ዶ/ር ደስታው አንዳርጌ ይህንን ጽፈዋል፣ ፊደል ካስትሮ፦ የኢትዮጵያና አፍሪካ የቁርጥ ቀን ወዳጅ፤ የክፍለዘመኑ ዳዊት የ፳ኛው ክ/ዘ ካፈራቸው ታላላቅ መሪወች ውስጥ ሁልጊዜም ፍትህና ነጻነት ከሚሹት ጋር በመቆም፤ ሁሌም በትክክለኛው የታሪክ ገጽ በመገኘት ፊደል ካስትሮን የሚስተካከል ማን አለ? ከኒካራጓና ቺሌ እስከ ቬትናም ከፍልስጤም እስከ አልጀሪያ ብሎም ደቡባዊ አፍሪካ ነጻነት ለናፈቃቸው ሁሉ የካስትሮን ያህል ታላቅ ድጋፍ ያደረገ ሌላ መሪ ማንም የለም። በተለይ የአፍሪካ አገራት ከኢምፔሪያሊስቶች ጋር ባደረጉት ትንቅንቅ የካስትሮና የኪውባ ቁርጠኝነት ከጉዳዩ ባለቤቶች ያልተለየ ነበር። ኪውባ ለአንጎላ ያደረገችው እጂግ መጠነሰፊና ከአስር አመት በላይ የዘለቀ ድጋፍ ለዚህ አይነተኛ ማሳያ ነው። ካስትሮ አንጎላ ከፖርቹጋል ቅኝ ነጻ ለመውጣት ካደረገችው ተጋድሎ ጀመሮ በአሜሪካ ድጋፍ … [Read more...] about ስለ ካስትሮ ምን ተባለ?
Opinions
የኔ ሃሳብ
ዲያስጶራዎቻችን
ዲያስፖራ (ዲያስጶራ) የሚለው ቃል ትርጉም ‹‹ብትን /የተበተነ›› ወይም በአጪር አነጋገር ከትውልድ አገሩ ውጭ ተበታትኖ ያለ ሕዝብ ማለት ነው፡፡ በዚህ ትርጓሜ ከኢትዮጵያ መቶ ሜትርም ይሁን አንድ ሺሕ ማይል ይራቅ ከድንበር ማዶ ያለ ሁሉ ዲያስፖራ ነው፡፡ የምንገኝበት አገር፣ የትምህርት ደረጃችን፣ የወጣንበት መንገድ፣ ሃይማኖታችን ወይም ብሔራችን ዲያስፖራ ከመሆን (ከመበትን) አያድነንም፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው በአውሮፕላንም ይሁን በመርከብ፣ ጥገኝነት ጠይቆም ይሁን አግብቶ፣ ፊደል የቆጠረም ይሁን ፕሮፌሰር የሆነ፣ እስላምም ይሁን ክርስቲያን፣ ዐማራም ይሁን ኦሮሞ ወይም ጉራጌ ወይም ሌላ ከድንበር ወጥተን ወደ ሌላ ሉዓላዊ አገር ከገባን ተበትነናል ማለት ነው፡፡ የምንገኝበት አገርም መመዘኛ አይደለም፡፡ አፍሪካ፣ አውሮፓ፣ አሜሪካ፣ ኤዥያ ወይም ኦሽኒያ መሆናችን ምንም ልዩነት አያመጣም፡፡ … [Read more...] about ዲያስጶራዎቻችን
“የኦሮሞ ህዝብ ሙስሊም ነው…” “BBN (አቶ አብዲረሂም አህመድ)
በኦሮሞ ስም እየተደረጉ ያሉትን አብዛኛዎቹን ስብሰባዎች ላስተዋለ ሰው፣ የኦሮሞ ጎሳ ብቻ ሳይሆን በአመዛኙ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ስብስብ እየመሰለም (“ሆኗል” አለማለታችን ይያዝልን) ሄዷል። አቶ ጃዋር ሙስሊም ከመሆኑ እና ራሱን የኦሮሞ የፖለቲካ ተወካይ/ተጠሪ አድርጎ በየመድረኩ ብቅ ካለበት ጊዜ ጀምሮ፤ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የኦሮሞ ተውላጅ ልሂቃን፣ አቶ ጃዋርን “በሜጫ አንገት የመቁረጥ” ፉከራው ጋር አዝለው፣ አንድም ጊዜ በአደባባይ ይቅርታ እንዲጠይቅ ማድረግ ሳይችሉ እና እነሱም ሳያወግዙ፣ እስካሁን ድረስ ተሸክመው የመዝለቃቸውም ነገር እኛ በ“ኢትዮጵያ ሴኩላር ሰብዓዊያን” ስር የተሰባሰብነውን ግለሰቦች እጅግ አሳዝኖናል፣ አሳስቦናልም። እሱ ሲገርመን አሁን ደግሞ በቅርቡ BBN በሚባል ስም የሚታወቀው፣ በጸረ-ህወሃት የፖለቲካ አቋሙ እና በእስልምና ሃይማኖት አራማጅነቱ … [Read more...] about “የኦሮሞ ህዝብ ሙስሊም ነው…” “BBN (አቶ አብዲረሂም አህመድ)
የኦሮሞ ብሔረ-ሰብ ቁጥር
መግቢያ ያለፉትን 40 ዓመታት ፖለቲካችንን ለመረመረ አገርን በሚመለከት የሚሰነዘሩት አስተያየቶች ወይም የሚሰጡት ትንተናዎች ሁሉ ሳንይሳዊ ይዘት ይኑራቸው አይኑራቸው የሚጠይቅ የለም። በተለይም ፖለቲካ ፍልስፍናዊ መሰረት ያለው ታላቅ ፅንሰ-ሃሳብ መሆኑ ግንዛቤ በሌለበት አገርና፣ ማንኛውም ህብረተሰብንና የአገርን አጠቃላይ ሁኔታ በሚመለከት ረገድ የግዴታ ሳይንሳዊ ትንተና መስጠት አስፈላጊ መሆኑ ቀርቶ ስሜት ዋናው መመሪያ በሆነበት አገር የሚሰነዘሩ አስተያየቶች ትክክል መሆናቸውንና አለመሆናቸውን ቁጭ ብሎ በሰከነ መንፈስ ለመመርመር የሚቃጣ ሰው በፍጹም የለም። እንደሚታወቀው በተለይም በአብዮቱ ወቅት ሳይንስና ፍልስፍና መመሪያ መሆናቸው ቀርቶ ስሜት የፖለቲካውን መድረክ በመያዙ እንደተከታተልነው ለብዙ መቶ ሺህ ህዝብ መሞትና ለአገር ውድመት የራሱን አስተዋፅዖ አበርክቶ አልፏል። ዛሬ … [Read more...] about የኦሮሞ ብሔረ-ሰብ ቁጥር
የሽግግር ሃሳብ
". . . ገብረሕይዎት በመንግሥት እና የህዝብ አስተዳደር መፅሃፉ መቅድም ላይ እንዲህ ይላል፤ «ሕዝቦችን ሁሉ የሚፈጥር አንድ አምላክ ነው። ይህም አምላክ የምንለው የሕዝቦች ፈጣሪ ሕዝቦችን ሁሉ ትክክል አንድ አድርጎ ፈጥሮ ላኗኗራቸውና ለልማታቸው የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሁሉ ከሙሉ ፈቃድና ስልጣን ጋር በእጃቸው ሰጥቷቸዋል። ስለዚህ ማናቸውም ህዝብ ቢለማም ቢጠፋም በገዛ እጁ ነው። ሕዝብ የሚጠፋበት አንዳንድ ምክንያት ቢያገኝ ያውም ምክንያት በአንዳንድ ሰው ቢመካኝ ትክክል አይደለም። የልማትን መንገድ ለማግኘት የሚጥር ሕዝብ ቢገኝ በአንዳንድ ክፉ ሰው ምክንያት ሊጠፋ አይችልም። እንዲሁም ደግሞ የልማትን መንገድ ለማግኘት የማይጣጣር ሕዝብ በአንዳንድ ደህና ሰው ኃይል ልማት ሊያገኝ አይችልም።» ይህ የገብረሕይዎት ተጠይቃዊ ሀሳብ ኢትዮጵያ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ለመመርመር ሲጠቀመን … [Read more...] about የሽግግር ሃሳብ
የዐማራ ድምፅ ሬድዮን እንርዳ
በአሁኑ ዘመን በኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉ ነገር እያለው ሁሉንም ያጣ ዜጋ ዐማራው ነው ቢባል የተጋነነ ነው ሊባል አይችልም። በግልጽ እንደሚታወቀው፣ ዐማራው ቋንቋው አማርኛ ነው። ይህንን ቋንቋውን ከሌሎች የኢትዮጵያ ጎሣዎች ቋንቋዎች ጋር አጣጥሞ በማሳደግ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ መግባቢያ እንዲሆን አበርክቷል። ይሁን እንጂ፣ በአሁኑ ጊዜ የአማርኛ ቋንቋ ለዐማራው ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ተለይቶ መከበሪያው መሆኑ ቀርቶ መጠቂያው ሆኗል። በአማርኛ ቋንቋ የሚጻፉት፣ በሬድዮ እና በቴሌቪዥን የሚቀርቡት ዝግጅቶች በአብዛኛው ማለት ይቻላል፣ ዐማራው የሚወገዝባቸው፣ የሚዋረድባቸው እና የሚኮነንባቸው እየሆኑ ከመጡ ዓመታትን ተሻግረው ዘመናት ተቆጥረዋል። ስለሆነም ዐማራን እና አማርኛን በጠላትነት ፈርጀው የጥፋት ተግባራቸውን ለፈጸሙና ለሚፈጽሙ ኃይሎች አጸፋውን በመስጠት፣ የአማርኛ ቋንቋም ሆነ የዐማራ ነገድ … [Read more...] about የዐማራ ድምፅ ሬድዮን እንርዳ
በጅዳ ሽሜሲ በር ላይ ወድቃለች የተባለችው እህት ጉዳይ!
ከትናንት ጅዳ ውስጥ በጠና ታማ እሷና ልጇ አደጋ ላይ አሉ ስለተባ ለችው እህት እየተሰራጨ ያለው መረጃ ደርሶኛል። መረጃውን በዝርዝር ያገኘሁት ከሊያ ሾው ነበር፣ ታመመች የተባለችውን እህት በቪዲዮ የተደገፈ መረጃ እንደደረሰኝ ወደ ጅዳ ቆንስል ደውዬ ለማጣራት ሞክሬ ነበር! በጅዳ ቆንስላ መረጃ ለማግኘት ከባድ እየሆነ መጥቷ ል፣ አንዳንዶች ኃላፊዎች ከዚህ ቀደም በማቀርባቸው ተጨባጭ ሂሶች አኩርፈው መረጃ ላለመስጠት ስልካቸውን ይዘጉብኛል፣ አንዳንዶች ደግሞ መረጃም ሆነ ጥያቄ ለመመለስ ፈቃደኛ አይደሉም! እጅ አዙር በሆነ መንገድ የጅዳ ቆንስል መረጃው እንዳልደረሰው ተነግሮኛል! ይህች እህት በሽሜሲ ጊዜያዊ እስር ቤት በር ላይ ተጥለላች መባሉን ሰምቸ ወደ ቦታው የሚያጣራልኝ የስራ ባልደረባዬን ልኬም ነበር፣ ዛሬ ረፋድ ላይ በር ላይ ተዟዙሮ የወደቀ ሰው አለመኖሩን አረጋግጦልኛል! ይህን … [Read more...] about በጅዳ ሽሜሲ በር ላይ ወድቃለች የተባለችው እህት ጉዳይ!
የወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን “ነገዎ” ማንነት
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ በፓልቶክ ክፍል ቀርቦ የኦሮሞ ተወላጅ መሆኑን አስረግጦ ተናግሯል። ካፈርኩ አይመልሰኝ ነገር። አንድ ሰው ከመሬት ተነስቶ ከዚህ ዘር ነኝ የማለት የተጠበቀ ነው። የዘር ቆጠራን ያመጡት ራሳቸው ስልጣን ላይ ያሉት ዘረኞች ናቸው እንጂ እኛ አይደለንም። ዛሬ የራሳቸው ቃል እስረኛ የሆኑ ይመስላል። ጥያቄው ዘሩን በገዛ ፈቃዱ የመቀየር ጉዳይ አይደለም። ተቃውሞው ሹመቱ ላይም አይደለም። በዘር ያመጡት የስልጣን ኮታ ዘሩ ባልሆነ ግለሰብ ሲደለደል - ጉዳዩን ለሚያውቁት ንቀት እና ስድብ ይሆናል። ወርቅነህ የኦሮሞ የገዳ ሥርዓት በሚፈቅደው "ጉዲፈቻ" እና "ሞጋሳ" ባህል መሰረት ወደ ኦሮሞነት ተቀይሮ ከሆነ ግልጽ ይሁን። ካልሆነ ግን የእሱን ማንነት የሚገልጸው ዶክመንት ተመልክቶ ፍርድ መስጠቱ ይበጃል። ለስድስት ዓመታት በድህንነት ሲሰራ በርካታ ንጹሃን … [Read more...] about የወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን “ነገዎ” ማንነት
የኢትዮጵያን ወቅታዊ ችግርና የመፍትሄ አቅጣጫ በሚመለከት የተሰጠ መግለጫና የሰላም ጥሪ
የኢትዮጵያን ችግር የመፍትሄ መንገድ በሚመለከት "ኢትዮጵያን ለማዳን እንነጋገር" በሚል ርእስ ቀደም ሲል አንድ የሰላም ጥሪ ማቅረባችንን እናስታውሳለን። መልእክቱም ባጭሩ ይህች ታላቅ ሀገር የገጠማት ችግር ሊፈታ የሚችለው በመሪዎቿና በልዩ ልዩ የተቃውሞ ጎራ በተሰለፉ የራሷ ልጆች ብቻ መሆኑን፤ መፍቻ መንገዱም ውይይትና ንግግር መሆኑን፤ ጊዜውም አሁን መሆኑን የሚያመላክት ነበር። ለዚህም ሁሉም ወገኖች ቢያንስ በችግሩ ላይ ለመነጋገር መስማማት እንዳለባቸው በመጠቆም ለሰላማዊ ውይይት እንዲተባበሩና ሃሳባቸውን እንዲገልፁልን አሳስበንም ነበር። ጥሪውን የተመለከቱ ድርጅቶችና ግለሰቦች የሰጡንን በጎ ምላሽና ማበረታቻ በምስጋናና በአክብሮት ተቀብለናል፤ ደስ ብሎናልም። የሰላም ውይይት ወደሰላም በር የሚወስድ ጠቃሚ ስልት መሆኑን በማመን ድርጅታችን ላቀረበው የውይይት መድረክ ዝግጅት ሃሳብ … [Read more...] about የኢትዮጵያን ወቅታዊ ችግርና የመፍትሄ አቅጣጫ በሚመለከት የተሰጠ መግለጫና የሰላም ጥሪ
የአሜሪካ ምርጫ:- ዶናልድ ትረምፕ ወይስ ሂለሪ ክሊንተን?
መግቢያ የዛሬ ስምንት ዐመት ባራካ ኦባማ ለፕሬዚደንትነት ምርጫ ለውድድር ሲቀርቡ፣ ከፕሪመሪው ጀምሮ የነበረውን የምርጫው ሂደት እዚህ አውሮፓ ሆነን በየሰዓቱ ሁኔታውን በጥብቅ እንከታተል ነበር። በማያጠራጥር መልኩ የብዝዎቻችን ፍላጎትና አድልዎ ለባራክ ኦባማ ቢሆንም፣ ባራክ ኦባማ ያንን አስቸጋሪ የፕሪመሪ ውድድር አልፈውና ተፎካካሪዎቻቸውን አሸንፈው የዲሞክራቲክ ፓርቲውን በመወከል ለፕሬዚደትነት ምርጫ ይቀርባሉ ብሎ የገመተ አልነበረም። የመጨረሻ መጨረሻ ወይዘሮ ሂለሪ ክሊንተን በአሸናፊነት በመውጣት ፓርቲያቸውን በመወከል የሪፓብሊካን ፓርቲን ከሚወክለው ጋር ለውድድር ይቀርባሉ የሚል ግምት ነበረን። አሁንም ቢሆን የኢንስቲቱሽናል ሬሲዝምነትና አጠቃላይ ሬሲዝምነት በነገሰበት በአሜሪካን ህብረተሰብ ውስጥ አንድ ጥቁር አሜሪካዊ ለፕሬዜደንትነት ምርጫ በመወዳደር በአሸናፊነት ይወጣል ብሎ … [Read more...] about የአሜሪካ ምርጫ:- ዶናልድ ትረምፕ ወይስ ሂለሪ ክሊንተን?










