• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ኮከብ ባየሁ ቁጥር እበረግጋለሁ” ዘ-ሃበሻ እግዜር ይይልሽ!

February 2, 2017 11:55 pm by Editor 1 Comment

ከሶቅራጥስ ዘመን ጀምሮ ሲነገር የኖረውን “እውቀት እና መረጃ ሃይል መሆኑን” መንገር፣ እንዲሁም “…መረጃን መገደብ… የአምባገነኖች እና ህዝብን የሚበዘብዙ እና የሚጨቁኑ …” ገዢዎች ስራ መሆኑን መጻፍም፣ አንባቢህን አለማወቅ/መናቅ ቢሆንም፣ ክፋት የለውም። “…መረጃዎች እንዳይወጡ ማድረግ የጨቋኞች ባህሪ ነው….”፣ በሚል መንደርደሪያ ተነስቶ፣ ከ“ጨቋኞች” የተጻፈ መሆኑን ለማሳየት/ለማጋለጥ አንድም ሃርግ መዘው ሳያወጡ እና ሳይተቹ፣ ባለፈው የለቀቅሁትን ጽሁፍ “የጨቋኞች ጽሁፍ … የመንደርተኛ ወሬ ነው…” ማለት አግባብ አይደለም። ጽሁፉ፣ ሙያዊ ግምገማ/ትችት እንኳን ባይመስላቸው “ከጨቋኞች የመጣ ነው” ማለቱ ራሱ፣ የዘሃበሻን ኢዲቶሪያል ቦርድ ትዝብት ላይ ይጥላል። በመሰረቱ ከ“ጨቋኝ” ጋር እየታገልን ነው ማለታቸውም ነው።

የዘሃበሻ “ኢዲቶሪያል ቦርድ”፣ ጋዜጠኝነት እና ታጋይነት የተደበላለቀበት ይመስላል። በመሰረቱ መታገሉ ባልከፋ ነበር። “…እባካችሁ ኮስተር ብለን እንታገል…”…. (ከታች በግራ በኩል የተለጠፈውን ቅጂ ይመልከቱ) ሲሉን መቼም አንዱ ትግል የህወሃት መንግስት የሚጠቀምበት ባንዲራ  “… ባለ ኮከቡ የሴይጣን ባንዲራ… (ከታች የተለጠፉትን ሁለት ቅጅዎች ይመልከቱ)” መሆኑን በማጋለጥ ነው። ጎሽ! እሰይ! እንዲህ ነው ጋዜጠኝነት!

ሲጀመር፣ የኢትዮጵያ ህዝብ አሁን ባለበት የመከራ አጣብቂኝ ውስጥ ሆኖ፣ ስለ “ኮከብ ሰይጣንነት…” ለመወያየት የቅንጦት ጊዜው ያለው አይመስለኝም። ባንዲራን/አገዛዝን ከሃይማኖት ጋር ማዛመድ፣ (ለምሳሌ የአሜሪካ ገንዘቦች ላይ ያለውን “god bless America…የሚለውን ጽሁፍ፤ እና የሳውዲ መንግስት፣ ሃይማኖቱን መሰረት አድርጎ የሰው አንገት የሚቆረጥበትን ጎራዴ … ምስል ማተማቸው…) ያለና የነበረ ቢሆንም፣ የ“ስብስቴ ነጋሲ”ው ጊዜ ጠሃፊ አለቃ ዘነብ እንኳን ያኔ “ባንዲራ ላይ ያለ ኮከብ የሴይጣን ምልክት ነው (በቀይ ክበብ ውስጥ ያሉትን ጽሁፎች ይመልከቱ)…” ብለው የሚጽፉ ቀርቶ የሚያስቡም አይመስለኝም። ዘሃበሻ ላይ የሚወጣውን ይሄን “የኮከብ እና የሴይጣን” ነገር ባሰብኩ ቁጥር  የሚታወሰኝ፣ በቅርቡ “ወለላዬ” ባደረገው ቃለ-መጠይቅ “ሰዎችን አለስማቸው ስም እየሰጠን አበላሽተናቸዋል…ሁሉም አለቦታው ተቀምጦ አገራችንም እኛም መቀለጃ የሆነው ለዚህ ነው…” ያለው እና፤ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም፣ ዲ/ን ዳንኤል ክብረትን “…ያውቃል እንዲባል የሚጽፍ አንጂ አውቆ የሚጽፍ አይመስልም” … ‘እንትንን እንትን ካላሉት፣ አብሮ ይፈተፍታል’…” ያሉት ነው። በመሆኑም፣ ከጋዜጠኝነት ሙያ አኳያ፣ እንዲህ የወረደ አይነት ሃሳብ እያዩ ዝም ማለት፣ የጋዜጠኝነትን ሙያ ማራከስ፣ ጋዜጠኛ የሆነን ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ሁሉ ትዝብት ላይ የሚጥል ነውና፣ በአደባባይ መናገር መጀመር ያለብን ይመስለኛል።

የዘ-ሃበሻ ኢዲቶሪያል ቦርድ በቅርቡ ለላክሁት ጽሁፍ ምላሽ በሚመስለው መግለጫው፣ ጋዜጣዋ “በአንዳንድ መመዘኛዎች ከኢትዮጵያዊያን ድረ-ገጾች በሙሉ በአንደኝነት የምትጠቀስ…” መሆኗን ሲነግረን እውነት አለው። “በአንዳንድ” የሚለው፣ እኔ እንደሚመስለኝ፣ እንደ ዘሃበሻ በርካታ ጽሁፍ እና ሌላም የሜዲያ ውጤት የሚያቀርብ ድረ-ገጽ ያለ አይመስለኝም።… ነገር ግን፣ ከኢትዮጵያ ድረ-ገጾች በአንደኛነት ከምትጠቀስ ጋዜጣ አዘጋጆች፦ “…ወያኔ … ሙድ ሲይዝብን ይውላል….ተቃዋሚዎች ሳይቀሩ ሙድ ሲይዙብን ከማየት በላይ የሚያም ነገር አለ? እባካችሁ ኮስተር ብለን እንታገል….”  የሚል ጽሁፍ ማንበብ ያለብን አይመስለኝም። ደሞ’ስ ጋዜጠኛ ይታገላል እንዴ? … የሆነውን ሪፖርት ማድረግ፣ በሆነው ላይ ትንታኔ መጻፍ፣ … ማስነበብ እና ማሳየት ነው። “ጀኒውን” የሆነ ዜናዊ ትንተና እና መሰል ጽሁፎችን በማቅረብ፣ በትግል ሂደቱ እየሆነ ያለውን በማሳየቱ ግን የሚያምንበትን ትግል ሊያግዝ ይችላል።

የዘሃበሻ አዘጋጆች “ሙድ ሲይዙብን…”፣ “..የሴይጣን ምልክት…” በማለት የሚያወጡት ጽሁፍ “አይ ‘ኩምክና ነው፣ እየቀለድን ነው’” የሚሉን ከሆነ (እንዲህ በወረደ ቋንቋ ሊጻፍበት የሚገባ ጉዳይ ባይሆንም) በጽሁፍ ይኼንኑ ይንገሩን። አለበለዚያ ግን ቆም ብለው ራሳቸውን መመርመር አለባቸው። ዘሃበሻ ብዙ ጎብኚ እንዳላት ባለፈውም ጽሁፍ መስክረናል። እንዲህ በብዛት መረጃ በድረ-ገጽ ላይ መኮልኮል ጋዜጣውንም ጋዜጣ፣ አዘጋጆቹንም ጋዜጠኞች ሊያስብላቸው ይችላል ማለት ግን አይደለም።

ሌላው….የጋዜጣው አዘጋጆች እንደሚፈልጉት “ለዘ-ሃበሻ በቀጥታ ገንቢ አስተያየቶችን መስጠት ሲችሉ…” የሚለውም፣ ባጭሩ “ታፈሰ ‘በጓዳ’ ቀስ ብሎ በሹክሹክታ ለምን አልነገረንም…?” የሚል ቅሬታ ነው። በአደባባይ ለህዝብ ለቀረበ ጽሁፍ፣ ምላሽ መሰጠት ያለበት በአደባባይ ነው። “የመንደርተኛ ወሬ…” ከማለት ሙያው እጅግ በጥቂቱ የሚጠይቀውን ምላሽ እንኳን መስጠት ሳይችሉ “ጨቋኝ፤ መንደርተኛ” ማለት ራስን ያስገምታል። ጽሁፉ በአብዛኛው በዘ-ሃበሻ ጽሁፍ የቋንቋ አጠቃቀም እና ሰዋሰው ላይ ያተኮረ ሰለሆነ፣ በጥቅሉ “ስነ-ጽሁፋዊ ትችት/ቅኝት” ሊባል ይችላል። ዘ-ሃበሻን በተቸሁበት ጽሁፍ ውስጥ በእንግሊዝኛው “fact-checking/እውነትነቱን ማመሳከር”ም አለበት።

ለምሳሌ “….የፌስ–ቡክ ገጻችንን ሃክ… ያደረጉ… የሕወሓት ተላላኪዎችም በሕግ የሚገባቸውን እርምጃ አግኝተዋል…” ለተባለው፣ በምጸት “…ተላላኪዎቹ እነማን ይባላሉ? ቅጣቱ ግርፋት ነው? ወይስ ስቅላት?”…የሚለው “እውነት ከሆነ በማስረጃ አሳዩን…” ማለት እና “እውነትነቱን ማመሳከር”ም ነው። በጣም ዝርዝር “አይነታው” ውስጥ እንግባ ከተባለ ደግሞ “ምጸታዊ” (satirical criticism”) ሊሆን ይችላል።  “…‘መቼም የፌስ ቡኩ መስራች ማርክ ዙከርበርግ፣ ለዘ-ሃበሻ ሲል …የህወሃት ተላላኪዎች… በግርፋት ይቀጡልኝ’ አይልም” ነው የምንለው። ጽሁፉን “ምጸታዊ ቅኝት” የሚያስብለውም ይኸው ነው፤ እንጂ፣ የዘ-ሃበሻ “editorial board”  እንዳለው፣ ነገር የመፈለግ “ጠጠር ውርውራ”ም፣  “የመንደርተኛ ወሬ”ም አይደለም። አዘጋጆቹ ጽሁፉ ለምን “የመንደርተኛ ወሬ” እንደመሰላቸው ባስብ፣ ባወጣና ባወርድ፣ አንድም ነገር ማግኘት አልቻልኩም፤ ስጠረጥር ግን ጋዜጣዋን “ሰከን በይ”፣ “ሙድ አትያዢብን” (“ሙድ…” እንኳን ታፈሰ ከዘሃበሻ ከራሷ የኮረጀው ቋንቋ ነው) የመሳሰለው፣ ግዑዟን ጋዜጣ በ“ሰውኛ” (personification) መግለጼ ይመስለኛል።

ለምሳሌ፣ ከዘሃበሻ ጋዜጣ ላይ የተገኘውን ጽሁፍ መሰረት አድርጎ፣ “ኮከብ ባየሁ ቁጥር እበረግጋለሁ”  በሚል የቀረበው የዚህ ጽሁፍ ርዕስ ምጸታዊ (satirical) እና “ሰውኛ (personified)” ነው። እንዲህ…፦

… ዘ-ሃበሻ እግዜር ይይላት! ኮከብ ባየሁ ቁጥር ያስበረግገኝ ጀምሯል። ዘ-ሃበሻ  “ኮከብ፣ የሰይጣን ምልክት መሆኑን ታውቃለችና ኮከብ ባለበት አጠገብ ዝር አትልም፣ እናም ገሃነም ከመግባት ዳነች። እኔ ግን “ኮከብ” ማለት “ሴይጣን” መሆኑን ገና አይምሮየ አልለመደው ሆኖ፣ ኮከብ ባየሁ ቁጥር መደንበር ሆኗል ስራዬ። እንደኔ አይነቱ፤ የሃይማኖት ማይም የሆነ አንባቢውን እንዲህ ሽብር በሽብር ማድረግ ራሱ፣ ዘሃበሻን ለገሃነም የሚዳርጋት ሃጢያት ይመስለኛል። … ጋዜጣዋን የራስ እምነት ማሳለጫ ማድረግም ከጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር አንጻር ትክክል አይደለም። አለበለዚያ “ዘሃበሻ” ስሟ “ዘ-ክርስቲያንከ ወ-ዘጋቢከ” በሚል ይተካልን።…”

የሚለው የአጻጻፍ ዘዬ፣ ምጸታዊ ግምገማ እንደሆነው ሁሉ፣ ያለፈውም ጽሁፍ ነገር ፍለጋ “ጠጠር ውርወራ…”፣ “የመንደርተኛ ወሬም” አይደለም።

ለአመታት በጋዜጠኝነቱ ሲታሰር፣ ሲገረፍ እና ሲጋዝ ከኖረ፣ ከአገርም ወጥቶ ዘጠኝ አመት ሙሉ ከጻፈ editor in chief፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች እየሞቱ እና እየተሰደዱ፣ እየታገሉ እና እየተጋደሉ ባሉባት አገር ኢትዮጵያ፣ ምዕራቡ አለም ሆኖ፦ “…ወያኔ … ሙድ ሲይዝብን…”፣ “…የኮከብ ምልክት ያለበት ባንዴራ የሰይጣን ነው…” የሚል ጽሁፍ ማቅረብ፣ በጋለ እና በተጋጋለው ትግል ላይ ቀዝቃዛ ውሃ እንደማፍሰስ ይቆጠራል። ታፈሰ “adios journalism” እንዳለው ነው– “ጋዜጠኝነት አለቀለት! ሙቶ ተቀበረ”።

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ቢያንስ ለሙያቸው ክብር ሲሉ፣ በአደባባይ መናገር/መጻፍ ይጠበቅባቸው ይመስለኛል።

በመዝገቡ ሊበን


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. abebeayalew says

    February 19, 2017 01:52 pm at 1:52 pm

    merejaw konjo new ketilubet

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule