ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፬” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አስራ አራት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡
መልስ
የወልደጊዮርጊስ ቢታይ ምስላቸው
ሁሉም ሰው አወቀ እስከታሪካቸው
እንደዚህ በሥራው ያገኘ ሰው ሞገስ
ምንግዜም ይኖራል በጥሩ ሲታወስ
ወልደዮሀንስም በልጃቸው ሥራ
አብረው ይጠራሉ ይዘው ትልቅ ስፍራ
ላሁኑ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፭” ደግሞ ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ በሚቀጥለው መልሱን በግጥም እናቀርባለን፡፡
ጥያቄ
አይቀርም ማትረፌ የአዕምሮ ወቀሳ
ከወልደጊዮርጊስ ጋር ተጣምረው የሰሩ
ትልቁ ሹመኛ እኚህም ነበሩ
የድሮውን ስቦ ወደፊት ጎትቶ
አቅርቦ ያመጣል ይናገራል ፎቶ
ይባላል እውነት ነው ይሄው አየናቸው
በሉ ተጥየቁ እኚህ ሰው ማናቸው?
Leave a Reply