ሶርያን ጊዜያዊ ማረፊያው አድርጎ አገሪቱን እያዳሸቀ፣ ህዝቡን እየበላ፣ ያለው የ“አረብ ጸደይ” ብዙዎች እንደሚሉትና የመፈክር ያህል እንደሚስተጋባው መነሻው የቱኒዚያ ምድር ሳይሆን ቆመች ስትባል መልሳ በምትናጠው ጎረቤታችን ሶማሊያ ነው። ይኸው የለውጥ “ቀይ” ነፋስ በሊቢያ ጋዳፊን እንደምናምንቴ በውሻ አይነት አሟሟት እስከወዲያኛው አሰናብቷል። ጋዳፊ ላይ ከተፈጸመው ጋር በንጽጽር ላስተዋለው አሁን በሶሪያ እየተከናወነ ያለው የዚያ ግልባጭ መሆኑን ለመረዳት የሚያዳግት አይደለም፡፡ በአገራችን አባባል “የቆላ ቁስል” እንደምንለው! ዓለምአቀፍ የግንኙነት ቡድን ተፈላጊ የሆነው አገር ስም እየተሰጠው በዓለምአቀፉ ኅብረተሰብ (በምዕራባውያን ወኪልነት) የሚቋቋመው ዓለምአቀፍ የግንኙነት ቡድን (International Contact Group) እየተባለ የሚጠራው አካል ለሶማሊያ የተመሠረተው እኤአ … [Read more...] about “የአረብ ጸደይ” ለኢትዮጵያ “የቆላ ቁስል” ይሆን?