የአሜሪካ ምርጫ ሲጠናቀቅ ተሸናፊው ሚት ሮምኒ ደጋፊዎቻቸው በተሰበሰቡበት አዳራሽ ምስጋና ካቀረቡ በኋላ እንዲህ አሉ፡- “… ሁለታችንም ለምንወዳት አገራችን የምንመኘውን ለማድረግ በተለያየ አቅጣጫ ሞከርን፤ … ሕዝባችን ደግሞ የሚፈልገውን መሪ መረጠ፤ … ስለዚህ ፕሬዚዳንቱን ደውዬ አነጋሬያቸዋለሁ፤ ባገኙትም ድል እንኳን ደስ አለዎ ብያቸዋለሁ፤ … በተለይ ለእርሳቸው፣ ለቀዳማዊ እመቤት እና ለልጆቻቸው ሁሉ መልካሙን እመኛለሁ፤ … አገራችን ከባድ ፈተናዎች ተጋርጠውባታል፤ … ባለቤቴና እኔ ለፕሬዚዳንቱና ቤተሰባቸው ከልብ እንጸልያለን፤ በሥራቸው ስኬት እንዲያገኙና ታላቋን አገራችንን በመምራት የሚያከናውኑት ሁሉ የተሳካ እንዲሁን እመኛለሁ፡፡” ይህንን ካሉ በኋላ ወደተለመደው ህይወታቸው ሄዱ - የፖለቲካ ገዳም ገቡ፡፡ ይህ ንግግር ወደራሳችን እንድንመለከት የሚያደርግ ነው፡፡ የእኛስ ፖለቲከኞች … [Read more...] about “ኦባማ መጀን” ወይስ “በእውቀት” መደራጀት?