• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከቅዳሜው የህወሓት ሰልፍ በፊት በትግራይ “ከዓቅም በታች የሰረቁ” ተፈረደባቸው

December 7, 2018 06:21 am by Editor 3 Comments

ቅዳሜ በህወሓት አስገዳጅነትና ተለማማጭነት አሁን በመላው ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ለውጥ የመቃወም እንደምታ ያለው ሰልፍ ተጠርቷል። እስካሁን ድረስ በርካታ መረን የወጣ ሌብነት የፈጸሙ፣ እጅግ አሰቃቂ የሰብዓዊ መብቶችን የጣሱና ሌሎች ተፈላጊ ወንጀለኞችን በትግራይ ደብቆ የያዘው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) በኤፈርት አልባሽነት ቅዳሜ “ሰላማዊ” ያለውን ሰልፍ በመቀሌ፣ ትግራይ ጠርቷል። ሌብነትን እንቃወማለን ለማለትም በአንዳንዶች ዘንድ “ከዓቅም በታች የሰረቁ” የተባሉ አነስተኛና ጥቃቅን ሌቦች ላይ ፍርድ አስተላልፏል።

የመቀሌ ከተማ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ዘመንፈስቅዱስ ፍሰሃን ጠቅሶ ኢዜአ እንደዘገበው የሰልፉ አንዱ ዓላማ “ህገመንግሥቱ ይከበር” የሚል ነው ብሏል። ይህ በህወሓት አነጋገር ከአንቀጽ 39 ጀምሮ በርካታ ነገሮችን ሊያስብል የሚችል አገላለጽ፤ ህወሓት ከሁለት ዐሥርተ ዓመታት በላይ ሳያከብረው የኖረውን ህገመንግሥት አሁን ግምባር ቀደም የመታገያ መሣሪያ ማድረጉ አስቀድሞ ለራሱ የሠራው ሥራ እንዳለ አመላካች ነው።

ከዚህ ሌላ በሰልፉ ላይ “የትግራይን ህዝብ ለማምበርከክ የሚደረጉ ሴራዎች ተቀባይነት” የላቸውም፤ “በማንነት ጥያቄና በአዋሳኝ አካባቢዎች ምክንያት በማድረግ የክልሉን ህዝብ የሚነኩ ትንኮሳዎች” አንቀበልም፤ የውጭ ጣልቃ-ገብነትና የውስጥ ሤራዎች እንዲቆሙ እንጠይቃለን፤ ወዘተ የሚሉ መልዕክቶች በሰልፉ እንደሚተላለፉ ዘመንፈስቅዱስ አመላክተዋል።

ይህ አስቀድሞ ምን ያህል ሕዝብ እንደሚወጣበት፣ ምን ዓይነት መፈክር እንደሚፈከርበት ተጠናቆና ተዘጋጅቶ የተጠራ ሰልፍ፤ የትግራይ ሕዝብን በየትኛውም መልኩ እንደማይደግፍ አንዳንድ የትግራይ ተወላጆች ይናገራሉ። ሆኖም በዚህ በ“ባሎኒ” ስታዲየም የተጠራውን ሰልፍ ሕዝባዊ ቁመና ለማላበስ ህወሓት የተለያዩ የሚዲያ ተወካዮችን በክልሉ መስተዳድር ስም በክብር በደብዳቤ ጋብዟል። ምን ያህሉ እንደሚገኙ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት ውስጥ በአሸባሪነት እስካሁን ተመዝግቦ የሚገኘው ህወሓት፤ የወንበዴው ቡድን አምበል የነበረውን የመለስ (ለገሰ) ዜናዊ ፎቶ ያለበትን ቲሸርት መቀሌ ላይ ሕዝቡን አስለብሶ ሐሙስ ዕለት የድጋፍ ሰልፍ አስወጥቷል። በመላው ኢትዮጵያ የሚገኘው ሕዝብ የመለስን ፎቶ ላለማየት ካለበት ቦታ ሁሉ አውርዶ አገሩን በተረከበበት ጊዜ (ከፓርላማም በዚህ ዓመት የመለስ ፎቶ ተወግዷል)፤ ህወሓት የማሌሊትን ጨርቅ በግድ አስለብሶ ሕዝቡ እንዲታይ አድርጓል።

በሌላ በኩል የሌባና የወንጀለኛ ተባባሪ ደባቂ በመሆን ሰሞኑን በተለያዩ ሁኔታዎች ስሙ ሲወቀስ የነበረው ህወሓት፤ በትግራይ 63 ግለሰቦችን በእስርና በገንዘብ ቀጥቻለሁ ብሏል። አሃዱ ሬዲዮ እንደዘገበው ከሆነ “የክልሉ የስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ የህዝብና የመንግስት ሀብትን በመዝረፍና ፍትህን በማዛባት ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል የተባሉ 63 ግለሰቦች በእስርና በገንዘብ እንዲቀጡ ማድረጉን አስታወቋል። በግለሰቦቹ ተዘርፎ የቆየ 8 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብና ከአንድ ሺህ ካሬ ሜትር በላይ የከተማ መሬት ወደ መንግስት ካዝና እንዲመለስ፤ ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ 52 ግለሰቦች ከ6 እስከ 8 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት፤ 11ዱ ደግሞ ከ9 እስከ 16 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ እንደተላለፈባቸው” ሬዲዮው ኮሚሽነሩን በመጥቀስ ዘግቧል።

ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ እንደሚሉት በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ እየተቃወመ ያለው ህወሓት፤ አሁን ደግሞ ሌቦችንና በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን ሸሽጎ ስለሚገኝ ለዚህ ማጣፊ እንዲሆን ያደረገው ነው ይላሉ። ሁኔታው ያልጣማቸውና ከዚህ በላይ በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ሌብነትና ወንጀል የፈጸሙትን የህወሓት ሰዎች አሳልፎ ከመስጠት ልቅ እነዚህን “ከዓቅም በታች የሰረቁ” ግለሰቦችን በመቅጣት ራሱን ከተጠያቂነት ለማስመለጥ የሚያደርገው ከንቱ ልፋት ነው በማለት አስተያየታቸውን ይሰጣሉ።

ከበረሃ ጀምሮ በውንብድና ተግባሩ በዓለምአቀፍ ደረጃ የሚታወቀው ህወሓት፤ ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም የግል ንብረቱ አድርጎ ሲበዘብዝና የፈለገውን ግፍ ሲፈጽም የቆየበት ጊዜ እያከተመ ሲመጣ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ብጥብጥ በማስነሳትና ስፖንሰር በማድረግ ዓላማውን ለማስፈጸም ሲጥር እንደነበር ይነገራል። በተለይ በሶማሊ ክልል ሤራው ከከሸፈ በኋላ በጋምቤላም በተመሳሳይ ሁኔታ አመራሮቹ ተነስተው ለውጥ በክልሎቹ ሥር እየያዘ ነው። በቀጣይነት ደግሞ ዋና ምሽጉ አድርጎ ሲንቀሳቀስበት የነበረው የአፋር ክልል በአሁኑ ጊዜ በለውጥ እንቅስቃሴ ላይ የሚገኝ ሲሆን ቤንሻንጉልም በዚያው መስመር ላይ ይገኛል። ይህ ሲጠናቀቅ ህወሓት በግፍ አፍኖ በያዘው የትግራይ ሕዝብ መተፋቱ እንደማይቀር ብዙዎች የሚስማሙበት ነው።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Filed Under: News, Politics Tagged With: Full Width Top, meles, Middle Column, tigray, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    December 7, 2018 03:29 pm at 3:29 pm

    የትግራይ ህዝብ ጠላቱ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ነው። ሌላው ሁሉ ለፓለቲካ ፍጆታ የሚናፈሰና መሰረት በሌለው በጅሎች የፓለቲካ እይታ የታጀበ ነው። ገና ከበረሃ ጀምሮ በትግራይ ህዝብ ስም ሃበሳን ሲያመነጭ የኖረው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ለ 27 ዓመት የከተማ አለቃ ከሆነም በህዋላ ለትግራይ ህዝብ ያደረገው ከዚህ ግባ የሚባል ነገር የለም። በበረሃ በትግራይ ህዝብ ስም ሲነግድና ሲያተርፉ የነበሩ በከተማም በትግራይ ህዝብ ስም ነጋዴና ቀማኛ በመሆን ለራሳቸውና ለዘመዶቻቸው በሃገርና በውጭ ያካበቱት ሃብት ምሥክር ነው።
    በቀበሌ ጥሩንባ ያለ ልቡ ለሰላማዊ ሰልፍ የትግራይ ህዝብ ወጣ የሚባለውም ትሩፋት የለሽ ውስልትና ነው። የወያኔ የማወናበጃ ዋና ተግባሩ የትግራይን ህዝብ ማስቀደምና ጥይት መተኮስ ነው። የትግራይ ህዝብ የታፈነ ህዝብ ነው። አፈናውም ነጻ አወጣንህ እያለ ቀንና ሌሊት በሚለፉት በወያኔ አመራሮችና ፍርፋሪ ለቃሚ ካድሬዎች ነው። የትግራይ ህዝብ ሃገሩን የሚወድ፤ ፈጣሪን የሚፈራ ህዝብ ነው። የህዝባችን እይታ ያጨለመው የወያኔ የዘር ፓለቲካ ነው። ዛሬ ሰርቀው፤ ሰቆቃ ፈጽመው፤ ጠ/ሚሩን ለመግደል ሙከራ ያደረጉ የመሸጉባት መቀሌ እነዚህን ሰዎች ለፍርድ አሳልፎ መስጠት እጅግ አሰፈላጊ ነው። ከዛ ውጭ በወያኔ ግፊት የሚደረጉ ፍሬ አልባ ሰላማዊ ሰልፎች ሁሉ ፉርሽና ተጨፈኑና ላሞኛችሁ እንደማለት ነው።

    Reply
  2. gi Haile says

    December 7, 2018 08:21 pm at 8:21 pm

    ኣሳነባሪው ነውን መያዝ ኣሳዎች መች አስቸግረው ያውቃሉ። የኣሳ ግማቲ ከጭንቅላቱ ስለሆነ ከበሰበሰ ክፉ የሕወአት የቀድሞ መሪዎች ምንም መልካም ነገር አይገኝም። ከወር በላይ የፈጀወሰ የግምገማ ስብሰባ በመቀሌ ጠቅላላ ይዘቱ ቢፈተሽ ግድያን ዘረፋን በምን መልክ እናት ድርግ ውጭ አይደለምና የያዛቸው የዘር ካንሰር እስኪጨርሳቸው ማየት ነው።

    Reply
  3. Tadesse says

    December 10, 2018 04:27 pm at 4:27 pm

    We are really alone fighting these shiftas.Even other people,Oromo/Amhara are shallow minds when it come to tjhis situation but the people of Tigray including me will better die than to live in this situation.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule