• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“የመሬት ባላባቱን” አባይ ማን ይድፈራቸው?

March 4, 2016 09:36 am by Editor 4 Comments

ከተለያዩ አቅጣጫዎች በተቃውሞና ዓመጽ የተወጠረው ህወሃት/ኢህአዴግ በአስሩም ክፍለከተሞች የሚገኙ እስከ 600 የሚደርሱ የመሬት ባለሙያዎችን ካገደ በኋላ የአዲስ አበባ የመሬት አስተዳደር ሞሳኞች ያላቸውን 85 አመራሮችና ሠራተኞችን በቁጥጥር ሥር አውሏል፡፡ “የመሬት ከበርቴውን” አባይ ጸሃዬንስ ማን ይደፍራቸው ይሆን የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል፡፡

በአባይ ጸሃዬ “ልክ እናስገባለን” ተግባራዊ እንዲሆን የታሰበው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በገጠመው ከፍተኛ ተቃውሞ ከተስተጓጎለ በኋላ ህወሃት/ኢህአዴግ ማስተር ፕላኑን “ትቼዋለሁ” ቢልም የኦሮሞ ሕዝብ ያስነሳው ተቃውሞ ግን እስካሁን አልበረደም፡፡

“መልካም አስተዳደርን አሰፍናለሁ” በሚል ኢህአዴግ የሕዝቡን ቀልብ ለመሳብ ከላይ ታች እየተራወጠ ነው የሚሉ ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ እንደሚሉት ኪራይ ሰብሳቢነት ለመዋጋት በሚል የሚደረገው ድራማ ሙስናን በማንኪያ የመንካት ያህል ነው፡፡ ምክንያቱም ከመሬት ጋር በተያያዘ በሙስናው እና በመሬት ዘረፋው የተጠመዱት ከፍተኛ የህወሃት ሹሞች ናቸው ይላሉ፡፡

“በየትኛውም ደረጃ ያሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ በደህንነት ውስጥ ያሉ ባለስልጣናትና መካከለኛ ደረጃ ሃላፊዎች በግልጽ ሙስና ውስጥ መዘፈቃቸው በመረጃ ቢቀርብም ጸረ ሙስና ኮሚሽን እርምጃ የማይወስደው ሙስና አንዱ የስርዓቱ እድሜ ማራዘሚያ መንገድ በመሆኑ ነው፤ ኢህአዴግን እያገለገሉ ያሉ ባለስልጣኖች ህወሃትን በሚገባ መከራከር የማይችሉትና በታዛዥነት እያጎበደዱ ለመኖር የሚገደዱት የገቡበትን የሙስና ማጥ ስለሚያውቁት ከተቃወምን እንታሰራለን” በሚል ፍርሃቻ መሆኑን የኮሚሽኑ ባልደረባ ለጎልጉል መናገራቸውን ከዚህ በፊት ዘግበን ነበር፡፡

በጥርስ አልባው የጸረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪዎች ዘንድ “የመሬት ባላባት/ከበርቴ” እየተባሉ የሚጠሩት አባይ ጸሃዬ ከሙሰኞቹ በቅድሚያ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ጎልጉል በመስከረም 2005ዓም ባተመው “የመሬት ባላባቱ” ሚኒስትር!! በሚለው ዜና ላይ አባይ ጸሃዬ በዘመዶቻቸው ስም በርካታ መሬቶችን መውሰዳቸውን፤ በተለይ በቦሌ ክፍለከተማ በመሬት አስተደዳር ሥልጣን የነበራቸው የአቶ አባይ የቅርብ ዘመድ መሆናቸውን፤ ከመሬት ጋር በተያያዘ የተፈጸመ ከፍተኛ ሙስና አለ በሚል ጸረ ሙስና በደረሰው ጥቆማ ምርመራ ጀምሮ ጉዳዩ “ወዳልተፈለገ” አቅጣጫ ሊያመራ ሲል ከበላይ በተላለፈ ትዕዛዝ ምርመራው እንዲቆምና በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩት መሃንዲሶች እንዲፈቱ መደረጉን ለጎልጉል ከደረሱት መረጃዎች ጋር በማጣቀስ ዘግበን ነበር፡፡

ሪፖርተር ጋዜጣ ረቡዕ ባወጣው ዜና 85 የመሬት አመራሮችና ሠራተኞች ሙስና ፈጽመዋል በሚል በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን፤ ከዚሁ የመሬት አስተዳደር ጋር በተያያዘ ከአዚህ በፊት 600 ሠራተኞች ላይ ዕርምጃ መወሰዱን ዘግቦ ነበር፡፡

ሰሞኑን የጎልጉል እማኝ ዘጋቢ (ireporter) በላኩልን መረጃ መሠረት እነዚህ 600 ያህል የሚሆኑት “ኪራይ ሰብሳቢነትን” እና “ሙስናን” ለመዋጋት በሚል “ዕርጃ የተወሰደባቸው” በትንሹ ለሰባት ዓመታት በመሬት አስተዳደር በመሃንዲስነትና ተመሳሳይ ሙያ ያገለገሉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በተለይ ደመወዛቸው አይነካም በሚል በዝቅተኛ የሥራ መደብ ላይ እንዲመደቡ የተደረጉት በራሳቸው ፈቃድ ሥራቸውን እንዲለቁና በምትኩ አንድን ወገን ያማከለ የታማኞች ቅጥር ለመፈጸም የተሰበ እንደሆነ እማኝ ዘጋቢው ያስረዳሉ፡፡

ከመሬት አስተዳደር ጋር በተያያዘ የሚፈጸሙ ወንጀሎችና የሙስና ተግባራት እንዳሉ የሚናገሩት ዘጋቢው ውሳኔው ወገንተኛና የሥርዓቱን ቁንጮዎች የማይነካ መሆኑ አግባብነት የሌለው ብቻ ሳይሆን ሕዝብን አፍ ማስዘጊያ የማባበያ ጥገናዊ ለውጥ እንደሆነ ይጠቁማሉ፡፡

ከዚህም ሌላ ሁለት መሠረታዊ ነጥቦችን እማኝ ዘጋቢው ይጠቅሳሉ፤ አንደኛው በሚነሱት ሠራተኞች ምትክ ባለሙያ ለመመደብ በቂ ዝግጅት አለመደረጉና በቅጥር ቦታቸውን ለመተካት የሚደረገው ሙከራ ኅብረተሰቡን ለተጨማሪ እንግልት የሚዳርገው ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ብዙ ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበት “የካይዘን መመሪያ (ፕሪንስፕል)” ለመተግበር በሚል በየክፍለከተማው የተሰጠው ሥልጠና ለነዚሁ ከሥራቸው የተነሱት ባለሙያዎች መሆኑ ሥልጠናውን ዋጋቢስ የሚያደርግ ሲሆን በሠራተኞቹ ላይ ተወሰደ የተባለው እርምጃ ግብታዊና ፖለቲካዊ ውሳኔ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡

ከዚህ ሁሉ በላይ የእማኝ ዘጋቢውም ሆነ የሌሎች አስተያየት ሰጪዎች ዋና ጥያቄ በሙስና የተዘፈቁትን የህወሃት ቁንጮ ባለሥልጣናትን ማነው የሚደፍራቸው የሚል ነው፡፡ “እነሱው ሙሰኛ፤ እነሱው የጸረ ሙስና ሕግ አውጪ፤ እነሱው የሕግ ተርጓሚ፤ እነሱው ፈራጅ፤ እነሱው አሳሪ፤ …” በሆኑበት አገር ዋንኞቹ የመሬት ነጣቂዎችና ከበርቴዎች ምንም ሳይሆኑ ከላይ ከላይ የሚወሰደው እርምጃ ጊዜያዊ ጥገናዊ መሻሻል እንጂ ተሃድሶአዊ ለውጥ እንደማያመጣ ይናገራሉ፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. gud says

    March 4, 2016 12:58 pm at 12:58 pm

    Abay is always clean of any corruption .

    Reply
  2. Yikir says

    March 6, 2016 06:38 pm at 6:38 pm

    Abayin yedefere jegina Meles ;Melesin yedefere ;ABEBE GELLAW SIHON ;ABEBE GELLAWIN YETEKAW ABEBE BIKILA NEW.

    Reply
  3. Solomon says

    March 24, 2016 05:41 pm at 5:41 pm

    Gud,

    I see now you are one of those members of the TPLF…. Why are you so coward to hide yourself say your name Tecklay or Kiflay no body is going to hunt you. I can tell that you are a 4th grader soldier but now a Minister.

    Reply
  4. Nimona Lammi says

    April 3, 2016 06:22 pm at 6:22 pm

    አባይ ፀሐይ ማለት የአመራር ብቃት ፣ የሥነልቦና ዝግጁነት ፣ የአካዳሚክ ዕውቀት ሳይኖረው በጫካ ውስጥ የውንብድና ተግባራት በመፈፀሙ በማሀይሞች ቡድን ላይ የነገሰ ሽፍታ እንጅ በምንም ታሀምር በኢትዮጵያ ውስጥ ወደ ሥልጣን የሚያመጣ ብቃትም ፣ ዕውቀትንም ሞራልም የሌለው መሐይም ነው ።በዚህ በዘገምተኛ እና በባዶ ጭንቅላቱ የሚፈፅማቸው የሚናገራቸው ነገሮች ከመናቅ ውጭ ምንም ልንለው አይገባንም ሰውዬው retarded (Ideot) ነው ።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአብን “ፀሐይ” ጎንደር ላይ ጠለቀች April 22, 2021 09:48 pm
  • ተፈትነን እንጂ ወድቀን አናውቅም April 22, 2021 10:55 am
  • ፍፁም ብርሃኔና ታምራት የማነ በቁጥጥር ሥር ዋሉ April 16, 2021 10:06 am
  • “ለአንድ ፓርቲ የማደላ ከሆነ ሄጄ እዚያው ፓርቲ እገባለሁ” ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ April 16, 2021 08:45 am
  • “ተዋግተን አይደለም ስንተኛ ብንውል እንኳን መቀሌና አዲስ አበባ አይገቡም” ጄኔራል ባጫ April 14, 2021 09:06 am
  • የስኳር ፋብሪካዎች ተሽጠው ዕዳቸውን እንዲከፍሉ ተወሰነ April 14, 2021 08:53 am
  • “ኤርትራዊ ነን” በማለት የመኖሪያ ፈቃድ ሲቀበሉ የኖሩ የትግራይ ሰዎችን መለየት ተጀመረ April 1, 2021 02:01 am
  • ምርጫ ቦርድ የኦነግን ጥያቄ ውድቅ አደረገ April 1, 2021 01:15 am
  • “እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ መንግሥት ኮሮጆ አይሰርቅም” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ April 1, 2021 01:09 am
  • መንግሥት ካልደረሰልን አሁንም ግድያ ይኖራል – ነዋሪዎች April 1, 2021 01:04 am
  • በትግራይ ሊዘረፍ የነበረ የእርዳታ እህል ተያዘ April 1, 2021 12:39 am
  • “በኢትዮጵያ ክብርና ጥቅም ከመጣችሁ አንገቴ ይቀላል እንጂ አልደራደርም” March 24, 2021 01:22 am
  • “ከዚህ በኋላ ህወሓት ማለት በነፋስ የተበተነ ዱቄት ነው” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ March 23, 2021 11:28 pm
  • እነ ስብሃት ነጋ ጥያቄያቸው ውድቅ ሆነ March 23, 2021 10:23 pm
  • በርግጥ ኢትዮጵያ ዝናብ አዝንባለች? March 23, 2021 10:15 pm
  • አሜሪካ በሴናተሯ አማካይነት “ለቅሶ” ደረሰች March 21, 2021 08:57 pm
  • ቪኦኤ በወለጋ ሆሮ ጉድሩ ለተጨፈጨፉ ኦነግ ሸኔን ከደሙ ንጹህ አደረገ March 19, 2021 04:32 pm
  • ባልደራስና የአብን የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ March 18, 2021 01:56 pm
  • ኤርሚያስ ለገሰ “የወያኔ የፕሮፖጋንዳ ሰራተኛ እያለ የለመደው የቁጥር ጫወታ አለቀቀውም” March 17, 2021 09:54 pm
  • በትግራይ ሰብዓዊ ድጋፍ በተቀላጠፈ ሁኔታ እየተካሄደ ነው – የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት March 17, 2021 04:54 am
  • ምርጫ ቦርድ ከፈቀደለት ኦነግ በምርጫው እንደሚወዳደር አስታወቀ March 17, 2021 04:30 am
  • በዓለምአቀፍ ሚዲያ ዘጋቢዎች ላይ እርምጃ ሊወሰድ ነው March 15, 2021 11:25 am
  • በሲዳማ/ሀዋሳ 128 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ፤ 2 መትረየስ ከ8,129 ጥይት ጋር ተያዘ March 15, 2021 10:13 am
  • የአክሱም ጅምላ ጭፍጨፋ ተብሎ የተሰራጨው ፎቶ የሐሰት ሆነ March 15, 2021 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule