• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የዳርፉሩ “ወንጀለኛ” ከደቡብ አፍሪካ አመለጡ

June 15, 2015 10:35 pm by Editor 2 Comments

* አልበሽር አገራቸው ሲገቡ “ደማቅ” አቀባበል ተደርጎላቸዋል

በዘር ማጥፋትና በሰብዓዊ ዘር ላይ ወንጀል በመፈጸም እንዲያዙ ማዘዣ የተቆረጠባቸውና ከደቡብ አፍሪካ እንዳይወጡ በፍርድቤት የተወሰነባቸው የሱዳኑ ተፈላጊ ወንጀለኛ ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር አምልጠው አገራቸው ገብተዋል፡፡

እሁድ ማምሻውን ከነበሩበት ቦታ በመሰወር ወደ ደቡብ አፍሪካ የአየር ኃይል ቤዝ በመደብ የቆዩት አልበሽር ሰኞ ዕለት ከተሰወሩበት አየር ኃይል ተነስተው አገራቸው ገብተዋል፡፡ እዚያም ሲደርሱ “ደማቅ” አቀባበል እንደተደረገላቸው ተነግሯል፡፡

1-jpgአልበሽርን ለመያዝ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩት የአይሲሲ ባለሥልጣናት ደቡብ አፍሪካ በፈጸመችው “ክህደት” በሚባል ተግባር እንዳዘኑ ገልጸዋል፡፡ ምክትል ዓቃቤ ሕጉ ጀምስ ስቴዋርት ለቢቢሲ እንዳሉት አሁንም ተስፋ በማድረግ ሥራቸውን እንደሚቀጥሉና ፍትህ እንዲበየን ቁርጠኛ አቋማቸው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የአልበሽር ማምለጥ ከተሰማ በኋላ ለጎልጉል አስተያየታቸውን የላኩ ወገኖች እንዳሉት ከሆነ የአልበሽርን እንዳይያዙ ሁኔታውን ካቀነባበረችው ደቡብ አፍሪካ ጀምራ በየትኛውም መልኩ ቢሆን ለአልበሽር አለመያዝ በሃሳብ ደረጃ እንኳን ሳይቀር የደገፉ ሁሉ ከኦማር አልበሽር ተለይተው እንደማይታዩ፤ ድርጊታቸውም እጅግ ጸያፍ እንደሆና ከሳሹ ማንም ይሁን የአልበሽር ደጋፊ የሆነ ሁሉ የዳርፉር ዕልቂት ደጋፊ ነው በማለትም አስታውቀዋል፡፡

በደቡብ አፍሪካ የተካሄደውንና የአልበሽር ጉዳይ ጥላ ያጠላበት የአፍሪካውያኑ መሪዎችን ስብሰባ በተመለከተ የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ አዜብ ታደሰና አርያም ተክሌ ያዘጋጁት ዘገባ እንደሚከተለው ይነበባል፡፡

የኧል በሽር ዉዝግብ የጋረደዉ የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤ

25ኛዉ የአፍሪቃ ሕብረት መንግሥታ የመሪዎች ጉባዔ ከትናንት ጀምሮ በደቡብ አፍሪቃ ጆሃንስበርግ ተካሄደ። በአይሲሲ የሚፈለጉት የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኧል በሽር ከደቡብ አፍሪቃ እንዳይወጡ አንድ ደቡብ አፍሪቃ ፍርድ ቤት ቢወስንም፤ ኧል በሽር ዛሬ ከቀትር በፊት ሃገሪቱን ጥለዉ ካርቱም ገብተዋል።

የአፍሪካ ሕብረት የወቅቱ ሊቀመንበር የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ በደቡብ አፍሪቃ ጆሃንስበርግ ላይ የተካሄደዉን የሁለት ቀን ጉባኤ በይፋ የከፈቱት በአፍሪቃ ጦርነት መቆም አለበት የሚል ጥሪን በማሰማት ነበር። ጆሃንስበርግ ላይ ለሁለት ቀናት የተሰየመዉ የአፍሪቃ ሕብረት ጉባዔ ግን ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት፣ አይሲሲ የእስር ማዘዣ ያስተላለፈባቸው እና በጉባዔው የተካፈሉት የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦመር ኧል በሽር ሀገር ለቀው እንዲወጡ አንድ ባሳለፈው ውሳኔ የተነሳ ተጋርዶ ነዉ የዋለዉ።

የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት አይሲሲ ለእስር የሚፈልጋቸዉ የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦመር ኧል በሽር ትናንት ደቡብ አፍሪቃ ጆሃንስበርግ ላይ በጀመረዉ የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤ ለመሳተፍ ቅዳሜ እለት ወደ ደቡብ አፍሪቃ ማቅናታቸዉ ጉባኤዉ በኧል በሽርና በአይሲሲ ዉዝግብ እንዲጋረድ ዳርጎአል። ትናንት እሁድ አንድ የደቡብ አፍሪቃ ፍርድ ቤት የሲዳኑ ፕሬዚዳንት ኧል በሽር ደቡብ አፍሪቃን ጥለዉ መዉጣት አይችሉም ሲል ወሰኔን ቢያስተላልፍም፤ የሱዳን የብዙኃን መገናኛዎች ኧል በሽርን የያዘዉ አዉሮፕላን ከፕሪቶርያ መነሳቱን ከቀጥር በፊት ቀደም ብለዉ ነበር ይፋ ያደረጉት። እንደ አብዛኞች እምነት ደቡብ አፍሪቃም ሮም ላይ የተረቀቀዉን ሕግ በፊርማ ያፀደቀች ሃገር በመሆዋ ኧል በሽርን ይዛ ለዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ተመልካች ፍርድ ቤት ማስረከብ አለባት አለባት የሚል ነበር። ደቡብ አፍሪቃ የአፍሪቃ ጥናት ተቋም ዳይሬክተር ዴቪድ ሆለ እንደሚሉት፣ ግን ደቡብ አፍሪቃ በአፍሪቃ ሕብረት ተስማምታ የፈረመችዉ ረቂቅ ፕሬዚዳንቶች ተይዘዉ እንዳይሰጡ የሚከላከል መድሕንን የሚሰጥ አንቀፅ አለ።sudan

“ደቡብ አፍሪቃ የአፍሪቃ ሕብረት አባል ሃገራት ከአይሲሲ ጋር እንዳይተባበሩ በሚያዘው ውሳኔ ላይ ድምፅ በተሰጠበት ጊዜ ነበረች፣ ውሳኔውንም በድምፅዋ አጽድቃለች። በዚህም ምክንያት የደቡብ አፍሪቃ መንግሥት በመጀመርያ ደረጃ እንደ እንደ ሕጋዊ የሕብረቱ አባል ሃገር ውሳኔውን የማክበር ግዴታ አለበት።”

በጉባኤዉ መክፈቻ የወቅቱ የአፍሪቃ ሕብረት መሪና የዚምባቢዉ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ፤ በአፍሪቃ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ሃገራት ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ አስምተዋል። ሙጋቤ ያለ ሰላም የአፍሪቃ የኤኮኖሚ አጀንዳ ስኬታማነት አይኖረዉም ሲሉም ተናግረዋል።

“በአንዳንድ የአህጉራችን ክፍሎች የሚታየዉ የፖለቲካ አለመረጋጋትና ፀጥታ መጓደል፣ የአፍሪቃ ሕብረት የተጠንቀቅ ጦር ርምጃ መውሰድ የሚችልበትን ሁኔታ ባስቸኳይ ማመቻቸት ምን ያህል አስፈላጊ መሆኑን አጉልቷል። ይህ ደግሞ እስከ ጎርጎረሳያዊዉ 2020 ዓ,ም ድረስ በአህጉሩ ማንኛዉም ጦርነት ለመግታት የያዝነዉን እቅዳችንን ከግብ በማድረሱ ጥረት ላይ ዋነኛ ርምጃ ነዉ።”

ሙጋቤ ሴቶች በአህጉሪቱ ለሚታየዉ ልማት ያላቸዉን አስተዋፅኦ በማወደስ ሴቶችን በንቁ ለማሳተፍ አፍሪቃ በቀጣይ ስልጣን ልትሰጣቸው እንደሚገባ ተናግረዋል።

የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ የአፍሪቃ ሃገራት በምዕራብ አፍሪቃ የተከሰተዉን ኤቦላ ተኃዋሲን ለመዋጋት ያደረጉትን ጥረት አወድሰዋል።

እንድያም ሆኖ በአፍሪቃ እያሻቀበ የመጣዉ ድሕነት፤ ሥራ አጥነትና ግጭቶች አህጉሪቱን ሥጋት ላይ መጣላቸዉ አልቀረም ሲሉ ነዉ የገለፁት። በዚህም ምክንያት በሽዎች የሚቆጠሩ አፍሪቃዉያን ብሩህ ሕይወትን ፍለጋ ወደ አዉሮጳ ለመግባት ሜዲተራንያን ባህር ላይ ያልቃሉ ሲሉ ድላሚኒ ዙማ ተናግረዋል።

“ሕዝባቻችንን በሳይንስ፣ በምሕንድስና፣ ቴክኖሎጂ እና በሂሳብ ትምህርት፣ እንዲሁም በምርምር ስራ ብናሳትፍ እና ብናሰለጥን ህዝባችን በሳህል በረሃ እና በሜዲተራንያን ባህር አደገኛ ጉዞን ያቆማሉ።”

የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ በበኩላቸዉ በሁለቱ ቀናት ጉባኤ መሪዎቹ አህጉሪቱን ለመቀየር በሚያስችሉ ነጥቦች ላይ ይነጋገራሉ።

“አፍሪቃ በአዲስ የልማትና እድገት ጎዳና ላይ ትገኛለች፤ ይህ ደግሞ በዓለም የፖለቲካ መድረክ ለመሳትፍ የሚሳችላት አቅጣጫ ነዉ።” ኧል በሽር ላይ የደቡብ አፍሪቃዉ ፍርድ ቤት ያሳለፈዉን ዉሳኔ ተከትሎ የደቡብ አፍሪቃ ገዥ ፓርቲ ANC እሁድ ICC ጥቅም የሌለዉ ተቋም ነዉ ሲል ዉሳኔዉን ማስተባበሉ ይታወቃል። እስካሁን ወደ 20 የሚጠጉ አፍሪቃዉያን ኔዘርላንድስ፣ ዴንሃግ በሚገኘዉ የጦር ወንጀለኞች ተመልካች ፍርድ ቤት ክስ የተመሰረተባቸዉ ሲሆን ፤ ከነዚህ መካከል የቀድሞ ኮት ዲቯር ፕሬዚዳንት ሎር ባግቦን ጨምሮ እስካሁን ሁለት ክሶች ብይን ማግኘታቸዉ ይታወቃል።

የአፍሪቃ ሕብረት መንግሥታትና ርዕሳነ ብሔራት ደቡብ አፍሪቃ ላይ ትናንት የጀመሩት ጉባኤ ዛሬ ምሽት ላይ በይፋ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል። በጉባኤ ላይ ከተነሱት በርካታ የመነጋገርያ ነጥቦች መካከል አሸባሪነትን፤ ስደትንና ድህነትን ማጥፋት የተሰኙት ርዕሶች ይገኙበታል።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Asefa says

    June 16, 2015 06:53 am at 6:53 am

    He may runaway from the physical court but not from his conscious. Hundreds of thousands of dead people are haunting him everyday.

    Reply
  2. በለው ! says

    June 16, 2015 10:03 pm at 10:03 pm

    “አልበሽር አሸብር! በረጅም ገመድ ታስረው ተለቀቁ በለው! ይህ ወንጀለኛ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሻርና መሰወር እሥር ቤት ሰብሮ እንዳመለጠ አንዲሁም (ፍርድ ቤትን መዳፈር) ድርብ ወንጀል ይሆናል። ምንም እንኳ ፍርድ ከመሰማቱ በፊት ጠፍተዋል ቢባልም ችሎቱ ከመሰየሙ በፊት የእሥር ማዘዣው ወጥቷል። ለመጥፋታቸው ፍቃድ የሰጡ የተባበሩ ሁሉ ተጠያቂ ናቸው አልበሽር ጥፋተኛነታቸውን በግልፅ አምነዋል! ።
    ***ደቡብ አፍሪካ(የአፍሪካ ሀገራት) የፍርድ ቤቶች ገለልተኝት እዚሁ ድርስ ነው(የደቡብ አፍሪካ ፍርድ ቤት አልበሽርን የእሥር ማዘዣ አወጣ የቁም እሥረኛ አደረጋቸው” “የዙማ መንግስት አልበሽርን አጅቦ ወደሀገራቸው ሸኛቸው!?”…
    ልክ እንደ ኢህአዴግ
    ___”ሰላማዊ ሰልፉ እውቅና አገኘ ይልና…. “ፖሊስ ሰልፉን ከለከለ ይላሉ…
    ___”ዳኛው እሥረኛውን በነፃ አሰናበቱ!ብሎ….”ፖሊስ ማስረጃ እያሰባሰብኩ ነው ብሎ ግለሰቡን አለቅም አለ ይላሉ…
    ____በሕገመንግስቱና በፓለቲካ ፓርቲው/ገዢው ፓርቲ/አውራው ፓርቲ/ህወአትኢህአዴግ መልካም ፍቃድ. ” ማናቸውም እሥረኛ በሕግ ጠበቃው በሃይማኖት መሪዎች ፣ በዘመድና በቤተሰቡ ይጎበኛል ይልና….. “የእስር ቤቱ ተረኛ ጠያቂዎችን ደብድበው አበረሩ ይላል
    እውነትም ህወአት/ኢህአዴግ ለሌሎች ሀገራት ተምሳሌት ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም ሁለተኛ ነው!? –

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule