• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኦማር አልበሽር ከደቡብ አፍሪካ እንዳይወጡ ታገዱ

June 15, 2015 05:41 am by Editor 1 Comment

ዓለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድቤት የከሰሳቸውና እንዲያዙ ማዘዣ የቆረጠባቸው የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ለአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ከሄዱበት ደቡብ አፍሪካ እንዳይወጡ እዚያ የሚገኝ ፍርድ ቤት ማዘዣ ሰጠ፡፡ በኢትዮጵያ በሰው ዘር ላይ ወንጀል ለፈጸሙ የህወሃት ሹሞች ይህ ታላቅ ማስጠንቀቂያ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ኦባንግ ሜቶ አስታወቁ፡፡

በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል አይሲሲ የሚባለው ዓለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድቤት የሱዳኑን ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር የዛሬ ስድስት ዓመት አካባቢ በዘር ማጥፋትና በጦር ወንጀለኝነት ክስ መስርቶ እጃቸውን እንዲሰጡ ወይም እንዲያዙ ማዘዣ ቆርጦባቸው ነበር፡፡ የተወነጀሉበት ክስም በደቡብ ሱዳን አማጽያንን ትረዳላችሁ በማለት ሦስት ጎሣዎች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም፣ ሴቶች እንዲደፈሩ፣ ነዋሪው እንዲፈናቀል፣ እንዲገደል፣ ወዘተ የጃንጀዊድ ሚሊሻዎችን በማስታጠቅ በሥፍራዎቹ አሰማርተዋል በሚል ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት 400ሺህ ዜጎች ሲሞቱ ከ2 ሚሊዮን በላይ ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል፡፡

ፍርድቤቱ ማዘዣውን ካወጣ ጀምሮ አልበሽር ጥፋተኛ እንዳልሆኑ ከመናገር ባሻገር ወደ ውጭ የሚያደርጉትን ጉዞ በመወሰን በወዳጅ የአፍሪካና የአረብ አገራት ብቻ ወስነው ቆይተዋል፡፡ ከኢህአዴግ መሪዎች ጀምሮ በርካታ የአፍሪካ አገራት አምባገነኖች ለአልበሽር ድጋፍና ከለላ ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡

በዚምቧብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ሊቀመንበርነት በሴቶችና ልማት ላይ ለተጠራው የአፍሪካbashir ኅብረት መሪዎች ስብሰባ ላይ የተገኙት የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ወደዚያው በሚያቀኑበት ወቅት የፍርድቤቱ ማዘዣ የሚጸና በመሆኑ እጃቸውን መስጠት እንዳለባቸው ሲነገር ነበር፡፡ ሆኖም አልበሽር ከዚያ በተጻራሪው በስብሰባው ላይ በመገኘት ከተሰብሳቢ የአፍሪካ መሪዎች ጋር የቡድን ፎቶ ሲነሱ ታይተዋል፡፡

በዓለምአቀፍ ደረጃ የሚንቀሳቀሱ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች ከደቡብ አፍሪካ ተሟጋቾች ማዕከል (Southern Africa Litigation Center) ጋር በመሆን የአልበሽርን በደቡብ አፍሪካ መገኘት በማስመልከት ፕሪቶሪያ ለሚገኘው ፍርድ ቤት ባቀረቡት ማመልከቻ መሠረት የሰሜን ጉተንግ ከፍተኛ ፍርድቤት ዳኛ ሃንስ ፋብሪሺየስ ኦማር አልበሽር ከደቡብ አፍሪካ እንዳይወጡ የፍርድ ቤት ማዘዣ ቆርጠውባቸዋል፡፡ የአልበሽር ጉዳይ እሁድ ይታያል ተብሎ ሲጠበቅ ጉዳያቸው ለሰኞ እንዲተላለፍና እስከዚያው ግን ከደቡብ አፍሪካ መውጣት እንደማይችሉ በዳኛው በኩል የተሰማው የፍርድ ትዕዛዝ ያስረዳል፡፡

ከኦማር አልበሽር በተጨማሪ የሙስሊም ጠበቆች ማኅበር የግብጹ ፕሬዚዳንት አብደል ፈታህ ኤል ሲሲ በአፍሪካውያኑ ኅብረት ስብሰባ በሚገኙበት ወቅት እንዲያዙ በፍርድ ቤት ማመልከቻ አቅርበው ነበር፡፡ ጠበቆቹ በማመልከቻቸው እንደገለጹት ኢል-ሲሲ የጦር ወንጀለኛ እና ከሁለት ዓመት በፊት በሕጋዊ መንገድ የተመረጡትን ሞሐመድ ሙርሲን በመገልበጥ ወንጀል ከሰዋቸዋል፡፡ አልሲሲ እንደ አልበሽር በዓለምአቀፉ ፍርድ ቤት የተከሰሱና ማዘዣ ያልተቆረጠባቸው ቢሆንም በአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ላይ ሳይገኙ ቀርተዋል፤ በምትኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢብራሒም ሜህሌብ መገኘታቸው ከሥፍራው የተገኘው ዜና ያስረዳል፡፡

stanton_and_metho
ዶ/ር ግሬጎሪ ስታንተንና አቶ ኦባንግ ሜቶ በዘር ማጥፋት የተባበሩት መንግሥታት ሸንጎ ፎቶ AJC

የፕሬዚዳንት አልበሽር ጉዳይ በዓለምአቀፉ ፍርድ ቤት ከመወሰኑ በፊት በኅዳር 1999ዓም በወቅቱ የአኙዋክ ፍትሕ ምክርቤት ዳይሬክተር የነበሩት ኦባንግ ሜቶ በተባበሩት መንግሥታት ዓለምአቀፍ የዜጎች ፍርድቤት (THE INTERNATIONAL CITIZENS’ TRIBUNAL FOR SUDAN) ላይ በዳኝነት ተሳትፈው ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የሚባል ለማኅበራዊ ፍትሕ መስፈን የሚታገል ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ኦባንግ የአልበሽርን ጉዳይ በተመለከተ የተላለፈው ውሳኔ በዘር ማጥፋት፣ በሰብዓዊ ዘር ላይ ወንጀል በመፈጸም እና በሌሎች ከፍተኛ ወንጀሎች ለሚጠረጠሩት የህወሃት ባለሥልጣናት ታላቅ ማስጠንቀቂያ እንደሆነ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል፡፡

ከ400 በላይ የአኙዋክ ተወላጆች መገደል በቀጥታ ተጠያቂ ከሆኑት የህወሃት ባለሥልጣናት መካከል መለስ ብቻ በሞት የተለዩ ቢሆንም ሌሎቹ ግን እስካሁን በህይወት ያሉ በመሆናቸው ከተመሳሳይ ፍርድ እንደማያመልጡ አቶ ኦባንግ አስታውቀዋል፡፡ ከአኙዋክ ዕልቂት ሌላ በኦጋዴን ለተደረገው ጭፍጨፋ እንዲሁም ምርጫ 1997ን ተከትሎ ለሞቱት 200 የሚጠጉ ዜጎች መሞት ተጠያቂ የሆኑት የህወሃት/ኢህአዴግ ባለሥልጣናት በየትኛውም መልኩ ቢሆን ከፍትሕ እንደማያመልጡ ኦባንግ ሜቶ ጨምረው አስረድተዋል፡፡

በኅዳር 1999 ዓም በተደረገው የዜጎች ፍርድቤት ውሳኔ አሠጣጥ ሥነሥርዓት ላይ አቶ ኦባንግ በተሰጣቸው የዳኝነት ሥልጣን ስለ ኦማር አልበሽር የውሳኔ ሃሳባቸውን ሲሰጡ እንዲህ ብለው ነበር፤ “የአልበሽር ጉዳይ ገና በዓለምአቀፉ ፍርድቤት የተወሰነ ባይሆንም እኛ እዚህ የምንሰጠው ውሳኔ ግን ህጋዊ ስለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለኝም፤ ኦማር አልበሽር ዛሬም ወንጀለኛ ነው፤ ነገም ወንጀለኛ ነው፤ የዛሬ ወርም ወንጀለኛ ነው፤ የዛሬ ዓመትም ወንጀለኛ ነው፤ የዛሬ አስር ዓመትም ወንጀለኛ ነው፤ . . . የዛሬ መቶ ዓመትም ወንጀለኛ ነው፤ ለዘላለም ወንጀለኛ ነው፤” ለተወሰኑ ጊዜያት ከፍትሕ የሚያመልጥ መስሎ ሊታይ ይችላል፤ በኃይልና በማታለል በሥልጣኑም ሊቆይ ይችላል፤ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ከፈጸመው ወንጀል ተጠያቂ ከመሆን መቼም አያመልጥም፤ “ጨካኞች የሰው ልጆችን በማሸበር የተሳካላቸው መስለው ቢታዩም በፍርድ የማያዳላው ፈጣሪ በመለኮታዊ ፍርድ ቤቱ ተጠያቂ አድርጎ ያቀርባቸዋል፤ በዚያ የፍርድ አሰጣጥ ወቅት የፈሰሰው ሰብዓዊ ፍጡር ደምና ሰቆቃ በሙሉ ምስክር ሆኖ ይቀርብባቸዋል፤ ዓለም ሁሉ ይህንን ሊያስተውል ይገባዋል” በማለት ኦባንግ ሜቶ የፍርድ ውሳኔያቸውን በወቅቱ ሰጥተው ነበር፡፡ (የአቶ ኦባንግ ሙሉ የፍርድ ውሳኔ እዚህ ላይ ይገኛል)

አልበሽር ከደቡብ አፍሪካ እንዳይወጡ ያዘዘው ፍርድ ቤት ዳኛ የደቡብ አፍሪካን የአገር ውስጥ ሚኒስቴር መ/ቤት ኦማር አልበሽር በየትኛውም መንገድ ማለትም በአየር፣ በየብስና በባህር ከደቡብ አፍሪካ እንዳይወጡ ሁሉንም የመውጫ ኬላዎች በጥብቅ እንዲቆጣጠር ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡ የዳኛውን ትዕዛዝ ተከትሎ የአልበሽር ጉዳይ እስኪጠናቀቅ ድረስ ፕሬዚዳንቱ ከደቡብ አፍሪካ አፈር እንዳይወጡ ጥብቅ ክትትል እያደረገ መሆኑን የሚኒስቴር መ/ቤቱ አስታውቋል፡፡

ከሱዳን ዘግይተው የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ኦማር አልበሽር ከፍርድ ቤቱ ማዘዣ በፊት ደቡብ አፍሪካን ለቅቀው መውጣታቸውን ቢገልጹም ፕሬዚዳንቱ ማዘዣው ከወጣ በኋላ በአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ላይ መታየታቸውንና ከአገሪቱ ለቅቀው አለመውጣታቸውን ያስረዳሉ፡፡ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በጉዳዩ ላይ ባደረገው ማጣራት መሠረት ኦማር አልበሽር በደቡብ አፍሪካ እንደሚገኙና ከዚያም ለቅቀው እንዳልወጡ ከመረጃ አቀባዮቹ ለመረዳት ችሏል፡፡

ከሁለት ዓመት በፊት በናይጄሪያ በተካሄደ ስብሰባ ላይ የናይጄሪያ ጠበቆች አልበሽርን ለማስያዝ ያደረጉት ሳይሳካ መቅረቱ ይታወሳል፡፡ ጠበቆቹ ውሳኔያቸውን በፍርድ ቤት ከማሳወጃቸው በፊት አልበሽር ስብሰባውን አቋርጠው ወዳገራቸው ተመልሰዋል፡፡ አሁን ግን ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲመጡal-bashir ወዳጆቻቸው የአፍሪካ አምባገነኖች መከታ ይሆኑኛል በሚል እንደሆነ ተገምቷል፡፡ ሰኞ የሚውለው ችሎት አልበሽር ወዳገራቸው መመለስ እንደሚችሉ ወይም በዓለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድቤት ማዘዣ መሠረት ለፍርድቤቱ ተላልፈው እንዲሰጡ ይወስናል፡፡ ፍርድ ቤቱ አልበሽር እንዲያዙ ከወሰነ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት አሳልፎ የመስጠት ሕጋዊ ግዴታ አለበት ሲሉ የሕግ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ሆኖም ግን የ1998 (እኤአ) የሮም ስምምነት ፈራሚ የሚባሉ አገራት ወንጀለኞችን አሳልፈው ለመስጠት ፈቃደኝነት የሚጠበቅባቸው ሲሆን በማያደርጉ አገራት ላይ ፍርድቤቱ ቅጣት የመበየንም ሆነ ወንጀለኛውን ለመያዝ ሊያሰማራ የሚችለው የፖሊስ ኃይል የለውም፡፡

የደቡብ አፍሪካ መንግሥት የአገሩ ፍርድቤት ባስተላለፈው ትዕዛዝ ላይ አስተያየት ከመስጠት የተቆጠበ ቢሆንም በአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ላይ የሚገኙ መሪዎች ያለመከሰስና ያለመታሰር መብታቸው የተከበረ መሆኑን ከመናገር በስተቀር ያለው አለመኖሩ በአልበሽር ጉዳዩ አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱን እንደሚጠቁም ተገልጾዋል፡፡ የሰብዓዊ መብት ጠበቆች እንደሚሉት ከሆነ አልበሽር የፍርድቤቱ ትዕዛዝ ከተላለፈ በኋላ በደቡብ አፍሪካ መቆየታቸው ተረጋግጧል፤ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ናቸው፤ ሰኞ ዕለት የሚሰየመው ፍርድ ቤት የዓለምአቀፉ ፍርድ ቤት የማዘዣ ውሳኔ ያጸድቃል፤ ደቡብ አፍሪካም ለፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ተገዢ መሆን አለባት ይላሉ፡፡ የዓለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድቤት ዓቃቤሕግ የሆኑት ፋቶው ቤንሱዳ “ፕሬዚዳንት አልበሽር ሔግ ለሚገኘው ፍርድ ቤት ተላልፈው እንደሚሰጡ እየጠበቅሁ ነው፤ ይህንን ማድረግ ትክክለኛና ሕጋዊ አሠራር ነው” ብለዋል፡፡ (የመግቢያው ፎቶ: Shiraaz Mohamed/Associated Press)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. በለው ! says

    June 15, 2015 08:00 am at 8:00 am

    ጨዋታው ደራ! ጭፍራው ደራ! አሉ//
    ..ደቡበ አፍሪካ ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ያልሆነች ለማን አፍሪካዊ ሀገር መሪና ህዝብ ልትሆን ነው!? በመሠረቱ የነጮችን ባሕል ግብረሰዶምን ተቀብሎ ለማፅደቅ..ይህ ሀገር ለእኔ ብቻ ነው.. ዘረኝነትን..የሌላ አፍሪካዊን መዝረፍና መግደልን ያከበረች ሀገር የባሪያ አሳዳሪዎቿ ያስፈረሟትን ጥፋተኛን ይዞ ለፍርድ የማቅርብ ሕግ የማትፈጽምበት ምንም ነገር የለም። መቼም በእኛ ወገኖች ሞት ያልጮሁ አፍሪካውያን ለአልበሽር ካላቀሱ ሁሉም ሌባ! ነፍሰ ገዳይ! አንባገነን! የተጠረነፉ ጥቅማጥቅመኛ መሪዎች ናቸው ማለት ነው። ፬፻ሺህ ቢሞት ፪ሚሊየን ቢሰደድ ምን ችግር አለ እነኝሁ የፍርድ ቤቱ አባላት ሀገሮች በሱዳን ነዳጅ ማውጣታቸው ንግድ ማጧጧፋቸው አልቆመም!።ይህ ሁሉ ሕዝብ ሞቶና ተሰዶ ባንበላስ አፈር እንብላ አላሉም! በልተው ያባላሉ ያበላሉ….!
    — የዓለም መሪዎች እንዲህ ለንፁሐን ድሃ ሱዳን የአፍሪካዊ ሕዝብ ተቆርቋሪ ከሆኑ ለምን በወቅቱ ከሥልጣን አላወረዱትም! አልበሽር በኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ኤርትራና የመን ሲንጎማለል አልነበረምን!? ይልቁንም ሸሽተው እስራኤል የተጠለሉ ሱዳናውያንን ሲያስሩ፣ ሲደበድቡ፣ በውሻ ሲያስነክሱ ከሀገራችን ውጡ ሲሉ ሲዘለፉ ይታይ አልነበረምን!? ስንቶች በባሕር በበረሃ ተደፍተው ቀርተው የለምን!? አብሮ የኖረን ሕዝብ በቁመት በቀለም በዘር በነገድ በሃኢማኖት ከፍሎ የሚያተራምሰው ማን ሆነና ነው?እጀ እረጃጅሞቹ አደሉምን!?–ነገሩ ጨዋታም ሊሆን ይችላል “አውርተን ከሚቀር እንደ ኬንያው ባለሥልጣን አድርሰን እንመልስሃለን ተብሎ ይሆናል ጠርጥር…
    —- ምንአልባትም እነ ጭር ሲል አንወድም አካባቢው ላይ ‘አልበሽርን አስረው’+ ‘አሲስን ፈተው ይለቃሉ’ = አሸብር ሆነ በለው!
    — አሁን ኀይለመለስ(ኢህአዴግ) ለዙማ ማስጠንቀቂያ ይጽፉ ይሆን? ወይንስ አይ ሲ ሲ(ICC) ቀርበው ነግ በእኛ ነውና ዘረኝነት ይቁም! እኛ ችግሩን እንፈታለንና አፍሪካ ውስጥ ድርሽ እንዳትሉ ይሉ ይሆን…ይች እጅ በማወናጨፍ የቀጠለች ዕራይ አንዱ ቦታ አላግባብ ገብታ ሳትቀበቀብ ወረዳ አስተዳዳሪነቱን ወይም አምባሳደርነቱን ቦታ በግዜ ቢይዝ መልካም ነው። አፍሪካን እንደመውደዳችን በአፍሪካዊነታችን እንደመኩራታችን በመሪዎቻችን እያፈርን አስከመቼ!?የሚያበድርና የሚያስለምኑ ሀገራት ትንሽ ቁንጢጥና ቁጣ ሲጨምሩበት ለምን እንዲህ አፋቸውን ከፍተው ያለቅሳሉ?ከዚህ ሁሉ የአፍሪካ አምባገነን ገዢዎች ለሕዝባቸው አገልጋይ እንጂ ህዝባቸውን ባሪያ አድረጎ ለመኖርና ለማኖር ማን ፈቀደላቸው? ለምን ይደክማሉ እንዳንዴም እንዲህ ማረፊያ ቤት ከተገኘ በእየተራ መሔድ ጥሩ ነው።ያልደረሰ ይድረሰው…ብለናል ለጉልበተኛም ጉልበተኛ በሠላም እንድንተኛ!!!!
    ********
    ነጭ አይደፍረንም የሚለው አፋቸው
    ሄደዋል አይሉ ቆመው አልሸኟቸው
    እንቢ አሉ አይሉ አላየናቸው
    አስረከብን ካሉ ማፈሪያዎች ናቸው
    አልበሽር ሲታገት ጀሌው ምን ዋጣቸው
    የአፍሪካ አንድነቶች ምን አሉ ሲገቡ አገራቸው!?

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን May 26, 2022 09:18 am
  • “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች” May 26, 2022 08:19 am
  • የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች May 19, 2022 09:37 am
  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am
  • አገር አፍራሹ ትህነግ ለቀለብ፣ መድኃኒትና ሥራ ማስኬጃ 76 ቢሊዮን ብር ቀርጥፏል May 16, 2022 08:30 am
  • ሰብዓዊ እርዳታ ወደ መቀሌ መግባት መቀጠሉ ተገለጸ May 16, 2022 03:07 am
  • እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ May 15, 2022 09:38 am
  • የትህነግና ሸኔ መሠልጠኛ የምትባለው ዩጋንዳ መከላከያ ሚ/ር ከኤታማዦር ሹሙ ጋር ተወያዩ May 13, 2022 09:55 am
  • በትግራይ የውጊያ ምልመላው ጉዳይ May 11, 2022 02:37 am
  • መከላከያ በተጨማሪ ድሮን፣ በሥልጠና፣ በዝግጅት ራሱን አብቅቷል May 11, 2022 01:35 am
  • ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ May 10, 2022 01:04 pm
  • ኤርትራ 8 ሩስያ ሠራሽ ድሮኖችን ተረክባለች May 10, 2022 12:37 am
  • ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ May 9, 2022 01:46 pm
  • በወልዲያ ፋኖዎች ተመረቁ May 9, 2022 12:51 pm
  • “ሠራዊታችን ድልን በአስተማማኝ መልኩ ማምጣት በሚችል ቁመና ላይ” ጀኔራል ጌታቸው May 9, 2022 11:57 am
  • ዋጋው 64 ሚሊዮን ብር የሚሆን (16 ኪሎ) ሕገወጥ ወርቅ ተያዘ May 9, 2022 11:51 am
  • አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ May 9, 2022 08:58 am
  • ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ May 9, 2022 08:17 am
  • በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ May 8, 2022 12:39 am
  • በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ May 6, 2022 09:35 am
  • በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ May 4, 2022 11:04 pm
  • ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ May 4, 2022 09:04 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule