እ.ኤ.አ. በ2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ መንግስት በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላት፣ ጋዜጠኞች፣ እና ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ አድራጊዎች ላይ እያደረገ ያለውን ጫና ቀጥሏል፤ አብዛኞቹ እንግልት፣ ዘፈቀዳዊ እስር እና በፖለቲካ የተቀናበረ ክስ ገጥመዋቿል፡፡
ገዢው ፓርቲ የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ግንቦት ወር በተካሄደው ምርጫ 547 የፓርላማ መቀመጫዎችን አሸንፏል፤ ይሄውም የሆነበት አንዱ ምክንያት ጠንካራ ተጻራሪ ሃሳብ የላቸው ወይንም ተቃዋሚዎች በመታፈናቸው ነው፡፡ በሰኔ ወር የዩናይትድ ስቴትስ (አሜሪካ) ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን ከመጎብኘታቸው አስቀድሞ የተወሰኑ ታዋቂ እስረኞች ከመፈታታቸው ባሻገር በኢትዮጵያን መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና መገናኛ ብዙሃኑን አስረው የያዙትን እጅግ አፋኝ ህጎች እና ፖሊሲዎች ለማሻሻል የተደረገ መሰረታዊ ለውጥ የለም፡፡
ምርጫ እና የፖለቲካ ምህዳሩ
በግንቦት ወር ብሄራዊ ምርጫ የተካሄደው ከፍተኛ ማስፈራሪያ በሰፈነበት እና እና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለልተኝነት አጠያያቂ በሆነበት ወቅት ነው፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላቶቻቸው በሃገሪቱ የደህንነት ሃይሎች እና በገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ከፍተኛ መስፈራሪያ እና እገታ እንደሚፈጸምባቸው አሳውቀዋል፤ ለምርጫ ምዝገባ የተቀመጡ እጅግ አስቸጋሪ ቅድመ ሁኔታዎችም የተቃዋሚ ፓርቲዎቹን እጩዎች የተሳትፎ እድል በእጅጉ አሳንሶታል፡፡
ለምርጫ ውድድሩ ቅስቀሳ ለማድረግ ያቀዱ ሰላማዊ ሰልፎችን ፈቃድ በመከልከል፣ አስተባባሪዎችን በማሰር እና ለተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ አገልግሎት መጠቀሚያ የሚዉሉ እቃዎቻቸውን በመንጠቅ የመንግስት ባለስልጣናት በተደጋጋሚ እንደሚከለክሏቸው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተናግረዋል፡፡
ከእነዚህ ገደቦች በተጨማሪ ነጻ መገናኛ ብዙሃን እና መንግስታዊ ያልሆኑ የሲቪክ ማህረሰብ ድርጅቶች አለመኖራቸው ከምርጫው አስቀድሞ የተቃውሞ ድምጾች የመሰማት እድል ወይንም ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ትርጉም ያለው ፖለቲካ ክርክር የመደረግ እድሉ እጅግ በጣም አናሳ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
የመሰብሰብ ነጻነት
እ.ኤ.አ. ከ2012 ዓ.ም. እስከ 2014 ዓ.ም. በመላው ኢትዮጵያ አጥለቅልቆት የነበረውን የሙስሊሞች ተቃውሞ የመሩ መሆናቸው የተገለጹ 18 ግለሰቦች በሐምሌ ወር ባልተገባ የፍርድ ሂደት የጸረ-ሽብር አዋጁን በመጣስ ጥፋተኛ ተብለው እያንድአንዳቸው ከ7 እስከ 22 ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ተፍርዶባቸዋል፡፡ እ.ኤ.አ. ሐምሌ ወር 2012ዓ.ም. ላይ የመንግስት ባለስልጣን አካላት መሪዎቹን ያገቱት የተወሰኑ የሙስሊም ማህበረሰብ አባላት መንግስት በሐይማኖታዊ ጉዳዮቻቸው ላይ ጣልቃ መግባቱን በማውገዝ ተቃውሞ ማሰማታቸውን ተከትሎ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የከተማዋን ድንበር ወደ ኦሮሚያ ክልል ለማስፋፋት ማቀዱን ተከትሎ እ.ኤ.አ. ከሚያዚያ እስከ ግንቦት 2014 ዓ.ም. በዘለቀው ተቃውሞ ምክንያት በቁጥር በውል ያልታወቁ የኦሮሞ ብሔር ተማሪዎች መታገታቸውን ቀጥለዋል፤ አብዛኞቹ የሚታገቱት ያለ ፍርድቤት ማዘዣ ነው፡፡ በተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ የሚያደርጉ ሰዎች ላይ የደህንነት ጥበቃ ሃይሎች ያልተመጣጠነ እና በአንድ እንድ ጊዜም ቀጥታ በጥይት መምታትን ጨምሮ የመግደል ደረጃ የሚያደርስ ሃይል ይጠቀማሉ፤ በዚህም በትንሹ በደርዘን የሚቆጠሩ ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ገድለዋል እንዲሁም በመቶዎች የሚቆጠሩትን ደግሞ አስረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ባለስልጣን አካላት ግድያውንም ሆነ ህገ-ወጥ የሃይል አጠቃቀሙን በተመለከት የተደረገ ምርመራ የለም፡፡ ከእስር የተለቀቁት ግለሰቦች በእስር ላይ እያሉ ግርፋት እና ያለተገባ የእስር አያያዝ እንደተደረገባቸው ተናግረዋል፡፡ የኦሮሞ ብሄረሰብ አባላት ከአጠቃላ የኢትዮጵያ ህዝብ በጥግግት 45 በመቶ ይሆናሉ፤ በተደጋጋሚም በዘፈቀደ ለእስር የሚዳረጉ ሲሆን በሃገር ውስጥ እገዳ ከተጣለበት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ጋር ግንኙነት አላችሁ የሚል ክስ ይቀርብባቸዋል፡፡
ሃሳብን የመግለጽ እና የመደራጀት መብት
መገናኛ ብዙሃን በመንግስት ጠንካራ እጅ ስር እንደወደቁ ይገኛሉ፤ አብዛኞቹ ጋዜጠኞች በራስ ላይ ከሚደረግ ቅድመ-ምርመራ፣ ለጥቃት እና እስር ከመጋለጥ፣ አልያም በግዞት ወደ ሌላ ሃገር ከመሰደድ አጣብቂኝ ምርጫ ውስጥ ወድቀዋል፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2010 ዓ.ም. ጀምሮ ቢያንስ 60 የሚሆኑ ጋዜጠኞች ወደ ሌላ ሃገር ተሰደዋል፡፡ ነጻ መገናኛ ብዙሃንን ለማፈን ከሚወሰዱ ስልቶች መካከል አሳታሚዎች፣ ማተሚያ ቤቶች እና አከፋፋዮች ላይ ላይ ትኩረት ማድረግ ይገኙበታል፡፡
በሰኔ ወር ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በኢትዮጵያ ካደረጉት ጉብኝት ትንሽ ቀደም ብሎ ጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙ እና አምስት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ስብስብ አባላት ጦማሪዎች እና ሌሎች ጋዜጠኞች የተፈቱ ሲሆን እ.ኤ.አ. በጥቅምት 16 ቀን ደግሞ የቀሩት አራት የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት ላይ ጦማሪዎች 39 ጊዜ ፍርድቤት እንዲቀርቡ ከተደረገ በኋላ እና 539 ቀናት በእስር ላይ ካሳለፉ በኋላ ተፈተዋል፡፡ በሌለችበት የተከሰሰችው የአምሰተኛዋ ተከሳሽ ጉዳይም ተዘግቷል፡፡ ሌሎች በርካታ ጋዜጠኞች፣ የተቃውሞ ሰልፍ አድራጊዎች እና የፖለቲካ ተፎካካሪዎች በጸረ-ሽብር አዋጁ መሰረት ክስ እየተመሰረተባቸው ይገኛል፤ እስክንድር ነጋ እና ውብሸት ታየን የመሳሰሉ ጋዜጠኞች እስካሁን በእስር ላይ ናቸው፡፡
እ.ኤ.አ. በ2009 ዓ.ም. ወጣው የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት አዋጅ በሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ዙሪያ የሚሰሩ በርካታ ገለልተኛ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የመስራት አቅም በእጅጉ እንደገደበ ይገኛል፡፡ ህጉ በሰብዓዊ መብቶች፣ በመልካም አስተዳደር፣ በግጭት አፈታት፣ እና የሴቶች፣ የህጻናት እና አካል ጉዳኛ ሰዎች መብት ዙሪያ የአድቮኬሲ ስራ የሚሰሩ ድርጅቶች ከዓመታዊ በጀታቸው 10 በመቶ የበለጠ ገንዘብ ከውጭ ድርጅቶች እንዳይቀበሉ ይከለክላል፡፡
መንግስት የተጠረጠሩ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላት ቤተሰቦችን እና ጓደኞቻቸውን የስልክ ግንኙነት በተከታታይ ይከታተላል እንዲሁም ይቀርጻል፤ የዲጂታል ግንኙነታቸውንም እጅግ በጣም በረቀቁ የስለላ ሶፍትዌሮች ይጠልፋል፡፡
ለኢትዮጵያ መንግስት የመሰለያ ሶፍትዌሮችን በመሸጥ የሚታወቀው እና በሚላን ከሚገኘው ሃኪንግ ቲም የተባለ ድርጅት የወጣ የኢሜይል መልእክት እደሚያሳየው ኢትዮጵያ የመሰለያ ሶፍትዌሩን ለአልተጋባ ጥቅም እያዋለችው እንደሆነ ማስጠንቀቂያ ቢቀርብም ድርጅቱ ለሃገሪቱ ጊዜያዊ ፈቃድ የሰጠ ሲሆን በሚያዚያ ወር ላይ 700 ሺህ የአሜሪካን ዶላር የሚያወጣ አዲስ ስምምነት ለማድረግ ድርድር ጀምረዋል፡፡
ግርፋት እና ዘፈቀዳዊ እስር (እገታ)
የኢትዮጵያ የደህንነት ሰዎች በይፋ በሚታወቁ እና ሚስጥራዊ በሆኑ እስር ቤቶች የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞችን የቀረበባቸውን ክስ እንዲያምኑ አሊያም መረጃ እንዲያወጡ ለማስገደድ በተደጋጋሚ ግርፋት እና ያልተጋባ የእስር አያያዝ ይፈጽሙባቸዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2014 ዓ.ም. የተባበሩት መንግስታት ዩኒቨርሳል ፔርዲክ ሪቪው ኢትዮጵያ በእስር ቤቶች ግርፋት እና ያልተገባ የእስር አያያዝ እንዳይኖር የሚያረጋግጥ እርምጃ እንድትወስድ የቀረበላትን የማስተካከያ ሃሳብ ተቀብላለች፤ ነገር ግን እንዚህን ጥቃቶች ያደረሱ የደህንነት አባላት ስለተወሰደባቸው ምርመራ ወይንም ቅጣት የሚያሳይ መረጃ የለም፡፡
ልዩ ፖሊስ በመባል የሚታወቀው በሶማሌ ክልላዊ መንግስት የሚገኝ ሽምቅ ተዋጊ የፖሊስ ሃይል የለምንም ግልጽ ህጋዊ ፈቃድ በሶማሌ ክልል ከኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) ጋር በሚያካሄደው ግጭት ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥቃት ማድረሱን ቀጥሏል፤ ያለ ፍርድ መግደል፣ ዘፈቀዳዊ እስር፣ እና ኦብነግን ይደግፋሉ የሚል ክስ የሚቀርብባቸውን ወይንም ለድርጅቱ ልዩ አመለካከት እንዳላቸው የተጠረጠሩ የማህበረሰብ ክፍሎችን እንደሚበጠብጥ ሪፖርቶች ወጥተዋል፡፡
የዩናይትድ ኪንግደም ዜጋ የሆነው እና መግስትን በሃይል ለማስወገድ ቅስቀሳ ያደርጋል በሚል በኢትዮጵያ እገዳ የተጣለበት የግንቦት ሰባት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንዳርጋቸው ጽጌ እ.ኤ.አ. በ2014 ዓ.ም. በህገወጥ መንገድ ትራንዚት ላይ እያለ ከየመን ወደ ኢትዮጵያ ከተወሰደ ወዲህ እስካሁን በእስር ላይ ይገኛል፡፡ በግንቦት ሰባት ውስጥ ባለው ተሳትፎ ከዚህ በፊት በሌለበት ሁለት ጊዜ የሞት ፍርድ ተፈርዶበታል፡፡ የአያያዙ ሁኔታ አሳሳቢነት እየጨመረ ባለበት ወቅት የዩናይትድ ኪንግደም ቆንጽላ ባለስልጣናት አንዳርጋቸውን ሁለት ጊዜ ጎብኝተውታል፤ በሚያዚያ ወር በተባበሩት መንግስታት የዘፈቀዳዊ እስርን በተመለከተ የተግባር እንቅስቃሴ የሚያደርገው የስራ ቡድን ኢትዮጵያ አንዳርጋቸውን እንድትፈታ እና ካሳ እንድትከፍለው ጥሪ አቅርቧል፡፡
ከልማት መርሐ-ግብር ጋር በተያያዘ የሚደረግ የሃይል ማፈናቀል
የዩናይት ኪንግደም ዓለም ዓቀፍ የልማት ማስተባበሪያ ክፍል እና የዓለም ባንክን ጨምሮ የተወሰኑ ለጋሽ ድርጅቶች እ.ኤ.አ. በ2015 ዓ.ም. ችግር በተፈጠረባቸው ቦታዎች ለመሰረታዊ አገልግሎቶች ጥበቃ የሚሰጥቱን ድጋፍ አስተላልፈዋል፡፡ መሰረታዊ አገልግሎቶች ጥበቃ በሰዎች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እያደረሰ አንደሆነ ከታወቀው ሰፈራ መርሐ ግብር ጋር ተያያዥነት አለው፤ በሰፈራ መርሃ ግበሩ መንግሰት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚጠጉ የገጠራማ አካባቢ ነዋሪዎችን ወደ ሌላ ቦታ በቋሚነት በማስፈር የሰዎቹን መሰረታዊ ግጋሎቶች ለማሻሻል ያለመ ነው፡፡ በጋምቤላ ክልል አ.ኤ.አ. በ2011 ዓ.ም. የተካሄዱ የተወሰኑ የሰፈራ መርሐ ግብሮች ደብደባ እና ዘፈቀዳዊ እስርን የጨመሩ ግጭቶችን ያስከተሉ ሲሆን ያለበቂ ምክክር እና ያለተገቢ ካሳ ነው የተካሄደው፡፡
የተወሰኑ የጋምቤላ ነዋሪዎች እ.ኤ.አ. በ2013 ዓ.ም. ለዓለም ባንክ የቁጥጥር ጉባኤ ቅሬታቸውን አቅርበዋል፤ ጉባኤው የድርጅቱ ነጻ ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ ገለልተኛ አካል ነው፤ ቅሬታው ባንኩ የአካባቢው ነዋሪዎችን እና በግዴታ የሚሰፈሩ ሰዎችን በተመለከተ የራሱን ፖሊሲ የሚጥስ ተግባር እየሰራ ነው የሚል ነው፡፡ አጣሪ ጉባኤው እ.ኤ.አ. ህዳር በ2013 ዓ.ም. ባቀረበው የማስተካከያ ሃሳብ በመሰረታዊ አገልግሎቶች መርሐ-ግብር ላይ ችግሮች እንዳሉ ጠቁሟል፤ ሆኖም የዓለም ባንክ ቦርድ የቀረበውን የምርመራ ውጤት በየካቲት ወር ላይ ክዷል፡፡ ለምርመራ ጉባኤው የትርጉም ስራ የሚያከናውን አንድ ግለሰብ መጋቢት ወር ላይ የታሰረ ሲሆን እ.ኤ.አ. መስከረም ወር 2015 ዓ.ም. በጸረ-ሽብር አዋጁ መሰረተ ክስ ተመስርቶበታል፡፡
በየካቲት ወር ዩናይትድ ኪንግደም የመሰረታዊ አገልግሎቶች ጥበቃ መርሐ-ግብርን በመደገፍ የትብብር መርኋን ጥሳለች በሚል አንድ ኢትዮጵያዊ አርሶ አደር ባቀረበው ክስ መሰረት ዓለም-ዓቀፉ የልማት ማስተባበሪያ ክፍል የመሰረታዊ አገልግሎቶች ጥበቃ መርሐ-ግብርን መደገፍ እንዳቆመ አስታውቋል፡፡ የዩናይትድ ኪንግደም ዓለም-ዓቀፍ የልማት ማስተባበሪያ ክፍል የኢትዮጵያ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ መብቶች ረገጣን በተመለከተ ስጋቱን ገልጻል፤ ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት እና የምርጫ ተፎካካሪነትን እንዲሁም የአሳሳቢነቱ ደረጃ እየጨመረ የመጣውን የመንግስት የደህንነት አካላት ተጠያቂነትን የተመለከቱ ጉዳዮች ተካተውበታል፡፡
በተለያዩ የሃገሪቱ ክልሎች የልማት ስራ ከሚከናወንባቸው ቦታዎች አስገድዶ የማፈናቀል እርምጃ እንደለ ይገለጻል፤ በአስገድዶ ማፈናቀረሉ ተግባር ለተጎጂዎች እጅግ በጣም ትንሽ ካሳ ወይንም ያለምንም ካሳ ክፍያ የሚደረግ ሲሆን በተለይ በየአካባቢው ሰዎች ጋር የሚደረገው ምክክር በቂ አይደለም፡፡ ከአዲስ አበባ መስፋፋት ጋር ተያያዥነት ያላቸው የንግድ እና የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች ምክንያት እና በታችኛው ኦሞ ሸለቆ የስኳር ፋብሪካ ልማት ተግባር ጋር በተመለከተ ቅሬታዎች እየጨመሩ ነው፤ 200 ሺህ የቀድሞ ነዋሪዎች በማፈናቀል 250 ሺህ ሄክታር መሬት የማጽዳት ሂደቶችን ያካትታል፡፡ በኦሞ አካባቢ የሚገኙ ማሕበረሰቦች ለከብቶቻቸው የግጦሽ መሬት ሲጸዳ እና ለሰብል ምርቶቻቸው ተገን የነበረውን ኦሞ ወንዝ እንዳይጠቀሙ እገዳ እንደተጣለባቸው ተገንዝበዋል፡፡ የልማት መርሐ-ግብሩን በተመለከተ ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎች ታስረዋል እንዲሁም ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል፡፡
እ.ኤ.አ. በ2015 ዓ.ም. በተወሰነ መልኩ የግጦሽ መሬት እና ሌሎች የተፈጥሮ ሃብቶችን ለመጠቀም በሚደረግ ፉክክር የተነሳ በተለያዩ ብሄር አባላት መካከል እና በመንግስት እና በብሔር አባላት መካከል የሚከሰት ብጥብጥ እየጨመረ ነው፡፡ ከሶሰተኛው የግልገል ጊቤ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ጀርባ የሚገኘው ውሃ ማጠራቀሚያ እ.ኤ.አ. በጥር ወር 2015 ዓ.ም. መሙላት የጀመረ ሲሆን በየዓመቱ የሚከሰት የተፈጥሮ ጎርፍን ተከትሎ በኦሞ ወንዝ ዙሪ ያሉ እርሻዎችን መሸርሸር ለመቀነስ ረድቷል፡፡
ቁልፍ ዓለምዓቀፍ ተዋናዮች
ኢትዮጵያ ከውጭ ለጋሽ ድርጅቶች እና አካባቢው ጎረቤቶች ከፍተኛ ድጋፍ ታገኛለች፣ ይሄውም የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በመሆኗ እና በአካባቢው ስልታዊ እንቅስቃሴ ስለምታደርግ በተለይ ለተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ተግባር አስተዋጽኦ ስለምታደርግ፣ የደህንነት እና የእርዳታ ትብብር ከምዕራብያዊያን ጋር ስላለት እና በልማት ጠቋሚ ነጥቦች እድገት እያስመዘገበች ስለሆነ ነው፡፡ በፖለቲካ ፓርቲዎች አባላት ላይ ከፍተኛ እገዳ እንደተጣለባቸው፣ ነጻ መገናኛ ብዙሃን እና መንግስታዊ ያልሆኑ የማህበራት ድርጅቶች አለመኖሩ የታወቀ ቢሆንም በግንቦት ወር ተካሂዶ የነበረውን ምርጫ የታዘበው ብቸኛው ዓለም ዓቀፍ ድርጅት የአፍሪካ ህብረት ምርጫው ተዓማኒነት ያለው ነው ብሎ አሳውቋል፡፡
ኢትዮጵያ በጦርነት ላይ የሚገኙ የደቡብ ሱዳን አካላትን ለማስታረቅ ጥረት ማድረጓን ቀጥላለች፤ የሃገሪቱ ሰላም አስከባሪ ጦር በግጭት ላይ የምትገኘው አቢይ ግዛትን አረጋግቶ ይዟል፡፡ ከአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ ጦሯን ሶማሊያ ውስጥ አስፍራለች፤ እ.ኤ.አ. በ2015 ዓ.ም. በጥቃት አድራሽነቱ የሚታወቀው የልዩ ፖሊስ ሃይል ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጋር ተዳምሮ በመስፈሩ በተመለከተ እየጨመሩ የመጡ አሳሳቢ ሪፖርቶች አሉ፡፡ ከደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ኤርትራ የተፈናቀሉ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ኢትዮጵያ ማስተናገዷን ቀጥላለች፡፡
በጋምቤላ ክልል ኦሞ ስምጥ ሸለቆ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎችን ለልማት ስራ በሚል በግድ ማፈናቀልን ጨምሮ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥቃት እንደምታደርስ የሚያስረዱ ሪፖርቶች ቢኖሩም በአፍሪካ ውስጥ ከለጋሽ ድርጅቶች ከፍተኛ እርዳታ ከሚቀበሉ ሃገራት አንዷ ኢትዮጵያ ነች፤ እ.ኤ.አ በ2015 ዓ.ም. ብቻ 3 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ እርዳታ ተቀብላለች፡፡ ለጋሽ ድርጅቶች ለልማት በሚል የሚሰጡት እርዳታ በኢትዮጵያ ለሚገኘው የሰብዓዊ መብት ጥሰት አስተዋጽኦ ስላለማበርከቱ አሊያም ጥሰቱን የበለጠ እንዲሰፋፋ ስላለማድረጉ የሚያሳይ መከታተያ እና ተጠያቂነትን የሚያሰፍን ስርዓት ለማጠንከር የሚረዳ ደንብ ስለማውጣታቸው የሚገልጽ ምንም ምልክት የለም፡፡
(ምንጭ: Human Rights Watch)
gud says
TPLF obsession syndrome
It is talking 24/7 about it
zekaryas zewdie says
very good
zekaryas zewdie says
good
Mame Nasir says
Ethiopia Freedom!