የትህነግ አመራሮች ልጆቻቸው በጦርነት ውስጥ አያልፉም። እንቅፋትና ሾህ አያገኟቸውም ብቻ ሳይሆን ስለእሾህና እንቅፋት ኮንሴፕቱም የላቸውም። ልጆቻቸው በውጭ ዩኒቨርስቲዎች ተሞላቀው ይማራሉ፣ በዛው በውጭም ተንደላቀው ይኖራሉ።
የራሳቸውን ልጆች በቅንጦት እያስተማሩና በድሎት እያኖሩ የትግራይ የደሃ ልጆችን ግን በመንግስት የሰላም አማራጭ ዕድል ተሰጥቷቸው (ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በየትኛውም ቦታና ጊዜ ) ሳለ ጦርነትን እንዲመርጡና እንደቅጠል እንዲረግፉ ያበረታታሉ። ይቀሰቅሳሉ። የትግራይ ሕዝብ የጀመረውን ተቃውሞ አጠናክሮ ሊቀጥል፣ የቀረበለትን የሰላም ዕድል ወደጎን ገፍቶ ለጋ ልጆቹን ሳይገብር በጦርነት ያገኘው ትርፍ እንደሌለና ለሰላምም ያለውን ጠንካ አቋም መግለፅ ይገባዋል።
የትግራይ ሕዝብ ከጦርነት ይልቅ ሰላምን ለመምረጡ ዋናው ምልክት ደግሞ የትህነግን የጦርነት መንገድ ባለመከተል ትህነግ ላይ ጀምሮት የነበረውን ተቃውሞ በማሰማትና በማመፅ ሲሆን ነው። በወያኔ የጦርነት ምርጫ እንደቅጠል ሊረግፉ ሊጎሳቆሉ የሚችሉት የትግራይ ልጆች እንጅ የትህነግ አመራር ልጆቻቸው አለመሆናቸውን ማወቅ ያስፈልጋል። ከማወቅም ባለፈ መጋፈጥን ይጠይቃል።
አገር ለማፍረስ በውጭ ታሪካዊ ጠላቶቻችን የሚላላኩ የትህነግን አመራሮች የጦርነት ምርጫ በመከተል ወደጦርነት የሚገባ የትግራይ ተወላጅ ስለመዋጋቱ ሳይሆን ሰሰለቀጣይ ታሪኩ ሊጨነቅ ቆም ብሎ ሊጠይቅ ይገባል።
ጦርነቱ ከመቶ 115 ሚሊዮን ሕዝብ ጋር መሆኑን አገር የማዳን ኮዝ ካለው ለሰላም ለትግራይ ሕዝብ ሲል ቅድመ ሁኔታዎችን አንስቶ ዕድል ከሰጠ ጦርነት ቀድሞ ካልጀመረ አሁንም እየተጠቃ ካለ ኢትዮጵያዊ ጋር መሆኑን በደንብ ማወቅ ያስፈልጋል። (ቶማስ ጀጃው ሞላ)
Leave a Reply