በፌደራል እና በክልል የፀጥታ ኃይሎች ጠንካራ እርምጃ ተወስዶበት ከተበታተነ በኋላ ንፁሃን ላይ ጥቃት እየፈፀመ ያለውን አሸባሪው ሸኔን ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እየተሰራ ነው ሲል የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።
ጠንካራ የህዝብ አደረጃጀት በመፍጠር በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በተሰራው ኦፕሬሽን የሽብር ቡድኑ ከበፊት ቁመናው እና ይዞታው መዳከሙን የቢሮው ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ጠቅሰዋል።
ጠንካራ እርምጃ ተወስዶበት የተበታተነው አሸባሪው ቡድን በተለያዩ ቦታዎች ንፁሃንን የማጥቃት የተለመደ የጥፋት ድርጊቱን እየፈፀመ ነው ብለዋል።
ይህን የጥፋት ድርጊቱን ለማስቆም በፌደራል እና በክልል የፀጥታ ኃይሎች በተቀናጀ መልኩ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሏል ነው ያሉት።
በመንግሥት መዋቅር ላይ ሆነው ከአሸባሪው ሸኔ ጋር በማበር በህዝብ እና በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ላይ ጥቃት እንዲደርስ የሚያደርጉ አካላትም በሕግ ተጠያቂ እየሆኑ ነው ብለዋል። (ኢብኮ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply