• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

መስፍን ኢንጂነሪንግ 30ሚሊዮን ዶላር አተርፋለሁ አለ

December 18, 2012 11:17 am by Editor 1 Comment

በኤፈርት ስር ከታቀፉት የህወሃት የንግድ ተቋሞች መካከል አንዱ የሆነው መስፍን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪያል በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት ሰላሳ ሚሊዮን ዶላር ለማትረፍ እንደሚሰራ አስታወቀ። ለሶስት ስኳር ፋብሪካዎች የአገዳ መቀቀያ ገንዳ (ቦይሊንግ ሃውስ) ለመስራት የሁለት ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር ስምምነት አደረገ። የአማራ ክልል በብሄር ብሄረሰቦች ቀን በዓል ድምቀት ላሳየው “ቁርጠኛነት” ተደነቀ፣ ጣና ሃይቅና አካባቢውን የወረረውን አደገኛ አረም ለማጥፋት የአንድ ለአምስት የጥርነፋ አደረጃጀት ማከናወኑ የአካባቢውን አርሶ አደሮች እንዳስደሰተ ተጠቆመ።

ኢቲቪ ትላንት ይፋ እንዳደረገው ከተቋቋመ አስራ ዘጠኝ ዓመት የሞላው መስፍን ኢንጂነሪንግ ከስኳር ፋብሪካዎቹ ጋር የገባውን ውል በአስራ አንድ ወራት ውስጥ ለማስረከብ ሃያ አምስት ቶን ብረት ከውጪ አስገብቷል። ስራውን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት ምክትል ስራ አስኪያጁ አቶ አማኑኤል ገብረኪዳን “መስፍን ኢንጂነሪንግ አገራዊና ግዙፍ ወደ ሆኑ ፕሮጀክቶች ግንባታ ተዛውሯል” ብለዋል።

መስፍን ኢንጂነሪንግ ቀደም ሲል ሲሰራቸው የነበረውን ስራዎች ለአነስተኛና ጥቃቅን ድርጅቶች በማስተላለፍ በከፍተኛ ፕሮጀክቶች ላይ በማተኮር እንደሚሰራ ያስታወቁት አቶ አማኑኤል፣ ድርጅታቸው አዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ በ35ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ከፍተኛና በአይነቱ ልዩ የሆነ ላቦራቶሪ (ካልቸር ሃውስ) በማስገንባት ላይ እንደሆነ አመልክተዋል።አያይዘውም በቀጣይ ሁለት ዓመታት 30 ሚሊዮን ዶላር ለማትረፍ መታቀዱን ተናግረዋል።

የህወሃት ንግድ ተቋሞች ወደ ከፍተኛ ደረጃ በመሸጋገር በወርቅ ማዕድን ፍለጋ፣ በአስመጪነትና በላኪነት፣ በባንክና በኢንቨስትመንት በከፍተኛ እመርታ ላይ እንደሚገኙ ወ/ሮ አዜብ መግለጻቸው አይዘነጋም። በቅርቡ ወ/ሮ አዜብ ይፋ ባደረጉት መረጃ መሰረት በቀጣዩ አምስት ዓመታት ትግራይን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ የሚያስችል እቅድ አቶ መለስ በነደፉት መሰረት እንቅስቃሴ እንደተጀመረ ታውቋል።

ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ሲዘግብ ወ/ሮ አዜብ የባለቤታቸውን የአቶ መለስን ማንነት በሚያጋልጥ መልኩ አስገራሚ መረጃዎችን ማውጣታቸውን ጠቅሶ ነበር። በወቅቱም “ኢትዮጵያ ህዳሴ ባለቤትና ባለራዕዩ መሪ” በመባል በራሱ በህወሓትና በመላው የኢህአዴግ ሰዎች “የሚመለኩት” አቶ መለስ ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ በጎሳና በቀበሌ ደረጃ ወርደው የሚያስቡ “የጎሰኛነት አባት” መሆናቸውን ባለቤታቸው አሳብቀዋል።

“በተዘዋዋሪ የህዝብ ንብረት ናቸው” ሲሉ የገለጿቸው የኤፈርት እህት ኩባንያዎች ለአስራ ሰባት ሺህ ሰዎች የስራ እድል መፍጠራቸውን ወ/ሮ አዜብ በወቅቱ ያመለከቱ ሲሆን መስፍን ኢንጂነሪንግ በሶስት፣ አልሜዳ ጨርቃጨርቅ በአምስት እጥፍ እንደሚያድግ፣ መሰቦ ሲሚንቶ የማስፋፊያ ስራውን በማጠናቀቁ ለበርካታ ሰዎች የስራ እድል እንደሚፈጥር ማስታወቃቸውን ድረገጻችን ጨምሮ ዘግቦ ነበር።

ሰሞኑን ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝ ከኤርትራ ጋር ለመደራደር መፈለጋቸውንና ካስፈለገም ለሰላም ሲሉ አስመራ እስከመሄድ እንደሚደርሱ በተደጋጋሚ መግለጻቸውን አቶ መለስ ትግራይን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ ከወጠኑት ዓላማ ጋር የሚያያይዙት አስተያየት ሰጪዎች ዕቅዱ ተግባራዊ እየሆነ በሚሄድበት ወቅት ህወሃት ከኤርትራ ጋር ሰላም መፍጠሩ ምንም አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በአናት ካለ የዘመናት ባላንጣ ጋር ስምምነት ሳይፈጽሙ ስለ ልማትና የኢንዱስትሪ ማዕከልነት ማውራትም ሆነ ማቀድ በአሮጌ አቁማዳ አዲስ ወይን መጨመር እንደሆነ ጨምረው አስረድተዋል፡፡

ታላቁ መሶብ በባህርዳር

ወጉ እንዳይቀርባቸው የየፓርቲያቸውን የንግድ ተቋማት የመሠረቱት የህወሃት “አቻ” ድርጅቶች በቀጣይ ስለሚሰሩት ስራና አሁን ስለደረሱበት የአቅም ደረጃ ብዙም አለመሰማቱ በደጋፊዎቻቸውና በሚመሩት ክልል ህዝብ ዘንድ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚታሙ ያስታወሰው የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ በአማራ ክልል በተካሄደው የብሄር ብሄረሰቦች በዓል የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች “በፖለቲካ ታማኝነት” መመስገናቸውን አመልክቷል።

በሌላ ዜና ክልሉ በብሄር ብሄረሰቦች ጭፈራ ተይዞ በከረመበት በዚሁ ሰሞን የጣና ሃይቅንና አካባቢውን እያጠፋ ስላለው አረም የክልሉ የሚዲያ ሰዎች ያስተላለፉትን ዜና አስገራሚ ተብሏል። በጣና በለስና አካባቢው በከፍተኛ ፍጥነት የተራባውን አረም ለማጥፋት የአካባቢው አርሶ አደሮች አንድ ለአምስት በተሰኘ አደረጃጀት መጠርነፋቸው ሲነገራቸው የተሰማቸው ደስታ እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ ተዘግቧል።

የአካባቢው አርሶ አደሮች ይህንን አደገኛ አረም ለማጥፋት “ቁርጠኛነታቸውን ገልጸዋል” በሚል ከክልሉ የተሰራጨው ዜና እንዳመለከተው አርሶ አደሮቹ “አረሙን በማጥፋት የመለስን ራዕይ እናሳካለን” ማለታቸውን አድንቆ ይገልጻል። የአረሙን አደገኛነት የተረዳው የክልሉ መንግስት ሁለት ሚሊዮን ብር መመደቡንና ግብረሃይል ማቋቋሙን ያወሳው ዜና የከብቶቻቸውን መኖና እርሻቸውን፣ ብሎም የውሃ ውስጥ እንስሳትን የሚያጠፋውን ይህንን አረም እስከመጨረሻው ለማጥፋት በመደራጀታቸው የተደሰቱት አርሶ አደሮች አረሙን በማጥፋት ቁርጠኛነታቸውን ያድሳሉ ብሏል።

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. አለም says

    December 18, 2012 05:01 pm at 5:01 pm

    ውድ ጎልጉል፦ የትግራይ ንግድ ድርጅቶች በአማራ፣ በደቡብ፣ በጉሙዝ፣ ወዘተ ተሠማርተው ሲሠሩ ይታያሉ። ከደቡብ፣ ከአማራ፣ ከጉሙዝስ በትግራይ ክልል ንግድ የሚያንቀሳቅሱ አሉ?

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am
  • በትግራይ የሰላም ስምምነቱን መሠረት ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደሚፈጸም ተገለጸ December 13, 2022 09:20 am
  • ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ሌብነት የተከሰሱት የደኅንነት መ/ቤት ሠራተኞች ክስ ተመሰረተ December 13, 2022 09:06 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule