• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኦነግ በአማርኛ መግለጫ ባወጣ ጥቂት ቀን “ትጥቃችንን ለኦሮሞ ሕዝብና ለአባ ገዳዎቻችን አስረክበናል” አለ

January 23, 2019 12:30 am by Editor Leave a Comment

ኢትዮጵያን “አቢሲኒያ ኢምፓዬር” በማለት ሲጠራ የኖረውና ራሱን የኦሮሞ ነጻአውጪ ግምባር ብሎ የሰየመው “ኦነግ” አቢሲኒያ ከሚላት ኢትዮጵያ ለመገንጠል ብቻ ሳይሆን አማርኛንም እንደ ጨቋኝ ቋንቋ በመቁጠር በዚያ ከመጠቀም ተቆጥቦ መኖሩ የሚታወቅ ነው። ለአብነት ያህል በቅርቡ ወዳገር ቤት የገቡት ገላሳ ዲልቦ እነ መለስ በጠሩት የሽግግር መንግሥት ምሥረታ ወቅት በእንግሊዝኛ ሲናገሩ ሌንጮ ለታ ከጎናቸው በመሆን በኦሮሚኛ ያስተረጉሙ ነበር። አሁን ደግሞ እኚሁ ገላሳ ዲልቦ በየሚዲያው በአማርና ቃለምልልስ ብቻ ሳይሆን ቅኔም ሲዘርፉ ሰምተናል።

በግሩም የአማርኛ ብሒል የታጀበውና “ግመል ሰርቆ ኣጎምብሶ” ኣይደበቅ ነገር በሚል ርዕስ የወጣው የኦነግ መግለጫ ያተኮረው መንግሥት ምዕራብ ወለጋን በአየር ስለመደብደቡ የጠ/ሚ/ሩ ፕሬስ ክፍል (እንግሊዝኛ) ቢልለኔ ስዩም ማስተባበላቸውን ተከትሎ ነው።

አራርሳ ቢቂላ

ከዚህ የኦነግ መግለጫ በኋላ ማክሰኞ በአዲስ አበባ በሚገኘው የኦሮሞ ባህል ማዕከል በተካሄደው ዕርቀ ሰላም ጉባዔ ላይ ዳውድ ኢብሳ “ከዛሬ ጀምሮ ትጥቃችንን ለኦሮሞ ህዝብና ለአባ ገዳዎቻችን አስረክበናል” ማለታቸው ተሰምቷል።

በሌላ በኩል የዳውድ ኢብሣ ምክትል ናቸው የሚባሉት አራርሳ ቢቂላ ደግሞ ይህንን ሲሉ በኦኤምኤን ላይ ተደምጠዋል፤ “ጦራችን ህዝቡን ብሎ ፍራፍሬ እና የእንጨት ልጣጭ እየተመገበ ብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ አልፏል። አሁን ዝለናል። ከዚህ በኋላ ጦርነት የሚባል ነገር አያስፈልግም። ከዚህ በኋላ ለኦሮሞ ህዝብ የሚያስፈልገው ሰላም ነው። ትብብር ነው። ጦሩ በሰላም ከህዝቡ ጋር እንዳይቀላቀል የሚያደርጉ ኃይሎችን ከዚህ በኋላ በዘመቻ መልክ ልንከላከላቸው ያስፈጋል። እኛ ሥልጣን ብለን አልመጣንም። እኛ ምን መደረግ እራሱ እንዳለብን ገና ከህዝባችን ጋር በደንብ አልተነጋገርንም። እኛ የምንፈልገው ወንበር አይደለም። እኛ የምንፈልገው ይሄ በሕዝባችን መሰዋዕትነት የተገኘው ለውጥ እንዳይቀለበስ ነው። ይህ ለውጥ እንዲቀለበስ ብዙ ኃይሎች ይፈልጋሉ። ስለዚህ እኛ የምንፈልገው ይህ ለውጥ እንዳይቀለበስና እውነተኛ ዲሞክራሲ በሀገራችን እንዲሰፍን ከመንግሥት እና ከሌሎች ኃይሎች ጋር በሰላምና በትብብር መሥራት ነው።”

በዕርቀ ሰላም መድረኩ ላይ በአባገዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎች፣ የተለያዩ ፓርቲዎች፣ አክቲቪስቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የወከሉ ግለሰቦች ተሳትፈዋል።

አባገዳዎች እና ሃደ ሲንቄዎች በመድረክ ላይ በአንድነት በመቆም በፓርቲዎች መካከል ዕርቅ እንዲሰፍንና ሰላም እንዲወርድ ያቀረቡት ጥያቄ በሁሉም አካላት ተቀባይነት አገኝቷል።

በጉባዔው ላይ የተገኙት የኦዴፓ ዋና ፀሀፊ አለሙ ስሜ በበኩላቸው እኛ የምንፈልገው ሰላምን ማስፈን አንድነትን ማጠናከር እንጂ ከኦነግ ጋር ምንም ችግር እንደሌለባቸው ተናግረዋል።

ኦነግ ቃሉን ከጠበቀና እንዳለውም ትጥቁን ለአባ ገዳዎች ያስረከበ ከሆነ “ተደረገብኝ” ከሚለው የአየር ድብደባ ብቻ ሳይሆን ወደፊትም ከሚደርስበት ከባድ ሽንፈት ራሱን ያድናል። “ነጻ አወጣዋለሁ” ለሚለው ሕዝብም የተሻለ አማራጭ ለማምጣት የሚችልበትን መንገድ ማመቻቸት ይችላል። ይህ ሳይሆን ቀርቶ እንደ ደብረጽዮን 45 ደቂቃ ለሰላም 45 ደቂቃ ደግሞ ለትጥቅ ትግል እጫወታለሁ ብሎ የሚያስብ ከሆነ “እታገልለታለሁ” በሚለው በራሱ ሕዝብ ይተፋል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ


በአማርኛ የወጣው የኦነግ መግለጫ ሙሉቃል እንዲህ ይነበባል፤

“ግመል ሰርቆ ኣጎምብሶ” ኣይደበቅ ነገር

(የኦነግ መግለጫ – ጥር 09 2011)

የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚንስቴር ጽ/ቤት በትናንትናው ዕለት (ጥር 09 2011) በቃል-ኣቀባዩ ወይዘሪት ብልለኔ ስዩም በኩል በምዕራብ ኦሮሚያ ጦሩ ያካሄደዉን የአየር ድብደባ ለማስተባበል በማሰብ ለተለያዩ የዜና አዉታሮች የሰጠዉ መግለጫ እጅጉን ከእዉነት የራቀ ነዉ። ይህ የአየር ድብደባ ለሁለት ተከታታይ ቀናት (ጥር 4 እና 5 2011) በቄሌም ወለጋ ዞን በጊዳሚ ወረዳ በቄሌም ከተማና አካባቢዋ በሶስት የተላያዩ ቦታዎች ለይ ነዉ የተካሄደዉ።

በዚህ ደረጃ የተካሄደዉን የአየር ድብደባ ለመካድ መሞከር ማለት “ግመል ሰርቆ ኣጎምብሶ” እንደሚባለዉ ኣይነት ልደበቅ የማይቻለዉን እዉነታ ለመደበቅ የሚደረግ ከንቱ ልፋት ነው።

ከዚሁ የአየር ድብደባ በተጨማሪም የኢሕአዴግ እግረኛ ጦር ሠራዊት በዚሁ ኣካባቢ ሰላማዊዉን ሕዝብ በመግደል፣ መኖሪያ ቤቶቹን በማቃጠል፣ ንግድ ቤቶቹን በማፈራረስና ንብረት በመዝረፍ እንድሁም ሰዎችን በጅምላ በማሰርና በማሰቃየት እኩይ ድርጊቶች ላይ ተጠምደዋል። በጊዳሚ ወረዳ ዉስጥ በአየር ሓይልና በእግረኛ ጦር በተካሄደዉ በዚህ ጥቃት እስካሁን የተረጋገጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የሰባት (7) ሰላማዊ (ትጥቅ-ኣልባ) ዜጎች ሕይወት ማለፉ ታዉቋል። ከሞቱት መካከል ኣንዷ ከአየር ወደ መሬት በሚወረወሩ ቦምቦች የፍንዳታ ድምጽ ልቧ ቆሞ የሞተች የሁለት ወር ሕጻን እንደሆነችም ታዉቋል። 8 የሕዝቡ መኖሪያ ቤቶች በእሳት ጋይቷል። 20 ንግድ ቤቶችም በኢሕአዴግ ወታደሮች ተዘርፎ ተፈራርሷል። እነዚህ በጊዳሚ ወረዳ ዉስጥ የአየር ጥቃቱ በተካሄደበት ኣካባቢ ብቻ የተፈጸሙ ናቸዉ። ግድያና ጦርነት እየተካሄደባቸዉ ባሉት በኣራቱ የወለጋ ዞኖችም በነዚሁ የኢሕአዴግ ወታደሮች የተገደሉት ሰላማዊ (ትጥቅ-ኣልባ) ሰዎች የተቃጠሉ ቤቶች፣ የተዘረፉና የወደሙ ንብረቶች ዝርዝራቻዉ በርካታ ስሆን ለወደፊቱ ተጣርቶ እንደሚዘገቡ እናሳዉቃለን።

ይህ የጠቅላይ ሚንስቴሩ ጽ/ቤት መግለጫ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) መንገድ መዝጋቱን፣ ባንኮችን መዝረፉን፣ ሕዝብን ማሰቃየቱን፣ እና ሌሎችም ፀረ-ሰላም ድርጊቶችን መፈጸሙን በማተት ለዚህ ጥቃት እንደምክንያት ያቀርባል። ይህ የመንግስት ክስ ፍጹም ከእዉነት የራቀ ነዉ። ኦነግ በሰላማዊ መንገድ ብቻ የተጀመረዉን የለዉጥ ሂደት ለማሳካት በሙሉ ልቡ እየሰራ ባለበት ሁኔታ የተላያዩ እንቅፋቶችን በመፍጠር የስምምነታችን መንፈስ እንድደፈርስና ስምምነቱን ተግባራዊ የማድረጉ ሂደት እንድጓተት እያደረገ ያለዉ ኦነግ ሳይሆን እራሱ ኢሕአዴግ ነው። ይህ ጦርነት ኢሕአዴግ በስመ ሃገር መከላከያ ሠራዊት ለራሱ ጥቅም ያደራጀዉና እስከዛሬም ሕዝባዊ ኣለኝታነትን ያልተላበሰዉን ጦሩን ተጠቅሞ ኦነግንና የግንባሩን የፖለቲካ አመለካከት ያላቸዉን ወገኖች ለማዳከም የሚያካሄድ ጦርነት መሆኑ ለማንም ግልጽ መሆን ኣለበት።

ኦነግ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተደረሰበት ስምምነት በሰላማዊ መንገድ ተግባራዊ ሆኖ ሃገርና ሕዝቦችም ሰላም ያግኙ ዘንድ ይህ ጦርነት በኣፋጣኝ መቆም ኣለበት ብሎ ያምናል። ከዚያም በመቀጠል በመንግስት በኩል እየቀረቡብን ያሉና እኛም በበኩላችን በእኛና በሕዝባችን ላይ እየተፈጸሙ ያሉ ግፎች ናቸዉ የሚንላቸዉ (የሁለቱም ወገን) ስሞታና ቅሬታዎች በገለልተኛ ወገን ተመርምሮና ተጣርቶ ሓቁ እንድወጣ/እንድታይ ኦነግ ኣጥብቆ ይጠይቃል።

ድል ለኦሮሞ ሕዝብ!
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር
ጥር 09, 2011

 

Filed Under: Politics Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule