• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ተቃውሞ አድራጊዎች ላይ የሚደረገው አፈና አልቀነሰም

February 22, 2016 02:36 pm by Editor Leave a Comment

ከኖቬምበር ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል በስፋት እየተካሄደ ያለውን ሰላማዊ ተቃውሞ የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይል በጉልበት እያፈነው እንደሚገኝ ሂውማን ራይትስ ወች ዛሬ አስታወቀ፡፡ ከ2016 ዓ.ም.  መነሻ ጀምሮ በእየለቱ ሰዎች እንደሚገደሉ እና በዘፈቀደ እንደሚታሰሩ ሂውማን ራይትስ ወች አስታውቋል፡፡

የወታደራዊ ሰራዊትን ያካተተው የጸጥታ ሃይል ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ላይ የሚገኙ በርካታ ሰዎችን ቀጥታ በመተኮስ ገድሏል፡፡ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ታስረው ያለምንም ክስ እንደታገቱ ይገኛሉ፡፡ ባለፉት ሳምንታት የተቃውሞው ድግግሞሽ የቀነሰ መስሎ ቢታይም አፈናው ግን ቀጥሏል፡፡

“ኦሮሚያን በበርካታ የጸጥታ ሃይሎች የማጥለቅለቅ እርምጃ የሚያመለክተው በተማሪዎች፣ ገበሬዎች እና ሌሎች ተቃዋሚዎች የሚደረገውን ሰላማዊ ተቃውሞ ባለስልጣን አካላቱ በከፍተኛ ሁኔታ አለመፈለጋቸውን ነው::” ብለዋል በሂውማን ራይትስ ወች የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ሌዝሊ ሌፍኮው፡፡ “መንግስት የፀጥታ ሃይሉን ሰብስቦ መመለስ ይኖርበታል፤ በስህተት የታገቱ ማንኛወንም ሰዎች መልቀቅ አለበት፤ አንዲሁም አላስፈላጊ ሃይል የተጠቀሙ የፖሊስ እና የወታደራዊ ሃይል አባላትን ተጠያቂ ማድረግ አለበት፡፡”

በጃንዋሪ 12 ቀን የአዲስ አበባ የተቀናጀ ልማት ማስተር ፕላን መሰረዙን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት በኦሮሚያ ያለው ሁኔታ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቋል፡፡ የዋና ከተማዋ አዲስ አበባን ማዘጋጃ ቤት ድንበር በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ወደሚገኙ የእርሻ ቦታዎች ለማስፋፋት ታቅዶ በነበረው አወዛጋቢ ማስተር ፕላን ምክንያት ሰላማዊ ሰልፎች ተቀስቅሰዋል፡፡oromo14

ሆኖም የእቅዱ መሰረዝ ተቃውሞውን አልገደበውም፤ አፈናውም በመላ ኦሮሚያ ቀጥሏል፡፡ በጃንዋሪ ማገባደጃ 2016 ዓ.ም. ሂውማን ራይትስ ወች ወደ 60 የሚጠጉ ከዲሴምበር እስከ ጃንዋሪ ባለው ጊዜ የነበሩ ተቃዋሚዎችን እና ሌሎች ምስክሮችን ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ቃለ-መጠይቅ አድርኋል፤ በተቃውሞው ወቅት ከጃንዋሪ አጋማሽ ጀምሮ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መኖሩን ቃለ-መጠይቅ የተደረገላቸው ግለሰቦች ገልጸዋል፡፡ ተጠያቂዎቹ እንደገለጹት የፀጥታ ሃይሉ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ በዘፈቀደ በቀጥታ ይተኩሳል፣ በተቃውሞ ላይ ያሉ ሰዎችን ገድሏል፣ በርካቶችን አፍኖ ይዟል እንዲሁም ያገታቸው ሰዎች ላይ ከፍተኛ ማሰቃየት ፈጽሟል፡፡

የተወሰኑ በውጭ ባለሃብቶች የተያዙ የእርሻ መሬቶችን ማውደም እና የመንግስት መስሪያቤቶችን መዝረፍ ጨምሮ በተወሰነ መልኩ አመጻ የተቀላቀለባቸው ተቃውሞዎች እንዳሉ የሚያመላክቱ ዘገባዎች ቢኖሩም ከኞቬምበር ጀምሮ የተካሄዱት አብዛኞቹ ተቃውሞዎች ሰላማዊ ነበሩ፡፡ በፌብሯሪ 12 ቀን የፌዴራል የጸጥታ ሃይሎች ከሰርግ በመመለስ ላይ ባለ አውቶብስ ተኩስ በመክፈታቸው እና ሰዎችን በመግደላቸው ሳቢያ ተቃውሞዎች እንዲነሱ እና እንዲቀጥሉ አድርጓል፡፡ መንግስት እንዳስታወቀው በፌብሯሪ 15 ቀን በፌዴራል የጸጥታ ሃይሎች እና ፖሊስ አልያም ሚሊሻ እንደሆኑ በተገመቱ የታጠቁ ሰዎች መካከል በተደረገ ግጭት ለሰባት የጸጥታ ሃይሎች ሞት ምክንያት ሆኗል፡፡

በጃንዋሪ 10 ቀን ጸጥታ ሃይሎች በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኘው የጅማ ዩኒቨርሲቲ ቦምብ በመወርወራቸው ምክንያት በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች መጎዳታቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ የተለያዩ የአይን እማኞች ለሂውማን ራይትስ ወች እንደገለጹት በጃንዋሪ 10 እና 11 ቀናት የጸጥታ ሃይሎች የጅማ ዩኒቨርሲቲን የተማሪዎች ማደሪያ ቤቶች በማጥለቅለቅ በርካታ የኦሮሞ ተማሪዎችን ለእስር እና ለድብደባ ዳርገዋቸዋል፡፡oromo13

የጸጥታ ሃይሎች ተማሪዎችን፣ መምህራንን፣ የመንግስት ባለስልጣናትን፣ ነጋዴዎችን፣ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን፣ የጤና ባለሙያዎችን፣ እንዲሁም ለሚያመልጡ ተማሪዎች እርዳታ የሚያደርጉ እና መጠለያ የሚሰጡ ሰዎችን አስረዋል፡፡ በኦሮሚያ የሚገኙ የአንደኛ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ከመጀመሪያዎቹ ተቃዋሚዎች መካከል ስለሆኑ በእብዛኞቹ የታሰሩት ከ18 ዓመት እድሜ በታች የሆኑ ህጻናት ናቸው፡፡

“ቀጥታ ወደ ግቢው በመግባት ባነጣጠሩት ጥቁር መሳሪያ ሶስት ተማሪዎችን ተኩሰው መተዋል” ብሏል አንድ የ17 ዓመት ተማሪ ማስተር ፕላኑን በመቃዎም በተደረገው ሰልፍ የጸጥታ ሃይሎችን እርምጃ ሲያስረዳ “ፊታቸው ላይ ነው ተመተው የነበሩ ስለሆነ ተገድለዋል፡፡”

ሂውማን ራይትስ ወች የተቃውሞ ሰልፉ ከተጀመረበት ከኖቬምበር 12 ቀን ጀምሮ ታግተው የነበሩ 20 ሰዎችን አናግሯል፤ ሁሉም ፍርድ ቤት አልቀረቡም፡፡ አስራ አራቱ ሰዎች በታገቱበት ወቅት እንደተደበደቡ ገልጸዋል፤ አንድ አንዴ ድብደባው የከፋ እንደነበረም አስታውቀዋል፡፡ በርካታ ተማሪዎች በወገባቸው ተንጠልጥለው ታስረው እንደነበር እና እንደተገረፉ አስታውቀዋል፡፡ አንድ የ18 ዓመት ተማሪ እግሩን በኤሌክትሪክ እንደነዘሩት ተናግሯል፡፡ ሁሉም ቃለ-መጠይቅ የተደረገላቸው ተማሪዎች ሌሎች ተማሪዎች ተቃውሞውን እንዲቀላቀሉ ቀስቅሳችኋል በሚል በባለስልጣን አካላቱ ተወንጅለዋል፡፡ በርካታ ታግተው የነበሩ ሴት ተማሪዎች በፀጥታ ሃይሎቹ ፆታዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል አሊያም ያልተገባ አያያዝ ተፈጽሞባቸዋል፡፡

የተገለጸው አያያዝ ሂውማን ራይትስ ወች እና ሌሎች የመብት ተሟጋች ቡድኖች በኦሮሚያ በግልጽ በሚታወቁ እና ድብቅ በሆኑ እስር ቤቶች እስረኞች ላይ የሚፈጸሙ የማሰቃየት እና ያልተገባ አያያዝ መንገዶችን ያሟላሉ፡፡ በርካታ የአይን እማኞች እና የቀድሞ ታሳሪዎች እንደገለጹት በምዕራብ ሸዋ እና ቦረና ዞኖች የጸጥታ ሃይሎች የንግድ ተቋማት እና የመንግስት ህንጻዎችን እንደ ጊዜያዊ የማገቻ ቦታነት ይጠቀሙባቸዋል፡፡

ይህ በሚጻፍበት ወቅት በኦሮሚያ የተወሰኑ ትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርሲቲዎች እንደተዘጉ ያሉ ሲሆን ይኼውም ባለስልጣን አካላት ተጨማሪ ተቃውሞዎችን ለስማቆም ሲሉ መምህራንን ስላሰሩ እና መገልገያ ቁሳቁሶችን ስለዘጉ ነው፤ በሌላ በኩል ደግሞ ተማሪዎች እንደ አንዱ የተቃውሞ መግለጫ ትምህርት መከታተል ስላቆሙ ወይንም እስርን በመፍራታቸው ነው፡፡ በርካታ ተማሪዎች በቅድመ ሁኔታ ከታገቱበት የተለቀቁ ሲሆን ቅድመ-ሁኔታውም ህዝብ በሚሰበሰብበት ቦታ ከአንድ ሰው በላይ ሌላ ተጨማሪ ሰው ጋር ላለመታየት ቃል መግባታቸው ነው፤ አንዲሁም በርካቶቹ ይህን ቅድመ-ሁኔታ ለመቀበላቸው ምክንያት እንደሆነ ለማሳያነት እንዲፈርሙ መደረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

ሂውማን ራይትስ ወች አጠቃላይ የተገደሉ ሰዎችን ቁጥር ለማረጋገጥ አልቻለም ምክንያቱም በኢትዮጵያ ያለው እንቅስቃሴ እና በነጻነት የመዘገብ ሁናቴ የተገደበ በመሆኑ ነው፡፡ ተሟጋቾች በተለይ ከማህበራዊ ድረ-ገፆችን መሰረት በማድረግ ባገኟቸው የቪዲዮ፣ የፎቶ እና የድረ-ገጽ ላይ ጽሁፎች መረጃዎች መሰረት ከኖቬምበር 12 ቀን ጀምሮ ከ200 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ጠቁመዋል፡፡ ያለው መረጃ እንሚጠቁመው በበርካታ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ታስረዋል፤ በርካቶቹ የት እንሚገኙም አይታወቀም፤ የሚገመተው በሃይል እንዲሰወሩ መደረጉን ነው፡፡oromo15

ሂውማን ራይትስ ወች ከዚህ በፊት ተገልጾ ያልነበረ የ12 ሰዎችን ግድያ መዝግቧል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የአብዛኞቹ ግድያ የተፈጸመው በደቡባዊ ኦሮሚያ የሚገኙት የአርሲ እና ቦረና ዞኖች ሲሆን እነዚህ ቦታዎች ተቃውሞዎች ሲካሄዱባቸው የነበሩ ቦታዎች ቢሆንም ከሌሎች አካባቢዎች አንጻር ዝቅተኛ ትኩረት የተሰጣቸው ቦታዎች ናቸው፡፡ “ይህ ሚያሳየው በአጠቃላይ በኦሮሚያ ያለው የተቃውሞ እና የሚፈጸም ጥቃት መጠን ከተዘገበው በላይ ሊሆን እንደሚችል ነው” ብሏል ሂውማን ራይትስ ወች፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በገለልተኛ የሲቪክ ማህበረሰብ ቡድኖች ላይ እና መገናኛ ብዙሃን ላይ በሚፈጽመው ወደር-አልባ እገዳ ምክንያት ከተጠቁት አካባቢዎች የሚገኘውን መረጃ እጅግ አነስተኛ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ነገር ግን ማሕበራዊ ድረ-ገጾች የተቃውሞ ሰልፎችን ፎቶ እና ቪዲዮ ባካተተ መልኩ በተለይ በኖቬምበር እና ዲሰምበር አሰራጭተዋል፡፡

የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኦኤምኤን) በተቃውሞው ወቅት መረጃ በመላው ኦሮሚያ እንዲሰራጭ ቁልፍ ሚና ተጫውቷል፡፡ ኦ ኤም ኤን ዳያስፖራን መሰረት ያደረገ የቴሌቪዝን ጣቢያ ሲሆን መረጃዎችን በተለይ በኦሮምኛ ቋንቋ በሳተላይት የሚያስተላልፍ እና በቅርቡም በአጭር ሞገድ የሬድዮ ፕሮግራም የጀመረ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት የዓለም አቀፍ ደንቦችን በሚጥስ መልኩ ኦ ኤም ኤን ስርጭት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለ15 ተከታታይ ጊዜያት የአየር ሞገዱን ለማገድ መሞከሩ ተዘግቧል፡፡ ሁለት ነጋዴዎች ለሂውማን ራይትስ ወች እንደገለጹት በንግድ ቦታቸው ላይ ኦ ኤም ኤንን አሳይታችኋል ተብለው ታስረው ነበር፡፡ በበርካታ አካባቢዎች ኦ ኤም ኤንን የሚያስተላልፉ የሳተላይት ዲሾንን የፌዴራል ፖሊስ አውድሟል፡፡ ተማሪዎች የተለያዩ ቪዲዮዎችን በማህበራዊ ድረ ገጾች አውጥታችኋል እንዲሁም ለኦ ኤም ኤን መረጃ ታቀብላላችሁ በሚል መወንጀላቸውን ገልጸዋል፡፡ ባለፉት ወራት በኦሮሚያ የሚደርሰውን ጥቃት በተመለከተ የሚወጣው መረጃ ጥቂት በመሆኑ ሳቢያ እስሩ እና እታሰራለሁ የሚለው ስጋት ጨምሯል፡፡

“የኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታ ሃይሎች የሚጠቀሙትን ከመጠን ያለፈ ሃይል ማስቆም አለበት፤ በዘፈቀደ የታሰሩ ሁሉንም ሰዎች ነጻ መልቀቅ አለበት አንዲሁም ግድያውን እና ሌላ የጸጥታ ሃይሎች ጥቃትን በተመለከተ ገለልተኛ ማጣራት መደረግ ይኖርበታል” ብሏል ሂውማን ራይትስ ወች፡፡ “የከፋ የመብት ጥሰት ያደረሱ አካላት በተገቢው መንገድ ክስ ሊመሰረትባቸው ይገባል፤ ጥቃቱ የተፈጸመባቸውም ሰዎች ተገቢው ካሳ ሊከፈላቸው ይገባል፡፡”

በጃንዋሪ 21 ቀን የአውሮፓ ፓርላማ አፈናውን በመቃዎም ጠንካራ አቋም አሳልፏል፡፡ ዩናይትድ ኪንግደም እና ዩናይትድ ስቴትስ ግጭቱን በተመለከተ ይፋዊ ውግዘት አላቀረቡም ይልቁንም ህዝባዊ ምክክር እና ውይይት እንደሚያስፈልግ በሁለት መግለጫዎች አስታውቀዋል፡፡ በሌላ በኩል የተወሰኑ መንግስታት የኢትዮጵያ መንግስትን ተግባር በተመለከተ ቅሬታ እንዳላቸው አስታውቀዋል፡፡ “ሁለቱ የኢትዮጵያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ወዳጆች ዩናይትድ ኪንግደም እና ዩናይትድ ስቴትስ አመጻ ያዘለውን አፈና ለማስቆም ተጨማሪ ማድረግ የሚችሉት ነገር እንዳለ እና ጥቃቱን በተመለከተ ገለልተኛ የማጣራት ተግባር እንዲካሄድ ጥሪ ማቅርብ አለባቸው” ብሏል ሂውማን ራይትስ ወች፡፡

“የኢትዮጵያ ለጋሽ ሃገሮች ምላሽ አርኪ አይደልም ሌላው ቢቀር በኦሮሚያ ለተገደሉት በርካታ ሰላማዊ ሰልፈኞች” ብለዋል ለዝሊ ሌፍኮው “ይህን ዘግናኝ ጭካኔ ችላ ማለትም ሆነ አቃሎ ማየት ማቆም ይኖርባቸዋል እንዲሁም በግድያው እና በተፈጸመው ጥቃት ዙሪያ መንግስት ገለልተኛ የማጣራት ተግባር እንዲካሄድ እንዲደግፍ ጥሪ ማቅረብ አለባቸው፡፡” (ምንጭ: HRW)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions, Politics Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ወርቁ አይተነው የሸሹት ከዝርፊያ፣ ውንብድናና ዕዳ ጋር በተያያዘ ነው September 21, 2023 02:38 pm
  • ወደ አማራ ክልል ሊተላለፍ የነበረ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ September 19, 2023 04:35 pm
  • በትግራይ መርዶ በይፋ ሊታወጅ ነው September 19, 2023 04:22 pm
  • ጃርቶች ለምን ይጮኻሉ? September 19, 2023 04:37 am
  • “ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” ጌታቸው ረዳ September 11, 2023 10:18 am
  • አቶ አገኘሁ መረጃ አሳልፎ በመስጠት ዋጋ እንደሚከፍሉ ተሰማ September 10, 2023 06:52 pm
  • ለዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ” ያደርጋል ያላችሁት ረቂቅ ሰነድ የታለ? September 10, 2023 01:58 am
  • ወደር የሌለው የኅብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ጀግና! ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ኃብተማርያም September 8, 2023 02:31 pm
  • የትግራይ መፍረስ በርዕሰ መስተዳደሩ አንደበት September 8, 2023 02:49 am
  • ከያቤሎ አዲስ አበባ የተላከ ኮንትሮባንድ ጉለሌ ተያዘ September 7, 2023 01:40 pm
  • “እንኳን ተለያይተንና እርስ በርስ ተባልተን በአንድነት ቆመንም ወጀቡን መሻገር አቅቶናል” September 7, 2023 01:31 am
  • ራሱን መሪ አልባ የሚያደርገው አማራ ክልል August 24, 2023 11:50 pm
  • ጀብደኛው August 24, 2023 10:06 am
  • ጎንደርና ባሕር ዳር ከተሞች ወደ ቀድሞ ሰላማቸው ተመልሰዋል August 13, 2023 10:55 pm
  • ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያውን ግዙፍ ወታደራዊ ኃይል አስመረቀች August 13, 2023 10:26 pm
  • ሪፖርተር የፓርላማ ወንበር አስልቶ የአስቸኳይ አዋጁ በፓርላማ እንዳይደገፍ አቅጣጫ አመላከተ August 13, 2023 09:11 pm
  • ወደ ኤርትራ በኮንትሮባንድ የሚሻገሩ ቆሳቁሶች እየተያዙ ነው August 11, 2023 12:52 pm
  • የአማራ ክልል ትልልቅ ከተሞች ተኩስ ዓልባ ሆነው ውለዋል August 10, 2023 04:31 pm
  • “አንድ ሰው ለመግደል ኅንፃውን ማቃጠል” የኢ-ዲሞክራሲና ጽንፈኛ ኃይሎች ቅዠት፤ (ክፍል ሁለት) August 10, 2023 09:44 am
  • “አርበኛ” መሳይ – “የድል ዜና” ሳይበርድ 50ሺህ ዶላር በጎፈንድሚ August 10, 2023 09:08 am
  • በሕዝቡ ድጋፍ ከተሞች ከዘራፊው መንጋ ሥጋት ነጻ መሆናቸው ይፋ ሆነ August 9, 2023 11:47 am
  • ትህነግ አራተኛውን ሞት ሞተ  August 8, 2023 05:47 pm
  • “ሃሳብ ሲነጥፍ ነፍጥ አንግቤ እዋጋለሁ” የሚሉ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል – የመከላከያ ሠራዊት August 1, 2023 09:25 am
  • ደቡብ አፍሪካ የመሸጉ ወንጀለኞች ለሕግ ተላልፈው ሊሰጡ ነው July 31, 2023 09:27 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule