡ ሸፍታ ማለት ያለ አገሩ መጥቶ የሰውን አገር የሚወር ይህ በመካከላችሁ መጥቶ የቆመ አረመኔው የኢጣሊያ ፋሺስት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለእርሱ እንዳይገዛ ውጉዝ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መሬት እንዳትቀበለው የተገዘተች ትሁን፡፡” አቡነ ጴጥሮስ፡፡ ዛሬ ሐምሌ 22 ቀን ጀግናው ሰማዕት አቡነ ጴጥሮስ በግፍ የተገደሉበት ቀን ነው፡፡ እኒህ ታላቅ አባት ለሰማዕትነት ያበቃቸው ዋናው ምክንያት በወቅቱ ለተጠየቁት ቀላል ለሚመስል ጥያቄ “ቃሌን አልክድም” ብለው በመቆማቸው ነበር፡፡ ፋሺስት ኢጣሊያ አገራችንን ወርሮ ሕዝቡን ባስጨነቀ ጊዜ አቡነ ጴጥሮስ ከአርበኛው ጋር በመቆም የጣሊያንን ሠራዊት በድፍረት ሲቃወሙና አርበኛውንም ሲደግፉ ቆይተዋል፡፡ ሆኖም ከጊዜያት በኋላ በፋሺስቶች ቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ ጣሊያኖች ራሳቸው በሰየሟቸው … [Read more...] about “ጴጥሮስ ያቺን” ቃል!
“አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል!”
2005 ዓ.ም ከ1998 ዓ.ም በኋላ በተግባር ሊታይ የሚችል የፖለቲካ እንቅስቃሴ የታየበት አመት ነው ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም ፡፡ በተለይ በግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ፣ም የሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ምንአልባትም ወደኋላ ይጓዝ የነበረውን የሀገር ውስጥ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ከማስቆም በዘለለ ወደፊት እንዲጓዝ ያደረገው ይመስለኛል፡፡ ከዚህ እለት በኋላ ባሉት ቀናቶች ውስጥ በርካታ ፓርቲዎች ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ይገኛሉ። በተለይ አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ለዚህ ማሳያ ነው፡፡ ድርጅቱ በደሴና በጎንደር የተሳኩ ሁለት ሰልፎችን በአንድ ቀን አድርጓል፡፡ ለዛሬ ይህን እንድጽፍ ያነሳሳኝ ግን ይህን እንቅስቃሴ ተከትሎ እየተነሱ ያሉት እንዳንድ አሉታዎችን ለማየትና የራሴን ምልከታ ለመጠቆም ያህል ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው የፕሬስ … [Read more...] about “አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል!”
“በስመ ተቃዋሚ ተቃቅፎ መሳሳም” – ለትልቁ ዓላማ?
ከጥቂት ጊዜያት በፌት አንድ የመጽሐፍ ዳሰሳ ዝግጅት ላይ ተገኝቼ ነበር፡፡ መጽሐፉ “ፌኒክሷ ዛሬም፣ ሞታም ታንቀላፋለች” ሲሆን ጸሐፊዋ የቀድሞው የሕወሓት አባልና አመራር የአቶ ገብሩ አስራት ባለቤት ወ/ሮ ውብማር ናቸው፡፡ በዳሰሳው ወቅት በትግል ጊዜ ለምን መጽሐፉ ላይ የተጠቀሱትን ችግሮች እንዳልፈቱ ሲጠየቁ ወይዘሮዋ እንዲህ ብለው መልሰው ነበር፡፡ “ደርግን የሚያህል ጠላት ከፊት ለፊታችን እያለ እንዴት እርስ በርስ በመጣላት ጊዜ እናባክናለን? ነጻ ስንወጣ የሕወሓት ፖሊሲና ፕሮግራም ሁሉንም ነገር ይፈታዋል::” ብለን ተውነው ይላሉ፡፡ በኋላ ላይ ደግሞ ሕወሓትን ስለመለወጥ ሲጠየቁ ‹‹ሕወሓት ከዚህ በኋላ የሚለወጥ ድርጅት አይደለም አርጅቷል፡፡ 40 ዓመት በኋላ የድርጅት ባሕሪይ አይቀየርም›› ሲሉ ይከራከራሉ፡፡ የትኛው ጠላት? የትኛው ትልቁ ዓላማ? አሁንም ሕወሓት ሥልጣን ከያዘ … [Read more...] about “በስመ ተቃዋሚ ተቃቅፎ መሳሳም” – ለትልቁ ዓላማ?
The implications of politicized education for academic freedom in Ethiopia
Despite the formal recognition of fundamental human rights and freedoms under the 1995 Ethiopian constitution, freedom of association and expression have been seriously restricted in Ethiopia in the last few years. Particularly after the controversial general elections in 2005, the Ethiopian regime has used different pretexts to restrict freedom of association and expression. For instance, the regime passed a new charity law that prohibits local civil society groups from engaging in the … [Read more...] about The implications of politicized education for academic freedom in Ethiopia
የንባብ ባሕል ለምን እንዴትስ ይፈጠራል?
ስለ ንባብ ባሕል ስናነሣ በሀገራችን ያለው የንባብ ባሕል በዓለማችን ብቸኛውና የመጠቀ የረቀቀ የመጨረሻው ደረጃም ላይ የደረሰ ነው፡፡ይህም ማለት መጻሕፍትን ጥሬ ንባባቸውን ብቻ ሳይሆን ከነምሥጢራቸው ጥጥት አድርጎ በቃል እስከ ማነብነብ ወይም መያዝ የደረሰ ፡፡ ሀገራችን ስላሏት እሴቶች ምንጭ ወይም አድራሻ ስናስስ ዞረን ዞረን የምንደርሰው አንድ ቦታ ነው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን፡፡ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከላይ የጠቀስኩትን የራሳችን የሆነን የንባብ ባሕል የፈጠረች ቤተክርስቲያን ነች፡፡ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ውስጥ እጅግ ብዙ ዓይነት መጻሕፍት አሉ የሚገርመው ታዲያ ከእነዚህ መጻሕፍት በሊቃውንቱ በቃል ያልተያዘ መጽሐፍ አለመኖሩ ነው እንዲኖርም አይጠበቅም፡፡ ይሄ ዓይነት የተለየ የንባብ ባሕላችን ታዲያ ሀገራችን በተደጋጋሚ በጠላት በተጠቃችና መጻሕፍት በወደሙ፣ በጠፉ፣ በተቃጠሉ ጊዜ … [Read more...] about የንባብ ባሕል ለምን እንዴትስ ይፈጠራል?