ከትናንት ጅዳ ውስጥ በጠና ታማ እሷና ልጇ አደጋ ላይ አሉ ስለተባ ለችው እህት እየተሰራጨ ያለው መረጃ ደርሶኛል። መረጃውን በዝርዝር ያገኘሁት ከሊያ ሾው ነበር፣ ታመመች የተባለችውን እህት በቪዲዮ የተደገፈ መረጃ እንደደረሰኝ ወደ ጅዳ ቆንስል ደውዬ ለማጣራት ሞክሬ ነበር! በጅዳ ቆንስላ መረጃ ለማግኘት ከባድ እየሆነ መጥቷ ል፣ አንዳንዶች ኃላፊዎች ከዚህ ቀደም በማቀርባቸው ተጨባጭ ሂሶች አኩርፈው መረጃ ላለመስጠት ስልካቸውን ይዘጉብኛል፣ አንዳንዶች ደግሞ መረጃም ሆነ ጥያቄ ለመመለስ ፈቃደኛ አይደሉም! እጅ አዙር በሆነ መንገድ የጅዳ ቆንስል መረጃው እንዳልደረሰው ተነግሮኛል!
ይህች እህት በሽሜሲ ጊዜያዊ እስር ቤት በር ላይ ተጥለላች መባሉን ሰምቸ ወደ ቦታው የሚያጣራልኝ የስራ ባልደረባዬን ልኬም ነበር፣ ዛሬ ረፋድ ላይ በር ላይ ተዟዙሮ የወደቀ ሰው አለመኖሩን አረጋግጦልኛል! ይህን ካደረግ ኩ በኋላ ምናልባት ይህች እህት በእስር ቤት ትገኝ እንደሁ ቢረዷት ለማሳሰብ ወደ ቆንስላው የሺሜሲ ተወካዮች ወደ አቶ ቡሩና አቶ አብርሃ ደወልኩ፣ ሁለቱም ስልክ አያነሱም። መልሸ ወደ ቆንስል ያለለት ደወልኩ ስለኬ ብሎክ የመደረጉ ምልክት ሰጠኝ። በዚህ ሁኔታ እስካሁን ከቆንስሉ ያገኘሁት መረጃ የለምና ወደ ሺሜሲ አመራሁ!
ሽሜሲ በር ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግበት ቦታ በመሆኑ በአካል ሄጅ በአካባቢው ወድቃለች የተባለቸውን እህት ዘወር ዘወር ብዬ ፈለግኳት፣ የለችም፣ ይሁን እንጅ ከዚህ ቀደም በአካባቢው ወድቃ የነበረች እህት ስለመኖርዋና ልጇንም እሷንም ለመርዳት ሞክረው አቅሙ ስለሌላቸው መረጃ የሚቻሉትን አደርገውላት የሄዱትን እህቶች ምስልና ምስክርነት ደርሶኝ ተመልክቸዋለሁ! ዛሬ እኔ ባላገኛትም ትናንትና ከትናንት በፊት ያገኟት እንዳሉ ማረጋገጥ ችያለሁ! እንግዲህ ሊሆን ስለሚችለው ብቻ በግምት ልናገር … በትክክል ቪዲዮው የተቀረጸው ጅዳ ሽሚሲ ስለመሆኑ መረጃው ደርሶኛል፣ ልጅቱ በእስር ላይ የምትገኝ ይመስለኛል፣ የቆንስሉ ተወካዮች ለምን ወደ ህክምና እንዳልወሰዷት አልገባ ኝም። አንድ በቦታው የነበረ ች እማኝ ይህች እህት ከእነ ልጇ ለቀናት ስትሰቃይ ማንም እንዳልደረሰላት ተናግራለች። አሁንም በእርግጠኝነት መናገር የምችለው ወይ በጠና ታማ ሀኪም ቤት ተወስዳለች አለያም ወደ ማረፊያ ወስደዋት ይሆናል፣ በመጠለያ ካለችም ተከ ታትለው ህክምና እንድታገኝ የእኛ ተወካዮች ሰራ አልሰሩ ይሆናል ፣ በቅርብ ሰአታት በደረሰኝ መረጃ መሰረት “ይህች እህት ከእስር ቤት አስወጥተው የጣሏት የሳውዲ ፖሊሶች ናቸው!” የሚለው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን በሊያ በኩል ተስተካክሎ ሰምቻለሁ!
በትክክል የሆነው በጠና በመታመሟ ወደ ሀገር ለመላክ አንቻልም መባሏን ነው፣ ይህ በመሆኑ ያለ ማንም ረዳት በበር ብርድና ጸሀይ እየተፈራረቀባት መሰንበቷ ልብን በሀዘን ይሰብራል 🙁 አሁንም አልመሸም፣ ያለችበት ቦታ ተጣርቶ ከተገኘች በጅዳ ቆንስል ተወካዮች ጎትጓችነት ወደ ህክምና ሊወስዷት ይችላሉ! ይህን በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ! ሀገሩ ሳውዲ ነውና በጠና በታመመና እስር ቤት ያለን የወገን ጉዳይ ተከታትሎ ህክምና እንዲያገኙና ወደ ሀገር ለመላክ ከኢንባሲና ከቆንስላ ውጭ አማራጭ የለም! ጌቱና ሊያ ሾው የወገን ጉዳይ ያገባኛል ብላችሁ የወገናችሁን ድምጽ በማሰማት ላደረሳችሁን መረጃ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ!
እንዲህ አይነት የወገን ጉዳት ሲደርስ፣ በተለይ ሰው በጠና ሲታመምና ወደ ሀገር ቤት ልግባ ብሎ እጁን የሰጠ ዜጋ በማቆያ እስር ቤት ሰማቅቅ ተራው ነዋሪ ሰው ለመደገፍ አቅሙ የለውም፣ ብቸማው ደራሽ እውቅና ያለው የመንግስት ተወካዮች ብቻ ናቸው! ለማጠቃለል ያህል ይህ መረጃ የሚደርሳችሁ የቆንስሉ ሹማምንትና ሰራተኞች ለፈጣሪ ብላችሁ ከነልጇ የምትከላተመው እህት ዜጋ ናትና እርዷት፣ መረጃ ስጡን ተለመኑን!
ቸር ያሰማን!
ነቢዩ ሲራክ
ህዳር 14 ቀን 2009 ዓም
(ከዚህ ጋር ያያዝኩትን ፎቶ ያገመሁት ከሊያ ሾው ነው)
Leave a Reply