• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ

December 14, 2022 09:59 am by Editor 2 Comments

ድሮ ገና ከዓመታት በፊት በ12 ዓመቱ ነበር ሰውን የመርዳት ፅንስ በትንሽ ልቡ ውስጥ የተጸነሰው። ሳድግ የራሴ የበጎ አድራጎት ድርጅት ኖሮኝ ሰዎችን እረዳለሁ እያለ ያወራ ነበር። የእድሜ አቻዎቹ ዶክተር፣ ኢንጅነር፣ ፓይለትና ሌሎችም እሆናለሁ በሚሉበት ለጋ እድሜ የሱ ትንሽ ልብ መሻት አድጎ ሰውን መርዳት መቻል ነበር። ዛሬም በሕይወት ጉዞው ላይ በብዙ ካደገም በኋላ የየቀን ንግግሩ የዘወትር ውዳሴው “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የሚል ቃል ነው። ሰው ስለሆነ ብቻ ሰው ይረዳልና።

የራስን ሕይወት ትቶ ስለሰው በሚኖረው ባሕሪው ከሰዎች መካከል ይለያል። የሥጋ ሕመሙ የነፍሱን ቁስል በሻረለት መልካም ሥራው ይታወቃል። ድንቅ የመልካምነት ምሳሌ፣ የመቻል አብነት፤ የደግ ልብ ጌታ ነው። የጥሩዎች ዕንቁ የደጎች አውራ ነው። ብዙዎች በተለያዩ ጊዜያት ደጋችን ነህ ሲሉ በይፋ አመስግነውታል። ዓመታዊው የቅን ልብ ባለቤቶችን እውቅና ሰጪው የበጎ ሰው ሽልማትም አንተ የመሰናዷችን ባለ በጎ ልብ ነህ ሲል ሽልማት ሰጥቶታል። የክብር ዶክትሬት ባለቤቱ የመቄዶኒያ ወላጅ ወጣት ቢንያም በለጠን።

ዘመኑ እናት ለልጇ አባት ወንድሙን እህት አክስቷን የተቸገሩበት፣ ሰው በሰው ላይ የጭካኔ በትሩን በገዛ ወገኑ ላይ የሚያሳርፍበት ቢሆንም ከዚህ በተቃራኒ ለሰው ልጅ በጎ የሚሠሩ ጥቂት ቅን ልቦች አሉ። በተለይ ሰው በሕመም ሲጎዳ እንኳን ባዳ ዘመድ ሩቁ ይሆናል። የታመመ ሰው ደግሞ በሕመም ጉዳት ምክንያት ብዙ አስቸጋሪ ነገሮች አያጣውም። በሚከብድ የሕመም ጣር ውስጥ ያለን ሰው አክሞ ወደ ቀድሞ ጤንነቱ መልሶ ተንከባክቦ ማኖር ግን በብዛት በቅርብ ሰዎች የሚከወን ተጨማሪ አቅምንም የሚጠይቅ ነበር።

ደፋሩ ቢንያም በለጠ ግን ይህን ከወነ፤ በኢትዮጵያ የጊዜ ቀመር 2004 የበጎነት ሥራውን አርባ ያህል ሰዎችን ከሜዳ በማንሳት አሐዱ አለ። አንዳንድ ሰው አይደለም በመኖር በሕመም ይማራል፤ በቀና ቀኖቹ ብቻ ሳይሆን የሕይወቱ ክፉ ቀናትም እሱን ለማስተማር ዝግጁ ሆነው ይቀርባሉ፤ ያኔ ከዓመታት በፊት ሰውና ቀን የጣላቸውን በማንሳት የተጀመረው የቀናነት ጉዞ ዛሬ ላይ ቁጥሩን አሳድጎ ከሰባት ሺህ አምስት መቶ ለሚልቁ ነፍሶች መጠጊያ ታዛ ሆኗል።

የክርስቲያኖች የሕይወት መሠረት በሚባለው ቅዱስ መጽሐፍ ላይ ተከትቦ የሚገኝ አንድ ቃል ዛሬ የብዙኃን መጠለያ ለሆነው መቄዶኒያ ስያሜ መነሻ መሆኑን ራሱ ቢንያም ይናገራል። እንዲህም አለ፤ የመቄዶኒያ ሰዎች በብዙ ተፈትነው ሳለ የድህነታቸው ጥልቀት የልግስናቸውን መጠን አብዝቶታል ይላል የተከተበው ቃል፤ ድሀ ቢሆኑም ለገሱ የሚል ትርጓሜንም ይይዛል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሠራተኛና አመራሮችም ዓመታዊ የሠራተኞች ቀናቸውን በመቄዶኒያ የአረጋውያንና አዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል በመገኘት ተረጂዎችን ምሳ በማብላትና የተለያዩ የበጎ አድራጎት ተግባራትን በማከናወን አሳልፈዋል።

እሁድ ረፋድ ላይ በመርጃ ማዕከሉ የደረሱት ሠራተኞች ፀሐይቷ ባለመራራት ያወረደችባቸው የንዳድ ውርጅብኝ ሳይሰማቸው በስፍራው ጉብኝት ጀምረዋል። በመርጃ ማዕከሉ የተሠሩትን ተግባራት የሚያስቃኝ ጥናታዊ ፊልም ሲቀርብ ገና አዳራሹ ኃዘን ባስነባቸው ሠራተኞች ተሞላ።

ማዕከሉ ውስጥ ለዘመናት አልጋን ተቆራኝተው የኖሩ፣ ሰዎችና ጊዜ የገፋቸው ምስኪኖች፣ የአዕምሮ ሕሙማን፣ እርጅና በሰፊ መዳፉ የደቆሳቸው፣ ብቻ ጤና ሰጥቶት ማዕከሉን ለመጎብኘት እድል ለተሰጠው ሰው ብዙ ማመስገኛ ምክንያት የሚሰጡ ሰዎች አሉበት። ከታማሚዎች፣ ከአረጋውያንና በቋሚነት ከቀጠራቸው ሠራተኞቹ ቁጥር ባልተናነሰም እዛው ታክመው ተረድተው የዳኑ በጎ ፍቃደኛ አገልጋዮችም ይገኛሉ። በሰው ተረድቶ ሰው መሆንን ተምረዋልና እነሱም ለተረኛ ተረጂዎች ሰው ሆኖ ለመገኘት እድላቸውን አያባክኑም።

የመርጃ ማዕከሉ መሥራች እንዲሁም ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ቢንያም በለጠ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሠራተኞችን አክብሮ በታማሚ ጎኑ በጉብኝታቸው መሐል በመገኘት መልዕክቱን አስተላልፏል። ስፍራው በቀን ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አለበት። ይህን ወጪውንም ደግ አሳቢዎች ነግ በኔ ማለትን የለመዱ ቅኖች በሚያሰባስቡት ገቢ ነው የሚሸፍነው፤ አሁንም ግን ድጋፍ ይሻል ብሏል።

በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ባልደረቦች የተሠራው መልካም ሥራ ከፈጣሪ ዋጋ የሚያሰጥ ነው፤ በማዕከሉ የሚገኙ ተረጂዎችን ቁጥርም ሃያ ሺህ ለማድረስ ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸውንም አቶ ቢኒንያም ተናግሯል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጌትነት ታደሰም ከጎብኚዎች መሐል ነበሩና መልዕክትና አደራቸውን አስተላልፈዋል። በነገ ቤታችንን በመቄዶኒያ መገኘት ለእኛ መልካም ነው፤ እዚህ በመገኘትና ማዕከሉን በመጎብኘት በብዙ አትርፌያለሁ ብለዋል።

አቶ ጌትነት ድርጅታቸው ለተቋሙ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለፅ እኔም የግሌን ለማበርከት አቅሜ በፈቀደ ሁሉ ከመርጃ ማዕከሉ ጎን እቆማለሁ፤ ለድርጅቱም ኪስና ጉልበቴን እፈትሻለሁ ሲሉ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

አቶ ጌትነት በስፍራው መገኘታቸው ልባቸውን ያቀና ውስጣቸውን ያከመ መሆኑን ገልጸዋል። የድርጅታቸውን ሠራተኞችም ማዕከሉን በቋሚነት መልካም ፍቃደኞት ሆናችሁ አገልግሉ፤ ስፍራውን በመደገፍም የሥጋም የነፍስም ጥቅም ተጠቀሙ ብለዋቸዋል። (አዲስ ዘመን)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, Social Tagged With: Binyam Belete, Macedonia

Reader Interactions

Comments

  1. Don't incite bloody conflict among brotherly people of Tigray and Amhara says

    December 26, 2022 09:34 am at 9:34 am

    Is it beacuse you are humanely and care for entire humanity that many of you were blindly and deliberately supporting the massacre of Tegaru

    Reply
  2. Samuel says

    October 16, 2025 11:29 am at 11:29 am

    Good job

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule