በትምህርትም ሆነ በሀብት ቀና የሚሉ የኦሮሞ ሕዝብ ልጆችን በተለያዩ የፀረ- መንግሥት እንቅስቃሴዎች በመፈረጅ ሲያሳስሩና ሲያስገድሉ የኖሩ የኦሮሞ ፍራቻ-ጥላቻ በሽታ ህመምተኞች በሚያከሂዱት ፀረ- ኦሮሞ ፐሮፓጋንዳ “ኦሮሚያ የህልም ዓለም ስያሜ ነው፤እስላሞችና ኦሮሞዎች የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ይጠይቁ፤ ስለኦሮሞ ሕዝብ ጨካኝነት የአገር ውስጥ የታሪክ ጸሐፊዎችና ተመራማሪዎች፤ እንዲሁም የውጭ አገሮች ጸሐፍት መስክረዋል፤ “ጋዳ/ገዳ” የማፊያ ሥርዓት ነው፤ምኒልክና ወታደሮቻቸው ክርስትያኖች ስለነበሩ የአርሲን ሕዝብ ጡትና እጅ አልቆረጡም፤ ይህንን የሚፈጽሙት አረመኔዎቹ ናቸው፤የኦሮሞን አመጽ ይመሩ የነበሩት የወለጋ ፕሮቴስታንቶች ናቸው፤ዛሬ ኢትዮጵያ ለአንድ ኢትዮጵያዊ ሙሉ በሙሉ አገሩ አይደለችም፤ወንድ ልጅን መስለብ የኦሮሞ ባህል ነው፤ኦሮሞ እረኛ ነው፤ ወዘተ… የሚሉ ከህሙም ህሊናዎች … [Read more...] about እውነት ኦሮሚያ የሚለው ስም በታሪክም በተረትም የማይታወቅ የህልም ዓለም ስያሜ ነው?
Opinions
የኔ ሃሳብ
እውን ሐበሻና ፊደሎቹ ከደቡብ ዓረብያ ፈልሰው የገቡ መጻእያን ወይም ውሑዳን ናቸውን?
የሥነ ልሳን ወይም የሥነ ቋንቋ linguistics ተመራማሪዎች ፊደልን ለመጀመሪያ ጊዜ ፈለሰፉ የሚሏቸው ከፊሎቹ ሱመራዊያን አሁን ኢራን በሚባለው አካባቢ እንደሆነ ሲናገሩ ከፊሎቹ ደግሞ በግብጽና በሜሶፖታሚያ እንደሆነ ለማስረዳት ይሞክራሉ፡፡ ነገር ግን እውነቱ ይህ እንዳልሆነ በሌላ ጊዜ በሚገባ እናየዋለን፡፡ እነኚህ ምሁራን የእኛን የግዕዝ ወይም የአማርኛ ፊደላትን ከደቡብ ዓረቢያ ባሕር ተሻግረው ወደ ኢትዮጵያ በገቡ አፍሮ ዓረቦች ወይም ኢትዮ ሴማዊያን አማካኝነት ከሦስት ሺህ ዓመታት በፊት ሃያ ዘጠኝ መሠረታዊ ፊደላትን ይዘው ገቡ በማለት ይናገራሉ፡፡ እንደመረጃ አድርገው ከሚያቀርቧቸውም ውስጥ አንድ ሁለቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ሴማዊ ቋንቋ የሚናገሩ ብሔረሰቦች መኖራቸውና እነኚሁ ብሔረሰቦች ደግሞ በመልክ ከሌላው አፍሪካዊ የተለዩ ስለሆኑ መጤዎች እንጂ ነባር አይደሉም ይላሉ፡፡ ከዚህ … [Read more...] about እውን ሐበሻና ፊደሎቹ ከደቡብ ዓረብያ ፈልሰው የገቡ መጻእያን ወይም ውሑዳን ናቸውን?
የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ማዕከላዊ ምክር ቤት
በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ተቃዋሚነት ጎራ የተሰለፉ ኃይሎች በቅድሚያ ትግላቸውን በብሔራዊ ነፃነት ዙሪያ ያድርጉ! እኛ የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ማዕከላዊ ምክር ቤት አባላት ከሰኔ ፲፬ - ፲፭ ቀን ፪ሺህ፮ ዓ.ም. (June 21 - 22, 2014) አራተኛ መደበኛ ስብሰባችንን በተሣካ ሁኔታ አካሂደናል። በሁለት ቀናት ጉባኤያችን የሥራ አስፈጻሚ እንዲሁም የቁጥጥርና ፍተሻ ኮሚቴዎች ያቀረቧቸውን የ፮(ስድስት) ወራት የድርጅቱን የሥራ እንቅስቃሴ ሪፖርቶችን አዳምጠን ጠቃሚ ውይይት አድርገናል። ድርጅቱ ያከናወናቸው መልካም ተግባሮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ በአፈፃፀም የታዩ ድክመቶች እንዲታረሙ በማስገንዘብ፣ ለድርጅቱ ዓላማ ዳር መድረስ የሚያግዙ የሚከተሉትን አቋሞች ወስደናል። ፩ኛ) የኢትዮጵያውያን ሉዓላዊነት፣ የአገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም መከበር እና የግዛታዊ አንድነት መጠበቅን … [Read more...] about የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ማዕከላዊ ምክር ቤት
“ፀሎታችን በቤታችን”
በተለያዩ ግዜያት ህጋዊ እና ህገወጥ በሆነ መንገድ ተሰደው ወደ ሳውዲ አረቢያ ከሚገቡ ኢትዮጵያውያን መሃከል ጥቂት የማይባሉ የኦርቶዶክ እምነት ተከታይ ወገኖቻችን የህዝብ ሙስሊሙን ሃይማኖታዊ ደንብ እና ስረአት አክበረው እንደሚኖሩ ይታወቃል። እነዚህ በሃገሪቱ ግዛቶች ሪያድ፣ ጅዳ፣ ደማም እና ጅዛን በሚባል ክፍለ ግዛቶች ውስጥ በተለያዩ ስራዎች ላይ ተሰማርተው እንደሚኖሩ የሚነገረው የእምነቱ ተከታዮች በደስታም ሆነ በሃዘን ግዜ ሃይማኖታቸው የሚያዘውን የፀሎት ስረአት ሃይማኖታዊ ወግ እና ስረአት ጠብቀው ለፈጣሪያቸው ጸሎት ማድረስ እንደማይቸሉ የሚገልጹ ምንጮች ሳውዲ አረቢያ በእስላማዊ ህግ የምትመራ እንደመሆኗ መጠን ሌሎች ሃይማኖቶችን ማራመድ በጥብቅ የተከለከለ በመሆኑ በመንግስት ዘንድ በይፋ ከሚታውቀው ሃይማኖት ውጭ ምንም አይነት አማራጭ የጸሎት ስፍራዎች ባለመኖራቸው በኢትዮጵያውያኑ … [Read more...] about “ፀሎታችን በቤታችን”
ኢትዮጵያ: አሁንስ ተስፋሽ እግዚአብሔር አይደለምን?
ነገሩ ግራ የገባው ነው! ለመሆኑ አሳባችን ምንድነው? እንዲሁ ስንጨቃጨቅና ስንነካከስ ምን ያህል ልንዘልቅ ነው? ንትርኩና መተላለፉ እጅ እጅ ብሎንና ሰልችቶን ሁሉን ትተን የእርቅ ያለህ! ለማለት ጊዜው ለመሆኑ መቼ ይሆን? ከጥል ወደ ፍቅር፤ ከመከፋፈል ወደ አንድነት፤ በስምምነት ለማደግ ቀጠሮ የያዝነው ለመቼ ነው? በፖለቲካው ውድድር ውስጥ ያለንን የበላይነት ለማስከበር የሞት የሽረት ትግል ስለምናካሄድ፤ የጋራ የሆነውንና የሁላችንም ችግር የሆነውን ይህን የእርቅ ጥያቄ እንዲስተናገድ ማን ቦታ ይስጠው? ይህ የእርቅ ችግር ግን እንደ ድልድይ ሆኖ ሁሉንም ጎራ ያገናኝ ነበር። በራሱ ችግራችንን ሁሉ ባይፈታም እንደ ጥሩ መነሻ ያገልግላል። ይህ የጋራ የሆነ የእርቅ ጉዳይ መደማመጥን ሊጠይቅ ነው። እኛ ደግሞ የለመድነው ሌላ ነው። ታዲያ ስንተላለፍና ስንዘላለፍ ችግራችንን አክርረነው እና … [Read more...] about ኢትዮጵያ: አሁንስ ተስፋሽ እግዚአብሔር አይደለምን?
እውን ክርስቶስ ኢትዮጵያዊ ነውን?
ከዓመታት በፊት “ኢየሱስ ክርስቶስ ኢትዮጵያዊ ነው” የሚለውን ጨምሮ ብዙ እንግዳ የሆኑ ነገሮችን የሚናገሩ ሦስት “አባቶችን” አውቅ ነበር አንደኛው ከሀገር ውጭ ናቸው፡፡ እነኝህ “አባቶች” ተከታዮች እያፈሩ መጡና ዛሬ ላይ እነሱ የሚሉትን የሚያምኑ ቁጥራቸው አነስተኛ የማይባሉ ሰዎችን እያየን ነው፡፡ እነዚህን እንግዳ አስተምህሮዎቻቸውንም በማኅበራዊ የብዙኃን መገናኛ (social media) በከፍተኛ ደረጃ እየናኙት ይገኛሉ፡፡ እውን ግን የናዝሬቱ ኢየሱስ መሲሑ ክርስቶስ ኢትዮጵያዊ ነው? ይሄንን ብለው እየሰበኩ ያሉ “አባቶች” ይሄንን ትምህርታቸውን በቀጥታ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ወይም ትውፊታዊ መረጃ በመስጠት አያረጋግጡም፡፡ የሆነ የራሳቸውን ነገር ይቀበጣጠሩና ክርስቶስንና ሌሎች ታላላቅ የመጽሐፍ ቅዱስ አባቶችን ሁሉ ኢትዮጵያዊያን ያደርጓቸዋል፡፡ እነኝህ አባቶች ሲያዩዋቸው የአእምሮ እክል … [Read more...] about እውን ክርስቶስ ኢትዮጵያዊ ነውን?
አህያውን ትቶ ዳውላውን
በአሁኑ ሰዓት በአብዛኛዎቹ ኢትዮጵያዊ የዜና መለዋወጫ መስኮች፤ “ትግሬዎች በዚህ መንግሥት ተጠቅመዋል? ወይንስ አልተጠቀሙም?” የሚለው ጉዳይ ዓይነታ መወያያ ሆኖ፤ መድረኮቹን ሁሉ አጣቦ ይዟል። በመጀመሪያ ደረጃ፤ አንድን ጉዳይ ኢትዮጵያዊ ታጋዮች ሲያነሱ፤ ከትግሉ ዋና ግብ አንጻር ነው። እንዲያው ለወግ ያህል ወይንም ቁጭትን ለመዘርገፍ የሚደረግ ውይይት፤ የታጋዮችን ቀልብ አይስብም። ይኼ ጉዳይ በትግሉ ሂደት ውስጥ ለኢትዮጵያዊ ታጋዮች ምን ይጠቅማል? ትግሉን ወደፊት ከመግፋትና ከግቡ ከማድረስ አኳያ ምን አስተዋፅዖ አለው? ይኼ ወሳኝ ነው። ትግል በመርኅ የሚካሄድ እንጂ፤ በየተመቸው የሚነዳ መንፈስ አይደለም። በትግሬዎችና ራሱን “የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር” ብሎ በተነሳው ድርጅት መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። በእርግጥ የዚህ ግንባር አባላት በሙሉ ትግሬዎች ናቸው። ይኼ በግልፅ ያለና … [Read more...] about አህያውን ትቶ ዳውላውን
በሳጥናኤል መንገድ ነጎዱ!
ሕዝበ ክርስቲያን በጰራቅሊጦስ መንገድ ሲሄዱ፤ፓትርያርክ፤ሊቃነ ጳጳሳት፤መነኮሳትና ቀሳውስት በሳጥናኤል መንገድ ነጎዱ። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about በሳጥናኤል መንገድ ነጎዱ!
በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት 3ሺ ህጻናትን በትኖ ሊዘጋ ነው!
በስደት አለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ህጻናት በተመጣጣኝ ዋጋ ተቀብሎ በማስተማር ከፈተኛ ስተዋጾ እያበረከተ የሚገኘው በሪያድ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት ላለትፉት ሁለት አስርት አመታት ሪያድ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚመኩበት እና የሚኮሩበት ተቋም ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል። ከቅርብ ግዜ ወዲህ በወላጆች እና በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች መሃከል በተፈጠረው አለመግባባት ት/ቤቱ እንደተቛም ህልውናውን ጠብቆ ወደፊት መቀጠል እንደተሳነው የሚናገሩ ምንጮች። ሰሞኑን የት/ቤቱ የኪራይ ዘመን እና የት/ቤቱ ህጋዊ ፈቃድ የግዜ ገደብ በመጠናቀቁን ተከትሎ በተቋሙ ህልውና ላይ የጋረጠው አደጋ አሳስቢ መሆኑን በመጥቀስ ከወራት በፊት በማን አለብኝነት ት/ቤቱን በበላይነት ተቆጣጥረው እንዳሻቸው ሲዘውሩት የከረሙት በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሹማምንቶች በትምህርት ቤቱ ዙሪያ ተከሰቱ … [Read more...] about በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት 3ሺ ህጻናትን በትኖ ሊዘጋ ነው!
ያለሽ መስሎሻል ተበልተሽ አልቀሻል
ባለፈው ሰሞን አንድ ከ “ሰማእታት” የመታሰቢያ ሐውልቶች ጋር በተያያዘ ታሪክ ቀመስ ጽሑፍ መጻፌ ይታወሳል "አሳ ጐርጓሪ ዘንዶ ያወጣል" እንዲሉ ይህ ጽሑፍ ለንባብ ከበቃ በኋላ በፊት ለምን እንደሆነ በቅጡ የማይገቡኝ የነበሩ እጅግ የሚገርሙ ነገሮች ለምን ይደረጉ እንደነበር ከተለያየ አቅጣጫ በአካልና በመልእክት ካገኘኋቸው ግብረ መልሶች ተረዳሁ፡፡ በዚያ ጽሑፍ ላይ ኦሮሞና ትግሬ ነን የሚሉ ካድሬዎች በተለየ ሁኔታ ትኩረታቸው ተስቦ ነበር፡፡ አንዳንዶችም አነጋግረውኝ ነበር፡፡ በንግግራችን ውስጥ ከዚህ በፊት ያልተረዳኋቸው ነገሮች ግልጽ ሆኑልኝ፡፡ ለነገሩ ያልተረዳኋቸው ማለት ይከብዳል ነገሩ እጅግ የማገርምና ለማመንም የሚቸግር በመሆኑ ሁል ጊዜ እንግዳ ሰለሚሆንብኝና ለጉዳዩ ሁሌም አዲስ እንግዳ ስለሚያደርገኝ ነው፡፡ ባይሆን ስጠረጥራቸው የነበሩ ብል ይሻል ይመስለኛል፡፡ እናም እጅግ ገረመኝ … [Read more...] about ያለሽ መስሎሻል ተበልተሽ አልቀሻል









