• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ኢትዮጵያ ኬኛ፣ ጣና ኬኛ!” ድንቅ መንፈስ!

October 12, 2017 08:26 pm by Editor 3 Comments

  • “ጣና ኬኛ!” መልዕክቱ ከእንቦጭ አረሙ በላይ ነው

  • የመለያየትና የመፈራረስን አደጋ ያከሸፈ መንፈስ

ከኦሮሚያ “ጣና ኬኛ!” እያለ የተመመው ወጣት ክፉውን የእንቦጭን አረም ነቃቅሎ እንደማያስወግድ ግልጽ ነው። ጥቂት ወጣቶች ተሸክመውት ጎጃም የገቡት የኢትዮጵያዊነት የአብሮነት የ”አንድ ነን” ግን መልዕክቱ ግን የእንቦጭ ተራ አረም አይደለም ኢትዮጵያን የማስወገድና የመታደግ መንፈስ የታመቀ መንፈስ አለው። ዛሬ ያየሁት ፍቅር፣ ዛሬ ያየሁት የአብሮነት፣ የህብረትና የአንድነት መንፈስ ከሰፊው የጣናን እንቦጭ አረም በላይ ነው።

“ጣና ኬኛ!” ብሎ ጎጃም የገቡትን ወጣቶች አደግድጎ በክብር ኩራት፣ በአባት አደር ወጉ ወገኖቹን ከደብረ ማርቆስ እየተቀበለ ተመልክተናል። ይቀጥልና እስከ ባህር ዳር ቄጠማ እያነጠፈ ለመቶ እንግዶቹ እልፍ አዕላፉ ለአቀባበሉ የሚያሸረግደ እንግዶቹን የሚቀበልበት ምክንያት ከጣና እንቦጭ በላይ የኢትዮጵያዊ መንፈስ ትንሳኤን ሲያበስረን መሆኑ ዛሬ በፈንጠዝያው መካከል ካልገባን፣ ነገ እውነቱ ሲገለጥልን ይገባናል!

“ጣና ኬኛ፣ ኢትዮጵያ ኬኛ” ይልሃል፣ ለአመታት ጀግናው ብርቱው ወገን … የተሸረበበትን የመነጣጠል መለያየት፣ የአድልኦ መንፈስ አሽቀንጥሮ፣ እንደ ስፖርቱ በአንዲት ሀገር ባንዴራ ማዕቀፍ ተከባብረን ተዋደን እንኖር ዘንድ ህዝብ መናገር፣ መመስከርና ማበሩን አላቆመም። የጎጃም ወገናቸው በነቂስ ወጥቶ ድጋፉን መስጠቱን የመመልከቱ ድንቅ የህብረት መንፈስ ትርጉሙ ከፍ ያለ ሀገራዊ መልክ አለው። በእርግጥም ለ200 ወጣት የኦሮሚያ ግዛት ተጓዥ በጎ ፈቃድ አድራጊ የጎጃም እንግዳ ኢትዮጵያዊ ኦሮሞው ወጣት የጎጃም ወጣት ሽማግሌ በነቂስ ወጥቶ በክብር የተቀበለበት ሚስጥሩ ለመሰጠረው ግዙፍ ነው። ለእኔ ኢትዮጵያዊው ኦሮሞና አማራው ለአመታት በክፉዎች ከጫፍ እስከ ጫፍ የተረጨበትን የመለያየት መርዝ ስለማክሸፉ ምልክት ነው።

በህዝቦች መካከል ያለው፣ የቆየ የመደጋገፍ መንፈስ ይታይ ዘንድ ከጣናው የእንቦጭ አረም ከፍ ባለ ደረጃ ዛሬ ታይቷል። ክፉዎች ተስፋ ይቆርጡ ዘንድ ኢትዮጵያዊው ኦሮሞ “ጣና ኬኛ” ዘመቻ እያለ ጎጃም ሲገባ ህዝቡ በክፉ በደጉ እንደማይለያይና ህብረትና አንድነቱን ናፋቂ መሆኑን ማሳያ ሆኖናል። በእርግጥም በጣም ጥቂት ወጣቶች በአሸናፊነት መንፈስ ከኦሮሚያ ተመው ጎጃም ሲገቡ የጎጃም ሕዝብ በአንጻሩ መልዕክቱ ደርሶታል። ጎጃሜው ታጥቆ አሸርግዶ የኦሮሞ ወጣት ወንድም እህቱን  በክብር በባህላዊ እስክታ፣ ሆታ ጭፈራ ተቀብሏል። የአቀባበሉ መንፈስ ደግሞ የኢትዮጵያውያን አንድነት፣ የኢትዮጵያውያን የህብረት አብሮነት ፍላጎት ማሳያ ግልጽ መልዕክት ይመስለኛል።

ይህ የአብሮነት መንፈስ ደግሞ እነሆ የኢትዮጵያን ትንሳኤ መልክት ነው። ተስፋችን በሚሰራው ስራ ብን ብሎ ሲጠፋ “ኢትዮጵያ እንደሁ አትጠፋም!” የምንለውን አራቂ መንፈስ አስታውሶ ኢትዮጵያ በልጆቿ ህብረት እንደማትጠፋ በእውን ያሳየን መልዕክት ነው! የኦሮሞ ወጣቶች በጎ መንፈስና የጎጃም አማራው የአቀባበል ደስታ ፌሽታ ስነስርአትን ላስተዋለው የኢትዮጵያዊነት የህብረት አንድነቱን መንፈስ እንመሰክር ዘንድ ያስገድደናል። ይህ ግዙፍ መንፈስ ጣናን ከወረረውን እንቦጭ በላይ ስለ ከበበን ስለወረረን በጎ ተስፋ ሰጭ መንፈስ ይናገራል! ለአመታት ያንዣበብንን የመለያየት የመፈራረስ አደጋ ዛሬ በ200 በጎ አድራጊ ኢትዮጵያዊ ኦሮሞ ወጣቶች የከሸፈን ያህል ተደስተናል። ብቻ “በጣና ኬኛ” ድንቅ ዘመቻ ነፍሴ ከፍ ያለ ደስታን አግኝታለች!

“ኢትዮጵያ ኬኛ፣  ጣና ኬኛ …!” ድንቅ መንፈስ!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

ነቢዩ ሲራክ

ጥቅምት 3 ቀን 2010 ዓም

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. በለው! says

    October 14, 2017 06:19 am at 6:19 am

    ሆ ብሎ ገባ ! አረም ቢወረው
    ያን ፌሶ ጥሊያን እንዲህ የነቀለው
    የአባቱን ጅብዱ በልጁ ዘመን የደገመው
    ልዩነህ ሲሉት አንድ ነን አለ መጣ እያገሳ
    የኢትዮጵያ ልጆች ይኽው ገጠሙ መሳ ለመሳ
    ጭፈራው ባሕል ቋንቋቸው ሀገር
    እምነታቸው ጽኑ ዓለም ምሥክር
    ወያኔ እና አረም አንድ እንቦጭ
    እንቦጭ ውሃ ህወሓት ደም መጣጭ
    ንቀል ጣል አለ መብቱን አወቀ ጣና ኬኛ
    ጨዋታው ደራ ውሉ ታወቀ ኢትዮጵያ ኬኛ!
    ፍቅር ሠላም ኅብረት ይበጀናል ለእኛ ።
    ***************
    ሥለሀገራቸው ደህንነት የሕዝብ አብሮ መኖር ቅን ያሰቡ ቀናው ይግጠማቸው!
    ከሸረኛ ምቀኛ ከፋፋይ አመጸኛ ተንኮለኛ ይሰውራቸው
    በቸር ይክረሙ።

    Reply
  2. Lemma says

    October 14, 2017 06:50 pm at 6:50 pm

    Endih yale Tiru melikt beergata metsaf neberebet.

    Reply
  3. Mulugeta Andargie says

    October 14, 2017 10:24 pm at 10:24 pm

    ጣና! ጣና!! አረ ጣና!!
    ያባይ ውልድ ያማራ ምንጭ ስብዕና
    በዕምቦጭ ተወረረ ይሉናል?? ወይ ፈተና!!!!
    ከሞኝ ሰፈር
    ይቆረጣል ሞፈር!!
    ወጣቱን ለቮሊንተር
    ብታሰልፈው ጥሩ ነበር
    ልብህ ባይቃዥ በሌላው አፈር!!
    ምንም ነውር የለውም መማማር!!!!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
Copyright © 2026 · Goolgule