
ዶ/ር ደስታው አንዳርጌ ይህንን ጽፈዋል፣
ፊደል ካስትሮ፦ የኢትዮጵያና አፍሪካ የቁርጥ ቀን ወዳጅ፤ የክፍለዘመኑ ዳዊት
የ፳ኛው ክ/ዘ ካፈራቸው ታላላቅ መሪወች ውስጥ ሁልጊዜም ፍትህና ነጻነት ከሚሹት ጋር በመቆም፤ ሁሌም በትክክለኛው የታሪክ ገጽ በመገኘት ፊደል ካስትሮን የሚስተካከል ማን አለ? ከኒካራጓና ቺሌ እስከ ቬትናም ከፍልስጤም እስከ አልጀሪያ ብሎም ደቡባዊ አፍሪካ ነጻነት ለናፈቃቸው ሁሉ የካስትሮን ያህል ታላቅ ድጋፍ ያደረገ ሌላ መሪ ማንም የለም። በተለይ የአፍሪካ አገራት ከኢምፔሪያሊስቶች ጋር ባደረጉት ትንቅንቅ የካስትሮና የኪውባ ቁርጠኝነት ከጉዳዩ ባለቤቶች ያልተለየ ነበር። ኪውባ ለአንጎላ ያደረገችው እጂግ መጠነሰፊና ከአስር አመት በላይ የዘለቀ ድጋፍ ለዚህ አይነተኛ ማሳያ ነው። ካስትሮ አንጎላ ከፖርቹጋል ቅኝ ነጻ ለመውጣት ካደረገችው ተጋድሎ ጀመሮ በአሜሪካ ድጋፍ አንጎላ የገባውን የአፓርታይድ ደቡብ አፍሪካ ጦር በሺ የሚቆጠሩ ወታደሮችን ልኮ ድባቅ በመምታት ለአንጎላ ብቻ ሳይሆን ለእነ ናሚቢያ ከአፓርታይድ ተጽዕኖ ነጻ መውጣት ጉልህና ቀጥተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ይህ ሽንፈት አሜሪካን ያሳፈረ ሲሆን ለአፓርታይድ ውድቀት የመጨረሻው መጀመሪያ ተደጎግ ይቆጠራል። ይህ በሆነ በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ ማንዴላ ከእስር ሲፈታ ቅድሚያ ከሰጣቸው ጉዳዮች ውስጥ ኪውባ ተጉዞ ካስትሮን ማመስገን አንዱ ነበር። እንደነ ሴኮቱሬ፤ ሳሞራ ሚሸል፣ ኔሬሬና ሌሎች የአፍሪካ ነጻነት ታጋዮችም ቢሆን ከአፍሪካ ውጭ ከካስትሮ የቀረበ የልብ ወዳጅ አልበራቸውም።
ካስትሮ ለኢትዮጵያ
የኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት እስከሚጀመር ድረስ ኪውባ እንደ ሶቭዬት ሁሉ የሶማሊያ ወዳጅ ነበረች። አሜሪካ ደግሞ በቃኘው ጣቢያ ላይ ያላት ፍላጎት እስኪቀዘቅዝ ድረስ መጠነኛ ርዳታ ለኢትዮጵያ ትሰጥ ነበር። በመሀል አብዮቱ ፈነዳ። አብዮቱን ተከትሎ ግን የአገራችን የወቅቱ መሪወች ባልገባቸውና በባዶው ሶሻሊስት ነን ሲሉ አወጁ። ያኔ አሜሪካና እንግሊዝ ሶማሊያን ማስታጠቅ ይጀምራሉ። ሶቭዬትና ኪውባ ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ይዞሩና ደርግን ከማስታጠቅ አልፈው ሶቭየት በርካታ የጦር አማካሪወች ኪውባ ደግሞ ፲፰ ሺ ጦር ልከው ሶማልያን ለመመከት ረድተውናል። የኢትዮጵያ ታላቅ ባለውለታወች!
ስካስትሮ ጥቂት
ተማሪወች እያሉ ከጓደኞቹ ጋር ምን መሆን እንደሚያስቡ ያወራሉ፤ አንዱ ሰዐሊ መሆን እፈለጋለሁ ሲል ሌላኛው መሀንዲስ ነው የምሆነው፣ ሌላው አለምን መዞር ነው ምኞቴ ሲል የካስትሮ መልስ አጭር ነበር፥ ግሎሪ (ክብር?)። ይህ እንደ አብዛኛው ሰው የግል ዝና ፍለጋ አልነበረም። ደሀ አልነበረም፤ ሀብት ግን ምኑም አልነበረም። አገሩ ኪውባ የያንኪ መጫወቻ መሆኗ ያበሳጨው ነበር። ኪውባ ከካስትሮ በፊት ለስሙ ነጻ አገር ብትሆንም እውነቱ ግን ሌላ ነበር። ኢኮኖሚው በአሜሪካዊያን ቁጥጥር ስር ነበር። ሀቫና የአሜሪካውያን እሁድ-ቅዳሜ መጫወቻ ሜዳ፤ የቁማርና የሽርሙጥና ማዕከል ነበረች። አብዛኛው ህዝብ በድህነት ሲኖር የአገሪቱ ፕሬዘደንት ባቲስታ በአሜሪካና በማፊያ የሚታዘዝ ሙሰኛ ነበር። ካስትሮ አንድ ነገር ማድረግ እነዳለበት አመነ። መጀመሪያ በምርጫ ሞከረ፤ ይሆን እንጅ መርጫው ይሰረዛል። ምርጫው እንደማይካሄድ ሲያውቅ አብዮት ለማቀጣጠል የሚሆን የጦር መሳሪያ ለመዝረፍ መቶ የሚሆኑ ጓዶቹን ይዞ በአንድ ትልቅ የጦር ካምፕ ላይ ጥቃት ያደርሳል። ይሁን እንጂ ጥቃቱ ይክሽፍና ታስሮ ፍርድቤት ይቀርባል። ጥፋተኛ ነህ ወይ ተብሎ ሲጠየቅ ወጣቱ በሞያው ራሱ ጠበቃ ቢሆንም የተንዛዛ የህግ ክርክር ማቅረብ አልፈለገም። አሁን ቆራጥ አብዮተኛ ነው፤ “ፍርዱብኝ። ለውጥ አያመጣም፤ ታሪክ ነጻ ያወጣኛል፤ ጨርሻለሁ” ነበር ያለው።
ከሁለት አመት እስር በኋላ በምህረት ይለቀቃል። ካስትሮ ግን ኪውባ ነጻነቷን ሳታገኝ የሚተኛ ሰው አይደለም። ከጓደኞቹ ጋር ሜኪስኮ ይሄድና ወታደራዊ ስልጠና ወስዶ ቸጎቬራን ጨምሮ ፹ የሚሆኑ አብዮተኞችን ይዞ ከመጠነኛ ስንቅ ጋር ግራንድ ማ ብሎ በሰየማት ትንሽ ጀልባ ወደ ኪውባ ይመለሳል። ነገር ግን የባቲስታ መንግስት መረጃ ደርሶት ኖሮ ገና ከጀልባዋ ሳይወርዱ የጥይት ሩምታ ይቀበላቸዋል። ብዙወቹ ይገደላሉ፤ ካስትሮና ቼ ኮቫራን ጨምሮ ፲፰ የሚሆኑት ብቻ ተረፉ። የተረፉት ግን በአሜሪካ የሚደገፈውና ሙሰኛውን የባቲስታ መንግስት ለመገልበጥ ቆራጥነትና የሁለት ዐመት ጊዜ ብቻ ነው የጠየቃቸው።
ዳዊት ጎልያድን
ካስትሮ ለአሜሪካ ኢምፔሪያሊዝም ያለው ጥላቻ ከልጅነቱ ነው አብሮት ያደገው። ቢሆንም ግን ጎልያድ ጋር መላተም ብልህነት አለመሆኑን ያውቃል። አሜሪካን ላለማስቀየም የቻለውን ሁሉ ያደርግ ነበር። የኪውባ አብዮት እንጂ ሶሽያሊዝም ወይ ኮሚኒዝም የሚባል ቃል አይወጣውም። ኮሚኒስት ሊያሰኙ የሚችሉትን ጉዳዮች ለወንድሙ ላራውልና ለ ቼ ነበር የሚተዋቸው። እንዲያውም የወቅቱ የሶቭየት መሪ ኒኪታ ክሩሽቸቭ ፊደል ኮሚኒስት ነው ወይ ተብሎ ተጠይቆ “ፊደል ኮሚኒስት መሆኑን አላውቅም፤ የማውቀው እኔ ፊደላዊ (የፊደል ተከታይ) መሆኔን ነው” ነበር ያለው። ግን ደግሞ ለማህበራዊ ፍትህ የቆመ አገር ወዳድ አብዮተኛ የአገሪቱ ኢኮኖሚ በአሜሪካ ኩባንያወች ቁጥጥር ስር ሆኖ ምንም አለማድረግ አይችልም ነበር። ስለሆነም በመጀመሪያ መሬት ላራሹ ያውጃል። በሂደቱ የብዙ አሜሪካውያን የግል መሬት (ራንች) ይወረሳል። መጠነ ሰፊ የትምህርትና የጤና ማሻሻያ ፕሮግራሞች ይነደፋሉ። ይህ ሁሉ ብዙ ገንዘብ ይጠይቃልና ኪውባ ቀስ በቀስ ለኪውባዊያን እየሆነት መጣች። ከመጀመሪያው አቅጣጫው ያላማረው የአሜሪካ መንግስት ካስትሮን ለማጥፋት መዶለት ያዘ። መሸነፍ የማይወደው ካስትሮ እንዲህ ከሆነማ ብሎ በአገሪቱ ያለውን ሀብት ናሽናላይዝ ያደርጋል። ከዚያማ የአሜሪካ መንግስት የኪውባን አየር ማረፊያወች በ ቢ ፳፮ ቦምብ ጣይ ካስደበደብ በኋላ ያሰለጠናቸውን ኪውባዊያን ስደተኞች አስታጥቆ ካስትሮን እንዲገለብጡ ላካቸው። የጦር ስልት አዋቂው ካስትሮ ግን ለሲአይኤ ጄሌወች ዕድል አልሰጣቸውም። የአሳማ ቤይ በሚባለው ይኸው ወረራ የሲአይኤ ብቻ ሳይሆን ለወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዘደንት ጆን ኤፍ ከኔዲ ታላቅ ክሽፈት ነበር። ማንም የላቲን አሜሪካ መሪ ሲአይኤ በሙሉ ክብደቱ የተሳተፈበትን ወረራ አሸንፎ አያውቅም። ሲአይኤ ብሄርተኛ መሪወችን አስወግዶ እንደነ ሞቡቱ፣ ሱሀርቶ፣ ፈርዲናንድ ማርቆስና፣ አውግስቶ ፖኖሼ ያሉ ታዛዥ አምባገነኖችን ወደስልጣን ለማምጣት ተቸግሮ አያውቅም።
ከአሳማ ቤይ ክሽፈት በኋላ ያለው አማራጭ ግልጽ ወረራ ነበር። ፈጣኑ ካስትሮ ግን አሁንም ቀደመ። ስቭዬቶችን አሳምኖ የሶቭየት ሚሳየሎች ኪውባ ላይ ተጠመዱ፤ የኒዮክሌር ፍጥጫ ተፈጠር። ፍጥጫው የረገበው ሶቭየት ሚሳየሎችን ከኪውባ ለማንሳት አሜሪካ ደግሞ ኪውባን ላለመውረር ተስማምተው ነበር። በመሆኑም ፕሬዘደንት ኤፍ ጆን ከኔዲ ወረራ ምናምን የምትሉትን ተውና ሰውዬውን (ካስትሮን) ብቻ አጥፉልኝ ይላል። ሲአይኤ በሚያውቀው ማፊያወችን ለመጠቀም ሞከረ፤ የተመረዘ ሲጋራ ለካስትሮ ለማቅረብና ሌላው ቀርቶ የካስትሮ ጺም ረግፎ መሳቂያ እንዲሆን ያላደረገው ጥረት አልነበረም። ሲአይኤ በካስትሮ ላይ በአጠቃላይ ከቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ አድርጎ ፮፻፴፰ የግድያ ሙከራ አድርጎ ሳይሳካለት ቀርቷል። ማነው አሸናፊ?
የአሜሪካ መንግስት የካስትሮን ህይወት ለማጥፋት ከማሴር ጎን ለጎን ኪውባን ለማዳከም የኢኮኖሚ ማነቆ ከጣለባት ግማሽ ከፍለዘመን አልፏል። በየጥቂት አመቱ ማእቀቡን በተመለከተ በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ድምጽ ሲሰጥ አለም በሞላ ማእቀቡ ሊነሳ ይገባል ሲል ሁለት አገሮች ብቻ ይቃወማሉ፥ አሜሪካና እስራኤል (እንግሊዝ ብዙ ጊዜ ድምጸ ተዐቅቦ ነው የምታደርገው)። አሁንስ ማነው የሞራል የበላይነት ያለው?
ሞት አይቀርም፤ ግን እንደካስትሮ ሁሌም በአሸናፊነት የኖረ የአገሩን ከብርና ሉዋላዊነት ከማስመለስ አልፎ ትንሽና ደሃ አገሩ በአለም ላይ ከክብደቷ በላይ ተጽዕኖ እንድትፈጥር ያስቻለ መሪ በርግጥም ታላቅ ነው። እንደ ካስትሮ ያሉ ጀግኖች ደግመው ደጋግመው ይፈጠሩ። ህዳር ፲፯ ቀን ፪ ሺ ፱ ዓ.ም (ጽሁፋቸውን ያገኘው እዚህ ላይ ነው)
Dr. Msmaku Asrat has this to say about Castro;
By the passing of Fidel Castro the world has lost one of its finest specimens of Humanity. Castro was one of the greatest leaders of the 20th Century and the greatest during the latter half of the Century. He was the first who brought equality between the black and white races of Cuba, the first and the last country to do so. The US has not been able to do so after a century of effort. The South African nation of Brazil, which has the highest number of blacks outside of Africa, have subjugated their black population akin to slavery to this day. Nobody knows or even seen a black Brazilian except the legendary Pele, since they don’t have the capacity to leave their country, even though they are the majority.
Cuba made education and health services free. Their doctors have given free service to a majority of African countries including the Caribbean and South America. Ethiopia was a benefactor of this as well. Ethiopians have a deep gratitude for Castro who sent his troops to repel Somali aggression, without whose help the DERG led by brutal dictator, Mengistu, would have surely suffered a decisive defeat.
Housing is almost free. Many observers have commented that the Cubans are the happiest people on earth. The Robber Barons of Corrupt Cuba and their children fled and were given free citizenship in the US. Their grand children are now shamelessly demonstrating their happiness for the death of Castro, in Florida, place of their refuge.
Cuba has withstood 60 years of TOTAL embargo and economic sanctions from the US. Over two dozen assassination attempts of Castro has been made by the US. They have tried to destroy their sugar cane (which produces the finest sugar in the world) and their tobacco (the Havana cigar is world famous) US has done this consistently for 60 years. It is the elephant smothering the ant but the ant miraculously survived.
US has been soundly and decisively defeated by Vietnam in unequal military combat, the first ever defeat of the mighty US army. America has also been mightily defeated morally by Cuba. In Cuba there are no guns and no violence and people enjoy their life of equality. That must be how heaven looks like.
Cuba, before the Revolution, was a playground for decedent gangsters. such as the mafia from the US, where prostitution and drug use was rampant and it was called “an island of sin” The US which run the scene was the de facto colonial power. It still occupies part of Cuba (Guantanamo).
After the revolution Cuba excelled in biotechnology having the largest research lab. in the world, it was the first to reach Sustainable Development goals, excelled in sports (beat US in medals in 1995) and has the finest pharmaceuticals and the best educated medical doctors in the world.
These and much, much more for a tiny island. If it was not for the support of the Soviet Union and later of Venezuela, Cuba would have been devastated by the vengeful US – reminiscent of Nagasaki and Hiroshima. But it was not to be thanks to the humane leadership of Castro.
When we mention Cuba we should also never forget Che Guevara the foremost revolutionary of the 20th Century (killed by US) who has a hand in shaping the destiny of Cuba.
Castro has managed to create heaven on earth. Now he belongs to the ages. RIP most honorable man.
Msmaku Asrat
“ከኢምፓየሯ ምንም ዓይነት ስጦታ/ገጸ-በረከት አንሻም” – ፊደል ካስትሮ
የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ዘገባ እንዲህ ይነበባል
የኰሙውኒስት አገራቸውን አመራር እ.አ.አ. በ2008 ለታናሽ ወንድማቸው ራውል (Raul) የሰጡት የ89 ዓመቱ ካስትሮ፣ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ያቺን አገር ባለፈው ሳምንት ለሦስት ቀናት ሲጎበኙ አንዴም እንዳልተገናኙ ይታወቃል።
አረጋዊው የኩባ አብዮተኛ ፊደል ካስትሮ፣ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ለተጀመረው የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ደንታ እንደሌላቸው በማመልከት፣ “ከኢምፓየሯ ምንም ዓይነት ስጦታ/ገጸ-በረከት አንሻም” ማለታቸው ተሰማ።
የኰሙውኒስት አገራቸውን አመራር እ.አ.አ. በ2008 ለታናሽ ወንድማቸው ራውል (Raul) የሰጡት የ89 ዓመቱ ካስትሮ፣ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ያቺን አገር ባለፈው ሳምንት ለሦስት ቀናት ሲጎበኙ አንዴም እንዳልተገናኙ ይታወቃል።
አንድ በሥልጣን ላይ ያለ የአሜሪካ መሪ ኩባን በ90 ዓመት ውስጥ ሲጎበኝ፣ ኦባማ የመጀመሪያው ናቸው።
ፕሬዚደንት ኦባማ፣ በጉብኝታቸው ወቅት፣ በሁለቱ አገሮች መካከል ለ50 ዓመታት የዘለቀው መለያየት መቆም እንዳለበት ይፋ አድርገዋል። (ፎቶ – ፊዴል ካስትሮ ሃቫና ኩባ ወስጥ እ.አ.አ 2015፣ AP)
ከዚህ በታች ያለው የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ዘገባ ነው ፎቶውም ጭምር
ካስትሮና ኢትዮጵያ
«እኛ የጠላነዉ፤ ላጭር ጊዜም ቢሆን መሸነፋችንን በመገመት ነዉ።» «መሸነፋችንን።» ይሕቺ ቃል ጦርነቱ የኢትዮጵያ-የሶማሊያ ብቻ ሳይሆን የኩባና የሶማሊያ፤የደቡብ የመንና የሶማሊያ መሆኑንም አረጋገጠች።ይሕቺ ቃል ጦርነቱ የሶቭየት ሕብረትና የዩናይትድ ስቴትስ፤ የሶሻሊስቱና የካፒታሊስቱ ዓለም ጦርነት፤ የቀዝቃዛዉ ጦርነት አካል መሆኑን አረጋገጠች።
በ1977 ኢትዮጵያ በድርቅ ተመትታ ዜጎችዋ በረሐብ ሲያልቁ «እኛ» አሉ-አሉ-ያኔ ሐቫና የነበሩ ኢትዮጵያዉያን «ለኢትዮጵያዉን የምንለከዉ ስንዴ የለንም፤ ቢኖረንም በቂ አይደለም።የምንልከዉ ግን አለን። ደማችንን።» እና የመጀመሪያዉ ሆነዉ ለኢትዮጵያ የሚላክ ደም ሰጡ። ፊደል ካስትሮ ሩዝ። አርብ ማታ አረፉ።
የትንሺቱ አፍሪቃዊት ሐገር ኬፕ ቬርዴ ፕሬዝደንት ዮርግ ካርሎስ ፎንሴካ «ግርማ ሞገስ» የተላበሱ እና አወዛጋቢ» መሪ አሏቸዉ ካስትሮን ባለፈዉ ቅዳሜ። የግዙፊቱ፤ የሐብታሚቱ፤ የዓለም አድራጊ ፈጣሪቱ የዩናይትድ ስቴትስ የ50 ዘመን ጠላት ሆነዉ አዋዛጋቢ የማይበሉበት ሰበብ፤ ምክንያት በርግጥ ሊኖር አይችልም። ለአብዛኛዉ ኩባዊ ግን ተወዳጅ፤ ቆራጥ፤ ፅኑ ጅግና፤ ደግና አዛኝ መሪ ነበሩ። ኩባ ለተማሩ ኢትዮጵያዉን ደግሞ ኢንጀነር ደረጀ እሸቴ እንደሚሉት አባት ነበሩ።አቶ ዝናዉ ተሰማ አከሉበት።
የቀድሞ ባልደረባዬ፤የቅርብ ወዳጄም ጋዜጠኛ ተፈሪ ለገሰ ካስትሮን እንደ ሐገር መሪ፤ እንደባለሥልጣን ወይም እንደ ታላቅ «አንቱ» አይላቸዉም።እንደ አባት ይወዳቸዋልና።እንደ ሩቅ ሰዉ በሁለተኛ ስማቸዉ አይጠራቸዉምም። በጣም ያቀርባቸዋልና። ፊደል-ይላቸዋል። ካስትሮን። ነፃ ኩባ፤ ነፃ፤ የተማረ፤ ጤናማ፤ ጠንካራና ሰላማዊ ኩባዊ ካለ ካስትሮ አይታሰብም ነበር።
ኩባ ትንሽ ደሴት ናት።የ11 ሚሊዮኖች ሐገር።ደሐ ናት።ረጅም ጊዜ የፀናዉ የዩናይትድ ስቴትስ ተደጋጋሚ ማዕቀብ፤ የሶቭየት ሕብረት መፈረካከስ፤ የኮሚንስቱ ዓለም መዳከም ሲታከልበት ድሕነቱ ጠንቷል። ተርባ ግን አታዉቅም። ማሐይም ዜጋ የላትም። በሕክምና እጦት የሚሞት ኩባዊ የለም።
አብዛኞቹ የደቡብ አሜሪካ ሐገራት የነገሰዉ የአደንዛዥ ዕፅ ንግድና ነጋዴ፤ ዘረፊ፤ ማጅራት መቺ፤ ገዳይ ለኩባዉያን በመገናኛ ዘዴ ከሚሰሙት የጎረቤት ሐገር ዜና ባለፍ አያዉቁትም። የጥቁር ነጮች ግጭት፤ ንቀት፤ ቁጭትን ኩባዉያን ከዩናይትድ ስቴትስ በሚሰራጭ ዘገባ እንጂ በገቢር አያዉቁትም። ኩባ ማይም ዜጋ የላትም። ያልተማረ-የሚባለዉ ዘጠነኛ ክፍል ነዉ። ተፈሪ ለገሰ የካስትሮና የባልደረቦቻቸዉ የሥራ ዉጤት ይለዋል።
ለኢትዮጵያዉን ፍቅር።
ፍቅር፤ አክብሮቱ እንዲሕ ተጀመረ። መጋቢት 14 1969። ሶማሊያን ለሰወስት ቀን የጎበኙት ፊደል ካስትሮ አዲስ አበባ ገቡ።አዲስ አበባን ሲጎበኙ ሁለተኛቸዉ ነበር።ዓላማቸዉ።ያኔ በጦር ሐል የደረጀችዉ የጄኔራል ዚያድ ባሬዋ ሶሻሊስታዊት ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ሶማሊያን፤ በአብዮት የምትናጠዋን በጦር ሐይል ደካማዋን፤ የኮሎኔል መንግሥቱ ሐይለማርያም ሕብረተሰባዊት ኢትዮጵያን እንዳትወር ለማግባባት ነበር።
ካስትሮ ከአዲስ አበባ ወደ ሰወስተኛዋ የአካቢዉ ሶሻሊስታዊት ሐገር ደቡብ የመን ተጓዙ።መጋቢት አስራ-አምስት። በሊቀመንበር መንግሥቱ ኃይለ ማርያም የሚመራዉ የኢትዮጵያ መንግሥት የመልዕክተኞች ጓድ ማምሻዉን ተከተላቸዉ።
«አደን የደርሰነዉ ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት ግድም ነበር።የኩባና የሶማሊያ መልዕክተኞች ቀድመዉን ደርሰዋል።» ይላሉ ኮሎኔል መንግሥቱ «ትግላችን» ባሉት መፅሐፍ።ፊደል ካስትሮና ምክትላቸዉ፤ የየመኑ ሶሻሊስታዊ ፓርቲ መሪ አብዱልፈታሕ ዑስማኤልና ተከታዮቻቸዉ የሸመገሉት ድርድር ያለ ዉጤት አበቃ።ዚያድ ባሬ ሌሊቱኑ ወደ ሞቃዲሾ ተመለሱ።
መንግሥቱ ወደ አዲስ አበባ ከመመለሳቸዉ በፊት ካስትሮን አነጋገሩ። «ጓድ ፊደል ሲቀበሉን ጦርነቱን ገጥመን፤ የተሸነፍን ይመስል በጣም በማዘንና በመጨነቅ ሊያፅናኑን ሞከሩ።» ይላሉ መንግሥቱ።ቀጠሉ። «ሶማሌዎች ዉጊያዉን ሊያሸንፉ ይችላሉ። በጦርነቱ ግን አሸናፊዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነዉ። በማለት እኛ መልሰን አፅናናቸዉ።»
ካስትሮ መለሱ፤- «ልክ ናቸሁ በጦርነት አሸናፊዉ አብዮት ነዉ። እኛ የጠላነዉ፤ ላጭር ጊዜም ቢሆን መሸነፋችንን በመገመት ነዉ።» «መሸነፋችንን።» ይሕቺ ቃል ጦርነቱ የኢትዮጵያ-የሶማሊያ ብቻ ሳይሆን የኩባና የሶማሊያ፤የደቡብ የመንና የሶማሊያ መሆኑንም አረጋገጠች።ይሕቺ ቃል ጦርነቱ የሶቭየት ሕብረትና የዩናይትድ ስቴትስ፤ የሶሻሊስቱና የካፒታሊስቱ ዓለም ጦርነት፤ የቀዝቃዛዉ ጦርነት አካል መሆኑን አረጋገጠች።
ኩባና የመን ወታደሮቻቸዉን ወደ ኢትዮጵያ ሲያዘምቱ ሶቬት ሕብረት ዘመናይ ጦር መሳሪያዋን አሰብ ላይ፤ በኮሎኔል መንግሥቱ ሐይለማርያም ቋንቋ «ዘረገፈችዉ።» የኢትዮጵያና የኩባ፤የኢትዮጵያና የየመን ወዳጅነት በደም ተሳሰረ።በጦርነቱ አባቶቻቸዉን ያጡት ኢትዮጵያዉን ለትምሕርት ወደ ኩባ ሲሄዱ ደግሞ በደም የተለሰነዉ ወዳጅነት ወደ ሁለተኛዉ ትዉልድ ተሻጋገረ።
ኢንጂነር ደረጀ።
አቶ ዝናዉ ተስማ።ኩባ ከኢትዮጵያ ጦር ጎን ሆኖ የሶማሊያን ጦር እንዲወጋ ያዘመተችዉ ሠራዊት 15 ሺሕ ይገመታል።ኩባ ይሕን ያሕል ጦር ያዘመተችበትን ምክንያት ለማወቅ አንድ የኢጣሊያዊ ጋዜጠኛ ካስትሮን ባንድ ወቅት ጠየቃቸዉ። ካስትሮ መለሱ፤-ጋዜጠኛ ተፈሪ ይንገረን።
ኩባዎች ኢትዮጵያን ከጥቃት ለመከላከል ሲዘምቱ የ1970ዎቹ የመጀመሪያዉ አይደለም።ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት ቢያንስ አንድ ኩባዊ የጦር መኮንን ከኢትዮጵያዉያን ጎን ሆኖ ለኢትዮጵ ነፃነት ተዋግቷል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምሕር አቶ ዮናስ አሽኔ የዚያን ኩባዊ ተጋድሎ የኢትዮጵያና የኩባ ግንኙነት መጀመሪያ ይሉታል።
ዶክተር ተስፋዬ ተርጓሚ ናቸዉ። ኩባ ከተማሩ ኢትዮጵያዉን ወጣቶች አንዱ መሆን አለመሆናቸዉን ላሁኑ አናዉቅም። የምናዉቀዉ ኩባ ዉስጥ ያደጉና የተማሩ በሺ የሚቆጠሩ ሐኪሞች፤ መሐንዲሶች፤ ጋዜጠኞች፤ የፋብሪካ ቴክኒሻኖች ሌላም ኢትዮጵያዉያን ባለሙያዎች መኖራቸዉን ነዉ ።የዚሕ ሁሉ መሠረት አንድም ካስትሮ፤ ሁለትም መንግሥቱ ናቸዉ።ሁለተኛዉ ተሰደዋል።የመጀመሪያዉ፤-
«ዉድ ኩባዉያን፤ ለዜጎቻችን፤አሜሪካና በመላዉ ዓለም ለሚገኙ ወዳጆቻን፤ በጥልቅ ሐዘን መናገር አለብኝ። ዛሬ ሕዳር 25 2016 ከምሽቱ 10 ሰዓት፤ከ29 ደቂቃ ላይ የኩባ አብዮት መሪ ፊደል ካስትሮ ሩዝ አረፉ።»ታናሽ ወድማቸዉና ያሁኑ ያሁኑ የኩባ መሪ ራዑል ካስትሮ።
ዩናይትድ ስቴትስ ከስድስት መቶ ጊዜ በላይ የቃጣችባቸዉን የግድያ ሙከራ አምልጠዋል። የፈጣሪዉን ግን በርግጥ ማምለጥ አይችሉም። አልቻሉምም። አሜሪካ-ኩባዉያን ፈነጠዙ። ኩባዉያን ደነገጡ። በመላዉ ዓለም የሚገኙ የኩባና የካስትሮ ወዳጆች አዘኑ።እንደ ፖለቲከኛ አንደበተ ርትዕ፤ እንደ ሕግ ባለሙያ ለፍትሕ ተቆርቋሪ፤ እንደ አብዮታዊ ቆራጥ፤ እንደ ሰዉ ለደሐ አዛኝ ነበሩ።አንድ ግን ታላቅ የታሪክ ምዕራፍ ተዘጋ። አዲዮስ አሚጎስ።
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ
በSHEGER FM 102.1 RADIO ፌስቡክ ገጽ ላይ የኔነህ ከበደ ይህንን ብሏል።
ታሪክን የኋሊት
(የነ ፊደል ካስትሮ አብዮት)
በላቲን አሜሪካ የአብዮቶች ታሪክ የኩባ አብዮት እጅግ ስኬታማው ተደርጐ ይታያል፡፡
በፊደል ካስትሮ ሩዝና በጓደኞቻቸው በተመራው የትጥቅ አመፅ፣ የዚያን ዘመን የኩባ ወታደራዊ አምባገነን መሪ፣ የፉላጂንሲዮ ባቲስታ አገዛዝ የተወገደው፣ የዛሬ 57 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡
ፊደል ካስትሮ ከባቲስታ ጨቋኝና ፈላጭ ቆራጭ ወታደራዊ መንግስት ጋር ጠብ ውስጥ የገቡት ገና ከወጣትነታቸው አንስቶ ነው፡፡
ከዋናው አብዮት ቀደም ብሎ ካስትሮና ጓደኞቻቸው 160 ሆነው በሳንቲያጐ የሚገኘውን የሞንካንዳ ጦር ሠፈር አጠቁ፡፡
ጥቃታቸው የጀብድ ያህል ነበር፡፡
የሞቱ ሞቱ፡፡ የተረፉትም እየተያዙ በየእስር ቤቱ ተወረወሩ፡፡ ኋላ፣ የባቲስታ መንግስት የፖለቲካ እስራኞችን እንዲፈታ ግፊት በረታበት፡፡ የሞንካንዳ አጥቂዎችም ተለቀቁ፡፡
ከተለቀቁት መካከል ፊደልና ወንድማቸው ራውል ካስትሮ ነበሩበት፡፡
ከእስር ከተለቀቁ በኋላ እነ ካስትሮ ወደ ሜክሲኮ ተሠደዱ፡፡
በሚክሲኮ ከግራ ክንፈኛው ተዋጊ ከአርጀንቲናዊው ቼ ጉቬራ ጋር ተዋወቁ፡፡
ወዳጆችና ባልንጀሮች ሆኑ፡፡
በሜክሲኮ፣ የሃምሌ 26ቱ ንቅናቄ የተሠኘውን የጦርና የፖለቲካ ድርጅት መሠረቱ፡፡
የሽምቅ ውጊያ ስልጠና ከወሰዱና ከተሠናዱ በኋላ፣ ግራንማ በተሠኘችዋ ጀልባ፣ 82 ሆነው ወደ ኩባ ቀዘፉ፡፡
በኩባ የባሕር ዳርቻ መጥፎ እጣ ገጠማቸው፡፡ የባቲስታ ወታደሮች በተኩስ ተቀበሏቸው፡፡ ብዙዎቹ ተገደሉ፡፡
የተረፉትም በደመነፍስ ወደ ሴራ ሜይስትራ ተራራ በተዘበራረቀ ሁኔታ ሸሹ፡፡
መልሰው መገናኘት የቻሉት ከብዙ ጥረት በኋላ ነበር፡፡
ወጣቶቹ ፋኖዎች በሴራ ሜይስትራ ተራራ አቅም አደራጁ፡፡
በሽምቅም፤ በፊትም ለፊትም፣ በባቲስታ ወታደሮች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን አበረቱ፡፡
ሊያጠፋቸው ይዘምትባቸው የነበረውን የባቲስታ ግዙፍ ሠራዊት በመቋቋም በአነስተኛ የሰው ኃይል አስደናቂ የሚባሉ ድሎችን ጨበጡ፡፡
የባቲስታ ሠራዊት የሞራል ድቀት አጋጠመው፡፡ ተፈታ፡፡
ከያቅጣጫው የተከፈተበትን ማጥቃት መቋቋም ተሳነው፡፡
ካስትሮ ባቲስታን በአምባገነንነት ከስሰው በትጥቅ አመፅ ከስልጣን አሸቀነጠሯቸው፡፡
በመንግስት ፍንቀላ ስልጣን ጨብጠው፣ ደሴቲቱን በብረት መዳፋቸው ቀጥቅጠው የገዙት ወታደራዊ መሪ ባቲስታ ከነጭፍሮቻቸው ወደ ዶሚኒካን ሪፖብሊክ ሸሹ፡፡
ኩባ ከአብዮቱ መባቻ ጊዜ አነስቶ እስከ ቅርብ ጊዜ ድርስ በፊደል ካስትሮ፤ ከ9 ዓመታት ወዲህም ደግሞ በወንድማቸው ራውል ካስትሮ መሪነት ስር ትመራለች፡፡
ኩባ ከቅርብ ጐረቤቷ አሜሪካ ጋር በፍልስፍናና በአስተዳደር ዘይቤ ልዩነት እየተሟገተችና የጐሪጥ እየተያየች ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ አስቆጥራለች፡፡
በቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን፣ ሁለቱን ታላላቅ ኃያላን፣ አሜሪካንና የቀድሞዋን ሶቪየት ህብረትን የኒኩሊየር የጦር መሳሪያ ለማታኮስ ያቃረበችበት አጋጣሚ፣ ዘግናኝ ትውስታ ሆኖ ይጠቀሳል፡፡
አሜሪካና ኩባ ከ50 ዓመታት በላይ በጠላትነት ስሜት ሻክሮ የቆውን ግንኙነት ለማደስ ዳግም መቀራረብ ከጀመሩ ከዓመት በላይ ሆኗቸዋል፡፡
እንደ ንጉስ የኖሩት ተራማጁ ፊደል ካስትሮ
በሚል ርዕስ አዲስ አድማስ ይህንን አስነብቧል:-
ታጋዮች የህዝብ ጫማ ናቸው፤ ታጋዮች የግል ጥቅምና ምቾታቸውን በሰፊው ህዝብ ጥቅምና ምቾት የቀየሩ የህዝብ መድህኖች ናቸው፤ ታጋዮች ለህዝባቸው ምቾትና ድሎት ሲሉ ከፍተኛ መስዋዕትነት የሚከፍሉ የህዝብ ቤዛዎች ናቸው፡፡…
እነዚህን የመሳሰሉ የአብዮታውያን የፕሮፓጋንዳ ርግረጋዎች የኢትዮጵያ አብዮት በግብታዊነት ፈነዳ ከተባለበት ከየካቲት 1966 ዓ.ም ጀምሮ አብዮታዊና ተራማጅ ነን ከሚሉ ሃይሎች ዘንድ ስንሰማው የኖርነውና ዛሬም እየሰማነው ያለነው ጉዳይ ስለሆነ ምንም አስደናቂ ነገር የለውም፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ይህ የአብዮታውያኑ መሀላ፣ የታጋዮቹን ሰውነትና የሰውን ልጅ ባህርይ በወጉ ከግምት ውስጥ ያስገባ አይደለም፡፡ እናም ነገሩ አብዛኛውን ጊዜ የሚባለውን ያህል ትክክል ወይም እውነት ሆኖ አይገኝም፡፡ ይህን ለማረጋገጥ ደግሞ ማስረጃ ፍለጋ የአለም አብዮተኞችን የታሪክ መዝገብ ማገላበጥ ጨርሶ አያስፈልገንም፡፡ የሀገራችን አብዮተኞች ታሪክ ከበቂ በላይ ነው፡፡
የጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስት መሪዎች በስልጣን ላይ በቆዩበት አስራ ሰባት አመታት ሰፊውን የኢትዮጵያ ህዝብ ከአስከፊ ድህነት ለማላቀቅ ሲሉ አንድም ቀን እንኳ ሳይደላቸውና ሳይስቁ ከፍተኛ መስዋዕትነት ይከፍሉ እንደነበር በተደጋጋሚ ይናገሩ ነበር፡፡ እነዚህ አብዮታውያን ወታደራዊ መሪዎች በተግባር ያደረጉት ግን ካለፈው እጅግ የከፋ ድህነትን ለሰፊው ህዝብ እኩል በማካፈል፣ ራሳቸውንና የራሳቸውን ወገን ከድህነት ማላቀቅ ነው፡፡
“አብዮታዊውን” ወታደራዊ መንግስት ለአስራ ሰባት አመታት በዘለቀ የትጥቅ ትግል የዛሬ 23 አመት አሸንፎ ስልጣን የተቆጣጠረው ኢህአዴግ፣ ተራራ ያንቀጠቀጡት ታጋዮቹ በግል ጥቅምና ምቾት የማይንበረከኩ፣ የህዝብ ጥቅም፣ ምቾትና ብልጽግና የመጀመሪያም የመጨረሻም የትግል ግባቸው እንደሆነና ለዚህም ግብ መሳካት የህይወት መስዋዕትነት እንደከፈሉ በተደጋጋሚ ሊያስረዳን ሞክሯል፡፡
ጥረቱ ያላቋረጠና ከባድ መሆኑ ሲታይ ደግሞ ኢህአዴግም እንደሌሎቹ አብዮታዊ ድርጅቶች ሁሉ የታጋዮቹን ሰውነት ጨርሶ የረሳ አስመስሎት ነበር፡፡ የማታ ማታ በተግባር የታየው ግን በቃል ከተወራው በእጅጉ የተለየ ነበር፡፡ የራሳቸውን ጥቅምና ብልጽግና ከምንም ሳይቆጥሩ ለህዝባቸው ጥቅም፣ ምቾትና ብልጽግና እውን መሆን የህይወት መስዋዕትነት ለመክፈል ለአፍታም እንኳ አያመነቱም ተብለው ብዙ እጅግ ብዙ የተነገረላቸው “አብዮታውያን” ታጋዮች “የከተማ ስኳር ፈታቸው፤ የድል ማግስት ህይወት ጽኑ የትግል መንፈስና ስሜታቸውን ሰልቦ ከማይወጣው የትግል አላማቸው አሳታቸው” ተብሎ በራሳቸው ድርጅት አንደበት ተነገረባቸው፡፡
ይህንን በይፋ የተናገረው ድርጅታቸው ኢህአዴግ፤ በዚህ ብቻ አላበቃም፡፡ በማግስቱ እንደ ከፍተኛ የድርጀቱና የሀገር መሪነታቸው ለሌሎች አርአያ መሆን ሲገባቸው፣ በከተማው ስኳር ተታለው ከህዝብ ጥቅምና ብልጽግና ይልቅ ለራሳቸው ጥቅም፣ ምቾትና ብልጽግና ሌት ተቀን ሲጥሩና ህገወጥ ድርጊቶችን ሲፈጽሙ አግኝቻቸዋለሁ ያላቸውን ከፍተኛ የኢህአዴግና የመንግስት ባለስልጣናት እንደ እጅ ስራቸው መጠን ህግ ያውጣቸው ብሎ ዘብጥያ አወረዳቸው፡፡
የአብዮታዊቷ ኩባ ታሪክም ከኢትዮጵያም ሆነ ከሌሎቹ አብዮተኛ ሀገራት የተለየ አይደለም፡፡ እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በ1959 ዓ.ም የባቲስታን መንግስት በትጥቅ ትግል አስወግደው ስልጣን ስለተቆጣጠሩት የኩባ አብዮታዊ ታጋዮች ያልተባለና፣ ያልተነገረ ገድል አለ ለማለት ያስቸግራል፡፡ በተለይ ደግሞ የኩባ አብዮት ግንባር ቀደም መሪና የኩባ ጭቁን ህዝብ አባት ስለሚባሉት ስለ ጓድ ፊደል ካስትሮ በቃል ያልተነገረ፣ በጽሑፍ ያልተፃፈ፣ በፊልምም ያልቀረበ… እራስን ለህዝብ ጥቅም አሳልፎ ስለመስጠት ገድል.. ለሞት መድሃኒት እንኳ ፈልጐ ማግኘት አይቻልም፡፡
ራሳቸውን ለሰፊው ጭቁን የኩባ ህዝብ ፍፁም አሳልፈው የሰጡና ከወታደር ካኪ ሌላ የረባ ልብስ እንኳ የላቸውም እየተባለ ነጋ ጠባ የሚወደሱት ጓድ ፊደል ካስትሮ ግን እንደሚወራላቸው አይነት ሰው ሳይሆኑ ይልቁንም ልክ እንደ አንድ ታላቅ ንጉስ እጅግ በተንደላቀቀ ሁኔታ በምቾት የኖሩ ሰው እንደሆኑ ከተለያዩ ወገኖች በሹክሹክታ ሲወራ ቢከርምም ማረጋገጥ ሳይቻል ቆይቶአል፡፡
ሁዋን ሮናልዶ ሳንቸዝ የተባለ የ65 አመት ጐልማሳ ኩባዊ ግን ይህንን የሚያረጋግጥ ማስረጃ በቅርቡ ይፋ አድርጓል፡፡ ከ1977 እስከ 1994 ዓ.ም የፕሬዚዳንት ካስትሮ የቅርብ አማካሪና ከታናሽ ወንድማቸው ከራውል ካስትሮ ቀጥሎ እጅግ ጥብቅ ሚስጥረኛቸው የነበረው ሁዋን ሮናልዶ ሳንቸዝ፣ በቅርቡ ባሳተመው መጽሐፍ፤ ፕሬዚዳንት ጓድ ፊደል ካስትሮ 20 ትላልቅ የቅንጦት መኖሪያ ቤቶች፣ የግል ደሴትና የመዝናኛ ጀልባ አሏቸው፡፡
የኩባው አብዮተኛ ጀግና ጓድ ፊደል ካስትሮ፤ በተጠቀሰው አመት ውስጥ በከፍተኛ ሚስጥር ይካሄድ በነበረ የእፅ ዝውውር ንግድ ውስጥ ተሳታፊ ነበሩ፡፡ ሀቫና ከተማ አቅራቢያ ባቋቋሙት የወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ ውስጥም እንደ አይ አር ኤ የመሳሰሉ ታጣቂ የሽብር ቡድኖችን ያሰለጥኑ ነበር፡፡
Castro!!! The unforgettable person. Who had given his everything for his people!! Who lived simple life with his people!! Castro!! The practical person!! Who had enough knowledge in military science. Never bitten!! Undefeated. Who had enormous knowledge I remembered Castro had a wonderful English language talent!!! But never in public showed! Castro was the East ideology mechanic. He had no a knowledge of “serunder.” in his vocabularies. Castro a man of multi knowledge!! Castro had everything in his mind.