• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“እንኳን በሳይበር የሚደረግ ጥቃት ይቅርና የወያኔ ተገንጣይ መንግስት እስር ቤትም ከዓላማችን አላሰናከለንም”

December 14, 2016 08:20 pm by Editor 1 Comment

ዘ-ሐበሻ ድረገጽ ከተመሰረተች 9 ዓመት ሆኗታል:: ባለፉት 9 ዓመታት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎችን መረጃ ከሚያቀብሉ የመረጃ መረቦች መካከል አንዷ በመሆን በአማራጭነት ሚድያነት አገልግላለች:: በየዕለቱ ድክመቶቻችን በማረም ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር በመራመድ አሁንም ተመራጭና ተአማኒ ሚዲያ ለመሆን ተግተን እየሰራን ነው::

እንደሚታወቀው የዘ-ሐበሻ አዘጋጆች የሚዲያን ሥራ የጀመሩት እዚህ ስደት ላይ ከወጡ በኋላ አይደለም:: በሃገር ቤት በኢትዮጵያ ነጻው ፕሬስ ውስጥ መስዋዕትነት የከፈሉ፣ የታሰሩ፣ የተገረፉና ብዙ መስዋዕትነት በከፈሉ ጋዜጠኞች የምትዘጋጅ ድረገጽ ናት::

ዘ-ሐበሻ ድረገጽ በተለይ ዕድሜያቸው ከ18 – 45 ዓመት ክልል ውስጥ በብዛት የምትጎበኝ፣ ወቅታዊ መረጃዎችንም በፍጥነት የምታደርስ መሆኗ የሕወሓትን መንግስት ሁሌም እንዳስደነገጠች ነው:: ባለፉት 9 ዓመታት በተለይ በእነዚህ ዕድሜ ክልሎች ባሉ ወገኖች ድረገጻችን በመጎብኘቷና በአብዛኛው 75% የሚሆነው የዘ-ሐበሻ ድረገጽ ጎብኚም ከኢትዮጵያ መሆኑ ያበሳጨው የሕወሓቱ መንግስት በርካታ ብሮችን በማፍሰስ ዘ-ሐበሻ የምታስተላልፈውን ነጻና ያልተገደበ መረጃ ለማፈን ብዙ ጥረቶችን አድርጓል:: ዘ-ሐበሻ ድረገጽን በሶስተኛ ወገን እንዲሸጥለት ከመጠየቅ አንስቶ ኮምፒውተሮቻችንን ከማጥቃት እስከ አዘጋጆቹ ቤተሰብ ድረስ ሄዶ የሕወሓት መንግስት ያላደረገው ያልሞከረው ነገር የለም:: አዘጋጆቹን በአካልና በንብረቶቻቸው ላይ ለማጥቃትም ብዙ ተሞክሮም ነበር::screen-shot-2016-12-14-at-7-51-21-pm

ባለፉት 9 ዓመታት የደረሰብን ፈተና እንዲህ በትንሹ ተጽፎ የሚያልቅ ብቻ አይደለም:: ዘ-ሐበሻ ድረገጽን ሃክ ለማድረግ ብዙ ወጪዎችን የሚያፈሰው የሕወሓት መንግስት ከድረገጻችን በተጨማሪ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ተከታይ ያለውን የፌስቡክ ገጻችንን ሃክ እስከማድረግ ደርሶ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው:: የፌስቡክ ገጻችንን ሃክ አድርገው የነበሩ የሕወሓት ተላላኪዎችም በሕግ የሚገባቸውን እርምጃ አግኝተዋል::

ይህን በሕወሓት መንግስት የሚደርሰውን የሳይበር ጥቃት ለማምለጥ ዘ-ሐበሻና አዘጋጆቿ በየ6 ወሩ ኮምፒውተሮቻቸውን ይቀያይሩ ነበር:: ብዙ ገንዘብ በማውጣትም የሳይበር ዘገበኛዎችን (ሴክዩሪቶዎችን) በመጫንም ጥቃቱን ስንከላከል ቆይተናል:: በዚህም መሃከል ግን ዘወትር ነጻ ሚዲያዎችን ለማፈን የማይተኛው የሕወሕት መንግስት እንደገና በዛሬው ዕለት ራሳቸውን “ጋዛ ሃከርስ” ብለው የሚጠሩ ሃከሮችን በመቅጠር የዋና አዘጋጁን ኢሜይል ሃክ በማድረግ እንዲሁም ድረገጹን ሃክ አድርገው በመቆጣጠር ለተወሰነ ሰዓታት ሲያውኩን ውለዋል::

የሕወሓት መንግስት የአዘጋጆቹን ኢሜይል ሃክ ቢያደርግ የሚያገኘው ምንም ምስጢራዊ መረጃ አይኖርም:: ዘ-ሐበሻ መረጃን ለሕዝብ ከማድረስ ውጭ ሌላ ምንም ዓይነት ተልዕኮ የሌላት በመሆኑ ምናልባት ወያኔዎች ኢሜሎቻችንን ቢበረብሩ የሚያገኙት ዞሮ ዞሮ በድረገጻችን ላይ በይፋ ተጽፈው የሚያገኟቸውን ጽሁፎች ብቻ ናቸውና ለልፋታቸውና ላጠፉት ገንዘብ ኪሳራቸው አስደስቶናል:: ድረገጻችንን ግን ሃክ ባደረጉትና ጥቃት በፈጸሙበት ቁጥር ግፋ ቢል እኛን የሚያስወጣን ገንዘብና መረጃ ልናደርሰበት የምንችልበትን ውድ ጊዜ ብቻ ነው::

ስለሆነም የሕወሓት መንግስት አንድ ሊገነበዘበው የሚገባው ትልቅ ነገር አለ:: የዘ-ሐበሻ አዘጋጆች በሃገር ቤት የስርዓቱን ማሰቃያ እስር ቤቶችንና ጨለማ ክፍሎችን እነማዕከላዊን፣ ከርቸሌን፣ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያንና ሌሎችንም በመቅመስ የቆሙለትን ዓላማ ያጠነከሩ እንጂ በደረሰባቸው እስር የተፍረከረኩ አይደሉም:: ዛሬም በሳይበር ሕወሓት በሚያደርስብን ጥቃት ከአቋማችን ምንም ፍንክች እንደማያደርገን፣ እንደውም በተጠቃን ቁጥር እንደምንጠነክር እንዲገነዘቡት ለመግለጽ እንወዳለን:: ለዚህም ነው በመግቢያችን ላይ “እንኳን በሳይበር የሚደረግ ጥቃት የወያኔ ተገንጣይ መንግስት እስር ቤትም ከዓላማችን አላሰናከለንም” ያልነው::

ዕውነት ያሸንፋል!
የዘ-ሐበሻ ኤዲቶሪያል ቦርድ

henocka2001@yahoo.com


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Tadesse says

    December 22, 2016 05:38 pm at 5:38 pm

    If anybody is involved in oppressing people in the name of the people of Tigray,he isn’t ours,individual or collective.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
Copyright © 2026 · Goolgule