ዲያስፖራ (ዲያስጶራ) የሚለው ቃል ትርጉም ‹‹ብትን /የተበተነ›› ወይም በአጪር አነጋገር ከትውልድ አገሩ ውጭ ተበታትኖ ያለ ሕዝብ ማለት ነው፡፡ በዚህ ትርጓሜ ከኢትዮጵያ መቶ ሜትርም ይሁን አንድ ሺሕ ማይል ይራቅ ከድንበር ማዶ ያለ ሁሉ ዲያስፖራ ነው፡፡ የምንገኝበት አገር፣ የትምህርት ደረጃችን፣ የወጣንበት መንገድ፣ ሃይማኖታችን ወይም ብሔራችን ዲያስፖራ ከመሆን (ከመበትን) አያድነንም፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው በአውሮፕላንም ይሁን በመርከብ፣ ጥገኝነት ጠይቆም ይሁን አግብቶ፣ ፊደል የቆጠረም ይሁን ፕሮፌሰር የሆነ፣ እስላምም ይሁን ክርስቲያን፣ ዐማራም ይሁን ኦሮሞ ወይም ጉራጌ ወይም ሌላ ከድንበር ወጥተን ወደ ሌላ ሉዓላዊ አገር ከገባን ተበትነናል ማለት ነው፡፡ የምንገኝበት አገርም መመዘኛ አይደለም፡፡ አፍሪካ፣ አውሮፓ፣ አሜሪካ፣ ኤዥያ ወይም ኦሽኒያ መሆናችን ምንም ልዩነት አያመጣም፡፡ አንድ ሰው አሥመራ፣ ናይሮቢ፣ ካይሮ፣ ዱባይ፣ ፓሪስ፣ ዲሲ፣ ሲድኒ ወይም አንድ የዓለማችን ከተማ ላይ ቢሆን ከኢትዮጵያ ተነቅሏል፤ ተበትኗል፤ ልዩነት የለውም፡፡ አፍሪካ የሚኖር ጀግና ወይም አሜሪካ የሚኖር ደፋር የሚያስብል መስፈርትም የለም፡፡ በእኛ አገር ዲያስፖራ መሆንን እንደ ምርቃት (ጥሩ እድል) የመቁጠር እሳቤ አለ፡፡ ከአገር ወጥቶ መበተን እርግመት ወይም ምርቃት ነው የሚለውን ለጊዜው እንተወውና ስለብትኑ ማኅበረሰባችን ፖለቲካ ትንሽ እንበል፡፡
ብትን ወገን (ዲያስፖራ) በፖለቲካው ረገድ እስካሁን የተዋጣለት ሥራ የሠሩት የኢዝራኤል ዲያስፖራዎች ናቸው፡፡ ኢዝራኤል የምትባለዋ አገር የተመሠረተችው በዲያስፖራዎች ነው፡፡ ለነገሩ አይሁዶች ከአገራቸው ሲርቁ የበለጠ ስለአገራቸው የሚያስጨንቅ ነገር አላቸው፡፡ ቀድም ባሉ በብሉይ ዘመናት ዮሴፍ በወድሞቹ ተሸጦ ወደ ግብጽ አገር በተሰደደ ጊዜ ለወገኖቹ የሚሆን ጥሪት ያጠራቅም እንደነበር ማስታወስ ይቻላል፤ ሙሴም ቢሆን ጊዜው ከመርዘሙ ውጭ የተበተኑ ወገኖቹን ወደ አገሩ መልሷል፡፡
የእኛ አገር የዲያስፖራ ማኅበረሰብ ከቁጥሩ አንጻር ካየነው ከዚህ ግባ የሚባል ለአገር ፋይዳ ያለው ውጤት እስካሁን ማምጣት አልቻለም፡፡ ያ ማለት ግን አይችልም ማለት አይደለም፡፡ በዲያስፖራው ማኅበረሰብ ያሉ የአንዳንድ ችግሮች ከተስተካከሉ ለውጥ ማምጣት የማይቻልበት ምንም ዓይነት ምክንያት አይኖርም፡፡ የዲያስፖራው ማኅበረሰብ በሰለጠነ አገር እየኖረ የሰለጠነ የውይይት ባሕል ማዳበር ከፍተኛ ችግር ይታይበታል፡፡ በዚህ ምስኪን ብትን ማኅበሰረብ ውስጥ በርካታ ውስብስብ ችግሮች ቢኖሩም ወደ ዲሞክራሲ የሚደረገውን የአገር ቤት ትግል ውጭ ባለው ጥገኛ እንዲሆን የተደከመው ድካም እና ዐማራውን ሕዝብ ‹‹በአንድነት ኃይልነት›› መድቦ ማሞኘት ሕዝባችን ከባድ ዋጋ እያስከፈለው ነው፡፡ በውጭ አገር የሚገኙ ድርጅቶችና ማኅበራት (ከአፍሪካ እስከ አውሮፓና አሜሪካ) ከጥቂት ግለሰቦች የመኖሪያ መንገድ (Livelihood) ብሎም ግለሰባዊ ዝና (ፌም) ማግኛነት ወደ ትክክለኛ ዓላማቸው መመለስ ካልቻሉ ወደ ነጻነት የምናደርገው ጉዞ መራዘሙ አይቀርም፡፡ ጥይት በጮኸበት ቦታ ሁሉ ከእግዚአብሔር መላዕክ ቀድሞ መድረሱም ከባድ ዋጋ የሚያስከፍል ይመስለኛል፡፡
(ይህ አስተያየት የተሰጠው ጠቅለል ተደርጎ ለብዙዎች ድርጅቶች መሆኑ ልብ ይባል፤ የሰለጠነ ውይይት ለማድረግ የማትፈልጉ ሰዎች ከእኔ ጋ ጓደኝነታችሁ ያቆማል፤ ዝርዝር ጉዳዮችን ወደፊት ይዤ ለመምጣት እሞክራለሁ፤ እንደ ግለሰብ እንጅ እንደ ድርጅት አቋም የለኝም)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
Ezira says
ሙሉቀን ተስፋው! አንተም “ዲያስፖራ” ከምትለው ኢትዮጵያዊ ከመቀላቀለህ በቀር በ25 ዓመቱ ኢህዴግን ለመቀየር ከሚደረገው ትገል አንፅር 25 ዓመት ብቅ ጥለም ካሉት ግለሶቦች የተለየህ አይደለህም። ዛሬ አንተም ጸጉረ ልዉጥ ከመሆንህ ዉጭ የምትገፋው ሃሳብ ፍራሽ አዳሽ ከመሆን አላለፈም። ብዙዎቹ አንተን መሰሎች ብቅ ከማለታቸው ደፍረታቸው “አስተማሪ” ሆነው መታበያቸው ነው። ከእነዚህ ዉሰጥ አንዱ በ 2005 /1997 መርጫ በኋላ ውደ “Dኢያስፕራነት” የተቀላቀለው “ወጣቱ” ጃዋር መሀመድ አንዱ ነው። ጃዋር ሙሃመድ ደግሞ በወጣት ምላሱ ማንነቱን ወዲያዉኑ ለብልቦ ያቃጠለ የ ዘማናችን “ፖለቲካ ተንታኝ” ነው። ፍየል ከመደረሱ ቅጠል መበጠሷ እንዲሉ ሙሉቀን ተሰፋዉና ጃዋአር መሃመድ በመሰምማማተም ይሁን ባለመሰማማት በሚዲያዊና ብበፌስ ቡኩ ኢንተርቪው ተደራጊ ጓዴኛሞች መሆናቸው በኮንኒስፓሪስ ቲዎሪ እይታ መሬት ላይ የሚታይ ሃቅ ነው። ተመሳሳይ ላባ ያላቸው ወፎች አብረው ይበራ! በርቱ እነ ሙሉቀን