ዛሬ ታህሳስ 3 ቀን 2009 ዓ.ም. ስመ ገናናው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ከዚህ አለም በስጋ ካለፉ 103 ዓመት ሲሆናቸው አባ መላ ኃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ ደግሞ ዘጠና አመት ሆናቸው። ዳግማዊ አጤ ምኒልክና አባ መላ በስጋ ካለፉ ወደ አንድ ክፍለ ዘመን የሚጠጋ ዘመን ቢቆጠርም ስለታላቅነታቸውና ስለአሻራቸው ግን ዛሬም ገና አውርተን አልጠገብንም።
በንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አጤ ምኒልክ ትዕዛዝ ወደ ኢትዮጵያ ከገቡ ለኢትዮጵያውያን አስፈላጊ የሆኑ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ውጤቶች መካከል ባቡር [1893]፣ ስልክ [1882]፣ ፖስታ [1886]፣ ኤሌክትሪክ [1889]፣ አውቶሞቢል [1900]፣ ባህር ዛፍ [1886]፣ የውሃ ቧንቧ [1886]፣ ዘመናዊ ህክምና [1889]፣ ሆስፒታል [1890]፣ የመድሃኒት መሸጫ ሱቆች [1904]፣ ባንክ [1898]፣ ገንዘብ [1886]፣ ማተሚያ [1898]፣ ጋዜጣ [1900]፣ ሆቴል [1898]፣ ፖሊስ ሰራዊት [1901]፣ የፅህፈት መኪና [1887]፣ ሲኒማ [1889]፣ ወፍጮ [1835]፣ ጫማ፣ ድር፣ የሙዚቃ ት/ቤት [1887]፣ የሙዚቃ ሸክላ [1889]፣ ፍል ውሃ [1897]፣ ላስቲክ [1898]፣ ትንባሆ [1900]፣ መንገድ [1896]፣ አራዊት ጥበቃና የጥይት ፋብሪካ [1899]፣ ብስክሌት [1893]፣ ቀይ መስቀል [1889]፣ የሚኒስትሮች ሹመት [1900]፣ ወዘተ. . . እያለ ይቀጥላል።
እነዚህ የዘረዘርኳቸውን በአጤ ምኒልክ ዘመን ወደ ኢትዮጵያ የገቡ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ውጤቶች በአይኗ የተመለከተች ባለቅኔ ንጉሰ ነገስት ዳግማዊ አጤ ምኒልክን በህይዎት ሳሉ እንዲህ ብላላቸው ነበር፤
ባቡሩም ሰገረ፤ ስልኩም ተናገረ፤
ምኒልክ መልዓክ ነው፤ልቤ ጠረጠረ።
ይህ ግጥም ወደ እንግሊዝኛ ሲመለስ እንዲህ ይሆናል. . .
The train is running and the phone is ringing;
MENELIK is Angel that’s what I’m feeling ! 🙂
በስጋ ተለይተውን መንፈሳቸው ግን ላልተለየን እምቢ ባይና የጥቁር ህዝብ ተምሳሌት ለሆኑ አያቶቻችን ክብርና ሞገስ ይሁን!
(Shufna foto mnC: አቻምየለህ ታምሩ)
Getachew Selassie says
አሜን፡
ግን፡ምን፡ያደርጋል፡የገዛ፡ልጆቿ፡ለእናታችን፡ለአገራችን፡ለኢትዮጵያ፡ካንሰር፡ሆኑባት።
Ezira says
አቻምየለህ ሆይ!
ስለ እምዬ ምንሊክ ያቀርብከው እዉነታ በታሪክ ተመዝግቦ የሚገኝ ሃቅ ነው። ልጨምርልህ። ስለ እምዬ ምንልክ ባይገርምህ የሚገራርሙ ታሪኮች ከእኛ በላይ በፈረንጆች ቤተ መጽሃፍትና በፈረንጆች ጸህፍት ዉስጥ ደምቆ ይነበባል። አንድ ለመንገድ ልጨምርልህና ወደ ጉዳዬ እመለሳለሁ። ምን አለ መሰልህ አቻም! ችይናዎች
የቻይናዎች አባት ወይም አባታችን የሚሉት ታላቁ መሪያቸው ማኦ ሴቱንግ፤ የአጼ ምንሊክ አድናቂና ተከታይ እንደነበር ስገልፅልህ በኩራት ነው ። VIVA ለታሪክ !! VIVA ለምንልክ !። ስለ ማኦ ሴቱንግ የተፃፈው የማኦ ሴቱንግ የባዮግራፊ ትልቅ መፅሐፍ ውስጥ ትልቅ ቦታ ሰጥቶ ምንልክን በክብር ያውደሳል። አቻምየለህ እርገጠኛ ነኝ ምንልክን የግራ ፖለቲካ አራጋቢ ነበሩ እንደማትል። ይሁንና የአንተን ዓይነት ሃሳብ ይዞ “ትግሬ” ተብድሏል እና በዚህ ምክንያት 17 ዓመት “ታግዬ ” የደረስኩበት ድል ነው፤ ስለዚህ ለዚህ ድሌ የሚመጥን ነው ብሎ ሕገ መንግሥት ቀርጾ ኢትዮጵያን እያፈራረሰ ያለው የቀለጠው ግራ ዘመሙ መለስ ዜናዉ ባይገርምህ ይሄንን ማኦ ሴቱንግ የአጼ ምንልክ አድናቂና ተከታይነቱ መሆኑን የሚገልፅውን አረፈተ ነገር ቢያየዉም እንዳላየው ሊይልፈው ይችላል። ። ምናልባትም መለስ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ተብሎ እንደተወራለቱ አንባቢ ሳይሆን በመኮረጅ ጊዜዉን ሲያጠፋ የኖረ በመሆኑ አይገርምም። ይቅርታ ይደርግልኝና ለእንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ማንበብ የግዴታ አይደለም። ሳያነቡና ሳያውቁም አንባቢና አውዋቂ መስለው መቅረብ የተካኑበትና ደፋሮችም ናቸው። ደግሞም እኮ መጽሐፍ ገላጭ ነን ለማለት ከመጽሃፍም ይጠቃቅሳሉ። ። አንዱ መገለጫቸውና በአደባይ የሚታይ ማንነታቼውም ይሄ ነው። ምክኒያቱም ብዙ ተናጋሪ እንጅ አድማጮች አይደሉም፤ ብዙ ጊዜ መድርክን የሚሹና የሚፈልጉ እንጅ ከመደረክ ጀርባ ሂወት ያለ የማይመስላቸው ግብዞች ናቸው። በማንነታቸው ላይም ስለማይተማመኑም ህዝብን ይንቃሉ። ሲነቃባቸው ደግሞ ህዝብን “ሸውድነው” እያሉ ራሳቸዉን በራሳቸው ስያንቆለጳጵሱ ይኖራሉ። ከመድረክ የጠፉ ከመሰላቸው ደግሞ አይጣል ነው። በሕይወት የመኖርና ያለመኖራቸው ወሳኝ ጉዳይና አብይ ዋስትናቸው አድርገው የሚመልከቱ ግብዞች ናቸው። ተፅፎ ያነበቡትንም ሁሉ ለራሳቸው ፍላጎት እንዲጠቅም አድርገው ስለሚበርዙትም ምናልባት ይህ የቀለጠው የግራ ፖለቲካኛና የአልባኒያ አድናቂ መሆኑን አቻምየለህ እንኳ የሚመስክርለት መለስ ዜናዊም ፤ ይሄን ታሪክ ባይጠቅሰው አያስገርምም ለማለት ነው። አሁን ወደዋናው ነጥቤ እየገባሁ ነውና አቻምየለህ እባክህን በጥሞና ተክታተልኝ። አንተና መስሎችህ አሁን የምትገፉት ሃሳብ የአጼ ምንሊክን ገድል የሚጻረርና እኛ የምንኮራበት ታሪካችንንም ዳግም መቀመቅ ውስጥ ለመክተት የምትገፉትን ሃሳብ (ከኢህአዴግ የተቀበላችሁ ወይም የተላካችሁ እስኪያስመስላችሁ ድረስ) ተግታችሁ መለፈፋአችሁን እየሰማን እያየን ነው። አሰደማሚው ሌላው ትንግርት ደግሞ ልንገርህ። የአንተን የኢኮኖሚስቱን የአቻምየለህን ሃሳብ አድንቆና ደግፎ፤ ዛሬ ዛሬ ለእኛ “ለምንሊክ ልጆች እና የልጅ ልጆች ማለትም ለነፍጠኞቹ ” ቂ ቂ ቂ ቂ ቂ ! (እንኳን ደስ አለን ) የስሜቴ ተከፋይ የሆነ ጎርምሳ አቻምን አገኘሁ በሚል ዜማ አቅሉን ስቶ እረፋ እስኪደፍቅ የሚደነፋው ጃዋር ማሐመድ ሳይቀር እነሆ በደስታ ሰክሮ ጮቤ ረግጧል የአንተ ኃሳብ እና የርሱ ኃሳብ አንድ ሆኖ በመገጣጠሙ እንኳን ደስ አለህ አልህ ። ጃዋር ምን ነበር ያለው! እኔ በተወልድኩበት አካባቢ አንድ (አማራ ነው ክርስቲያን ያለው) ቢገኝ አንገቱን በሜንጫጫጫ። ለማንኛውምም ለዚህ አይነቱ መሠል ወንድማማችነት አንድ የምወዳት አባባል አለችና ተጠቀምኩባት – ተመሳሳይ ላባ ያላቸው ወፎች አብረው ይበራሉ የሚሉት ፈርንጆች ናቸው መሰለኝ። በዲያስጶራው ዘንድ ያለነው እኛ ደግሞ ጃዋር መሓመድን ስናውቀው የምዬ ምኒልክን ኣፅም(እንደ ህንዶቹ ሬሳን የማቃጠል ባህል ) ቢቻለው መቃብሩን ቆፍሮ በማውጣት ቤንዚን አርከፍከፎ በዉሰጡ ያለዉን የማነነትት ቀውስ ) ማብረጃ ለማደረግ ያነደው ነበር ። እናም ፕሮፌሰር አቻምየለህ ሆይ! አያድርስ ዝቅተኝነት የሞት ታናሽ ወንድምነው። ዝቅተኝነት ደግሞ ሁሌም ዝቅ ያለ ነገርን ነው የሚያደንቅ፤ የሚያወድስ። ለምሳሌ ፀረ ኢትዮጵያ የሆነው ህወሓት ኢትዮፕያን ጠልቶ 100ሚልዮን ህዝብ የሚኖርባትን አገር ሃበት እየፌለገና እየቦጠቦጠ ነገር ግን ከትግራይ አሳንሶ 6 ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርበትን የትግራይ ክፍለ ሃገርን “ታላቋ ትግራይ” እያለ ያወድሳል! ያደንቃል! ይዘምራልም።”ታላቋ ትግራይ” አይደለም ከኢትዮጵያ ከዐለምም ”ታላቅ” ናት ብሎ ይቃዣልም። ተሳሳትኩ እንዴ አቻምየለህ ? ለዝቅተኞች ለጅክ አያስፈልግም። ለጃዋርም “ታላቋ ኦሮሞ” የ ዐለም ሁሉ ታላቅ ናት። ማን ነበር መቃዥት መብት ነው ያለው? በዝቅተኝነት ስሜት የሚጠራውዝ ሰው ቀድሞውኑ ሰውነቱን መቀብል ያቅተዋል፤ ሟቷልና ነገሮችን በምክንያታዊ ወይም በሎጂክ መመልከት አይችቻለውም። “ጓድ”አቻምየለህ አንተም ብትሆን ዘግይተህ የመጣህ የጃዋር ኮፒ እና መንደርተኛ ግለሰብ እንጅ እንደ እምዬ ምንልክ ሰፊና ትልቅ ሃሳብ ይዘህ በዓለም ላይ ታሪካዊቷን ኢትዮጵያ የምታወደስ አይደለህም። ምሁሩ አቻምየለህ ቅድሚያ AMHARA FIRST !ባይ ነውና አልሸሹም ዞር አሉ እንለዋለን። ጃዋር በ አማራ ጥላቻ ተነስቶ ዛሬ የራሱን ማንነት ለመፈጠር ሲጣጣር መጀመሪያ ያደረገው አማራ እናቱን መግደል ነው። አቻምየለህም እርግጥ ነው በአፉ እናቱን ሲገድል ባይሰማም፡ አካሄዱን አይቶ ስንቁን ይቀሙታል እንደተባለው የአቻምየለህ የመጀመሪያ መፍክሩም አማራ መጀመሪያ ራሱን ሲታደግ ነው ኢትዮፕያ የምትኖረው ባይ ነው። እርሱምይሄን አባባሉን የሚያስድግፍበት ወይም የሚያጠነጥንበት የራሱ የሆነ የጥላቻ ሎጅክ አለው። እናም አቻምየለህ ታምሩ OROMO FIRST ከሚለው ጃዋር የሚለየው ምናልባት ጃዋር ከአቻም ቀደሞ በየመድርኩ ራሱን በመሸጡና በማንባረቁ ካለሆነ በቀር በይዘት ምንም ልዩነት የሌላቸው መሆናቸው ተግባራቸው ያሳያል። በቅርፅ ግን ከስማቸው ጀምሮ ልዩነት ያላቸው ግለሰቦች ናቸው። ጃዋር አቻምየለህ፤ አቻምየለህ ጃዋር ተብለው ይጠራሉና የቅርጽ ልዩነታቸውን ገላጭ የሆነው አንዱ ሳይንሳዊ ማሳያ ይሄ ነው። ነገር ግን በይዘት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች እና ሁለት የመንደር ጎርምሶች ናቸው። የሚደንቀው ደግሞ ሁሉቱም እንኳንስ የ ኦሮሞ እና የ አማራን ህዝብ ሊወክሉ ቀርቶ ራሳቸዉን በትክክል የማይገልጹ እና ለ50 መደረክ 50 ጊዜ ተገለባብጠውና ተሠርተው የሚቀረቡ ሰዎች ናቸው። ለዚህ ማሳያው ጃዋር አንዱ ሲሆን አቻምየለህ ደግሞ አሁን እንድናነበው የለጠፈው “የምንልክ ታላላቅ ስራዎች” እያሉ ማላገጥ አንዱ ነው። አቻምየለህ ቀላል ሰው አይደለም። ድብቅ አጀንዳውን ውስጥ ለውስጥ ነው የሚያስኬደው። ደግነቱ ከአጨብጫቢዎቹ አንዱ የሆነው ሄኖክ የሽጥላ የአቻምን አቋም አትንኩብን እኛ የምንለው አማራ እየተገደለ ነው በቅድምያ አማራን እናድን የሚል ነውና ጃዋርን እንጅ እኛን አትንኩን ባይ ነው። አምላክ ምሥጋና ይግባውና ኢትዮጵያ ምንጊዜም ወደቃ አትወደቅም። የዛሬን አያድርገውና ሄኖክ ዬሽጥላ ስለ ኢትዮፕያ በረቀቀ የግጥምሥነ ጽሁፉ ሲገጥምላት ይታወቃል። ከእነዚህ ውስጥ አንዱ አባይ የሚለው ግጥሙ ዋናውና የሚጠቀስለት ነው። ታዲያ ስለ አባይ ኢትዮጵያዊነት የመሰከረ ግለሰብ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን እየለበሰ በየመደረኩ የብዕሩን ፍላጽ ያነበበና ያስነበበ ሰው፤ ዛሬ በድንገት ከኢትዮጵያዊነት ጋር የሚላትም ምን ተገኝቶ ነው 90 ድግሪ ተገልብጦ ከኢትዮጵያዊነት በፊት መጀመሪያ አ …ማ…ራ…..ነኝ ብሎ ሲንዘፈዘፍ ለመሰማት የተገደድነው…? ብሎ ጠያቂ ቢበዛ ጠያቂው ሳይሆን ተወቃሹ በየፌርማታው ፍሬቻ ሳያሳይ የተገለባበጠው እና የሚገለባበጠው ሾፌር ነው ተጠያቂ የሚሆነው ማለት ነው። አለበለዚያ እንደተለመደው በ “ሜንጫ” ብሎ ሜንጫውን በየመድረኩ ሲያውናጭፍ የኖረው ጃዋር ዛሬ ደረሶ እነ አቻምየለህን ደግፎ ከማንም ከምን በላይ ሜንጫ ለተመኘለት አማራ ሲንገበግብ ማየት ወይ 8ኛው ሽህ ብልን ጭጭ እንድንል ነው ያስባሉ ማለት ነው። ከኅላ የመጣ ዓይን አወጣ ይሏል እንዲህ ነው። ተለዋዋጭ ባህሪ ያላቸው የእነዚህ ዓይነት ሰዎች እንዲህ ዓይነቱ አካሄድ መገለጫ ነውና “ኢኮኖሚስቱ”‘ አቻምየለህ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላሉ? ። በነገራችን ላይ አጨብጫቢ ያልኩት እንደዚህ አይነት ባህሪ የተላባሱ ሰዎች አጨብጫቢ እንጅ ሁነኛ ሰው ለማፍራት ያልታደሉ በመሆናቸው ነው። ምክንያቱም ሲጀመር የራሳቸው ሰዎች አይደሉምና ነው። ሲቀጥል ደግሞ እነዚህ ሰዎች መደረክ ባዩ ቁጥር በየመደርኩ 50 ቦታ የሚጣዱና እንደ ፌንጣ የሚዘሉ መሆናቸውም አልቄረም። ስለዚህ አቻምየለህ ዛሬ፤ ስለ እምዬ ምንልክ ገደል የሚትረክ ቅንጣቢ ጽሁፍ ለማቅረብ መዳዳቱ ከልብ እውን ምንሊክን ወዶና አክብሮ አክብሮ ሳይሆን የማንነት ቀውስን በፈቃደቸው ለተላበሱት ለእርሱ አጨብጫቢዎች የምታስተላልፍላቸው የቃላት ጨዋታ መሆኑን አላጣነዉም ለማለት ነው። ስማ እስቲ አቻምየለህ! ለመሆኑ ምኒልክ የ ኢትዮጵያ ንጉስ የነበሩ እንጅ እንዳ አንተ ሎጂክና ትንታኔ ከሆነ የአንተን ሃሳብ እና አካሄድ የሚወክሉና አርዓያህ አድርገህ ልታነሳቸው የሚገባህ ናቸዉን…. ? እንዲያማ ከሆነ በቅድሚያ ራስክን ነው እየተቃረንክ ያለኽው ማለት ነው። ለነገሩ እንዲህ አይነት ሰዎች መጀመሪያዉን ጠባቸውና ጥላቻቸው ከራሳቸው ማንነት ጋር ነው ። ለዚህ ደግሞ አንደኛው ምሳሌ ጃዋር ሲሆን፤ ለአችምየለህ ደግሞ {መቀሌ ዩኑቨርስቲ ያስተማረ ነው የተማረ} በመሆኑ በቅርብ የሚያውቃትን አዜብ ጎላን እንደ አብነት ማንሳት ይቻላል፡፤ ለአቻምየለህ ንፅፅር መለስን ያላነሳሁት አዜብ ወልቃይቴ ነኝ ባይ ሆና ከእነ ስብሃት በላይ ስብሃት ነኝ ስለምትለን ነው። ወደ ነጥቤ ስመለስ። አሁንም የአቻምየለህ ሞዴል ወይም አርዐያ ሆኖ ሊነሳ የሚችለው የኦሮሞ ፈርስት ባለቤት ጃዋር መሐመድ እንጅ በምንም መመዘኛ እምዬ ምንልክ ሊሆኑ አይችሉምና ሰው አያውቅም/አይስተውልም ብትል እንኳ ፈጣሪ ያዬኛል ብለህ ፈጣሪን እንድትፈራ ለማሣሰብ ነው። ምክንያቱም አንተም የምትለው ኣምሓራ ፈርስት የሚል ስለሆነ አምሃራ ፈርሰት የሚል ሰው ምንልክን መጥቀስ ጃዋር እንደሚለው ምንልክ “አማራ” ነው የሚለዉን የደንቆሮዎችን ሎጅክ ለማስረገጥ የተጠቀምክበት ነው ተግባባን? እስቲ እንዳረሳ አቻምየለህ ለመሆኑ አዲሱን የፕሮፌሰር ፊቅሬ ቶሎሳን መጽሐፍ አግኘተው ይሆን …? ካላገኝኽው እልክልሃለሁ። ለማንኛዉም ነቄ ብለናል የዘመኑ ፍንዳታዎች!!
Lusif says
Even though he looked backward feudal king for the current generation, he was a great king of his time and least of patriotic people and generation. He established the present political boundary and saved the generation from colonial slavery. He pioneered some modern achievements. That was great deeds in his capacity and awareness level of the time. He can not be accused beyond and above of the level of the time.
When we come to the next generation the remnants of the old kept the country free and heroism and love of country was the norm. The new offspring, however better educated, were self- obsessed and self- indulgent. Educated and above everybody else was the mentality. That mentality produced a bunch of arrogant, uncompromising, mentally fridged and obstinates that promoted division and animosity more among themselves than being congenial and cooperative. The leaders of the current ruling party and leaders of the so called oppositions are remnants of those offspring.
Their undesirable behavior and the divisive culture those oldies established is equally haunting them ( they never win) and damaging a certain section of current generation.
I give credit for EPRDF for its limitless, bottomless appetite for corruption and nepotism and tribal domination that produced kin, inquisitive, fearless generation of youth.
I am glad being part, and I believe it is this generation of youth that has seen political evil physically. To your surprise, I have touched it. It is the most ugly and disgusting.
I heard in those oldy days it was the government that provided job for graduate students. The salary and the privilege was close to royal families. Now once you graduated, unless you have somebody or party member you are thrown on the street or live at the mercy of your parents.
Here is the difference between the old generation and the current one.
The old generation was struggling and still is, for more income, for more status and privilege. We are struggling for basic necessities and survival– to be allowed to live. If there was a responsible government, is that too much to ask?
For current generation “either,or, or” is not an option. That is for the oldies. If they win they could be much better off. If they don’t they are still better off than the average and ordinary citizens.
For the youth, in order to survive winning is the only option. Winning is not always coming only through violence. Respecting each other is the first step. Listening to each other concerns, hummer out difference, compromise and squeeze out the best, the common good, we all can live by. That is honorable winning.