ኢትዮጵያ የዘውድ ስርዓት ከወረደ በኋላ ባልተረጋጋ የለውጥ ማዕበል ውስጥ መናጥ ከጀመረች 40 ዓመታት እየደፈነ ነው። የየካቲት 1966 ዓም አብዮት ዘንድሮ 40 ዓመት ይሞላዋል። ከ 1966 ዓም በፊት በነበሩት ስልሳ አመታት ውስጥ ሀገራችን ከሁለት መቶ አመታት በላይ በዘመነ መሳፍንት የእርስ በርስ ግጭት ከቀረው ዓለም ጋር የነበራት ግንኙነት በብዙ መልኩ የተለያየ እና ጠንካራ የማይባል ነበር። ከ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመርያ እስከ አጋማሹ ማለትም 1966 ዓም በነበሩት ዓመታት ውስጥ ሀገራችን ፍፁም ከሆነው የፊውዳል ስርዓት ወደ ዘመናዊነት ለመግባት ብዙ ነገሮች በየዘርፉ የጀመረችባቸው አመታት ነበሩ። ዘመናዊ መንግስት ስርዓት- እንደ ፓርላማ፣ ዩኒቨርስቲዎች፣ የአየር መንገድ አገልግሎት፣ የመብራት ኃይል ማስፋፋት፣ በዓለም አቀፍ ግንኙነትም ሆነ በአህጉራዊ እና አካባቢያዊ ፖለቲካ ውስጥ ተፅኖ ፈጣሪነት እና የመሳሰሉት ባጭሩ ሊገለፁ የሚችሉ የዘመናቱ ስራዎች ነበሩ።
ከ1966 ዓም ወዲህ ባሉት አርባ አመታት ውስጥ ኢትዮጵያ የተረጋጋ የመንግስት ስርዓት እና ህዝብን ያማከለ አስተዳደር ቢኖራት ኖሮ ዛሬ ካለአንዳች ማጋነን ደቡብ ኮርያ ከደረሰችበት የስልጣኔ እና የእድገት ደረጃ የመድረስ ዕድል ነበራት። ይህ ግን አልሆነም።
በእነኚህ አመታት ውስጥ በተገቢው ደረጃ እንዳናድግ ያደረጉን ብዙ ምክንያቶች አሉ። ከእነኝህ ውስጥ በቀን በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የበላ ጦርነት በሰሜናዊ የሀገራችን ክፍል ለአስራ ሰባት አመታት መካሄዱ፣ የነበሩት በእውቀት ክህሎታቸው እና በልምዳቸው ለሀገራቸው አስተዋፅኦ ያደርጉ የነበሩ ምሁራን የመስራት መብታቸው መታፈኑ፣ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ግንኙነት ብልህነት ያልተሞላበት የነበረ መሆኑ፣ ካለፉት 22 አመታት ወዲህ ደግሞ ብሄርን መሰረት ያደረገ የሀገሪቱ የአስተዳደር መዋቅር ወደባሰ አደገኛ የህዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ማምራቱ፣ ብሄርን መሰረት ያደረገ አድሏዊ ስርዓት ምጣኔ ሃብቱን በተወሰኑ እና ጥቂት ሰዎች እጅ እንዲገባ ማድረጉ፣ የፈጠራ ስሜት እጅጉን እንዲጎዳ መደረጉ፣ ሀገሪቱ ያለወደብ ቀርታ ለባሰ የባዕዳን ጥቃት ተጋላጭ መሆኗ ወዘተ የሚሉትን መጥቀስ ይቻላል።
ከላይ በተጠቀሰው 20ኛው ክ/ዘመን (1900 – 2000 ዓም) ውስጥ ኢትዮጵያ ስድስት የለውጥ መዘውሮች (turning points) ውስጥ አልፋለች። እነኝህ የለውጥ መዘውሮች (turning points) በሀገራችን የፖለቲካ መረክ ላይ ይከሰቱ እንጂ አብዛኞቹ ብሩህ ተስፋ ይዘው የመጡ የሚመስሉ ግን የከሸፉ ናቸው። የመክሸፋቸውን ምክንያት ለታሪክ ተመራማሪዎች ትቼ ክስተቶቹ ምንነት ላይ ብቻ ላተኩር።
1/ የለውጥ መዘውር ነጥብ (turning point) አንድ፡-
በ20ኛው ክ/ዘመን መጀመሪያ ላይ የመጀመሪያው የለውጥ መዘውር የነበረው የንግሥት ዘውዲቱ ስልጣን ወደ አልጋወራሽ ተፈሪ በኋላም በ1923 ዓም የንግስና ማዕረግ ያገኙት የቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ ወደ ስልጣን መምጣት ነው። በወቅቱ በጥቂት የተማሩ እና ‹‹ተራማጅ›› ተብለው ይጠሩ በነበሩ ወጣቶች ይደገፉ ነበር። ቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ ገና በአልጋ ወራሽነት ዘመናቸው ሳሉ አውሮፓን መጎብኘታቸው እና የአውሮፓን ስልጣኔ መመልከታቸው በኋላም የጣልያን ኢትዮጵያን መውረር እና በትምህርት እና በስልጣኔ ምን ያህል ወደኋላ እንደቀረን ግልፅ መሆኑ ቁጭት በንጉሱም ሆነ በወቅቱ በነበሩት ወጣቶች ዘንድ በሀገሪቱ ልማት ላይ ለውጥ ለማምጣት ስሜትን ኮርኩሯል። በእዚህም መሰረት ሀገራችን ከምንም ከሚባል ደረጃ በአፍሪካ እና በዓለም ተሰሚ የመሆን ደረጃ ደርሳ ነበር።
2/ የለውጥ መዘውር ነጥብ (turning point) ሁለት፡-
ሁለተኛው የለውጥ መዘውር መነሳሳት የተከሰተው በ1953 ዓም የተነሳው በብ/ጄ መንግስቱ ንዋይ እና ገርማሜ የተመራው በንጉሡ ላይ የተሞከረው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ነው። ከ1935 እስከ 1953 ዓም ድረስ የዓለም የፖለቲካ ሁኔታ ተለወጠ። አዲሱ ትውልድ አዳዲስ አስተሳሰብ ይዞ መጣ። ንጉሡ ምንም ለሀገሪቱ የመስራት ፍላጎታቸው እና ውጤታቸውን ቢያደንቅም መጪውን ግን በእዚህ አይነት አሰራር መቀጠል እንደማይቻል ያሰቡ መኮንኖች የመፈንቅል ሙከራ አደረጉ። ይህ መፈንቅል ተሳክቶ ቢሆን የሀገራችን የፖለቲካ ገፅታ ዛሬ ምን ይሆን ነበር? በርካታ መልሶች ይኖሩታል።
3/ የለውጥ መዘውር ነጥብ (turning point) ሦስት፡-
ሶስተኛው የለውጥ መዘውር ነጥብ አርባኛ አመቱን የሚደፍነው የየካቲቱ 1966 ዓም አብዮት ነው። ይህ አብዮት አሁን እስካለንበት ሁኔታ ድረስ ተፅኖ ፈጣሪ የሆነ እና በአሁኑ ጊዜ ያሉት ብዙዎቹ የፖለቲካ ድርጅቶች በእዚህ ወቅት ከነበረው የፖለቲካ አሰላለፍ ባንድም በሌላም ያለፉ ናቸው።
4/ የለውጥ መዘውር ነጥብ (turning point) አራት፡-
ሜ /ጄኔራል ፋንታ በላይ እና ሜ/ጄኔራል አምሃ ደስታ በኮ/ል መንግስቱ ላይ መፈንቅለ መንግስቱን ከመሩት መኮንኖች
አራተኛው የለውጥ መዘውር ነጥብ በ1981 ዓም በኮ/ል መንግስቱ ሃይለማርያም ላይ የተሞከረ የመፈንቅለ መንግስት ነው። ይህ መፈንቅለ መንግስት ቢሳካ ኖሮ ለሀገራችን ምን አዲስ ነገር ይዞ ይመጣ ነበር? አሁንም ለታሪክ ተመራማሪዎች እተወዋለሁ። የክስተቱ ተፅኖ ግን ብዙም ሳይቆይ በተለይ ከፍተኛ ልምድ የነበራቸው የሀገሪቱ የጦር መኮንኖች በኮ/ል መንግስቱ መገደላቸው የሰራዊቱን አቅም አዳክሞ ለሽምቅ ተዋጊዎች ‘ሰርግና ምላሽ’ ሁኔታ መፍጠሩን ብዙዎች ይስማማሉ።
5/ የለውጥ መዘውር ነጥብ (turning point) አምስት፡-
አምስተኛው የለውጥ መዘውር ከ1981 ዓም ብዙም ሳይቆይ በ1983 ዓም ግንቦት ወር ላይ የኢህአዲግ ሰራዊት አዲስ አበባ መግባት ነው። ይህንን ተከትሎ ሀገራችን በዘመኗ አይታ የማታውቀው የብሔር ፖለቲካ እና መከለል ውስጥ የገባችበት፣ ሀገሪቱ ወደብ አልባ የሆነችበት፣ በክልሎች ደረጃ የድንበር ቁርሾ የተነሳበት በአስተዳደር ዘይቤ በዘመናዊው ዓለም ውስጥ የምትኖር የዘመነ መሳፍንት ውስጥ ያለች ሀገር የመሰልችበት ክስተት ተከሰተ። ይህ የለውጥ መዘውር እጅግ አደገኛ ያደረገው የህዝቡ ኩራት እና ማንነት ከሆነው ከኢትዮጵያዊነት የተጣላ ስርዓት መሆኑ ነው። ይህ ስርዓት የምጣኔ ሃብቱን፣ የጦር ኃይሉን እና ፖለቲካውን እራሱን በጥቂት ሰዎች እና አካባቢ ሰዎች ስር መጣሉ የሀገራችንን መፃኢ ዕድል እጅግ አደገኛ አድርጎታል።
6/ የለውጥ መዘውር ነጥብ (turning point) ስድስት፡-
ስድስተኛው የለውጥ መዘውር ነጥብ በ1997 ዓም ኢትዮጵያ በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ሕዝቧን ያነቃነቀ ነፃ የምርጫ ስርዓት ያየችበት እና እንደ 1967 ዓም መፈክር ”ያለምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም” ልንዘመር ነው ተብሎ የተናፈቀበት ወቅት ነበር። ሆኖም ግን ክስተቱ በመቶ የሚቆጠሩ ወጣቶችን ሕይወት በኢህአዲግ ሰራዊት አማካይነት አስቀጥፎ እና ብዙዎችን ለእስር እና ለስደት ዳርጎ እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ሀገራችንን ላለፉት አርባ አመታት በነበረችበት የአምባገነንነት ስርዓት ውስጥ እንድትቀጥል ተፈረደባት።
7/ የለውጥ መዘውር ነጥብ (turning point) ሰባት?
ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ሕዝባዊ አብዮት በታሪክ ካደረገች አብዮቱንም በወታደራዊ ደርግ ከተነጠቀች በኋላ፣ ሰሜናዊው ህዝቧ እና መሬቷ እንዲነጠል ተደርጎ፣ ወደብ አልባ ሆና ለወደብ አገልግሎት በጎረቤት ጂቡቲ ላይ ጥገኛ እንድትሆን ተደርጋ፣ ሀገሪቱ በክልል ተከልላ እርስ በርስ የማይተማመን ሕዝብ ለመፍጠር ብዙ ሴራ ተስርቶባት፣በ 1965 ዓም በዓለም ላይ ሁለት ስደተኞች ብቻ የነበሯት ሀገር ዛሬ ከሁለት ነጥብ አምስት ሚሊዮን በላይ ስደተኛ በመላው ዓለም በትና እና ብዙ አስር ሺህ ሕፃናቷ በጉድፈቻነት ሸጣ ባጠቃላይ በብዙ ችግሮች ውስጥ ሆና ነው ሰባተኛውን የለውጥ መዘውር እየቀረበ መሆኑ ይሰማኛል የምለው። ሰባተኛው የለውጥ መዘውር በማን እንዴት መቼ እንደሚመጣ በእርግጠኝነት መናገር አሁን አይቻል ይሆናል። የህዝብ ፍላጎትን እና በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ግራ መጋባትን ተመልክቶ መረዳት ግን ብዙ አዋቂነትን አይጠይቅም።
ለሰባተኛው የለውጥ መዘውር ለማምጣት የተነሱ በሰላማዊውም ሆነ በትጥቅ ትግል ውስጥ የገቡ ኃይሎች ብቅ ብቅ እያሉ ነው። እነኝህ ኃይሎች ባብዛኛው ከስድስተኛው የለውጥ መዘውር ሙከራ ማለትም ከ1997 ዓም ወዲህ የተነሱትንም ማካተቱ ይታወቃል። በሃገርቤት በሰላማዊ ትግል ያለችውን ቀዳዳ እየተጠቀሙ ያሉትን ጨምሮ በትጥቅ ትግል ላይ ያሉት እንደ ‹‹ግንቦት 7››፣ አርበኞች ግንባር ወዘተ ያሉት ስርዓቱን በኃይል ለመጣል በሥራ ከተጠመዱት ውስጥ ናቸው።
ከአቶ መለስ ዜናዊ እረፍት ወዲህ በብዙ የውስጥ ቅራኔዎች መዋከቡ የሚነገረው ኢህአዲግ-ወያኔ ራሱን ለመሰረታዊ ለውጥ አለማዘጋጀቱ፣ ራሱን የቻለ ችግር ሆኖ የቀጠለ ክስተት ቢሆንም ለሰባተኛው የለውጥ መዘውር በለውጥ አስፈላጊነት ላይ ከመስማማት ባለፈ የኢትዮጵያን ያለፈውን እና የመጪውን የእድገት ትልሟን የሚያመላክት ጥርት ያለ ፖለቲካዊ ፍልስፍና አሁንም አስፈላጊያችን ነው። እዚህ ላይ ከፖለቲካ ፍልስፍና ይልቅ ነፃነት መቅደም አለበት የሚሉትንም መዘንጋት አይገባም። ለሁሉም ግን እርግጠኛ የምንሆንባቸው ሁለት ነገሮች አሉ። የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ በሃያኛው ክፍለዘመን አጋማሽ ጀምሮ የተረጋጋ የመንግስት ስርዓት ከተመለከትን 40ኛው ዓመት ላይ መሆናችንን። ሁለተኛው ደግሞ ጊዜውን አሁን መተንበይ ባንችልም ሰባተኛው የለውጥ መዘውር ምን መምሰል አለበት? ወዴት እንዴት ነው መሄድ የሚገባን?ያለፉት ስህተቶች እንዳይደገሙ ምን ይደረግ? የመሳሰሉት ጥያቄዎች ሊነሱ የሚገባበት ጊዜ ላይ መሆናችንን አለመርሳት የሚሉት ናቸው።
(ጉዳያችን ጡመራ አጭር ጥንቅር)
ጌታቸው በቀለ: ኦስሎ
አንተነህ ጌትነት says
በእውነቱ ጎልጉሎችም ግንቦት7 በትጥቅ ትግሉ ደፋ ቀና እያለ ነው ብላችሁ መጻፍ ከአንድ ነጻ ሚዲያ ነኝ ከሚል የሚጠበቅ አይደለም። ታሳዝናላችሁ። ሁሉም የግንቦት7 አሽከር መሆኑ።
Editor says
አንተነህ ጌትነት
ለአስተያየቱ እናመሰግናለን:: ሆኖም ግን እኛ የጽሁፉ ባለቤት ወይም ጸሃፊ አይደለንም:: ይህ አባባል የራሳቸው የጸሃፊው ነው:: እኛ ሃላፊነት የምንሥድባቸው ጽሁፎች በራሳችን የተጻፉትን ዜና እና ሪፓርታዥ እንዲሁም ርዕሰአንቀጽ የመሳሰሉትን ነው:: ለዚያም በግልጽ አስቀምጠን እንገልጻለን:: ሆኖመ እንደሚዲያ ባለን ኤዲቶሪያል ፓሊሲ መሠረት የሚመጥኑ ጽሁፎችን እናትማለን:: እንደ እርስዎ ያሉ አንባቢያን ደግሞ እንደ አንባቢ ካልተስማማቸው የምላሽ ጽሁፍ ይጦምራሉ – እኛም እናትማለን:: ሃሳብ በዚህ መልኩ ይስተናገዳል:: እኛ በጻፍነው ላይ የሚጻፍ ማንኛውንም የምላሽ አስተያየት በደስታ ስናስተናግድ ቆየተናል አሁንም እንቀጥላለን – እንደ ባህል እንዲለመድም እናደፋፍራለን:: ከዚያ በተረፈ የምናራምደውን አቁዋም ለማወቅ ለሚሹ – እርስዎንም ጨምሮ – “ስለ እኛ” የሚለውን በድረገጻችን አናት ላይ የሚገኘውን ማንበቡ ከጅምላ ማጠቃለያ ለመጠበቅ ይረዳል::
ከምስጋና ጋር
አርታኢ/Editor
ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ/Golgul: the Internet Newspaper
http://www.goolgule.com
editor@goolgule.com
betti says
isn’t it better all the free medias should serve the will of the majority including Ginbot 7? What is your concern here? Should Golgul serve the interest of Woyane in stead of Ginbot 7? You can watch CNN, BBC, Walta, ETV, etc if you think they are free. Don’t be dumb. There is no free media as such in the whole wide world. Medias serve this or that group. The lucky ones serve the will of the majority. If you do not like this, then you can watch porn in your computer.
Abe says
I strongly admire the writer, and the editors response to one of the critics here. The responsibility of the free media is, apart from siding with the people and telling the truth, it is to create the opportunity and the forum where others speak out their ideas and minds be it liked by some and not by others. That’s what Golgul is doing since they were on this media.
No body can avoid and take out “Ginibot7” or other groups who resorted to armed struggle from the Ethiopian political change equation. It’s upto the critic not to support “Ginbot7”, but he can’t tell others not to mention or write about this group. Worst still is calling others as “ሁሉም የግንቦት7 አሽከር መሆኑ።” phrase. This is an insult to others and a nonsense idea to be rejected.
Ethiopia has lost great development opportunities the last 40 years. Most of the Emerging Market countries we see trimphant in the world today were not better than Ethiopia 30 and 40 years back. China, Malaysia, Singapore, India, etc. can be taken as examples. The Chinese started thier development agenda of today in 1978 while we were still struggling from the hangover of the 1974 Revolution.
ezra says
በቅድሚያ ለዚህ አስተያየቴ መነሻ የሆነኝ የአንተነህ ጌትነት አስተያየት ነው።
ውድ ኤዲተር! ሆይ
በፈረንጆች አባባል Do Not Forget እንደሚባለው
አንርሳ! ብዙዎቻችን ከሃገራችን በግዳጅ ፣ በጣም ጥቂቶች ደግሞ በፍላጎት ተሠድደን ወደ ተለያዩ ባዕድ አገሮች እንመጣ እንጅ የአብዛኛዎቻችን አስተሳሰብ በጣም ብዙ እንደሚቀረውና ገና እንደሆንን በመልዕከት ሳጥናችሁ በምናስቀመጠው መልክቶቻችን እንኳ መገንዘብ ይቻላል። በአደጉ አገሮች ተቀመጠን እንኳ እነርሱ በሠሩት የዴሞክራሲ ሥርዓት ተጠቃሚ ሆነን ሳለ ያን እኛም እየተጠቀምንበት ያለዉን የዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ሥርዓት እያንዳንዳችን ወደ ራሳችን ሕሊና መልሠን ልንጠቀምበት በተነሳን ቁጠር የሚያደናቅፈን የራሳችን የሆነ እንቅፋት አለን። ዋናዉና ተቀዳሚው ህጸፃችን ማንም ሳይሆን የእኛው የራሳችን ያላተቀየረውና ለመቀየረም እያንዳንዳችንን የሚፈታተነን ድብቅ ያስተሳሰብ ባህሪያችን ሁሌም መሠናክል እየሆንብን ነው።
ስለሆነም ለእንዲህ ዓይነቱ ኃላቀር አስተሣሰብ መድኃኒቱ የእናንተ ዓይነት እና መሠል ድረ ገጾች መኖር ዋስትና ነው። በተጨማሪም የማያስተምሩና አንዳንዴም ፀያፍ ሊባሉ የሚችሉ ህፅፆቻችንን የሚያሳዩንና እንድንቀርፋቸዉም የሚረዳን ሃሳቦችን (idea)ን፣ እንደልብ ማንሸራሸሪያ ቦታዎች በበቂ ሲኖሩን እና እነዚያንም ደግሞ በአግባቡ መጠቀም ስንችል ብቻ ነው ተጠቃሚዎች የምንሆነው። ለምን ቢሉ እያንዳንዱ ሰው የባህሪው ተገዥ ነው ይባላልና ነው። 1000 እርምጃን ለመሄድ በ 1 እርምጃ ይጀመራል ነው ነገሩ። ሽዎችን ለመቀየረና ለማነፅ የሚደርገው ጉዙ አድካሚና አሠልች ይምሠል እንጅ በአንፃሩም ብዙ የሚማሩበት ሂደት መሆኑንም ሁሌም ግምት ውስጥ ማስግባት የአዋቂዎች ወይም የብልሆች መስፈርት ነው።
እናም የምንፅፈዉና በየአስተያየት መስጫውች የምንተዋቸው አጫጭር መልክቶቻቸን እንኳ ሳየቀር የሚያመላክቱት፣ ምን ያህል መሥራት እንዳለባችሁና ብዙ እንደሚቀረን አንዳንዴም (ድብቁንም ሆነ ግልጹን) ባህሪያችነን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። ለዚህም ነው ዛሬ የምናናንቃቸው አያት ቅደም አያቶቻችን “ከፈረንጅ በልኃቱን እንጅ ክፋቱን አይማሩም” ብለው ለክፋት ብዙ እንዳንተጋ እና ከ Negative እንዳነነሳ ለዛ ባለው ቋንቋቸው ለእኛ ለተከታይ ለልጆቻቸው ሊያስቀመጡልን የተገደዱት ።
ለመማረና ለመለወጥ/ለመቀየር የሚፈለግ ሰው (በአስተሳሰብ ማለቴ ነው) መጀመሪያውኑ ምንም ዓይነት አስተያየቶችን ከ positive Spirit ተነስተን ለማዬት ከሞከርን መዳረሻችንም ሆነ መደምደሚያችን ቀና(Positive Spiritን )የተጎናፀፍ ይሆናል ማለት ነው። ይህ ቀና መንፈስ (Spirit) ካለን የማይመቹን ትችቶችንም ቢሆን የምናይበት፣ የምንቃኝበት ወይም የምንተችበት መንፈስ ራሱ ለመማር ሆነ ለማስተማር ምርኩዝ ሆኖ ያገልግለናልና ነው። በመሆኑም የሚመቹንን ትችቶች እንደምንወዳቸው/እንደሚያስደስቱን ሁሉ የማይመቹን ትችቶችንም ቢሆን እንድንወዳቸው ወይም እንድንደሰትበት የሚገፋፋን (ሁላችንንም ለማለት ባልደፈረም) አብዛኛዎቻችን Positive Spirit ወይም Positive Thinking ሆንን ከተጓዝን ብቻ መሆኑን አሌ ማለት አይገባም
በሌላ በኩል የምንተችበት መንፈስም በመልዕክተኛው ላይ ሳይሆን በመልዕክቱ ይዘት ላይ እንዲሆን እና/እንድናተኩር እነዚህ Positive Spirit ቶች ያደፋፍሩናል ወይም የረዱናል እንደ ማለትም ጭምር ነው። ስለሆነም ትችቶቻችን ሁሉ የሚያነጣጥሩት ትችትን ጋባዥ በሆነው ጉዳይ ወይም ቁም ነገር ላይ ይሆንና ያ ልንተቸው የፈልግነው ጉዳይ/ቁም ነገር የሚመለከተዉ ካለ…. ግለሰብ ወይ ቡደን ወይ ተቋም ወዘተ ሊሆን ይችላል እዚያ ላይ ሊያነጣጥር ይግባል እንጅ እንዲያው በድፍኑ ከኑግ ጋር የተገኘኝህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ ዓይነት አካሔድን እንዳንከተልም የሚረዳን ቕንነት ወይም ቀና መንፈስ(ስፕሪት) መሆኑን ለአፍታ መዘንጋት የለብንም ባይ ነኝ ። እንደ አገርና እንደ ህዝብ የብዙ ጥሩ አስቴች ባለቤቶች ነን። ከእነዚህ አሴቶቻችን ውስጥ በኃይማኖቶቻችን ውስጥ እንኳ ሳይቀር የሚጠቀሰው ገናና አባባል ምንም ነገር ለማደረግ ከመነሣታችን በፊት « ቀናውን አሳየኝ፤ ቅን ሁን ቀና እንድታገኝ፡ ቸር አዉልኝ »የሚል ነውና ይሄንን ምልካም ምኞትን ተመኝተን ነው የየቀን ውሏችንን በቀና ለመጀመር ከልባችን ወይም ከህሊናችን ጋር ዉል የምንቋጥረበት ትውፊታችን እንድናደረገው የሚያስገድዱን ። እንዲህ አይነት መንፈስ እንዲኖረን ወይ እንድናሳድር ደግሞ በማንኛውም መመዘኛ ሃሳቦች መንሸራሸራቸው የሚደገፍና የሚበረታታ ነው ። ስለዚህ ጎልጉሎች እንደሰማችሁ ሆናችሁ ትቀጥሉ ዘንድ እንዲሁም አሁን የምንጠቀምበት ሃሳቦችን የማንሸራሸሪያ መድረካችሁ ይበልጥ ይጠናከርና ይሰፋ ዘንድ ድረ ገጻችሁ ሚናው ቀላል አይደልም።