
ከቀናት በኋላ በሚካሄደው ሮም ማራቶን ኢትዮጵያዊው ሯጭ በባዶ እግሩ በመሮጥ ታሪክ ሊደግም ነው።
የፊታችን እሁድ የ2023 በሚካሄደው የሮም ማራቶን ኢትዮጵያዊው የባዶ እግር ሯጭ እንዲሁም ለረጅም አመታት በኢትዮጵያ ታላቁ ሩጫ ቁልፍ ሰው (ዳይሬክተር) በመሆን የሰራው የ45 ዓመቱ ኤርሚያስ አየለ ሙሉ ማራቶን በባዶ እግሩ በመሮጥ የታላቁን አትሌት አበበ ቢቂላን ታሪክ ሊደግም ይችላል እየተባለ ነው።
ኤርሚያስ ከዚህ ቀደም የታላቁ ሩጫንና የሀዋሳ ግማሽ ማራቶንን በባዶ እግሩ የሮጠ ሲሆን ይህንን የሚያደርገውም ለኢትዮጵያው ታላቅ አትሌት አበበ ቢቂላ ክብር እንዲሁም ለሀገር ገፅታ ግንባታ ሲል መሆኑን ተናግሯል።
የሮም ውድድሩ ቀላል እንደማይሆንና ስሜታዊም የሚያደርግ እንደሆነ የገለፀው ኤርሚያስ “ይህን ትልቅ ትርጉም ያለውና ታሪካዊ ውድድር ለማድረግ ዝግጅቴን አጠናቅቄያለሁ” ብሏል።
ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘ
Leave a Reply