በአዲስ አበባ በየቦታው ቆሻሻ ለሚጥሉና በቅርቡ የተተከሉትን ዘንባባዎች ለሚገጩ የሚከፈለው ቅጣት ያነሰ መሆኑን በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ። ተግባሩን ለመከላከል የሌሎች አገራት ልምድ ተግባራዊ እንዲደረግና ጥፋቱን ለመቀነስ የቅጣት መጠኑ መጨመር እንዳለበት ነው ነዋሪዎች የተናገሩት። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለከተሞች የሚገኙ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ጋር ባደረገው ኢመደበኛ ጥናት ሁሉም ተጠያቂዎች የሰጡት ምላሽ ጥፋቱን በሚፈጽሙ ላይ የተበየነው ቅጣት ከዚህ መጨመር እንዳለበት ነው። ሌላው የሰጡት ምላሽ የሌሎች አገራትን ተሞክሮ በማጥናት በአገራችን ላይ ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት ሲሆን፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘ እንደ ጥንቃቄ የሰጡት ምላሽ ሁሉም ሰው አውቆ ዘንባባ ስለማይገጭ እንደ አገጫጩ ምክንያትና ዐውድ ቅጣቱም በዚያው መልኩ አጥፊዎችን ከአደጋ አድራሾች … [Read more...] about ቆሻሻ የሚጥሉና ዘንባባ የሚገጩ ቅጣት አንሷል ተባለ