አሜሪካ 2 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር የሚያወጡ የልምምድና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቀሶችን ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማድረጓን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታወቀ።
ይህ ድጋፍ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው አልሸባብ የሽብር ቡድን እና ሌሎች የሽብር ድርጅቶችን ሊፈጥሩት የሚችሉትን አደጋዎች ለመመከት የሚያግዘው መሆኑ ተጠቁሟል።
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታጎን) ከኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን የገለፀው ኤምባሲው በተያዘው ዓመት የተደረገው ድጋፍም የዚሁ አካል ነው ተብሏል።
ድጋፉም አምቡላንስ፣ ላንድ ክሮዘር፣ የእቃና የነዳጅ መጫኛ ተሸከርካሪዎችን እንዲሁም የምሽት አጉሊ መነፀር እንደሚያካትት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ሽብርተኝነትን ከመከላከል ጋር ተያይዞ የተደረገ አንደኛው የድጋፍ አይነት ነው ተብሏል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Melese Degaga says
ምርጥ ጋዜጠኛ።