“. . . ገብረሕይዎት በመንግሥት እና የህዝብ አስተዳደር መፅሃፉ መቅድም ላይ እንዲህ ይላል፤
«ሕዝቦችን ሁሉ የሚፈጥር አንድ አምላክ ነው። ይህም አምላክ የምንለው የሕዝቦች ፈጣሪ ሕዝቦችን ሁሉ ትክክል አንድ አድርጎ ፈጥሮ ላኗኗራቸውና ለልማታቸው የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሁሉ ከሙሉ ፈቃድና ስልጣን ጋር በእጃቸው ሰጥቷቸዋል። ስለዚህ ማናቸውም ህዝብ ቢለማም ቢጠፋም በገዛ እጁ ነው። ሕዝብ የሚጠፋበት አንዳንድ ምክንያት ቢያገኝ ያውም ምክንያት በአንዳንድ ሰው ቢመካኝ ትክክል አይደለም። የልማትን መንገድ ለማግኘት የሚጥር ሕዝብ ቢገኝ በአንዳንድ ክፉ ሰው ምክንያት ሊጠፋ አይችልም። እንዲሁም ደግሞ የልማትን መንገድ ለማግኘት የማይጣጣር ሕዝብ በአንዳንድ ደህና ሰው ኃይል ልማት ሊያገኝ አይችልም።»
ይህ የገብረሕይዎት ተጠይቃዊ ሀሳብ ኢትዮጵያ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ለመመርመር ሲጠቀመን የሚችል ይመስለኛል። ሁላችን ከተባበርን በወያኔ ተንኮል ብቻ ኢትዮጵያ አትፈርስም።
እኛ እውነተኛ ራዕይና አላማ ኑሮን በጋራ ጉዳዮቻችን ዙሪያ በአንድነት ከቆምን በወያኔ ማኪያቬሌያዊ ጥበብ ብቻ የወያኔ ፍላጎት የሆነው የኢትዮጵያ መፍረስ ያለገደብ ሊፈጸም አይችልም። ስለዚህ መንፈሳዊ ወኔውን አግኝተን ራሳችንን መመርመር ከቻልን፤ እጣፋንታችን የተሳሰረ መሆኑን ተገንዝበን በአንድ ጉዳይ ሁለት አቋም፤ በሁለት ጎራ የተከፈለ አተያይ መያዛችን የጋራ ጉዳት መሆኑን ከተገነዘብን፤ እንደ ሱልጣን አሊሚራህ «የኢትዮጵያ ኃይሏ አንድነቷ ነው» ብለን የምናምን ከሆነ ኢትዮጵያን አሁን ካላችበት አደጋ ማውጣት ብቻ ሳይሆን ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ሁልጊዜ እንደሚሉት የምንመካባትና የምንኮራባት አገር ልናረጋት ችሎታው አለን፤ ይህንን የማድረግ ፈቃደኝነቱ ካለን ጊዜ ሳንወስድ አሁኑኑ መጀመር አለብን።
(ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
Leave a Reply