በኦሮሞ የባሕል ማዕከል ኦዴፓ ከኦነግ ጋር ስምምነት ባደረገበት ወቅት ዕርቀ ሰላሙን ከመሩት የአገር ሽማግሌዎች መካከል ኦቦ ኃይሌ ገብሬ እጅግ ጥልቅ ንግግር አድርገው ነበር። ይህ በአፋን ኦሮሞ እያለቀሱ የተናገሩት ልብ የሚነካ ንግግር ወደ አማርኛ ሲመለስ እንዲህ የሚል ነበር፤
“ዕርቀ-ሰላም በሚሆንበት ጊዜ እንዲሳካ ከብት ማረድ ካስፈለገ ገዝተን እናርዳለን፤ አይ ከብት አይደለም ሰው ይታረድልን የምትሉ ከሆነ ይኸው የኔን ደም አፍስሱና ኦሮሞን አስታርቁልኝ”።
ይህንን ዓይነት መስዋዕትነት የተከፈለበት ዕርቀ-ሰላም አንቀበልም የሚሉ በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኃይሎች ለራሳቸው ሲሉ ከዚህ በኋላ ጥንቃቄ ቢያደርጉ መልካም ነው በማለት ስምምነቱን የተካፈሉ ይናገራሉ። የኦሮሞ ሕዝብ ከዚህ በኋላ ማንኛውንም ዓይነት ከፋፋይና ደም አፋሳሽ ተግባር መሸከም የሚችልበት ትከሻ የለውም። በኦሮሞ ስም ሊያበረክቱት የሚፈልጉት ካለ ሕዝባቸውን በቅንነትና በታማኝነት ማገልገል ብቻ ነው፤ እንደ ኦቦ ኃይሌ ገብሬ ዓይነቱን ጨዋና አገር ወዳድ እጅግ ያበርክትልን በማለት ለጎልጉል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
gi Haile says
የሕዝባችንን ደም ሲያፈስና ሲያስፈስስ የነበረው ሰይጣንና ሰይጣን የጠየቃቸውን ደም በመፍረስ አብት ያካበቱ በጠንቋይ እየተመሩ መንግስን ስልጣን ቆንጥጠው የቆዩት የሰው ደም በአደባባይ በጥይት እያፈሰሱ በሰውር ደግሞ ደም እየገበሩ ኸሰይጣናዊ አይልና ጉልበት ሲቀበሉ ቆይተዋል። ፨መንፈሳዊ ነገር ያልነቃው ሕዝቤ ቤተሰቡን ልጆቹን መሬቱን ደም እያፈሰሱ ሲገዙና ሲያርዱት የነበረው ለሰይጣን ብለው ነበር። ሰይጣን የሰውና የፈጣሪም ኘላት ሰለሆነ በአጋንንት መንፈስ እየተነዱ አገርና ሕዝቡን የሚገድሉትን በሰይጣን የተሞሉ ሰዎችን ለይታችሁ ለማወቅ መቻል ያስፈልገናል ። የሰው ደም ለማፍሰስ የሚቸኩል ሁሉ በሰይጣን ቁጥጥር ስር ያለ የሰይጣን አገልጋይ እንጂ ሰው ብለን የምንጠራው ከተግባሩ ተቆጥቦ ለሰው ሁሉ መራራት ሲጀመር ብቻ ነው። በ27 የቀለብነው ሰይጣን ከእባብ ወደ ዘንዶ ከዘንዶ ወደ ተምዘግዛጊ ሻርክ ተለዋውጠዋል። አሁን ግን ታላቁ እባብ ሌዋታን የሰው ልጅ ሁሉ ጠላት ጥላቻ፣ ዘረኝነት ፣ ድንቁርና፣ ቅናት፣ ፍርሃት፣ የበታችነት አመለካከት ፣ ነቀትና ትዕቢት ወደ ጉድጓድ ገብተዋል የኢትዮጵያ ሕዝብ በጉድጓዱ ላይ አፈር በመመለስ ለመጨረሻ ጊዜ መቀበር አለበት። ሰላም ለኢትዮጵያውያን እንዱሁም ሰላም ለሰው ልጅ በመሉ። ፈጣሪ አንድ ነው የሰው ዘርም አንድ ነው። ግርማ
Tesfa says
በአለፉት 40 ዓመታት ገደማ የኦሮሞ ህዝብ መብት ተሟጋች ኦነግ እንደነበር ህዝባችን ጠንቅቆ ያውቃል። ኦነግ የራሱን ባንዲራ ያውለበለበ ኦሮሚያ የምትባል ሃገር እንመሰርታለን በማለት ይበልጥ ዘመኑን በአስመራ የመሸጎ የኖረ ድርጅት ነው። በአንጻሩ በእየዓለማቱ በልዪ ልዮ ምክንያት ከሃገር የወጡ ቆራጥና ለኦሮሞ ህዝብ የሚታገሉ ለመኖራቸው እኔ የዓይን ምሥክር ነኝ። ከእነዚህም ቀዳሚውና በመገናኛ አውታሮች ጎልቶ የሚታየው ጆዋር መሃመድ ነው። ጀዋር ባለፉትና በቅርብ ጊዜ ከጀርባችን ላይ ከወረደው የወያኔ አገዛዝ ጭምር የኦሮሞ ህዝብ ግፍ ሲፈጸምበት ያየ እና ለዚህ ህዝብ ነጻነትና እፎይታ በትጋት የታገለ ወገናችን ነው። ያው የእኛው ሃገር ፓለቲካ እድሜ ለወያኔ ሁሉንም በየወገንህ በማለቱ ሰው በፊት ካሳለፍናቸው መንግሥታት ይልቅ በወያኔው አሻጥር ክልልና ቋንቋን ተገን ማድረግ ሲገልና ሲጋደል እንደኖረና አሁንም እንዳለ የየእለቱ የዜና ዘገባዎች ያስረዳሉ።
የሃገሬ ሰው የሚለው አንድ አባባል አለ ” በየወገንህ ቢሉት የመቶ ዓመት ቆዳ ገቢያ ወጥቶ ቆመ” ይላሉ። ወገንተኝነት አፈረሰን እንጂ አልሰራንም። ዛሬ ለኦሮሞ ህዝብ እንቆረቆራለን የሚሉ ወደ 17 የሚጠጉ ድርጅቶች አሉ። ከእነዚህ ሁሉ የሚከፋው ኦነግ ነው። በወለጋ ህዝባችንን ሲገድል ሲዘርፍ መሪው አቶ ከተማ ተቀምጦ ነጻ አውጣሃለሁ የሚለውን ህዝብ ወታደሮቹ ሲገድሉ የሚያምታታ የፓለቲካ መግለጫ ለዜና አውታሮች በመስጠት የወያኔ የሰውርና የገሃድ ተላላኪ መሆኑ አስነዋሪ ነው። ትጥቅ አልፈታም ማለት ምን ማለት ነው? ኦነግ ትጥቅ ታጥቆ የነበረው የኦሮሞ ህብን ሰቆቃ ለማስታገስ ከሆነ ዛሬ ዝርፊያውና ግድያው ለምንድን ነው? ኦነግ አንድ ማወቅ ያለበት ትልቅ ነጥብ አለ? የኦሮሞን ህዝብ የዛሬ 40 ዓመት በተተለመ አላማ ዛሬ መምራት አይቻልም። ጊዜው ተለውጦአል። ኦነግና ወታደሮቹም ጠበንጃቸውን አስቀምጠው ጠኔና ችጋር ያልተለየውን ህዝባችንን ከድህነት ለማውጣት አፈሙዝ የለሽ ፓለቲካን መከተል አለባቸው። ከዚህ አንጻር ጀዋር መሃመድ በየጊዜው የሚሰጣቸው ወቅታዊና ሃገራዊ እይታዎቹን እጋራለሁ። በርታ አይዞህ እንላለን። ሌሎችም ለምሳሌ ያህል እንደ ዶ/ር አለሙ፤ ዶ/ር መራራና ሌሎች ለኢትዮጵያ አንድነትና ለኦሮሞ ህዝብ ሰላም በፊትም ዛሬም በመታገል ላይ ይገኛሉ። የኦነግ አመራሮች/ደጋፊዎች ያለፈን የጥይት ፓለቲካ በመተው ለህዝባችንና ለሃገራችን በአንድነት እንስራ!