• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የትግራይ ተወላጆች በሙሉ ከቢሾፍቱ ተጭነው ተወሰዱ

October 8, 2016 07:07 pm by Editor 4 Comments

በደብረዘይት (ቢሾፍቱ) ይኖሩ የነበሩ የትግራይ ተወላጆች  ዛሬ ቅዳሜ (8 ኦገስት) ሙሉ በሙሉ ከተማዋን ለቀው መውጣታቸውን በስልክ ካነጋገርናቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ማረጋገጥ ችለናል።

የትግራይ ተወላጆቹ ከተማዋን ለቅቀው የወጡት በቢሾፍቱ የኢሬቻ በዓል የሰዎች ሕይወት መጥፋቱን ተከትሎ የአካባቢው ሕዝብ  ከጫፍ እስከጫፍ ነቅሎ በወውጣት እያካሄደ ባለው ሕዝባዊ አመጽ ሊመጣ ካለው አደጋ ለማምለጥ ነው። ህወሃት በዜጎች ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያ በከተማዋ ያሉ ሁሉ ሲቃወም የትግራይ ተወላጆች ግን  ዝም ማለታቸው ሕዝቡን በእጅጉ እንዳስቆጣው ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

የትግራይ ተወላጆቹ ሃብት ንብረታቸውን እየጣሉ ከተማዋን ለቅቀው ወዴት እንደሄዱ የታወቀ ነገር የለም።

ላለፉት አራት ቀናት በደብረዘይት እንደ አብዛኞቹ ከተሞች የንግድ እና የስራ እንቅስቃሴ ቆሟል። ሱቆች ተዘግተዋል፣ ሕዝብም ከቤቱ አይወጣም። አልፎ አልፎ የከባድ መሳሪያ ድምጽ የሚሰማ ሲሆን መንግስታዊ ተቋማት እና ከህወሃት/ኦህዴድ ጋር ንክኪ ያላቸው ተቋማት ወድመዋል።

በዱሮ አጠራሩ ሊበነ ዝቋላ ወረዳ ውስጥ ዝቋላ አቦ ገዳም አካባቢ የምትገኘው አዱላላ ማርያም ወረዳ የህወሃት/ኦህዴድ ንብረቶች እና ጽ/ቤቶች ወድመዋል። ሊበን ዝቋላ ወረዳ አመራሩ ተነስቶ ወረዳው በሕዝብ እየተመራ ይገኛል። ወንጂ የስኳር ፋብሪካው ብቻ ሳይሆን አገዳውም ሙሉ በሙሉ መቃጠሉን ከስፍራው ያነጋገርናቸው እማኞች አረጋግጠዋል።

ከዱከም አንስቶ እስከ አገረማርያም የሚወስደው የጦር ቀጠና በመምሰሉ ምንም አይነት ተሽከርካሪ ላለፉት 6 ቀናት እንዳላዩ እማኞች በስልክ ተናግረዋል። ከደቡብ መስመር አንጻራዊ ሰላም የሚታየው በአዋሳ ከተማ ብቻ ነው።

በዲላ እና ወንዶገነት የህወሃት ባለስልጣናት መኖርያ ቤቶች አጋይቶባቸዋል። ባለስልጣናቱ እና ካድሬዎቹ በሙሉ ከተማዎቹን እየለቀቁ ወደ አዋሳ ከተማ ገብተዋል።

በዲላ መስጊዶች እና አብያተ-ክርስትያናት በዛሬው እለት ባልታወቀ ሃይል ወድመዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች የህወሃት ካድሬዎች  ሆን በለው የሃይማኖት ጸብ ለመቀስቀስ እንዳቃጠሉት ነው የሚናገሩት።

ደምቢዶሎ እና ምእራብ አርሲ የጦር ቀጠና ሆነው መሰንበታቸውን እና በጦርነቱ በርካታ ሰዎች ማለቃቸን የአሜሪካ ድምጽ ራድዮ እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News, Politics Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Abe says

    October 9, 2016 01:01 pm at 1:01 pm

    አዱላላ ማርያም ናዝሬት ከተማ መግቢያ ላይ የምትግኝ ወረዳ አደለችም። በዱሮ አጠራሩ ሊበነ ዝቋላ ወረዳ ውስጥ ዝቋላ አቦ ገዳም መንግድ ላይ ወይም አካባቢ ያለች ከተማ ወይም ስፍራ ነች።አዱላላ ከናዝሬት ወይም አዳማ ይልቅ ለአዳአ ወረዳ ዋና ከተማ ቢሾፍቱ ወይም ደብረዘይት ትቀርባለች። ”ሊበን ጭቆላ“የሚለውም “ሊበን ዝቋላ” ተብሎ ቢታረም መልካም ነው፤_ለአቶ ክንፈ ወይም ለኤዲተሩ ማስታወሻ ነው።

    Reply
    • Editor says

      October 10, 2016 05:46 am at 5:46 am

      Abe

      ከአክብሮት ምስጋና ጋር አስተካክለናል

      የጎልጉል አርታኢ

      Reply
  2. Kebede Mulugeta says

    October 10, 2016 12:19 pm at 12:19 pm

    በተቃውሞ ስም የሚነደው ንብረት እጅግ አሳዛኝ ነው፡፡ አንድ ፋብሪካ ሲቃጠል በዚያ ፋብሪካ ኢኮኖሚያቸውን የሚደጉሙ በርካታ ቤተሰቦች ተጠቂ እየሆኑ ነው፡፡ የስኳር ፋብሪካ በማቃጠል የሚጎዳው ማነው? በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የዕለት ገቢያቸው ከፋብሪካው ህልውና ጋር የተያያዙ ዜጎች እንዲሁም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስኳር ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ ይህንን ተቃውሞ እንመራለን የምትሉ ሰዎች ህዝቡ በስሜት ተገፋፍቶ የራሱን ንብረት እንዳያወድምና ተቃውሞውን በሌላ መንገድ እንዲያደርግ መምከሩ ሃገርን ከጥፋት ያድናል፡፡

    Reply
    • Zemede says

      October 12, 2016 02:27 am at 2:27 am

      Ante Seli Diabetes Yemiyameta sikuar ticheneqaleh hageritu beand gosa bicha , yawim anasa le 25 amet sitinaqor ante sile fabirika tidesekuraleh,, Sima Ate Minilik Betorinet new enji be selama were hager alaqoyulinim, telatin madfakem new eskemechereshaw. Atimogn/

      Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule