• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“በትግራይ ያለውን የወጣቶች እንቅስቃሴ ሕዝቡ … መደገፍ ይኖርበታል” ዶ/ር አብርሃም

August 7, 2020 01:33 am by Editor Leave a Comment

ካልተወም በግፊት እንዲተው ማስገደድ ያስፈልጋል ብዬ አምናለሁ

በትግራይ እያታየ ያለው የወጣቶች እንቅስቃሴ ህዝባዊ ዓላማ እስከአለው ድረስ ህዝቡ የእኔ ነው ብሎ መደገፍና ሥርዓት ይዘው እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ ይኖርበታል ሲሉ የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ አስታወቁ። የህወሀት ጥገኛ ቡድን እንቅስቃሴ የኢትዮጵያን ህዝብ ፍላጎት በተለይ ደግሞ የትግራይን ህዝብ የማይመጥን እንደሆነም አመለከቱ።

ህዝቡ የወጣቶቹን እንቅስቃሴ ሊቀበልና ሊደግፍ እንደሚገባ ዶክተር አብርሃም ጠቅሰው፣ በትግራይ ያለው አፋኝ አገዛዝ ወይም ፓርቲ ወጣቶችን እንዳያሰቃያቸው ከለላ መሆን ያለበትም ህዝቡ መሆኑን አስገንዝበዋል። ለህዝብ ጥያቄ የተንቀሳቀሰ ወጣት ሲገደል እንዲሁም ለምን ተናገርክ ተብሎ ሲጨፈጨፍና ሲታሰር ካየ፤ ለህዝብ ብሎ እየተጨፈጨፈ ላለው ለእዚህ ወጣት ህዝቡ ራሱ ከለላ መሆን መጀመር መቻል አለበት ብለዋል።

በዚህ ረገድ የወጣቶች እንቅስቃሴ ብቻ ሳይሆን የፓርቲ እንቅስቃሴም የሚያደርጉ አካላት አባሎቻቸው እየታሰሩ እና እየተሰቃዩ መሆናቸውን በየጊዜው እየገለጹ መሆናቸው ዶክተር አብርሃም ጠቅሰው፣ ያልሆኑ ሃሳቦችና ንግግሮች በእነሱ ተቃኝተው ወጣቱ እንዲገለጹላቸውና እንዲናገራቸው ይደረጋሉ ዕምቢ ካለ ደግሞ ይታሰራል፤ ይደበደባል፤ ይሰቃያል። ትግራይ ውስጥ ያለው ይሄ ነው። ሰዎች እስከ መገደል የደረሱበት ሁኔታም እየታየ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ዶ/ር አብርሃም ይሄንን በማድረግም የፓርቲ እና የወጣቶች እንቅስቃሴን የሚከለክልና የሚያፍን፤ ዴሞክራሲያዊ ሁኔታ እንዳይፈጠር የሚያደርግ፣ ብዙ ሃሳብና እውቀት በሞላበት ክልል ውስጥ የሃሳብ ፍጭት እንዳይኖርና ሃሳብ እንዳይንሸራሸር የሚያደርግን አካል ተው ብሎ ማስተው፤ ካልተወም በግፊት እንዲተው ማስገደድ ያስፈልጋል ብዬ አምናለሁ፤ ይህ ደግሞ የህዝቡ ሃላፊነት ጭምር ነው ብለዋል።

አንድ በትክክል መገንዘብ ያለብን ነገር ህወሃት ፓርቲ መሆኑን ነው ያሉት ዶክተር አብርሃም፣ ፓርቲ ደግሞ ጠቅላላውን ህዝብ እንደማይወክል ተናግረዋል። “አለመታደል ሆኖ ምንጩ ከትግራይ ሆኖ በአገራችንም እንደ አጠቃላይ፤ ከአገራችንም በተለየ ደግሞ በትግራይ ውስጥ ከፍተኛ የክፋት እንቅስቃሴዎች እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፤ ሰው የማሰር፣ የመግረፍ፣ የማሰቃየት፣ ብሎም በኔትዎርክ የጥቅመኝነት እንቅስቃሴ እና ተደራጅቶ አገርን የመረበሽ እንቅስቃሴ እያደረገ ያለ ቡድን አለ” ሲሉ ያብራራሉ።

በአጠቃላይ ህወሓት በሚል ባይገለጽም በጣም ጥሩ መሆኑን ተናግረው፣ ህወሓት ውስጥ ሆነው የትግራይን ህዝብ ፍላጎት፣ በትግራይ ውስጥ ዴሞክራሲ እንዲኖር፤ የሚፈለገው ልማት እንዲመጣ፣ ሰላም እንዲሰፍን የሚሰሩ፣ በሌብነት የማይንቀሳቀሱ፣ በኔትወርክ ጥቅም ያልተሳሰሩ፣ ለህዝብ ብለው የሚኖሩ ብዙ አባላት እንዳሉም ዶክተር አብርሃም አብራርተዋል።

እንደ ዶክተር አብርሃም ገለጻ፤ የህወሓት ከላይ ያለው ቡድን የሚናገረውና የሚያደርገው ይለያያል። ሴራዎቹ ሌሎች ናቸው፤ ፊት ለፊት መልካም የሚመስሉ ነገሮች ሊናገር ይችላል፤ ተደብቆ የሚሰራቸው ደግሞ ያው ይፋ እየተደረጉ እየታዩ ናቸው። ፓርቲው የወያኔን እንቅስቃሴ ይዞ የተነሳና ከህዝብ ጋር ያለው ቁርኝት ጠበቅ ያለ ስለነበር፤ ፓርቲው ፊት ለፊት የሚናገራቸውን መልካም ነገሮች እያየ፤ ከፓርቲው ጋር ተሳስረው የቆዩ፣ እውነታውን በትክክል ያላወቁ አንዳንድ አባላት የተደበቁበትም ነው።

እንደ ህወሃትም ሁሉንም በአንድ አይን ማየት በጣም ትክክል አይደለም ያሉት ዶክተር አብርሃም፣ እዚህ ሆነው በዋናነት ችግር እየፈጠሩ ያሉት፤ ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የሚሰሩት፤ ሰላም ትግራይ ውስጥ እንዳይኖር የሚያደርጉት፤ ፍትህ እንዳያገኝ፣ የአፈና ስራው ከላይ እስከታች እንዲዘረጋ እያደረጉ ያሉት እዚህ ከፍተኛ ጉዳት ሲፈጽሙ የነበሩ፤ ለትግራይ ህዝብ ምንም ሳያደርጉለት እዚህ የራሳቸውን ኔትዎርክ ሲያስተካክሉ፣ ሀብት ሲዘርፉ፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሲፈጽሙ የነበሩ ቡድኖች እንዳለ ተሰብስበው ከነሃጢያታቸው ወደ ህዝባችን ሄደው ተለጥፈዋል ሲሉ አብራርተዋል።

“ከዚህ በኋላ ትግራይን ለማልማት ነው የተመለስነው” በሚል የማዘናጊያ ቋንቋ ወደ ህዝባችን ገብተዋል ሲሉ ጠቅሰው፣ ህዝባችን ደግሞ የዋህ ነው ልጆቹን አይጥልም። ህዝቡም ትግራይን ያለማሉ ብሎ አምኖ ነው የተቀበላቸው ብለዋል። እነርሱ ግን እዚህ ሲፈጽሙት የነበረን ሴራ በሙሉ ትግራይ ውስጥ ለመድገም እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ዶክተር አብርሃም አስታውቀዋል። ከሚታወቁት የኢኮኖሚ ሴራዎችና የሰብዓዊ ጥሰቶች አልፈው፤ ትግራይ ውስጥ ሌላ አገርን የማበጣበጥና አገርን የመበተን ፍላጎቶች ይዘው እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የእነሱን ጥፋት የሚሸፍን ወይም ደግሞ ሸፍኖ የሚያቆይና እድሜ የሚሰጥ እስከ ሆነ ድረስ እነዚህ ሰዎች የማያደርጉት እንደሌለም አስታውቀው፣ እነዚህ ሰዎች ወይም ቡድኖች (ህወሓት በሚል በሙሉ መጥራት አልችልም) እዚህም እዛም የፈጸሙት ጥፋት ሰፊ መሆኑን ገልጸዋል። ሰላም ከሆነና ለውጥ ከመጣ ተጠያቂ ነን ብለው እንደሚያምኑን ተናግረው፣ እነዚህ ሰዎች በሰላም ጊዜ እነሱ በማይመሩበት ምህዳር ላይ እድሜ አይኖራቸውም። ጥፋታቸው በጣም ከባድ ስለሆነ ይሄን ያውቁታል ብለዋል። (ምንጭ፤ ወንድወሰን ሽመልስ፤ አዲስ ዘመን)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Interviews, Middle Column, Politics

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule