አንድ ሰው በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን በሚናገራቸው/በሚጽፋቸው ጽሁፎች አስተሳሰቡ እና ብቃቱ ይገመታል፤ የሚመራውን ድርጅት/ተቋም ብቃትም ይናገራል። እንደ ግለ-ሰብ ስለ ራስ፣ ስለ ቤተሰብ እና ስለ ጓደኛ የሚናገራቸው ወይም የሚጽፋቸው ጽሁፎች ከሙያዊ ብቃት እና ችሎታ አኳያ ብዙም የሚያስከትለው ተጽዕኖ አይኖርም። ጋዜጠኛ ነኝ ያለ ሁሉ ጋዜጠኛ እንዳልሆነ ግምት ውስጥ በማስገባት፣ የጋዜጣ አዘጋጅ ስትሆን፣ ከዚያም ብዙ ተከታዩች ሲኖሩህ እና ስለ አገር እና የማህበራዊ ጉዳይ የምትጽፋቸው ሲሆን ግን ቢያንስ ከጋዜጠኛነት ሙያ፣ ከጭብጥም ሆነ ከቋንቋ አጠቃቀም አኳያ ይሄን ያህል መወረድ በ“ሙደኞች” (“ሙድ” የዘ-ሃበሻ የራሷ አማርኛ ነው) ቋንቋ ሙያዊ “ቅሽምና” ነው። ስለዚህ እኛም ዘ-ሃበሻን በ“ሙድ” ልንተች ነው።
“ወያኔ በየቀኑ ህዝባችንን እየገደለና እያሰረ ሙድ ሲይዝብን…” እንዳለችው ሁሉ፣ ዘ-ሃበሻም ሙድ እየያዘችብን ነው የምር! ከሰሞኑ በሳይበር ጥቃት “ከአላማየ ተሰናከልኩ” የምትንለን ዘ-ሃበሻ “በሳይበር የሚደረግ ጥቃት ከዓላማችን አላሰናከለንም” በማለት “ሙድ” ይዛብናለች።
እስቲ ይሄን በሳጥን ውስጥ የተጻፈውን የዘ-ሃበሻን የፌስቡክ “ርዕስ አንቀጽ?” … እና … እባክሽ! ስለ እዝጊሃር ብለሽ፤ ዘ-ሃበሻ! የጋዜጣ ቋንቋ ተናገሪ።
ደሞስ “የሸኖ እና የማረቆ የነጻ አውጪ መንግስት…” የሚባል ተፈጥሯል እንዴ? እውነትም “ከዚህ በላይ የሚያም ነገር” የለም! ዘ-ሃበሻ እውነት ብለሻል። እኛ በቅርቡ የሰማነው “የአማራ ነጻ አውጪ ግንባር” ነው። “ሸኖ” እና “ማረቆ” እያሉ ማድበስበስ ከአንጋፋ፣ በየእስር ቤቶች ተፈትና ከወጣች ጋዜጣ አይጠበቅም።
“…ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር በመራመድ” ተግታ የምትሰራው ዘ-ሃበሻ እንዴት በሃከር እንደተሰናከለችም እግዜር ይወቅላት። ለነገሩ ግን ድረ-ገጻችንን “እንዳሰናከለችብን”፣ የ“ማጀቴ ቆሌ አድባር መጀን” ወያኔን ስንክል ያድርጋት አቦ!… እንዲህ ታምረኛ የሆነችው እና ቀን ተሌት በወያኔ ስትሳደድ የምትውለው ጋዜጣችንን….ባይሆን በአማርኛችን ላይ ሙድ ባትይዝብን ይሻላታል፣ የምር!
ይሄ ከዚህ በታች የሰረፈው በአንዱ ድረ-ገጽ ላይ “ዘ-ሃበሻ” በሙድ የለቀቀችብን ጽሁፍ ነው። አላግባብ የገባውን እና ግድፈቱን በቀይ፣ ጠማማውን ስናቃና እና/ወይም ትክክለኛ አማርኛ ነው ያልነውን ደግሞ በአረንጓዴ፤ በጣም “ሙድ ስንይዝባት” ደግሞ በወይነ-ጠጅ እያቀለምን እና እንዲህ {እያቀፍን} ሽንፍላ ማጠባችንን ልንጀምር ነው–በዘ-ሃበሻ ጭብጥ፣ ቋንቋ እና ሰዋሰው ላይ።
“በሳይበር የሚደረግ ጥቃት ከዓላማችን አላሰናከለንም” – ከዘ–ሐበሻ የተሰጠ መግለጫ
“እንኳን በሳይበር የሚደረግ ጥቃት ይቅርና የወያኔ ተገንጣይ መንግስት እስር ቤትም ከዓላማችን አላሰናከለንም {ይህ እንግዲህ በጋዜጠኝነት ቋንቋ በእንግሊዝኛው “lead” የምንለው መሆኑ ነው። “lead” በአንድ ዜና/ዜና ሃተታ ውስጥ የጽሁፉ ጠቅላላ ሃሳብ በመጀመሪያው አንቀጽ በአጭሩ የሚገለጽበት፣ አንባቢ ቀድሞ የሚያነበው እና ወደፊት ገፍቶ ለማንበብ ወይም ላለማንበብ የሚወስንበት ወሳኝ ክፍል ነው።}– ከዘ–ሐበሻ የተሰጠ መግለጫ {ድግግሞሽ ነው}
ዘ-ሐበሻ ሃክ በተደረገበት ወቅት መረጃዎቻችን ጠፍተው እንዲህ [ገጹ ጠፍቶ ይታያል] ነበር ድረ-ገጻችን የሚታየው {ጾታዋ ወንድ ነው እዚህ]:: የዘ-ሐበሻ ድረ-ገጽ ከተመሰረተች {transgender surgery …? ሴት ሆነች] 9 ዘጠኝ ዓመት ሆኗታል። ባለፉት 9 ዘጠኝ {እንዲያውም ድግግሞሽ ነው፣ እናም} በነዚህ ዓመታት ውስጥ {ቢባል የተሻለ ነበር} በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎችን መረጃ ከሚያቀብሉ የመረጃ መረቦች መካከል አንዷ በመሆን በአማራጭነት ሚድያነት አገልግላለች እያገለገለች ትገኛለች:: በየዕለቱ ድክመቶቻችንን በማረም ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር በመራመድ {ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር የምትራመድ ዘ-ሃበሻ በ“ሃከር” ስትጠቃ መኖሯ ምነው?} አሁንም ተመራጭና ተአማኒ ሚዲያ ለመሆን ተግተን እየሰራን ነው:: እንደሚታወቀው የዘ-ሐበሻ አዘጋጆች የሚዲያን ሥራ የጀመሩት እዚህ ስደት ላይ ከወጡ በኋላ አይደለም {ይቺን እንኳን ለ“Resume” ብትጠቀሚ ይሻልሻል ዘ-ሃበሻ}:: በሃገር ቤት በኢትዮጵያ ነጻው ፕሬስ ውስጥ መስዋዕትነት የበከፈሉ፣ የበታሰሩ፣ የበተገረፉና ብዙ መስዋዕትነት በከፈሉ ጋዜጠኞች የምትዘጋጅ ድረ-ገጽ ናት {መገረፍ፣ መታሰሩ እውነት ሆኖ፣ ያኔ በቅንጅት ጊዜ “ጋዜጠኛ ነኝ” ይል የነበረው ሁሉ ጋዜጠኛ አልነበረም። በሽምግልና ስም ህወሃትን አፈር ከላሰበት በማስነሳት የሚታወቁት ፕ/ር ኤፍሬም ይስሃቅ እና ቡድናቸው ስለ እርቅ ያወሩ በነበረበት እና ትልቅ ዜና ሆኖ በነበረበት ጊዜ “…እንዴ! ሁለቱ ከታረቁማ እኛ {ጥቂት ጋዜጠኞች} ምን ሰርተን ልንበላ ነው…?} ይሉ የነበሩ እንደነበሩ እና የታሰሩ እንደነበሩም እናውቃለን፣ የታሰረ ሁሉ ብቃት ያለው ጋዜጠኛ ነበር ማለት ግን አይደለም። በጋዜጠኝነት ትምህርትም፣ በልምድም፣ በሁለቱም ጥምረት እና ጥረት በሂደት የተማሩ፣ የተካኑ ያኔም አሁንም በህወሃት በግፍ የተገደሉ፣ የታሰሩ፣ ተሰደው የሚገኙ ጋዜጠኞች እንዳሉ ግን ሃቅ ነው። … ወደ ሽንፊላ አጠባዬ ልግባ እናቴ….} ዘ-ሐበሻ ድረ-ገጽ በተለይ ዕድሜያቸው ከ18 – 45 ዓመት ክልል ውስጥ [በሆኑ አንባቢያን] በብዛት የምትጎበኝ {“ጎብኚ” ናት “ተጎብኚ?” መጥበቅ እና መላላትን መለየት ያስፈልግ ነበር እዚህ}፣ ወቅታዊ መረጃዎችንም በፍጥነት የምታደርስ መሆኗ የሕወሓትን መንግስት ሁሌም እንዳስደነገጠች እንዳሳሰበች ነው {ህወሃት በድንጋጤ “ስትሮክ” ሳይዛት አይቀርም መቼም}:: ባለፉት 9 ዘጠኝ ዓመታት በተለይ በእነዚህ ዕድሜ ክልሎች ውስጥ ባሉ ወገኖች ድረ-ገጻችን በመጎብኘቷና በአብዛኛው በግምት 75% የሚሆነው የዘ-ሐበሻ ድረ-ገጽ ጎብኚም ከኢትዮጵያ መሆኑ ያበሳጨው ያሳሰበው {መንግስት “ተበሳጨ” አይባልም። አቤት! ከጭብጡ ሙትነት፣ የቋንቋው ድህነት!} የሕወሓቱት መንግስት በርካታ ብሮችን በማፍሰስ {1ኛ) ህወሃት ብሩን እያፈሰሰ አይደለም፤ ፤ ዘ-ሐበሻ የምታስተላልፈውን ነጻና ያልተገደበ መረጃ ለማፈን ብዙ ጥረቶችን አድርጓል {እውነት ዘ-ሃበሻን ብቻ ለይቶ ለማጥቃትም ያን ያህል የሚደክም ማስመሰለም አግባብ አይመስለኝም}:: ዘ-ሐበሻ ድረ-ገጽን በሶስተኛ ወገን እንዲሸጥለት ከመጠየቅ አንስቶ ኮምፒውተሮቻችንን ከማጥቃት እስከ አዘጋጆቹ ቤተሰብ ድረስ ሄዶ የሕወሓት መንግስት ያላደረገው ያልሞከረው ነገር የለም:: በአዘጋጆቹን በአካልና በንብረቶችቻቸው ላይ ለማጥቃትም ጥቃት ለማድረስም ብዙ ተሞክሮም ነበር:: ባለፉት 9 ዘጠኝ ዓመታት የደረሰብን ፈተና {እነ እስክንድር፣ ርዕዮት፣ ተመስገን ደሳለኝ እና ሌሎቹ አሁንም ድረስ ዋጋ እየከፈሉ ያሉ ጋዜጠኞች ምን ይበሉ?} በእንዲህ በትንሹ {በትላልቅ ፊደላት አትጽፊውም ኖሯል?} በግማሽ ገጽ ተጽፎ {ወይም “በአጭሩ ተዘርዝሮ የሚያልቅ ብቻ አይደለም:: ዘ-ሐበሻ ድረገጽን ሃክ ለማድረግ ብዙ ወጪዎችን የሚያፈሰው የሕወሓት መንግስት {ዘሃበሻን ለይቶ? የምር?} ከድረገጻችን በተጨማሪ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ተከታይ ያለውን የፌስቡክ ገጻችንን ሃክ እስከማድረግ ደርሶ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን {“…ትዝታ በፖስታ ልኬልሻለሁ…” አለ ያ ዘፋኝ} ነው:: የፌስቡክ ገጻችንን ሃክ አድርገው የነበሩ የሕወሓት ተላላኪዎችም በሕግ የሚገባቸውን እርምጃ አግኝተዋል {ርምጃ ተወሰደባቸው? ትልቅ ዜና ከእጅሽ ላይ አምልጦሻል ዘ-ሃበሻ! ይኼን ዜና ነበር መጻፍ የነበረብሽ፤… ለመሆኑ ተላላኪዎቹ እነማን ይባላሉ? ቅጣቱ ግርፋት ነው? ወይስ ስቅላት?…. ሙድ አትያዢብን ባክሽ! ይሄ እንኳን አቶ ማርክ ዙከርበርግን እና ቡድናቸውን ማሳጣት ይመስለናል}::
ይህን በሕወሓት መንግስት የሚደርሰውን የሳይበር ጥቃት ለማምለጥ ዘ-ሐበሻና አዘጋጆቿ በየ6ስድስት ወሩ ኮምፒውተሮቻቸውን ይቀያይሩ ነበር {“የማይመስል ነገር ለሚስትህ አትንገር” አለ ያገሬ ሰው… ከሳይበር ጥቃት ለመዳን በየስድስት ወሩ ኮምፒውተር መቀያየር እንዴት እንደሚያዋጣ የገባት ዘ-ሃበሻ ብቻ መሆን አለባት። እኛ መቼም “how to prevent cyber attack” ብለን ጎልጉለን ካገኘናቸው በአስራዎች ከሚቆጠሩት ዘዴዎች ውስጥ፣ “ኮምፒውተር መቀያየር” የሚል አንድም አላገኘንም።… ይልቅየ ኪሳችንን ዳበስ ዳበስ እናድርግ ጎበዝ!}:: ብዙ ገንዘብ በማውጣትም {ይኼው! ያልነው ነገር፣ ዳበስ ዳበስ …} የሳይበር ዘገበኛዎችን (ሴክዩሪቶቲዎችን) {“ዘገበኛ” ማለት (“ሴክዩሪቲ” ማለት መሆኑን ገና ዛሬ ተማርኩ፤ “Thank You Ze-habesha)} በመጫንም ጥቃቱን ስንከላከል ቆይተናል:: በዚህም መሃከል ግን ዘወትር ነጻ ሚዲያዎችን ለማፈን የማይተኛው የሕወሕሃት መንግስት እንደገና በዛሬው ዕለት ራሳቸውን “ጋዛ ሃከርስ” ብለው የሚጠሩ ሃከሮችን በመቅጠር {እንደ ህወሃት ያለ ፈሪ መንግስት በምድር አለም ያለ አይመስለኝም የምር! ይኼ ነገር እውነት ከሆነ} የዋና አዘጋጁን ኢሜይል ሃክ በማድረግ እንዲሁም ድረገጹን ሃክ አድርገው በመቆጣጠር ለተወሰነ ሰዓታት ሲያውኩን ውለዋል:: የሕወሓት መንግስት የአዘጋጆቹን ኢሜይል ሃክ ቢያደርግ የሚያገኘው ምንም ምስጢራዊ መረጃ አይኖርም {ምስጢር እና ጉዳት ከሌለው ታዲያ ይሄ ሁሉ “ኢሜል ሃክ ተደረገ” ዋይታ ምን ያደርጋል እዚህ?}:: ዘ-ሐበሻ መረጃን ለሕዝብ ከማድረስ ውጭ ሌላ ምንም ዓይነት ተልዕኮ የሌላት በመሆኑ ምናልባት ወያኔዎች ኢሜሎቻችንን ቢበረብሩ የሚያገኙት ዞሮ ዞሮ በድረ-ገጻችን ላይ በይፋ ተጽፈው የሚያገኟቸውን ጽሁፎች ብቻ ናቸውና ነውና ለልፋታቸውና ላጠፉት ገንዘብ ኪሳራቸው አስደስቶናል {Adios! Journalism}:: ድረገጻችንን ግን ሃክ ባደረጉትና ጥቃት በፈጸሙበት ቁጥር ግፋ ቢል እኛን የሚያስወጣን ገንዘብና መረጃ ልናደርሰበት የምንችልበትን ውድ ጊዜ ብቻ ነው::
ስለሆነም የሕወሓት መንግስት አንድ ሊገነበዘበው ሊገነዘበው የሚገባው ትልቅ ነገር አለ:: የዘ-ሐበሻ አዘጋጆች {ስንት ናችሁ? መቼም ዋና አዘጋጅዋ አቶ ሄኖክ ታስረው እንደነበረ በሳይበር ላይ መከላከያ ሚ/ር የነበሩቱ ሲናገሩ ሰምተናል! አዘጋጁ ከህወሃት ግፍ እና መከራ ባጭሩ በመገላገላቸው እንኳን ደስ ያላቸው እንላለን} በሃገር ቤት የስርዓቱን ማሰቃያ እስር ቤቶችንና ጨለማ ክፍሎችን እነማዕከላዊን፣ ከርቸሌን፣ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያንና ሌሎችንም በመቅመስ {በህወሃት የመታሰር ጣዕሙ ጉድ ነው! …ግን ምን ምን ይላል? ከሆነ አይቀር ጣዕሙም ይነገረን እንጂ! እንደ እሬት ይምረራል? ወይስ ይጎመዝዛል?} የቆሙለትን ዓላማ ያጠነከሩ እንጂ በደረሰባቸው እስር የተፍረከረኩ አይደሉም {…ዘ-ሃበሻን ግን “… ስለ መታሰርሽ ሁሌም ስላወራሽ፣ ብቁ ጋዜጣ አያደርግሽም” የሚል መልዕክት ቢያስተላልፉልን ደግ ነው}:: ሕወሓት ዛሬም በሳይበር ሕወሓት በየሚያደርስብን ጥቃት ከአቋማችን ምንም ፍንክች እንደማያደርገን፣ እንደዲያውም በተጠቃን ቁጥር እንደምንጠነክር {‘አቻዩ ዲፌሮ’ አለ ጥልያን} እንዲገነዘቡት ለመግለጽ እንወዳለን:: ለዚህም ነው በመግቢያችን ላይ “እንኳን በሳይበር የሚደረግ ጥቃት የወያኔ ተገንጣይ መንግስት እስር ቤትም {ይሄን የእስራት ወሬ መስማት አሁንስ ደከመኝ፣ የምር! ይኼን የ“ታስረን ነበር” ዜና/ር ዕስ አንቀጽ ሆኖ ስናነብ ምናልባትም አሁን ለ10ኛ ጊዜ ይሆናል። ካገር የተሰደደው ጋዜጠኛ ሁሉ ለሙያው ክብር ሲል እንዲህ አይነቱን የወረደ ነገር እየሰማ እና እያነበበ ዝም ማለት አልነበረበትም} ከዓላማችን አላሰናከለንም” ያልነው::
ዕውነት ያሸንፋል!
የዘ-ሐበሻ ኤዲቶሪያል ቦርድ
ዘ-ሃበሻ ምናልባትም ከሁሉም የኢትዮጵያ ሜዲያዎች በላይ ጎብኚ እንዳላት እርግጥ ይመስለናል። ምክንያቱ ደግሞ በራሷ ቋንቋ ከዚህ ቀደም “ብዙ ጎብኚ ያለን … ድረ-ገጻችንን በኢንፎርሜሽን በማጨቃችን ነው” እንዳለችው ነው። ይኼው ነው። በዘጠኝ አመት ታሪኳ፣ አንድም የራሷን ዜና፣ ዜና ሃተታ እና ርዕስ አንቀጽ ሰርታ አታውቅም (እስከማውቀው ድረስ፣ ጥቂት ሚዲያዎች አልፎ አልፎ እንደ መግቢያ አይነት ጽሁፎችን የሚያወጡ ከመሆናቸው በስተቀር፣ በመደበኛነት የራሳቸውን ዜና እና ርዕስ አንቀጽ የሚጽፉ ጋዜጦች ብዙም የሉንም። ከማናቸውም ከአገር ውጭ ከሚገኙ/ከተመሰረቱ እና እኔ ከማውቃቸው የድረ-ገጽ ጋዜጦች/ሜዲያዎች ውስጥ የራሱን ዜና በተለይም የራሱን ርዕስ አንቀጽ በመደበኛነት በመጻፍ “ኢሳት {ሪሶርሱም የሰው ሃይሉም የተሻለ ስለሆነም ጭምር ነው} እና “ጉልጉል” የመጀመሪያውን ደረጃ የሚይዙ ይመስለኛል። የሪሶርስ መኖር እና አለመኖር በተወሰነ መልኩ ሊረዳ ቢችልም፣ የሃገር፣ የሙያ፣ እና የአላማ ጽናትና ፍቅር ካለ እንደ ፕ/ር አል-ማርያም ለአስር አመት ሙሉ፣ አንዲትም ሰኞ ሳያጓድሉ መጻፍ … እኔ የሚገርመኝ የፕሮፌሰሩ የዕለት ከዕለት የሙያ እና ህይወት ዲሲፕሊኑ ነው። …
ጎልጉል ለምሳሌ የወቅቱን ፖለቲካችንን እና በጋምቤላ ዜጎቻችን ላይ የደረሰውን እልቂት አስመልክቶ በአንድ ሳምንት ውስጥ ሁለት ጽሁፎችን አውጥቷል። “ጎልጉል” በአንድ ነገሩም ልዩ ነው–የ“ጎግል”ም ሆነ የሌላ ሰርጎ-ገብ ማስታወቂያ ድንገት የምታነበው ገጽ ላይ እየተደቀነ “አንጎል” አያደርግህም። ዘ-ሃበሻን እኮ በመደበኛነት ማየት በጣም ያስፈራኝ ጀምሯል፣ ቀድሞ ነገር ምንነቱን የማታውቀው ማስታወቂያ ድንገት ገጹ ላይ ይደቀናል። ሲመስለኝ ዘ-ሃበሻ ሃክ የመደረጓ ምክንያት፣ ካለ ምርጫ የምታግበሰብሰው የሶሻል ሜዲያ ጓደኛ፣ RRS feed, ወዘተ ሊንክ መዐት ይመስለኛል። ህወሃት ዘ-ሃበሻን ብቻውን ለይቶ ሃክ ለማድረግ የማይተኛ መንግስት አድርጎ ማቅረብ መሰረት የለውም።
በተረፈ ዘ-ሃበሻ “ስትታሰር፣ ከርቼሌ ስትወርድ፣ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ዘብጥያ ወርዳ፣ ስትሰቃይ ወዘተ…” መክረሟን እና መከራዋን ያየችበት ጋዜጠኝነት እንዲያው መና ይቅር አይባልም! ይሁን። ነገር ግን ከተመሰረተች ከዘጠኝ አመታት በኋላም እንኳን እንዲህ ያለ ጋዜጠኝነት ያሳየችን ዘ-ሃበሻ፣ ያኔ የሰራችው ጋዜጠኝነት እንዴት ቢሆን ይሆን? እንላለን መቼም ሙድ ስንይዝባት! ዘ-ሃበሻ እባክሽ ሰከን በይ ትንሽ! … ይሁኔ በላይን …።
በታፈሰ ወርቁ
tafeseworku2016@gmail.com
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
Leave a Reply