• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጠ/ሚ/ር ዐቢይ የህወሃት ወንበዴዎችን የሽምግልና ልመና ውቅድ አደረጉ

November 10, 2020 02:06 am by Editor 1 Comment

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የቀረበውን የሽምግልና ጥሪ ሳይቀበሉ ቀሩ።

የቀጣናዊው ተቋም መሪ የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ በ4 የተለያዩ ጊዜያት ስልክ በመደወል የኢትዮጵያ አቻቸውን ለማግባባት ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።

ሱዳን ትሪቢውን የሃምዶክን ቢሮ አጣቅሶ የዘገበውን ሂቃያት ጋዜጣን ዋቢ አድርጎ በድረ ገጹ እንዳሰፈረው ዘገባ ከሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጉዳዩ ዓለም አቀፋዊ መልክ ሊይዝ የማይገባው የሃገር ውስጥ ጉዳይ ነው ብለዋል።

ሃምዶክ ባለፈው ዓመት የኢጋድ ሊቀመንበር ሆነው ዐቢይ አህመድን መተካታቸው ይታወሳል።

“የህወሀት ጁንታ ቡድን ትላንት የቀረቡለትን የድርድር እና የውይይት ዕድሎች ሁሉ አምክኖ ግብአተ መሬቱ ሊፈጸም ሲቃረብ የአደራዳሪ ያለ ብሎ መጮህ ጀምሯል” ሲል መግለጫ ያወጣው ብልጽግና ፓርቲ “አሁን ሰዓቱ የድርድር ሳይሆን የፍርድ ሆኗል” ብሏል።

“ትዕግስት ሊቀይረው ያልቻለው ጁንታ” ያለውን ህወሓትን “በህግ አግባብ ተጠያቂ ማድረግ ግዴታ የሆነበት ሰዓት ላይ” እንደደረሰም ነው የገለጸው።

“የተጀመረው ጉዞ ጦርነት ሳይሆን የህግ ማስከበር ስርዓት ነው” ያለም ሲሆን “በአጭር ጊዜ ወንጀለኞችን ወደ ፍርድ በማቅረብ” እንደሚጠናቀቅም አስታውቋል።

ብልጽግና ህወሓት ድርድን እናስቀድም የማለቱ ዋና ዓላማ “ሰላምን ማውረድ ሳይሆን በድርድር ምክንያት ጊዜን መግዛት ነው” ሲል ትናንት በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ማስታወቁ ይታወሳል።

“ኢትዮጵያ ወደ ትርምስ ትገባለች የሚለው ስጋት የሃገሪቷን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት ካለመረዳት የመነጨ ነው” ሲሉ በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ “አሁን እየተካሄደ ያለው ህግ የማስከበር ስራ ሰላምንና መረጋጋትን በማስፈን ወንጀለኞችን ለህግ ለማቅረብ ያለመ ነው ይህም በአጭር ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል” ሲሉ መልዕክት ማስፈራቸውም አይዘነጋም። (አል-አይን)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Left Column, News Tagged With: operation dismantle tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    November 10, 2020 09:17 am at 9:17 am

    ለዘመናት ወያኔ ከሃዲ ነው ስንል እንደ ጊዜው ሰዎች በዘርና በቋንቋ እይታ ተገፍተን አልነበረም። ከበረሃ እስከ ከተማ የፈጸሙት የዘር ማጥፋት ዘመቻና የዘረፋ ሰንሰለት በደል የጀርመኑ ኒዚ ካደረሰው ግፍ ይልቃል። ግን የጥቁርን መከራ ሌላው ዓለም ግድ አይሰጠውምና ኡኡታ ያሰማ የለም። አሁን ወያኔ በሃገሪቱ ጦር ላይ በተኙበት የከፈተው ጦርነት በድል ካልተጠናቀቀ ወያኔ ሰላምንና ሽንፈትን ተቀብሎ አብሮ በምድሪቱ በሰላም ይኖራል ብሎ ማሰብ ከጊንጥ ጋር ተኝቶ አልነደፍም እንደ ማለት ነው። ሩቅ ሳንሄድ የሃገር ሽማግሌዎች ተው ታረቁ ይህ ነገር ጥሩ አይደለም ሲሏቸው የመጣችሁት ዘግይታችሁ ነው ነበር ያሉት። ያ ማለት ለጦርነት ተዘጋጅተናል ማለታቸው ነበር። የነቃ ግን አለነበረም! አንዴ ሻቢያ ሊወርህ ነው፤ ሌላ ጊዜ አብይ ሊያጠቃህ ነው እያሉ የትግራይን ህዝብ የሚያምታቱት እነዚህ ደም መጣጮች አሁን በአለም ዙሪያ በዘረጓቸው የስለላ መረቦችና የዲፕሎማቲክ የክፍያ ደጋፊዎች በመረዳት ጦርነቱ የኢትዮጵያ መንግስት እንደ ጀመረው፤ የትግራይ ህዝብ በአየርና በምድር እየተደበደበ እንደሆነ በየድህረ ገጻቸውና በበሉበት ዙሪያ በሚጮሁ የፓለቲካ ውሾች ነገርን ማተራመስ ጀምረዋል። ከዚህም ቀዳሚው ደም አፍሳሹና ዘረኛው የአለም የጤና ተቋም ዳሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም ስልጣኑን ተጠቅሞ ጉድ ጉድ እያለ ነው። ጽፈናል ለመንግስታት፤ ለተቋማት እንዲሁም ለራሱ ለመ/ቤቱ ይህ ሰው ፓለቲካን ከጤና በመለየት በጊዜው ኮሮና ቫይረስ ላይ እንዲያተኩር እንጂ ከማዶ የወያኔ ተወካይ በመሆን ነገርን እንዳያማታ። ሌሎችም አሉ ሰላማዊ ሰልፍ የሚወጡ፤ በማያውቁት ነገርና ባልገባቸው ላይ ጡርንባ የሚነፉ። ግን እነዚህ በወያኔ የስውር አሰራር እየተገፉ ለራሳቸው የስለላና የሃብት ዝውውር ስራ ተወካይ ለመሆን በየአለማቱ የተበተኑ አፍቃሪ ወያኔዎች እንጂ የትግራይን ህዝብን አወክሉም። የሚሞተው ቆሎ ቆልታ፤ ጠላ ጠምቃ ያሳደገችው ያ ደሃ ልጅ ነው። እነርሱ በውጭ ሃገር በዶላር ነው የሚገባበዙት። እኔ የትግራይ ልዪ ሃይል ብሆን ወይ ገድዬ እሞታለሁ ወይም እንደምንም በማለት አምልጬ እጄን እሰጣለሁ። ይህ ጦርነት እብደት ነው። ማንም ሊሞትለት የማይገባ ወንድም ወንድሙን የሚገድልበት። ይህን በሰው እይታ አይቶ ወያኔ እጅ እንዲሰጥና ከስልጣኑ ወረዶ የትግራይ ህዝብ የራሱን ሰው መርጦ የሚተዳደርበት ጊዜ መቼ ይሆን? ነው ሰርክ ዓለም በውጊያ ሲሞትና ሲገል ይኖራል?
    ዶ/ር አብይ የማንንም ጫና ሳይሰማ እነዚህን የሙታን ጥርቅሞች ለቅሞ ለፍርድ እስካላቀረበ ድረስ ምንጊዜ ለትግራይ ህዝብና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ነቀርሳ መሆናቸው አይቀሬ ነው። አብሮ የተሰለፈ ወታደር ወንድሙን ከውስጥና ከውጭ የሚያጠቃ ይህ ሃይል ጋር እንዴት ነው እርቅ የሚደረገው? ማን ማንን ያምናልና! አሁን መንግስት ደብቆ የያዘው ሚስጢር በዚህ ጥቃት እልፎች እንደሞቱ አለመናገሩ ነው። የተሰራውን ግፍ ለህዝባችን ምንም የፓለቲካ ፕሮፓጋንዳ ሳይጨመርበት ማስታወቅ ተገቢ ነው። ዝም ብሎ ይህን አሸንፈኩ ያን ደበደብኩ ማለቱ ብቻ ጠቃሚነት የለውም። ጦሩ እንዴት እንደተጠቃ፤ ከውስጥ እነማን እንዳጠቁት፤ ከውጭ የተሰነዘረው ጥቃት የት የትና በስንት ሰአት ተጀምሮ በስንት ሰአት እንዳለቀ ከእነርሱም በኩል የቆሰለ፤ የሞተ፤ በይፋ መነገር አለበት። ሃገር አተራማሹ ወያኔና የወያኔ ወታደራዊ መኮንኖች ዋጋ መክፈል አለባቸው። ቤታቸው፤ ንብረታቸው በመቀሌም ሆነ በሌሎች የሃገሪቱ ክፍል መወረስ አለበት። የሃገሪቱን የመከላከያ ሰራዊት ያጠቃ ሃይል በምድሪቱ ሊኖርባት አይገባም። ከሃዲው ወያኔ ግን እውነተኛ ባህሪውን አሳይቶናል። የሚገርመው ግን የሰሜኑ ጦር ምንም አይነት የሰውር የስለላ መረብ እንዳልነበረው ያሳያል። እንዴት እንደሚጠቃ ይጠፋዋል የተሾመለትን መሪ አንቀበልም በማለት እንዲመለስ ሲያረጉት? ከሃዲ ወያኔ ሃገር የሸጠ፤ ሰው እንደ ከብት ያረደ፤ ጉድጓድ ቆፍሮ ሰው ቀብሮ በጢስ የፈጀ ነው። የድሮ የወያኔ ታጋዮች የሚናገሩትን መስማት ሰው መሆን ያስጠላል። ግብረ ሶዶም በእስር ባሉ ወንድና ሴቶች ላይ የሚፈጽም ይህ በድን ቡድን ስብዕና ኑሮት በሰላም ይኖራል ብሎ ማመን ተንጋሎ መትፋት ነው። ዶ/ር አብይ በምንም አይነት መንገድ ጦርነቱ የፈጀ ይፍጅ በድል ካላጠናቀቀው የራሱ መንግስትና የሃገሪቱ የመኖር እድል ፈንታ ጨለማ እንደሚሆን ከወዲሁ መተንበይ ይቻላል። ተጀምሯል ወያኔን አፍር ማስገባት ተገቢ ነው። የትግራይ ህዝብም እፎይ ይበል! በቃኝ።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule