• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢትዮጵያ በጅቡቲ ወደብ መገንባት ጀመረች

December 19, 2012 11:39 am by Editor 5 Comments

በጅቡቲ አዲስ የሚገነባው ወደብ ወጪ በኢትዮጵያ እንደሚሸፈን ተገለጸ። ወደቡ በቀጥታ ከትግራይ ከሚነሳው አዲሱ የባቡር መስመር ጋር እንደሚገናኝም ታውቋል። እያደር ይፋ በመሆን ላይ ያሉት ፕሮጀክቶች አቶ ሃይለማርያም አስመራ ድረስ ለመሄድ ያሳዩትን ፈቃደኛነት “ለኢሳያስ የቀረበ የፖለቲካ አይስክሬም” በማለት አስተያየት ሰጪዎች ተናገሩ፡፡

ባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የመሰረት ድንጋይ ለማስቀመጥ ጅቡቲ መጓዛቸውን የዘገቡት ያገር ውስጥ መገናኛዎች ያድበሰበሱት ጉዳይ ይፋ የሆነው ዲሰምበር 18/2012 ለአሜሪካ ሬዲዮ መግለጫ የሰጡት በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የአፍሪካ ፖለቲካ ተንታኝና የታሪክ ምሁር የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር አየለ በከሬ ናቸው።

ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋ እያደገ በመሄዱ ተጨማሪ ወደቦች እንደሚያስፈልጓት የጠቆሙት እኚሁ ምሁር በጅቡቲ የሚሰራው አዲሱ የታጁራ ወደብ  ወጪ በከፍተኛ ደረጃ የሚሸፈነው በኢትዮጵያ መሆኑን ይፋ አድርገዋል። አዲስ የሚሰራው የባቡር መስመር ግንባታ ሲጠናቀቅ መቀሌ ከታጁር ወደብ ጋር እንደምትገናኝም አመልክተዋል።

ስለ ባቡር ግንባታ ሲያስረዱ መቀሌን፣ ወልዲያን፣ አፋርንና አዋሽን በማቋረጥ የሚያልፈው የባቡር መስመር ከሌሎች የኢኮኖሚ ተግዳሮት በተጨማሪ በዋናነት “አፋርና ትግራይ” ውስጥ የተገኘውን 1.3 ቢሊዮን ቶን የፖታሽ ምርት ወደ ወደብ ለማጓጓዝ መሆኑን ባለሙያው ተናግረዋል።

በከፍተኛ ደረጃ የተገኘውን የፖታሽ ክምችት የማምረት ስራ እየሰራ ያለው የካናዳ ኩባንያ ስራውን አጠናቆ ማምረት ሲጀምር በጅቡቲ ወደብ በነጻ ለመጠቀም አስቀድሞ ስምምነት የፈጸመ መሆኑ በአሜሪካ ሬዲዮ ጋዜጠኛ አዳነች ፍስሃዬ ተጠይቆ በመላሹ ተረጋግጧል። በዚሁ መሰረት የታጁራ ወደብ ግንባታ እንደተባለው በከፍተኛ ደረጃ ለሚመረተው የፖታሽ ምርት በዋናነት ይውላል መባሉ ሚዛን የሚደፋ አልሆነም። ጉዳዩ “አቶ መለስ ትግራይን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ” አቅደው እንደነበር ካሳበቁት የወ/ሮ አዜብ ንግግር ጋር ይያያዛል የሚል ጥርጣሬም ከወዲሁ ተሰምቷል።

“የታጁራ ወደብ ከአጤ ሚኒሊክ በፊት የነበሩ የሸዋ ነገስታት ይጠቀሙበት የነበረ ወደብ ነበር” ሲሉ የገለጹት ምሁሩ ቀደም ሲል የተተወው ወደብ መሰራቱ ጠቃሚነቱ የጎላ መሆኑን አሁን ካለው ፍላጎት ጋር በማያያዝ አስረድተዋል። እሳቸው ይህንን ቢሉም ትግራይን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግና የኤፈርት የንግድ ተቋማትን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማሸጋገር የተወጠኑት እቅዶች ይፋ መሆናቸውን ተከትሎ አቶ ሃይለማርያም ደፋ ቀና የሚሉለት የወደብ ግንባታ በቀጣይ ቅሬታዎች ሊበራከቱበት እንደሚችል ግምታቸውን ያስቀመጡ አሉ።

ምሁሩ ግን እንቅስቃሴው የኢትዮጵያን ብሔራዊ የኢኮኖሚ እድገት በተግባር የሚያሳይ ነው በማለት የተናገሩት በአዳነች ፍስሃዬ “ሌሎችም ፕሮጀክቶች አሉ” በሚል የማስታወሻ ጥያቄ ከቀረበላቸው በኋላ ነው። ቀጥለውም ከዓመት በፊት አቶ መለስ ከኬንያና ከደቡብ ሱዳን አቻቸው ጋር ናይሮቢ ላይ በደረሱት ስምምነት መሰረት በላሞንግ ደሴት ላይ በጋራ ገንዘብ በማዋጣት የሚሰራውን ወደብ ተከትሎ በሚዘረጋው የባቡር መስመር የደቡብ ኢትዮጵያ ክፍል ተጠቃሚ እንደሚሆን ነው።

434 ቢሊዮን ብር (23 ቢሊዮን ዶላር) የሚፈጀው ይህ ወደብ ሲገነባ ከጁባ ተነስቶ ኬንያ የሚዘልቀው የአውራ ጎዳናና የባቡር መስመር የደቡብ ሱዳንን፣ የደቡብ ኢትዮጵያንና፣ የኬንያን ሰሜናዊ ክፍል በማገናኘት ከፍተኛ ፋይዳ ያለው የኢኮኖሚ መነቃቃት እንደሚፈጥር ምሁሩ አስረድተዋል። ከአረብ እና ሳውዲ ፈንድ በተገኘ ብድር የሚሰራው ይህ ወደብ የነዳጅ ማጣሪያና ከዚህ አንጻር የተያዙ ብሄራዊ ይዘት ያላቸው ዕቅዶች እንዳሉት በመጠቆም አገራዊነቱ ለማጉላት ሞክረዋል።

አቶ መለስ ህይወታቸው ካለፈ በኋላ በርካታ ፕሮጀክቶች ይፋ መውጣታቸውና የኤፈርት የካፒታል መጠን በምስጢር መያዝ እንደተገጣጠመባቸው ያመለከቱ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር “በቅርቡ መግለጫ የምናወጣበት ጉዳይ ነው። የታጁር ወደብ አቅሙን ድብቅ ያደረገው ህወሃት በምስጢር ሊዝ ከጅቡቲ መንግስት ጋር በግለሰብ ስም ተደራድሮ በስምምነት የሚገነባውና ወደፊት የራሱ (የኤፈርት) የሚሆን ንብረቱ ወይም ላሁኑ በሽርክና የያዘው ቢሆንስ?” የሚል ጥያቄ አንስተዋል። መላምታቸው መነሻ መሰረቶች እንዳሉትና ወደፊት አስፈላጊ ሲሆን ይፋ እንደሚያደርጉትም አስታውቀዋል። አንቀጽ 39ንም ከዚሁ ጋር አስታክከው አስታውሰዋል። መንግስት ፕሮጀክቱ ለሁለቱ አገሮች ጠቀሜታ እንዳለው በማስታወቅ ዝርዝሩን ደብቆ ባለፈው ሳምንት መዘገቡ ይታወሳል።

ገለልተኛ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት “አለመተማመን የኢትዮጵያን ፖለቲካና የወደፊት አቅጣጫ እየበላው ነው” ካሉ በኋላ “መንግስት የጀመራቸውን ስራዎች ይበልጥ ህዝባዊ ለማድረግ ከሁሉም ወገኖች ጋር የፖለቲካ ሰላም በማውረድ ቢያንስ ልማቱ ላይ ያለውን ብዥታ ማስወገድ ካልቻለ የወደፊቱ አደጋና በአገር ስም የሚፈጸመው ስምምነት የልጅልጆቻችንም ከፍለው የማይጨርሱት ይሆናል” ብለዋል። በተለይም አስተያየት ሰጪዎቹ ያሰመሩበት “ቂም የሚቋጥሩ ፕሮጀክቶች ከህዝብ ስለሚርቁ ዋስትና አይኖራቸውምና ኢህአዴግ ከወዲሁ ሊያስብበት ይገባል። ተቃዋሚዎችም መቃወምንና ልማትን ለይተው በመመልክት አገርን ሊያስቀድሙ ይገባል” በማለት ጠንከር ያለ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በሌላ ተመሳሳይ ዜና ጅቡቲ በአባይ ግድብ ከፍተኛ ቦንድ መግዛቷን የትግራይ ዩኒቨርስቲው ምሁር ተናግረዋል። ረዳት ፕሮፌሰር አየለ የቦንዱ መጠን ከፍተኛ እንደሆነ ከመገለጽ ውጪ ትክክለኛ አሃዝ አልተናገሩም፤ ጥያቄውም አልቀረበላቸውም። በአባይ ግድብ ዙሪያ ቦንድ በመግዛት ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው አገሮች እንዳሉ ከመሰማቱ ውጪ በግልጽ አገሮቹና የገዙት የቦንድ መጠን እስካሁን ይፋ አልሆነም። ምሁሩ እንደሚሉት እንዲህ ያለው ስምምነት ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ጋር በጋራ፣ በስምምነት መስራት እንደምትችል የምታሳይበት ነው።የታጁራ ወደብ መገንባት ኢህአዴግ ከሻእቢያ ጋር ለመታረቅ ያለውን የተሰበረ መንገድ አመላካች እንደሆነ የገለጹ አስተያየት ሰጪዎች፣ ሰሞኑን አስመራ በመሄድ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋር ለመወያየት ዝግጁ መሆናቸውን የገለጹት የጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝን አቀራረብ “የፖለቲካ አይስክሬም” ብለውታል። በማያያዝም በትግራይ ሊገነቡ የታሰቡትና ተገንብተው ያሉት የኢኮኖሚ ተቋማት ሻዕቢያ አሁን ባለበት ደረጃ ከቀጠለ ስጋቱ ከፍተኛ ስለሚሆን በቀልዱ ፖለቲካ ውስጥ እሬት ፖለቲካ መኖሩን አመላክተዋል።

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. yeKanadaw kebede says

    December 20, 2012 07:08 am at 7:08 am

    እንደተመኙት ቀላል ሆኖ አላገኙትም እንጅ “የመጀመሪያ ፕላናቸው ከፖርት ሱዳን በወልቃይት አልፎ ሽሬ የሚገባ የባቡር መስመር ነበር” ይላሉ ውስጥ አዋቂዎች። ልክ እንዳሁኑ በትዕቢትና ከኔ በላይ ብልጥ የለም በሚል ትምክህት የታቀደ ስለነበር ዕውን ሳይሆን ቀርቷል። ይሄኛውም ዋና ዓላማው ‘ነፃዋን’ የትግራይ ሪፐብሊክ ከውጩ ዓለም ጋር ለማገናኘት በነ ስብሐት ነጋ ጭንቅላት የተቦካ የሞኝ ህልም ነው። ሰመራን ከተማ አስመስለው ዩኒቨርሲቲ ሲከፍቱና ደረቅ ወደብ ሲሰሩ፤ ከዚያም በቀጥታ ትግራይ የሚወስድ የባቡር ሐዲድ ለመሥራት ከሕንድ ጋር ሲዋዋሉ ልብ ብሎ ያላስተዋለ ካለ የነሱው ዓይነት ሞኝ መሆን አለበት።
    ወያኔ የኢትዮጵያን ጥቅም ከትግራይ ጥቅም አስበልጦ ተመልክቶ አያውቅም። ከነስሙስ “የትግራይ ነፃ አውጭ ግምባር” አይደለም እንዴ?
    ደርግ ነብሰ-ገዳይ ሳይሆን በፊት “የተኛችሁ ንቁ፤ የነቃችሁ ተጠንቀቁ” ብሎ ነበር ጳውሎስ ኞኞ።

    Reply
  2. kefe says

    December 24, 2012 09:48 am at 9:48 am

    if this article was a little close to honesty and truth, it could have told us the railway to bahirdar is more close to the tajura port than to mekelle. even if not, mekele is also ethiopian. very simple to tell this article is very far from balance…. it is pathetic.

    Reply
    • Editor says

      December 25, 2012 11:35 am at 11:35 am

      Dear Kefe,

      Thanks for your comments. Since you have raised an issue that matters to what we have posted here, we wanted to say few words.

      You raised the issue of honesty, truth, balance …. Well said! First of all if you have paid due attention to the article you should have seen the map we posted on the left side that shows how, where and which parts of the country the rail system is going to cover. We posted this so that readers can see the “balance”.

      Let’s get a little deeper regarding this issue of “balance” – look at the map that shows the whole rail system in the country very carefully. The rail system has two phases – Phase I, all the lines in green, and Phase II those in red. Please take your time to study how long it will take to complete the 1st and the 2nd phases. What is the color from Weldiya to Bahir Dar versus Weldiay to Mekelle? Also we want to answer the question of distance you’ve raised by asking you a question? Which one is really shorter? The distance from Bahir Dar to Weldiya which is 355KM or Weldiya to Mekelle which is 268KM? What kind of mathematical calculation convinced you to say – “bahirdar is more close to the tajura port than to mekelle?”

      The issue here is not about what you thought it is – in fact if we have to talk about the rail system itself we could have raised tonnes of question – like why is there no rail system in the regions of Gambella and Somali – not even in the second phase? Why Oromia, the largest region, is not well covered by this rail system? Why is most of the Amhara region scheduled in the second phase? so on and on. However, the main issue here is why do we need to have the port now? Is it for the potash business? If you’ve read the article properly we’ve said this “በከፍተኛ ደረጃ የተገኘውን የፖታሽ ክምችት የማምረት ስራ እየሰራ ያለው የካናዳ ኩባንያ ስራውን አጠናቆ ማምረት ሲጀምር በጅቡቲ ወደብ በነጻ ለመጠቀም አስቀድሞ ስምምነት የፈጸመ መሆኑ በአሜሪካ ሬዲዮ ጋዜጠኛ አዳነች ፍስሃዬ ተጠይቆ በመላሹ ተረጋግጧል።”

      We are happy to entertain any kind of issue for or against what we are publishing. If you feel that there is too much to be said – put it in article form and argue your points. We will definitely post it.

      Regards,

      አርታኢ/Editor
      ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ/Golgul: the Internet Newspaper
      http://www.goolgule.com
      editor@goolgule.com

      Reply
  3. Dawit says

    December 25, 2012 12:11 pm at 12:11 pm

    Many thanks for the editor. thanks to Mr Kefe, now all the readers have the opportunity to know more about the issue.

    Reply
  4. Alem says

    December 25, 2012 07:06 pm at 7:06 pm

    Kefe’s comments are standard with woyane groups. First they deny. Then they attack. And finally they ask, [even if the report is true] Is not Mekelle also Ethiopian? They often get away with the last part of the comment. That is why we say, Ya Lebba Ayna Daraq, Mal’ so Leb Yadarq. Good job Golgul for not letting it pass.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am
  • በትግራይ የሰላም ስምምነቱን መሠረት ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደሚፈጸም ተገለጸ December 13, 2022 09:20 am
  • ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ሌብነት የተከሰሱት የደኅንነት መ/ቤት ሠራተኞች ክስ ተመሰረተ December 13, 2022 09:06 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule