
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከኢትዮጵያ ጀርባ ከአሸባሪው ትህነግ ጋር በመደራደር የራሱን ህግ ጥሷል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከኢትዮጵያ ጀርባ ከአሸባሪው ትህነግ አመራር ጋር በቀጥታ በመደራደር የራሱን ሕግ መጣሱ ታውቋል።
የድርጅቱ ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ባለፈው ሳምንት ከአሸባሪው የህወሓት ቡድን ሊቀመንበር ከሆነው ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።
ዋና ጸሀፊው ይህንን ከአሸባሪው ድርጅት መሪ ጋር የመነጋገራቸው መረጃ የታወቀውም፤ የድርጅቱ ቃል አቀባይ ስታፌን ዱጃሪች ለተመድ ጉዳይ ዘጋቢ ጋዜጠኞች ጽፈውት ሾልኮ ከወጣው ኢሜይል ነው።
የዋና ጸሀፊው ድርጊትን ተከትሎ በርካቶች ጉዳዩን በማንሳት ተገቢነት የጎደለው መሆኑን እየገለጹ ነው።
ትህነግ በዓለም አቀፍ የሽብር መረጃ ቋት (Global Terrorism Database) ውስጥ ዛሬም ድረስ ተመዝግቦ ያለ፤ በሽብር ስራው የሚታወቅ ድርጅት ሆኖ ሳለ ዋና ጸሀፊው ይህንን ማድረጋቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ድንጋጌዎችነ የጣሰ መሆኑ ተገልጿል። (ኢፕድ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Is that true our officials too were talking with the terrorist TPLF?