የትምህርት ሚኒስቴር አካሄዱኩት ባለው የዳሰሳ ጥናት፣ በበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከ30 በመቶ በላይ መምህራን እንደማያስፈልጉ መታወቁን ሚኒስትሩ አስታወቁ፡፡ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የተቋማቸውን የ2015 ዓ.ም. ሩብ ዓመት አፈጻጸም ማክሰኞ ኅዳር 20 ቀን 2015 ዓ.ም. ለፓርላማ ሲያቀርቡ፣ ዩኒቨርሲቲዎች በአማካይ በሴሚስተር አራት ኮርስ ወይም 12 ክፍለ ጊዜ መያዝ እንዳለባቸው ቢጠበቅባቸውም፣ ብዙዎቹ መምህራን በሴሚስተር አንድ ኮርስ አስተምረው የሙሉ ጊዜ መምህራን ተብለው እንደሚጠሩ ተናግረዋል፡፡ በዚህም የተነሳ የዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ መሆን ከበጀታቸው ጋር አብሮ ሊሄድ የሚችል የመምህራን ቁጥር በመያዝ፣ በልካቸው ሊራመዱ እንደሚገባ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪ ዩኒቨርሲቲዎች ከሌሎች የገንዘብ ምንጮች በሚያገኙዋቸው ገቢዎች ተወዳዳሪና ተመራጭ … [Read more...] about በበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ከ30 በመቶ በላይ የሚሆኑት መምህራን አያስፈልጉም