• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“የኦሮሞ ህዝብ ሙስሊም ነው…” “BBN (አቶ አብዲረሂም አህመድ)

November 29, 2016 07:01 am by Editor 1 Comment

በኦሮሞ ስም እየተደረጉ ያሉትን አብዛኛዎቹን ስብሰባዎች ላስተዋለ ሰው፣ የኦሮሞ ጎሳ ብቻ ሳይሆን በአመዛኙ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ስብስብ እየመሰለም (“ሆኗል” አለማለታችን ይያዝልን) ሄዷል። አቶ ጃዋር ሙስሊም ከመሆኑ እና ራሱን የኦሮሞ የፖለቲካ ተወካይ/ተጠሪ አድርጎ በየመድረኩ ብቅ ካለበት ጊዜ ጀምሮ፤ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የኦሮሞ ተውላጅ ልሂቃን፣ አቶ ጃዋርን “በሜጫ አንገት የመቁረጥ” ፉከራው ጋር አዝለው፣ አንድም ጊዜ በአደባባይ ይቅርታ እንዲጠይቅ ማድረግ ሳይችሉ እና እነሱም ሳያወግዙ፣ እስካሁን ድረስ ተሸክመው የመዝለቃቸውም ነገር እኛ በ“ኢትዮጵያ ሴኩላር ሰብዓዊያን” ስር የተሰባሰብነውን ግለሰቦች እጅግ አሳዝኖናል፣ አሳስቦናልም።

እሱ ሲገርመን አሁን ደግሞ በቅርቡ BBN በሚባል ስም የሚታወቀው፣ በጸረ-ህወሃት የፖለቲካ አቋሙ እና በእስልምና ሃይማኖት አራማጅነቱ የሚታወቀው የመገናኛ ብዙሃን አዘጋጅ አቶ አብዲረሂም አህመድ “…የኦሮሞ ህዝብ ሙስሊም ከመሆኑ አንጻር…(ይቺን ይጫኑ)” ሲል ተናግሯል። ይህ ተቆርጦ እዚህ ከተለጠፈው ንግግር በፊትም ሆነ በኋላ የተነገረው ሁሉ በቋንቋውም ሆነ በአውድ ደረጃ ደጋግመው ቢያዳምጡት “ኦሮሞ ሙስሊም ነው” የሚለውን የግለሰቡን አባባል ጨርሶ አይቀይረውም (እነሆ ንግግሩን በሙሉ ማዳመጥ ይቻላል። እንዲህ አይነት ሃላፊነት የጎደላቸውን እና ውሸት የሆኑ ንግግሮች በማንኛውም ግለሰብ፣ ድርጅትም ሆነ ተቋም ሲነገር፣ ይኼን ለማውገዝ የመጀመሪያዎቹ መሆን የነበረባቸው ራሳቸው የእስልምና ተከታይ የሆኑ አድማጮች መሆን ነበረባቸው። የሆነ ግን አይመስለንም። አሳዛኝም አስፈሪም ነው። እናም እስካሁን ለተነገሩትም ሆነ ለወደፊት ለሚነገሩት፣ እና ንግግሮቹ በአገራችን ኢትዮጵያ ለወደፊት ለሚያደርሱት መዘዝ ተጠያቂ በሚያደርግ መልኩ ለሚመመለከታቸው ተቋማት ሁሉ ሪፖርት የማድረግ ሃላፊነት እንዳለብን እንገልጻለን።

ይህ ከእውነት የራቀ የBBNኑ አቶ አብዲራሂም እና የOMNኑ አቶ ጃዋር የሜጫ ንግግር፣ በግለሰብ ደረጃ ለግለሰብ የተነገረ ቢሆን “ሰው ሆኖ የማይሳሳት የለም…” ተብሎ እንዲሁ ሊታለፍ ይችል ይሆናል። በአገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ እየደረሰ ያለውን የፍትህ መዛባት (ግድያ፣ ስቅየት፣ እስራት፣ እንግልት፣ ስደት፣ ተስፋ መቁረጥ…) እና የግለሰብ መብት የሆነውን ሃይማኖትን ያህል ነገር እንኳን በነጻነት ማምለክ በማይቻልበት አገር ውስጥ፣ እንዲህ አይነት ንግግሮች ሊያስከትሉ የሚችሉትን መዘዝ አለመገመት፣ አምባገነንነት በገነነባቸው አገሮች (ሶማሊያ፣ ናይጄሪያ፣ ሶሪያ፣ የመን፣ ቦስኒያ/ዩጎዝላቪያ…) ውስጥ አሁን እየደረሰ ያለውን (የደረሰውን) የርስ በርስ ጦርነት እና በሩዋንዳ ላይ የደረሰውን የቅርብ ጊዜ አሳዛኝ ክስተት መርሳት ይሆናል።

ሃይማኖትን በተመለከተ የሚደረጉ ንግግሮች፣ በተለይም ከእንደ “… 99% እስላም ነው [1% የሚሆነውን ክርስቲያኑን] በሜጫ አንገት እንቆርጣለን”፣ የመሰለ እጅግ ግልብ እና አደገኛ የሆነ የአመጽ እና የግድያ ዛቻ ሲደረግ፣ “ኦሮሞ እስላም ነው” የመሳሰሉ ሃላፊነት የጎደለው እና ፍጹም ውሸት የሆነ ንግግር፣ በተለይም የመገናኛ ብዙሃንን በእጃቸው ያደረጉ ግለሰቦች (ጃዋር የኦ.ኤም.ኤን፣ አብዲረሂም ደግሞ የቢ.ቢ.ኤን. መስራቾች እና አሁንም የሚቆጣጠሯቸው ናቸው) ሲናገሩ እየሰማን ዝም ማለት፣ በማናቸውም መልኩ ተቀባይነት የለውም። በመገናኛ ብዙሃን የሚተላለፉ ንግግሮች እጅግ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን የ“BBNኑ አዘጋጅ በዚህ ቃለ-መጠይቅ ላይ ያነሳቸው ነጥቦች እና ያነጋገራቸው የኦሮሞ አክቲቪስቶች (ሮባ እና ጃውሃር [የOMNኑ ጃዋር አይደለም])፣ ዋና አጀንዳቸው የለንደኑ ኮንፈንስ ሆኖ፣ የ“ኢትዮጵያ ትበተን” እና መሰል ንግግሮችን አስመልክቶ የሰጧቸው አስያየቶች ህወሃትን ለማስወገድ በሚደረገው ትግል ላይ ያሳደረውን አፍራሽ ሚና በተመለከተ መሆኑን እና ተሳታፊዎቹ ሮባ እና ጃውሃር የሰጧቸው አስተያየቶች፣ በኮንፈረንሱ ላይ የተደረገውን አፍራሽ ንግግር በማውገዝ ላይ የተመሰረተ መሆኑን እና የቢቢኤኑ አዘጋጅም እነዚህን አክቲቪስቶች ለማነጋገር ያደረገው ተነሳሽነት የሚበረታታ ነው። “… የኦሮሞ ህዝብ ሙስሊም ነው…” የሚል አደገኛ ውሸት (ካፍ ያመለጠ ስህተት ነው ለማለት እጅግ ይከብደናል) ግን የ“ተሳስቻለሁ ይቅርታ” ብቻውን የሚበቃ አይመስለንም። እጅግ ደጋግሞ በመገናኛ ብዙሃኑ አማካይነት ማንሳት እና ማስተባበል ይገባ ይመስለናል። እውነት ለመናገር “በሜጫ አንገት እንቆርጣለን” እና “ኦሮሞ እስላም ነው” ከመሳሰሉት ከእንደዚህ አይነት ሃላፊነት የጎደላቸው ንግግሮች ለመዳን “… አገር ቤት ውስጥ ብሆን ኖሮ እንዲህ ብዬ እናገር ነበርን?” ብሎ ራስን መጠየቅ ከጥፋት የሚያድን ይመስለናል።

እኛ እጅግ ጥቂት ሆነን የኢትዮጵያ ሴኩላር ሰብዓዊያን ማህበርን የመሰረትን መስራች አባላት፣ ከማንኛውም ሃይማኖት ጋር ያልወገንን መሆናችንን እየገለጽን እና ሃይማኖት የግል መሆኑን ከመገንዘብ ጋር፣ ሃይማኖተኞች ከመሆናችን በፊት ሰው ሁነን የተፈጠርን በመሆኑ ሰብአዊነትን እናስቀድማለን። እናም በህዝባችን መካከል ያለው እጅግ አስፈሪ እና አስጨናቂ የሃይማኖት ውድድር ሩጫ፣ እና በሃገራችን ያለው መንግስትም እጅግ ሃላፊነት የማይሰማው፣ በስልጣን ለመቆየት ሲል ማንኛውንም ህዝብን ለመከፋፈል የሚያስችል ክፍተት ለመጠቀም የማያመነታ እና እስካሁንም የተጠቀመበት አካሄድ ከመሆኑ እና አብዛኛው ህዝብ የገባበት የድህነት፣ ስራ አጥነት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ነጻነት ማጣት፣ የዘር ፖለቲካ ወዘተ… ተደራርበው የህዝባችን መጨረሻው ያሳስበናል።

የጃዋር እና መሰሎቹ አይነት እኩይ ራዕይ እውን የሚሆነው፣ እንደ ቢቢኤኑ አብዲራሂም አይነት ፍጹም ሃሰት የሆኑ ያላፊነት የጎደላቸው ሃይማኖት ነክ ንግግሮች ሊያስከትሉ የሚችሉትን መዘዝ ማስወገድ የምንችለው፣ ሃይማኖት የግል እና የግለሰብ ብቻ መሆኑን በሚያምኑ፣ በሚያረጋግጡ ከሁሉም በላይ ግን ከሃይማኖት በፊት ሰብዓዊነትን በሚያስቀድሙ ሰዎች ተሳትፎ ነውና፣ ሃሳባችንን የምትጋሩ ሁሉ በየሜዲያው ሃሳባችሁን በመግለጽ እንድትቀላቀሉን በአክብሮት እንጠይቃለን። (ፎቶ: Advocacy for Oromia)

በፌስ ቡክ እና ትዊተር ላይም ተከተሉን እንከተላችሁ
የኢትዮጵያ ሴኩላር ሰብዓዊያን
Ethiopian Secular Human (ethiopiansh@gmail.com)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Eunetu Yeneger says

    December 8, 2016 06:26 pm at 6:26 pm

    ለእንደዚህ መሰል አፍራሺና ግላዊ የእብድ መገለጫ ንግግሮች ዳኛው በስሙ የሚነገድበትና በእሳት ውስጥ ሆኖ የመከራውን ጽዋ በጉልበተኞች በግድ እየጨለጠ ያለው የኦሮሞ ሰፊ ሕዝብ መሆን አለበት!የሚያሳዝነው ግን የእብዱ ተናጋሪ ”ኢትዮጵያን ማፍረስ አለበን” ንግግር ሳይሆን በአገር ቤት ባለው አብዛኛው የኦሮሞ ሕዝብ ስም ነጻ በሆነች በለንደን ሲቲ ማክዶናል እየበሉ የሚኖሩ የስብሰባው ታዳሚዎች በጭብጨባ ያሳዩት ድጋፍ ነው! በዚች ታላቅ ሲቲ የምትኖሩ ታማኝ ኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ምስሉን ደጋግማችሁ በማየትና በመለየት ልታናግሯቸውና ልታርሟቸው ትችላላችሁ፤ የሚሰሙ ከሆነ!ተናጋሪው ግለሰብ የግለሰቦችን ድጋፍ ባያገኝ እንደዚህ ባለ ድፍረት መናገር ባልቻለ ነበርና!አንዳንድ በስብሰባው ላይ የነበሩ ሰዎችም ንግግሩ ለኢሕአዴግ መንግሥት ያስገኘለትን የፖለቲካ ፍጆታ ተመልክተው ”የተናጋሪው የግል ድካም ነው” በማለት የሰጡት አዲስ የሽፋን አስተያየት ህሊና ላለው ሰው አብረው በመሆን አጨብጨብው ያጸደቁትን አገርን የማፍረስ አጀንዳ መልሰው መቃረን ስለሚሆን ገና ወደፊት ላለው ለጋራ ዓላማ አብሮ መሰለፍ የሚያስችል አቅምና የመታመን ብቃት የሌላቸው ስለመሆናቸው ታላቅ የማንነት መገለጫ ምልክት ነው የሚሆነው።

    ስለዚህ እንደዚህ ላሉ ወገኖቻችን ያለኝ ወንድማዊ ምክር የጠራና ለጋራ ዓላማ መሳካት የሚጠቅም እውነተኛ አቋም ይኑራችሁ፤ መታመን ከሊለ እንኳን እንደዚህ ያለ ታላቅ ሃገራዊ ሥራ ከሌሎች ወገኖች ጋር መሥራት ይቅርና የየእለት የግል ኑሮንም መምራት ያስቸግራል!ለውጤት ጽናት ያለው አቋም እጅግ ወሳኝ ነውና አብሮነትን በዚህ መልኩ እናጠናክረው!!!ቸሩ በቸርና ፍሬ ባለው ሥራ በጋራ ይጥመደን!!!

    ምንጊዜም ቢሆን
    እውነቱ ይነገር
    ካለሁበት

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule